አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በሆቴሎች እና በሬስቶራንቶች ሰራተኞችን ከስርአቱ ዉጪ አለባበስ እንዲከተሉ ማድረግ እንደሚያስቀጣ ተገለፀ!

የመስተንግዶ ሰራተኞች ከሀገሪቱ ባህል ዉጪ ልበሶችን እንዲለብሱ በሚያደርጉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቱሪዝም ቢሮ አሳወቀ።ለሆቴል ባለንብረቶች ንግድ ዘርፍ ማህበራት የመስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስን በሚመለከት በተፃፈዉ ደብዳቤ ከባህል የወጣ አለባበስ እንዲቆም ተጠይቋል።

ባለኮከብ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ከፍተኛ እና አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ ፔንሲዮኖችን ጨምሮ በሌሎችም ስራዎች በአስተናጋጅነት አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን ከስነምግባር ዉጪ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ባህል የወጣ አለባበስ እንዳይከተሉ አሳስቧል።የከተማዋ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እንዳሳወቀዉ በደብዳቤው ላይ የተገለፀውን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

Via Addis Zeybe
https://t.me/lawsocieties
ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺ
👇👇👇የቀጠለ..👆👆👆

የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

The Fighting against corruption with fashion or passion?

Key Note Speaker;
Samuel Kassahun:
Director of Transparency International Ethiopia
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

የትራንስፓረንሲ ኢንተናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን

እሁድ ምሽት 2:30 ቀጥታ ስርጭት

🔘 Live on Telegram 👈👈
https://t.me/lawsocieties
#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
በሐሰተኛ የምስክር ወረቀቶች መገልገል የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት ምን ያህል ያውቃሉ?

**

በኢት
ዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 375 መሰረት ማንም ሰው የሌለውን ሰው መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት፣ ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ማናቸውንም መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ:-
.....የቀጠለ
ሀ)  ሕጋዊ ክርክሮች ሲካሄዱ በማስረጃነት የሚቀርቡ፣ አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ወይም የሚያረጋግጡ የሚመስሉ እንደ ጽሑፍ፣ ሌሎች ሰነዶች ወይም ግዙፍ ነገሮች የመሳሰሉትን የፈጠረ እንደሆነ፣ ወይም

ለ) ሐሰተኛ ሰነድ ለማዘጋጀት በሌላ ሰው የጣት ፊርማ፣ ፊርማ፣ ምልክት ወይም ማህተም የተጠቀመ እንደሆነ፣ ወይም

ሐ) እውነተኛውን ጽሑፍ በመለወጥ ወይም በመደለዝ በሐሰተኛ ፊርማ በእጅ በተደረገ ምልክት፣ ወይም በጣት ፊርማ  በማህተም ወይም የሌለውን ስልጣን ወይም ችሎታ እንዳለው አስመስሎ በመፈረም ሐሰተኛ ሰነድን የፈጠረ እንደሆነ፣ ወይም

መ) አንድን ሰነድ፣  በተለይም የፈራሚውን ስም ወይም ፊርማ ወይም የሰነዱን ይዘት፣ አሃዝ፣ ፍሬ ነገር ወይም ዝርዝር መግለጫ በሙሉ ወይም በከፊል በመለወጥ፣ በማሻሻል፣ በመቀነስ ወይም በመጨመር፣ ወይም በማጥፋት ወደ ሐሰተኛነት የለወጠ እንደሆነ፣ ከሶስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ወይም ነገሩ ከባድ በሆነ ጊዜ ከአስር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡

አንቀጽ 378 - ማንም ሰው በሐሰት በተዘጋጀ ወይም ወደ ሐሰት በተለወጠ ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት እንደሆነ፣ በአንቀጽ 375 ላይ በተደነገገው መሰረት ይቀጣል፡፡
አንቀጽ 379 (1) - መንግስታዊ ወይም ወታደራዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወይም ወደ ሐሰት መለወጥ የተፈጸመው:-

ሀ) በአንድ የመንግስት መዝገብ፣ በታወቀ ሰነድ ወይም የህዝብን ጥቅም የሚመለከት ሰነድ ላይ እንደሆነ፣ ወይም

ለ) በመንግስት ወይም በህዝብ መዝገብ በገባ ሰነድ ወይም ሟች ራሱ በእጁ በጻፈው ኑዛዜ ላይ እንደሆነ፣ ወይም

ሐ) የአገር መከላከያን፣ የመከላከያ ሰራዊት አቋምን፣ ድርጅትን፣ የሥራ ተግባርን ወይም ጉዳይ በሚመለከት ሰነድ ላይ እንደሆነ፣ ቅጣቱ ከአስራ አምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይሆናል፡፡

አንቀጽ 379 (2) - ወንጀሉ የተፈጸመው እነዚህን የመሳሰሉትን መዝገቦች፣ ጽሑፎች፣ የታወቁ ሰነዶች ወይም ሌሎች ሰነዶችን እንዲያዘጋጅ፣ እንዲመዘግብ፣ እንዲጠብቅ፣ ወይም ከእነዚህ ውስጥ ቅጂዎች እንዲሰጥ ኃላፊነት በተሰጠው የመንግስት ሰራተኛ እንደሆነ፣ ቅጣቱ ከ5 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይሆናል፡፡

የወንጀሉ አፈጻጸም በጣም ከባድ በሆነ ጊዜ ቅጣቱ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በህጉ መደንገጉን ኢቢሲ አትቷል፡፡
Federal Ethics and Anti corruption commission
https://t.me/lawsocieties
Gizachew.doc
1.8 MB
Bahir Dar University, Module on law of traders and Businesses
Ministry of Finance Amended the new policy which ban importing of duty free capital goods after business license.

Please check the letter below from ministry of finance regarding importing a capital good duty free, even after business license, but the letter clearly stated that if they get business license and practically start to sell thier product and service, this amndement is not applicable.

EII.
ወንጀል ማለት ፡-
በወንጀል ህግ የተከለከሉ ድትጊቶችን መፈፀም ወይም እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ ወይም ግዴታ የተጣለበቸውን ድርጊቶች አለመፈፀም ነው፡፡


በዚህ መሠረት የወንጀል ህጉ ኃላፊነትን የማያስከትል ተግባር የፈፀሙ ሠዎች በወንጀል እንዳይጠቁ ማድረጊያና ወንጀል የፈፀሙ ቢሆንም እንኳን በህጉ ላይ ከተመለከተው ቅጣት ውጪ በዘፈቀደና ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንግድ እንዳይቀጡ መከላከያ መሣራያ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
የነፃነት መብት
 
በህገ መንግስስቱ አንቀፅ 17 መሠረት ማንኛውም ሰው የነፃነተ መብት እንዳለው ተቀምጧል፡፡ ይህ መብት የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

☑️ከቦታ ቦታ መዘዋወር
☑️በመረጡት ስፍራ መኖር
☑️በፈለጉት ጊዜ ወጥቶ በፈለጉት ጊዜ መግባት
☑️ከመረጡት ሰው፣ ቤተሠብ ወይም
☑️ህብረተሠብ ጋር መቀላቀል
☑️ቢፈልጉም በብቸኝነት መኖር
☑️በማናቸውም ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ተሣታፊ ለመሆን መቻል እና የመሣሠሉት ናቸው፡፡
እነዚህ እውቅና የተሠጣቸው መብቶች ፈፅሞ አይደሉም፡፡ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 17(1) መሠረት በህግ መሠረት ማንኛውም ሰው ነፃነቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ በወንጀል ህጉ ተለይተው ከተቀመጡት ቅጣቶች አንዱ ማገድና መለየት ነው፡፡ የዚህ ቅጣት አላማ ወንጀለኞችን ከህብረተሠቡ ነጥሎ በማስቀመጥ ሌሎች ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ መከላከል ነው፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ወንጀለኛ እሰራት ቢፈረድበት እስሩን እስኪጨረሰ ድረስ ሌላ ወንጀል በመፈፀም የህብረተሠቡን ሠላም አያናጋም የሚል ግምት ስላለ በህገ መንግስቱ እውቅና የተሠጠው የነፃነት መብት ሊያጣ ይችላል፡፡
በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጡትን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በወንጀል ህጉ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ሙሉ በሙሉ መዘርዘር የዚህ ፅሁፍ ዋና አላማ ባይሆንም ከላየ የተዳሰሱት የህገ መነግስቱ አንቀፆች ህገ መንግስቱ እና የወንጀል ህጉ በቀጥታ ትስስር እንዳላቸው ያመለክታሉ፡፡
መንግስት የህብረተሰብን ሠላምና ፀጥታ እንዲሁም የግለሰብን መብትና ነፃነት የማስከበር ሃላፊነት አለው፡፡ ይሄንን ሃላፊነት ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው እና በሚያዘው መሠረት ተገባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ ከእነዚህ እርምጃዎች አንዱ የወንጀል ህግ መደንገግ እና ይህንን ህግ የተላለፉ ሰዎች ወደ ህግ ማቅረብ ይጨምራል፡፡ በነዚህ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ንፁህ ግለሰቦች ሣይጐዱ የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ሣይስተጓሎል ጥፋተኞች እንዲቀጡና ከጥፋታቸው እንዲማሩ ማድረግ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የእነዚህ ህገ መንግስታዊ መርሆች ዋና አላማ መንግስት ከለይ የተገለፀውን ሃላፊነት ሲወጣ ሊያልፈ የማይችለውን ገደብ ማበጀት ነው፡፡ በአጠቃላይ ህገ መንግስት በባህሪው መብቶችና ግዴታዎችን በጥቅል መልኩ የሚያስቀምጥ ሰነድ ነው፡፡ የወንጀል ህግ ደግሞ በህገ መንግስቱ ውስጥ ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶችና ነፃነቶች ተግባራዊ ማድረጊያ መንገድ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
ውድ የተከበራችሁ #የአለ ህግ ቤተሰቦች የዛሬ ፕሮግራማችን በአለም ዋንጫ ምክንያት ለሚቀጥለው ሳምንት ተራዝሟል።

ሰላም ቆዩ


https://t.me/lawsocieties
ተንቀሳቃሽ ንብረትን ዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለው አዋጅ
=======================
ታኅሣሥ 9/2015 ተንቀሳቃሽ ንብረትን ዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለው አዋጅ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ገለጹ።

የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና የገቢዎች ሚኒስቴር ከክልል የፕላን፣ የገንዘብና የገቢ ቢሮዎች ጋር የሚደረገው የምክክር መድረክ ዛሬም  በአርባ ምንጭ ከተማ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ ወቅት የፋይናንስ ተደራሽነትን እና ተንቀሳቃሽ ንብረትን በዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለውን አዋጅ በማስመልከት ገለጻ ያደረጉት የብሔራዊ ባንክ ገዢው፤ አዋጁ በተለይም ገጠራማውን የአገሪቱ አከባቢ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች እስከአሁን ከ330 ሺሕ ለማይበልጡ ሰዎች ብቻ ብድር መስጠታቸውን ገልጸዋል።

በተያያዘ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከ6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ብድር መስጠታቸውን ተናግረዋል።

በሀገሪቷ ካሉት ዜጎች  አንጻር ብድር የወሰዱ ዜጎች እጅግ አነስተኛ መሆናቸውንም አንስተው፤ ለዚህ ደግሞ የብድር ዋስትና ቋሚ ንብረት ላይ ትኩረት ማድረጉን በምክንያትነት አንስተዋል።

አሁን ላይ ይህን ችግር ለመፍታት ተንቀሳቃሽ ንብረትን በዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት የሚሰጥበት አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ነው የጠቆሙት።

በዚህም በተለይ አርብቶ አደሩ እና አርሶ አደሩ እንስሳትን፣ ግመሎችን፣ የግል ደኖችን፣ የመሬት መጠቀሚያ ደብተሮችን እና የመሬት መብትን በማስያዝ እና በሌሎችም ብድር ማግኘት የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አዋጅም በቅርቡ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
"ገንዘብ ካላመጣሽ እንገድልሻለን ብለው አግተውኛል” በሚል የሃሰት ምክንያት ባለቤቷ በባንክ ገንዘብ እንዲያስገባላት የጠየቀችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

***
ወንጀሉ የተፈፀመው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው ሰርጢ ማርያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡  ተጠርጣሪዋ የሁለት ልጆቿ አባት ለሆነው ባለቤቷ ስልክ ደውላ እንደታገተችና  150 ሺህ  ብር እንደተጠየቀች፤ ገንዘቡንም በራሷ የንግድ ባንክ አካውንት ገቢ እንዲያደርግላት፣ ገንዘቡን ካላስገባላት ግን እንገድልሻለን ብለው እንደዛቱባት ነግራው ስልኳን ትዘጋለች፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው በድጋሚ ስልኳን ከፍታ ”የተባላችሁትን ገንዘብ በአስቸኳይ አስገቡ“ ብሎ ሌላ ግብረ አበሯ ባለቤቷን እንዲያወራው ካደረገች በኋላ ባለቤቷም ጉዳዩን ተጠራጥሮ ለፖሊስ አመልክቷል፡፡

ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ሲያሰባስብ እና ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ግለሰቧ እንዳልታገተች እና መንገድ ላይ ስትንቀሳቀስ እንደታየች በደረሰው ጥቆማ  በዚያው ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሸገር ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዘመድ ቤት ውስጥ ተደብቃ በቁጥጥር ስር አውሏታል፡፡ አባሪ ተባባሪ በመሆን በዚህ ወንጀል ተሳትፎ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
Addis Ababa Police
Legal Advisor
Baheran Trading PLC

Addis Ababa
Full–time

Job Requirement
• Qualification: LL.B in Laws from recognized university
• Work Experience:
Minimum 4 year experience, preferable experience in PLC

Work Place: Addis Ababa

How to Apply
The Company might relocate the work place as per its demand.
Interested & qualified applicants are invited to submit their non-returnable applicants , CV and copies of educational testimonies with original documents with in 5 (Five) consecutive days from the date of announcement in person to Baheran Trading PLC Human Resource Department located Addis Ababa in front of Lideta Church Dashen Bank Building 7th floor , office No.7-14. Or
send it to hr@baherantrading.com.
Tel. 0111 56 88 72
https://t.me/YehigGuday
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ምድብ ችሎት ዳኛ ትንሳኤ በላይነህ እራሱን ከ13 ፎቅ ላይ ወርውሮ ህይወቱ ማለፉ ተሰማ!

ታሕሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር

ይህ ግለሰብ የአ/አ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ የሆነች ዙፋን ተፈሪ አለሙ የምትባል አብራዉ በፍቅር የምትኖረዉን ጓደኛዉን በሽንኩርት ቢላ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ

ከምሽቱ 1:45 ሰዓት ገደማ መገናኛ አምቼ ፊት ለፊት ባለዉ የፌደራል ዳኞች መኖሪያ ጊቢ ውስጥ እራሱን ከ13ኛ ፎቅ ወደ መሬት ወርዉሮ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ተችሏል።

አስከሬናቸው ለምርመራ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዷል።

ከሰዓታት በፊት በፌስቡክ ገፁ ላይ የሌሎች ዳኞችን ስም በመጥቀስ ይህን መልክት ፅፎ ነበር።

በዚህ ዳኛ ላይ አልፎ አልፎ የፍርሀትና የጭንቀት የስነልቦና ችግሮች እንደነበሩበት ከቅርብ ጎደኞቹ መረዳት ተችሏል።

Via Tarik Adugna
via አሻራ ሚዲያ
https://t.me/lawsocieties
የ12 ዓመት ታዳጊ የቤት ሰራተኛቸውን ገድለው በድብቅ ሊቀብሩ ሲሉ የተያዙት ቀጣሪዎች በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።

በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ ምርመራውን በመምራት ክስ መስርቶ ክርክር በማድረግ አጥፊዎቹ እንዲቀጡ አድርጓል።

ክርክሩን የመራው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ነው።

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው 1ኛ ልጃለም ጌታቸው ታዬ እና 2ኛ ቆንጂት ሙለታ በቀለ የተባሉት ባልና ሚስት ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ማንጎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከታህሳስ 17/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 17/2014 ዓ.ም ባለ ጊዜ ሟች አስቴር ነገሰን ተከሳሾች በተደጋጋሚ በተለያየ ጊዜ በፍልጥ እንጨት፣ በእርግጫ፤ በሞባልይ ቻርጀር ገመድ ጀርባዋን፣ ወገቧን እና እግሯን ደጋግመው በመደብደብ፤ ከገደሏት በኋላ የሟችን አስከሬን በሳጥን በማድረግ በድብቅ ለመቅበር ሲሰናዱ ተይዘው ምርመራ ሲጣራ በሟች ላይ በርካታ የቆዳ መጋጋጥ እና የመበለዝ፣ ከአንገትዋ የፊተኛው ክፍል አንስቶ ወደ ቀኝ እና ግራ ትከሻዋ የተሰራጨ የመበለዝ፣ በደረትዋ የላይኛው ፊተኛና ጎን 1/3 ክፍል የመበለዝ፣ በቀኝና በግራ ቂጥዋ ጭን የላይኛው ኋለኛ ክፍል እና በጀርባዋ የታችኛው ክፍል ላይ በርካታ የቆየ የቆዳ መጋጥ፣ በራስ ቅልዋ ፊተኛ መካከለኛ ክፍል የመበለዝ፣ በእጅ እና እግሮቿ ላይ ወደ ውስጥ ደም የመፍሰስ፣ የመሰራጨትና የመበለዝ ጉዳት ምክንያት ህይወቷ ማለፉ በማስረጃ በመረጋገጡ ዐቃቤ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶ ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ተከሳሾችም በችሎት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸው ድርጊቱን አልፈፀምንም ጥፋተኛም አይደለንም ብለው የተከራከሩ ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አስደግፎ ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው በበቂ ሁኔታ ያረጋገጠ በመሆኑ እና ተከሳሾችም ይህን የዐቃቤ ህግ ክስ እና የቀረበባቸውን ማስረጃ አንዲያሰተባብሉ በተሰጠ ብይን መሰረት 2 የመከላከያ ምስክር አቅርበው ያሰሙ ቢሆንም የቀረበባቸውን ክስ እና ማስረጃ ያላስተባበሉ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ህግ በቀረበባቸው ክስ እና ማስረጃ መሰረት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ፍርድ ሰጥቶ ቅጣት ለመወሰን ለታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ክርክሩን የመራው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎትም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ 02/2006 መሰረት የወንጀል ደረጃውን 2 እርከን 39 ስር በማድረግ መነሻ ቅጣት በመያዝ፣ ሁለቱም ተከሳሾች ሪከርድ የሌለባቸው በመሆኑና የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናቸው 2 የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው በእርከን 37 ስር ተከሳሾችን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራል ያለውን እያንዳንዳቸው በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ እና እንዲሁም ተከሳሾች ለ5 ዓመት ከመብቶቻቸው እንዲሻሩ ሲል ወስኖባቸዋል፡፡

በቤት ሰራተኞች ላይ የሚፈጸመው አብዛኛው በደል በቤት ውስጥ የሚፈጸም እንደመሆኑ መረጃ የማግኝት ሂደቱን አስቸጋሪ የሚያደርግ ቢሆንም በአቅራቢያ በሚገኙ ከፍትህ ጎን በሚቆሙ ሰዎች አማካኝነት አጥፊዎች ተቀጥተው ፍትህ ይሰፍናልና የቤት ሰራተኞች ሲበደሉ አይተው አይለፉ መልዕክታችን ነው።

https://t.me/lawsocieties