አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የችሎት ዜና

በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰዉ ግለሰብ በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ- ሳሙኤል ሽሙ ተገኘ
እድሜ 28 ዓመት
አድራሻ ደሴ ከተማ 010 ቀበሌ መገናኛ
የሆነው ግለሰብ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፊ.ድ.ሪ የወ/ህ/ አንቀፅ 620(2) (ሀናለ) የተመለከተውን በመተላለፍ ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከሌሊቱ በግምት 7፡00 ሰአት ሲሆን በደሴ ከተማ ቀበሌ 010 ልዩ ቦታዉ መገናኛ እየተባለ ከሚጠራዉ ቤቱ እድሜዋ 16 ዓመት የሆናትን የግል ተበዳይ፤ በቤት ሰራተኝነት ቀጥሯት በቁጥጥሩ ስር የምትገኘዉን፤ ከቤቱ በረንዳ ላይ አፋን በማፈንና አንገቷን በማነቅ አስገድዶ የደፍራትና ክብረ ንጽህናዋን የገረሰሰ በመሆኑ፤ ከዛም በኋላ በተለያዩ ቀናት ድርጊቱን የደጋገመው በመሆኑ በፈጸመዉ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ተከሶ መቅረቡ ነው የውሳኔው መነሻ።

ምርመራዉን የደሴ ከተማ 4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ አጣርቶ ለደሴ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በማቅረብ ዐ/ህግም ክሱን በማጠናቀር ለደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አቀረበ፡፡

በመሆኑም የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በመመርመር የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎችን በመስማትና በማየት የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም ጥፋተኛዉን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል ባለው በ 8 ዓመት ከ 5 ወር/በስምንት ዓመት ከአምስት ወር/ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤትም ህብረተሰቡም ከዚህ ቅጣት እንዲማርበትና አጥፊዎችን ለህግ በማቅረብ ሂደት ነቅቶ እንዲሳተፍ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት -የህ/ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት
👍4👎4
በፍትሐብሔር ክርክር ቅድመ-ሙግት ሂደት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች
የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት ከሙግት በፊት ያሉ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደቶች አንድን ክርክር ላይ ያላቸዉን ሚና ማጉላት እና ፋይዳቸዉን ማሳየት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ሂደት ቅደመ ሙግት የሚባለዉ ለክርክሩ መሪ ጭብጥ ተይዞ ግራ ቀኙ ማስረጃ ማሰማት ከመጀመራቸዉ በፊት ያለዉ ሂደት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ዋናዉ ሙግት የሚጀምረዉ ጭብጥ ተይዞ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 257 እና ተከታይ ድንጋጌዎቹ ተከራካሪዎች ማስረጃዎቻቸዉ የሚያስረዷቸዉን ጭብጥ እያስመዘገቡ ማስረጃ ማሰማት ሲጀምሩ ነዉ፡፡ ከዋናዉ ሙግት በፊት ባለዉ የቅድመ ሙግት ሂደት በዋናነት ክስና ማስረጃ ማቅረብ፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መልስ እና ማስረጃ መቅረብ፣ ክስ መሰማት እና የክስ መቃወሚያዉ ላይ የመወሰን ተግባሮች ይፈፀማሉ፡፡ ይህ የክርክር ሂደት ክርክሩን ለመምራት ዋና መሰረት የሆነዉ ነዉ፡፡ የክርክሩ አቅጣጫ የሚወሰነዉም በዚህ የክርክር ደረጃ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ነዉ፡፡ ክርክሩን ግልፅ እና አጭር በሆነ ሂደት ለመፈፀም የሚያስችለዉም የቅድመ ሙግት ሂደቱ ጤናማ መሆን ከቻለ ነዉ፡፡

ክርክሩ ሳይንዛዛ እንዲያልቅ ከተፈለገ በቅደመ ሙግት ሂደት መከናወን ያለባቸዉ ነገሮች ሁሉ ጥንቅቅ ብለዉ መከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ክርክሩ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ከተፈለገም በቅድመ ሙግት ሂድት የሚከናወነዉ መጥሪያ አደራረስ ሰርዓት በተገቢዉ መንገድ መፈፀም ይኖርበታል፡፡ ከሙግት በፊት በዳኛዉ ሆነ በሬጅስትራር ሊከናወኑ የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች ያሉ ቢሆንም ለዚህ ጽኁፍ ዓላማ ሲባል ሶስት ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ይደረጋል፡፡ የመጀመሪያዉ ክስ እና መልስ ሲቀርብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 145 መሰረት እንዲቀርብ የሚጠየቀዉን ማስረጃ ይመለከታል፡፡ ሁለተኛዉ መልስ በሬጅስትራር የማቀባበል ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ ሶስተኛዉ ክስ ከመስማት ጋር በተገናኘ መቃወሚያ እና ፍሬ ነገር ክርክሮች የሚደረጉበት ሁኔታ ይመለከታል፡፡ ይህ ጽሑፍም ሶስቱን ጉዳዮች በሕግ ያላቸዉን ማዕቀፍ እና ተግባራዊ አፈፃፀማቸዉን በመዳሰስ ከሥነ-ሥርዓት ሕጉ ዓላማ አንፃር ለክርክር ፍጥነት፣ ግልፅነት እና ፍትሐዊነት ያላቸዉን አስተዋጽዖ ይዳስሳል፡፡
በ፦ ፍቃዱ አንዳርጌ መኮንን
https://www.abyssinialaw.com/blog/pre-trial-proceedings
👍8
በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት ስህተትን ስለማረም
ባለሥልጣኑ በታክስ ሕግ መሠረት ለታክስ ከፋዩ የሰጠው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ በታክስ ሕግ ወይም በጉዳዩ ኩነቶች ላይ ትርጉም ጥያቄ የማያስነሳ የጹሑፍ፣የሂሳብ ስሌት ወይም ሌላ ማንኛውንም ስህተት የያዘ በሚሆንበት ጊዜ ባለሥልጣኑ ስህተቱን ለማረም ሲባል የታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ወይም ሌላውን ሰነድ የታክስ ስሌት ማስታወቂያው ወይም ሰነዱ ለታክስ ከፋዩ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5/አምስት/ ዓመታት ውስጥ ማሻሻል ይቻላል፡፡
በዚህ መሠረት የሚታረም የታክስ ስህተት የሚባለው:-
• የመደመር፣ የመቀነስ፣ የማባዛትና የማካፈል ስህተት፣
• በስሌት ማጠቃለያ ላይ ከመንደርደሪያ ሀሳብ መለየት ወይም መቃረን፣
• ከአንድ የሒሳብ ቁጥር ከፊት ወይም ከኋላ የቁጥር መጨመር ወይም መቀነስ ወይም የሒሳብ ቁጥር ቦታ መቀያየር (transposition)፣
• የገቢ ወይም የወጪ ኮድ አመዘጋገብ ስህተት፣
• የቃል ወይም የሐረግ በአዎንታ ወይም አሉታ መቀያየር፣
• የሒሳብ ቁጥር ወይም ሀሳብ መተው ወይም መዘለል (omission)፣
• ከግብር ነጻ የሆነ ገቢን ግብር በሚከፈል ገቢ ውስጥ መጨመር፣
• በአንድ ታክስ ከፋይ ሒሳብ ውስጥ የሌላ ታክስ ከፋይ ሒሳብ መጨመር ወይም ማቀያየር፣
• የታክስ መጣኔን ወይም የትርፍ ህዳግን መሳሳት፣
• በታክስ ቅሬታ አጣሪ የሥራ ክፍል፣ በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ወይም በመደበኛ ፍ/ቤት እንዲስተካከል የተወሰነን ጉዳይ አለማስተካከል፣
• በዚህ መሠረት ስህተት ሊታረም የሚለው በታክስ ውሳኔ መጠን ላይ በመጨመር ወይም በመቀነስ ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን ብቻ ሆኖ ለውጥ የማያመጣ በመሆኑ የማይታረም ስህተት ሲኖር ለታክስ ከፋዩ በጽሑፍ ይገለጻል፡፡
በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት ቀጥሎ በተመለከተው መንገድ የሚታረም ይሆናል፡፡
🔹የግምት የታክስ ውሳኔ ላይ ስህተት አለበት የሚል ታክስ ከፋይ የግምት ታክስ ስሌት ማስታወቂያ በተሰጠው ከ5 ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የታክስ ስሌቱን ላከናወነው ወይም ውሳኔውን ለሰጠው የሥራ ሂደት ጥያቄውን በጽሑፍ በማቅረብ ስህተቱ እንዲታረምለት ሊጠይቅ ይችላል፡፡
🔹የግምት ታክስ ስሌቱን የሠራው ሥራ ሂደት የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ከተሰጠ በኋላ በታክስ ስሌትና አወሳሰን ሂደት የተፈጸመ ግልጽና የማያከራክር ስህተት የፈፀመውን ባለሙያ ወይም የሌላ ባለሙያ አስተያየት ጭምር በማያያዝ ስህተቱ እንዲታረም የውሳኔ ሀሳብ ለቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ያቀርባል፡፡
🔹የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ስህተቱ እንዲታረም ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በአግባቡ መመርመር ያለበት ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበለትን ባለሙያና የሥራ ሂደት አስተባባሪን ጠርቶ ማነጋገርና ማወያየት ይችላል፡፡
🔹ታክስ ከፋዩ ጥያቄ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥያቄው ላይ ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡
🔹የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሊታረም የሚል ስህተት አለመኖሩን በመግለጽ ውሳኔ የሰጠ እንደሆነ ታክስ ከፋዩ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ካለው ውሳኔው በደረሰው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዋና መ/ቤቱ የሚመለከተው ዳይሬክቶሬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ዳይሬክቶሬቱም በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ለሀገር ውስጥ ታክስ ከፋይ ወይም ለሕግ ማስከበር ም/ዋና ዳይሬክተር (ሚኒስትር ዴኤታ) ያስተላልፋል፡፡
🔹በቀረበው ቅሬታ ላይ የሀገር ውስጥ ታክስ ወይም የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ለጥያቄው በቀረበ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል፡፡
🔹 በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ታክስ ከፋይ ውሳኔው በደረሰው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዋና ዳይሬክተሩ በጽ/ቤቱ በኩል ሊያቀርብ ይችላል፡፡
🔹ጥያቄው በቀረበ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት በኩል ለታክስ ከፋዩ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
🔹ስህተቱ እንዲታረም ከተወሰነ፡- የታረመው ውሳኔ የመጀመሪያ ውሳኔ በሰጠው የሥራ ክፍል በኩል የተስተካከለ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ይሰጣል፡፡
🔹ለታክስ ከፋዩ ተስተካክሎ የሚሰጠው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ቀደም ሲል የተሰጠው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የተሻረ መሆኑን የሚገልጽና ስህተቱ በታረመበት ጊዜ ያለውን ቀንና ቁጥር የያዘ መሆን አለበት፡፡
🔹ስህተትን ለማረም የሚወስደው ጊዜ በታክስ ውሳኔ ላይ በመደበኛ መንገድ ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜን ከመቆጠር የሚያስቀር አይሆንም፡፡
🔹ከላይ በተዘረዘሩት መሠረት የሚቀርብ ስህተት የማረም ጥያቄ ጉዳዩ በቅሬታ ወይም በይግባኝ ወይም በፍ/ቤት ደረጃ ደርሶ የታየ ቢሆንም የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

via #taxandbusinesslawblog
https://t.me/lawsocieties
👍10
በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች
።።።።።።።።።።።።።።👆👆👆👆👆
በህይወት መኖር ከሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች ወይም ሰብዓዊ መብቶች በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ሰብዓዊ መብቶች የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያለው መብቶች ናቸው፡፡ በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 14 ስር ስለ የህይወት፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በህይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው፡፡ በመሆኑም የሰው ልጆች በህይወት የመኖር መብት፣ የአካል ደህንነቻቸው የመጠበቅ መብት፣ የነፃነት መብት፣ ከኢ-ሰብዓዊ አያያዝ የመጠበቅ እና በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት የተዘረዘሩት ሰብዓዊ መብቶች አሏቸው፡፡ ሌሎች ሰዎች በሰው ህይወት ወይም አካል ላይ ጉዳት አድርሰው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

በህገ መንግስቱ የተዘረዘሩት መሰረታዊ የመብቶችና የነፃነት ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሠነዶች መርሆች ጋር በተጣጣመ መንገድ ይተረጎማሉ፡፡ እነዚህ ሰብዓዊ መብቶች በህገ መንግስቱ ሽፋን ከማግኘታቸው በተጨማሪ በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ውስጥ በስፋት እና በዝርዝር መብቶቹን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀል የሆኑትን ድርጊቶች እና የሚያስከትሉት ቅጣት ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም ሰዎች በየእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው እነዚህን ድንጋጌዎች ላለመተላለፍ እና የሰዎችን መብት ለማክበር ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ትምህርታዊ ፅሁፍ በወንጀል ህጉ ውስጥ የተካተቱ በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ምን ምን እንደሆኑ እና የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነትና ቅጣት እንመለከታለን፡፡

 በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች

ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት እንዳለው እና በህግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ህይወቱን እንደማያጣ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 15 ስር ሰፍሯል፡፡ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ ለዚህ መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ጥበቃ ለማድረግ የወንጀል ድንጋጌዎችን አስቀምጧል፡፡ በሰው ህይወት ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መካከል አንደኛው የሰው መግደል ወንጀል (Homicde) ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡

ከወንጀል ህጉ አንፃር የሰው መግደል ወንጀል ሆን ተብሎ (ታስቦ) የሚፈፀም የሰው መግደል ወንጀል፣ በቸልተኝነት የሚፈፀም የሰው መግደል እና ህፃንን መግደል በሚል ተከፍሎ ሊታይ ይችላል፡፡ ማንም ሰው አስቦ ወይም በቸልተኝነት በማናቸውም መሳሪያ ወይም ዘዴ ሌላውን ሰው የገደለ እንደሆነ ነፍሰ ገዳይ ነው ( የወ/ህግ አንቀፅ 538/1) ፡፡ አስቦ ወይም በቸልተኝነት ሰውን በመግደል ጥፋተኛ የሆነ ሰው ላይ የሚጣለው ቅጣት እንደ አገዳደሉ ሁኔታ በቀላልነት እና በከባድነት ይወሰናል፡፡ አስቦ ወይም በቸልተኝነት ሰውን የገደለ ሰው ሁሉ የሚቀጣው ሕጋዊ በሆኑ የፍርድ ሂደቶች እና በውሳኔዎች መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡

 ታስቦ የሚፈፀም የሰው መግደል ወንጀል

በወንጀል ህጉ እንደተደነገገው ታስቦ የሚፈፀውን የሰው መግደል ወንጀል በሶስት ተከፍሎ እናገኘዋለን፡፡ ይኸውም በአንቀፅ 539 ከባድ የሰው ግድያ፣ በአንቀፅ 540 ተራ የሰው ግድያ እና በአንቀፅ 541 ቀላል የሰው ግድያ ተብለው በንፅፅር ዓይነት ተመልክተዋል፡፡ የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 539 ቅጣትን የሚያከብዱ ምክንያቶች በሚኖሩበት ጊዜ ያለውን የሚመለከት ሲሆን የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 541 ደግሞ ቅጣት የሚያቀሉ ምክንያቶች (በራሱ በድንጋጌ ውስጥ የተመለከቱት ሁኔታዎች) በሚኖሩበት ጊዜ ያለውን የሚመለከት ነው፡፡

በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 541 ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውጪ ሆን ተብሎ የሚፈፀሙ የሰው መግደል ወንጀሎች ደግሞ ተራ የሰው ግድያ በሚለው በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 540 ድንጋጌ መሰረት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ከዚህ አንፃር ተራ የሚለው ቃል የግድያውን ቀላልነት የሚያሳይ ሳይሆን በከባድ ግድያና በቀላል ግድያ መካከል የሚገኝ የግድያ ዓይነት መሆኑን ለማሳየት የተቀመጠ ነው፡፡

የሰው መግደል ድርጊት በራሱ ጨካኝነት፣ ነውረኝነት፣ አደገኝነት፣ የሚያሳይ ተግባር ስለሆነ በወ/ህ/አ 539 ላይ ገዳዩ በተለይ ጨካኝ፣ ነውረኛ ወይም አደገኛ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ የሚለው ግድያው ሆን ተብሎ መፈፀሙን ብቻ ሳይሆን መሰረት የሚያደርገው የግድያውን አፈፃፀም እና የአገዳደሉን ሁኔታ ነው፡፡ ስለሆነም ጨካኝነት፣ ነውረኝነት እና አደገኝነት ወንጀሉን ለማቋቋም ሊኖር የሚገባው መመዘኛ መሰረት የሚያደርገው ምክንያት የህብረተሰቡን ማህበራዊ እድገት እና ባህላዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡

 ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል (አንቀፅ 539)

ማንም ሰው ፡-

ሀ/ ሰውን ለመግደል አስቀድሞ የነበረው አሳብ፣ ወይም ምክንያት፣ ለመግደል የተጠቀመበት መሳሪያ ወይም ዘዴ፣ የገዳደሉ ሁኔታ ወይም ግድያው የተፈፀመበት ቅጣትን የሚያከብድ ጠቅላላ ምክንያት /አንቀፅ 84/ ወይም ሌላ ምክንያት /አንቀፅ 86/ ሲታይ ገዳዩ ጨካኝ ፣ ነውረኛ ወይም አደገኛ መሆኑን በሚገልፅ ሁኔታ፣

ለ/ ሰውን ለመግደል ወይም የውንብድና ወንጀልን ለመፈፀም የተደራጀ የወንበዴ ቡድን አባል በመሆን፣

ሐ/ ሌላ ወንጀል ለመፈፀም እንዲመቸው ወይም የተፈፀመ ወንጀል እንዳይገለፅ ለማድረግ ሲል አስቦ ሰው የገደለ ሰው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡

 በተራ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል (በአንቀፅ 540)

ማንም ሰው አገዳደሉ በአንቀፅ 539 የተመለከተውን ያህል ከባድ ወይም በአንቀፅ 540 የተመለከተውን ያህል ቀላል ባልሆነ ሁኔታ አስቦ ሰውን የገደለ እንደሆነ ከአምስት ዓመት እስከ ሀያ ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል፡፡

 ቀላል የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል (በአንቀፅ 541)

የአስገዳጅ ሁኔታ ወሰንን በመተላለፍ ወይም ህጋዊ መከላከልን ከመጠን በማለፍ ወይም ከፍ ባለ ደም በሚያፈላ ምክንያት ወይም ባልተጠበቀው ሕሊናን በሚያውክ ድንገተኛ ምክንያት ወይም በከፍተኛ ስሜት ወይም በብርቱ ዝንባሌ የተነሳ ሆኖ፣ በአዕምሮ ግምት ይህን ለማድረግ በሚያደርስና በከፊል ይቅርታን በሚያሰጡ ሁኔታዎች አስቦ ሌላ ሰው የገደል እንደሆነ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል፡፡

 በቸልተኝነት የሚፈፀም የሰው መግደል ወንጀል

ከወንጀል ህግ አንቀፅ 543 አኳያ በቸልተኝነት ሰው በመግደል የሚፈፀሙ ወንጀሎች በሶስት ተከፍለው ይታያሉ፡፡ እነሱም፡-

 ማንኛውም ሰው የሚፈፅመው የቸልተኝነት ግድያ ፡- ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት ሊደርስ በሚችል ቀላል እስራት ወይም ከ 2ሺ እስከ 4ሺ ብር ሊደርስ በሚችል መቀጮ ያስቀጣል፡፡

 በተለየ ህይወት፣ ጤንነት ወይም ደህንነት የመጠበቅ የሙያ ወይም የሌላ ግዴታ ያለበት ሰው ግዴታውን በመጣስ የሚፈፅመው የቸልተኝነት ግድያ፡- ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት ሊደርስ በሚችል ቀላል እስራት እና ከ3 ሺ እስከ 6ሺ ብር ሊደርስ በሚችል መቀጮ ይቀጣል፡፡
👍6👏1
 ጥፋተኛው ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን የገደለ ወይም ወንጀሉን የፈፀመው ግልፅ የሆነ ደንብ ወይም መመሪያን ተላልፎ እንደሆነ ወይም የሚያሰክሩ ወይም የሚያፈዙ ንጥረ ነገሮችን ወይም መጠጦችን በመውሰድ እራሱን ከሀላፊነት በሚያስወጣ ሁኔታ ካስገባ በኃላ የተፈፀመ ግድያ ፡- ከ5 ዓመት እስከ 15 ዓመት ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስራት እና ከብር 10 ሺ እስከ 15 ሺ በሚደርስ መቀጮ የሚቀጣባቸው ናቸው፡፡

 ሕፃንን መግደል

በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት ለህፃናት ከተሰጡ መብቶች መካከል በህይወት የመኖር መብት ቀዳሚው ነው፡፡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 36/1/ሀ ስር ማንኛውም ህፃን በህይወት የመኖር መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ የህፃናትን የህይወት እና የአካል ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነትና ግዴታ በዋናነት የወላጆች እና ያሳዳሪዎች ነው፡፡ ለህፃናት ህይወት በህገ መንግስቱ ከተደረገላቸው ጥበቃ በተጨማሪ የወንጀል ህጉ ይህንን ጠበቃ በመጣስ የህፃናት ህይወት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሰው የሚከተሉት የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል፡፡

የወንጀል ህግ አንቀፅ 544 ህፃንን መግደል

 አንዲት እናት ለመውለድ ምጥ በተያዘች ጊዜ ወይም የምጥ ስሜቷ ሳያልፍ ልጇን የገደለች እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት ትቀጣለች፡፡

 አንዲት እናት በዚህ አንቀፅ 1 ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውጭ ልጇን አስባ ወይም በቸልተኝነት የገደለች እንደሆነ፣ ግድያን የሚመለከቱት መደበኛ የህጉ ድንጋጌዎች ማለትም የወ/ህ/አ 539፣ 540፣ 541፣ 543 ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 በተመለከተው ወንጀል በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ተካፋይ የሆነ ሌላ ሰው የህጉ ልዩ አስተያየት ሳይደረግለት እንደነገሩ ሁኔታ እንደ ጥፋቱ መጠን ሰው ስለመግደል በተመለከቱት መደበኛ የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ይቀጣል፡፡

በመጨረሻም በወንጀል ህጉ በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በተመለከተ ከተቀመጡ ድንጋጌዎች ውስጥ በፅንስ ላይ የሚደረግ ፅንስ የማስወረድ ወንጀል ይገኝበታል፡፡ በማንኛውም የእርግዝና ደረጃ የሚገኝን ፅንስ በህግ ከተፈቀደው ምክንያት ውጪ ማስወረድ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ ፍርድ ቤት የቅጣቱን ዓይነትና መጠን የሚወስነው የማስወረድ ተግባሩ የተፈፀመው በእናቲቱ ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገን መሆኑን፣ ድርጊቱ የተፈፀመው በሦስተኛ ወገን ከሆነ እናቲቱ ፈቅዳ ወይም ሳትፈቅድ መሆኑን ከግምት በማስገባት ይሆናል (የወንጀል ህግ አንቀፅ 545) ፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
👍14
ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ👇👇👇👇
እሁድ #ችሎት ከምሽቱ 2:30 በሙስና የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

By #Samuel Kassahun:
Director of Transparency International Ethiopia

#የእለቱ_ችሎት

በትራንስፓረንሲ ኢንተናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን ይመራል

#የችሎቱ_ጭብጥ
ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺን
የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

The Fighting against corruption with fashion or passion

#ውሳኔ
ችሎቱ ቢያመልጥዎት በሌሉበት የሚሰማ ይሆናል።

ቀጠሮው እሁድ ማታ በስልክዎት በ @lawsocieties የቴሌግራም ቻናል በመዝገብ ስዓት ቁጥር 2:30 የመገኘት መብትዎ የተከበረ ነው።

#ትዕዛዝ
ለከሳሽ እና ተከሳሽ ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺን መዝገቡ ክፍት ነው።
ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይመለሱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#የሚነበብ#አለ_ህግ ስም አለበት
https://t.me/lawsocieties
👍2🔥1
በሆቴሎች እና በሬስቶራንቶች ሰራተኞችን ከስርአቱ ዉጪ አለባበስ እንዲከተሉ ማድረግ እንደሚያስቀጣ ተገለፀ!

የመስተንግዶ ሰራተኞች ከሀገሪቱ ባህል ዉጪ ልበሶችን እንዲለብሱ በሚያደርጉት ላይ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቱሪዝም ቢሮ አሳወቀ።ለሆቴል ባለንብረቶች ንግድ ዘርፍ ማህበራት የመስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስን በሚመለከት በተፃፈዉ ደብዳቤ ከባህል የወጣ አለባበስ እንዲቆም ተጠይቋል።

ባለኮከብ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ከፍተኛ እና አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ ፔንሲዮኖችን ጨምሮ በሌሎችም ስራዎች በአስተናጋጅነት አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን ከስነምግባር ዉጪ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ባህል የወጣ አለባበስ እንዳይከተሉ አሳስቧል።የከተማዋ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እንዳሳወቀዉ በደብዳቤው ላይ የተገለፀውን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

Via Addis Zeybe
https://t.me/lawsocieties
👍151👏1
ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺ
👇👇👇የቀጠለ..👆👆👆

የልቦና ውቅር ለውጥ‼️

The Fighting against corruption with fashion or passion?

Key Note Speaker;
Samuel Kassahun:
Director of Transparency International Ethiopia
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

የትራንስፓረንሲ ኢንተናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን

እሁድ ምሽት 2:30 ቀጥታ ስርጭት

🔘 Live on Telegram 👈👈
https://t.me/lawsocieties
#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
👍2
በሐሰተኛ የምስክር ወረቀቶች መገልገል የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት ምን ያህል ያውቃሉ?

**

በኢት
ዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 375 መሰረት ማንም ሰው የሌለውን ሰው መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት፣ ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ማናቸውንም መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ:-
👍3🥰1
.....የቀጠለ
ሀ)  ሕጋዊ ክርክሮች ሲካሄዱ በማስረጃነት የሚቀርቡ፣ አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ወይም የሚያረጋግጡ የሚመስሉ እንደ ጽሑፍ፣ ሌሎች ሰነዶች ወይም ግዙፍ ነገሮች የመሳሰሉትን የፈጠረ እንደሆነ፣ ወይም

ለ) ሐሰተኛ ሰነድ ለማዘጋጀት በሌላ ሰው የጣት ፊርማ፣ ፊርማ፣ ምልክት ወይም ማህተም የተጠቀመ እንደሆነ፣ ወይም

ሐ) እውነተኛውን ጽሑፍ በመለወጥ ወይም በመደለዝ በሐሰተኛ ፊርማ በእጅ በተደረገ ምልክት፣ ወይም በጣት ፊርማ  በማህተም ወይም የሌለውን ስልጣን ወይም ችሎታ እንዳለው አስመስሎ በመፈረም ሐሰተኛ ሰነድን የፈጠረ እንደሆነ፣ ወይም

መ) አንድን ሰነድ፣  በተለይም የፈራሚውን ስም ወይም ፊርማ ወይም የሰነዱን ይዘት፣ አሃዝ፣ ፍሬ ነገር ወይም ዝርዝር መግለጫ በሙሉ ወይም በከፊል በመለወጥ፣ በማሻሻል፣ በመቀነስ ወይም በመጨመር፣ ወይም በማጥፋት ወደ ሐሰተኛነት የለወጠ እንደሆነ፣ ከሶስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ወይም ነገሩ ከባድ በሆነ ጊዜ ከአስር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡

አንቀጽ 378 - ማንም ሰው በሐሰት በተዘጋጀ ወይም ወደ ሐሰት በተለወጠ ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት እንደሆነ፣ በአንቀጽ 375 ላይ በተደነገገው መሰረት ይቀጣል፡፡
አንቀጽ 379 (1) - መንግስታዊ ወይም ወታደራዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወይም ወደ ሐሰት መለወጥ የተፈጸመው:-

ሀ) በአንድ የመንግስት መዝገብ፣ በታወቀ ሰነድ ወይም የህዝብን ጥቅም የሚመለከት ሰነድ ላይ እንደሆነ፣ ወይም

ለ) በመንግስት ወይም በህዝብ መዝገብ በገባ ሰነድ ወይም ሟች ራሱ በእጁ በጻፈው ኑዛዜ ላይ እንደሆነ፣ ወይም

ሐ) የአገር መከላከያን፣ የመከላከያ ሰራዊት አቋምን፣ ድርጅትን፣ የሥራ ተግባርን ወይም ጉዳይ በሚመለከት ሰነድ ላይ እንደሆነ፣ ቅጣቱ ከአስራ አምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይሆናል፡፡

አንቀጽ 379 (2) - ወንጀሉ የተፈጸመው እነዚህን የመሳሰሉትን መዝገቦች፣ ጽሑፎች፣ የታወቁ ሰነዶች ወይም ሌሎች ሰነዶችን እንዲያዘጋጅ፣ እንዲመዘግብ፣ እንዲጠብቅ፣ ወይም ከእነዚህ ውስጥ ቅጂዎች እንዲሰጥ ኃላፊነት በተሰጠው የመንግስት ሰራተኛ እንደሆነ፣ ቅጣቱ ከ5 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይሆናል፡፡

የወንጀሉ አፈጻጸም በጣም ከባድ በሆነ ጊዜ ቅጣቱ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በህጉ መደንገጉን ኢቢሲ አትቷል፡፡
Federal Ethics and Anti corruption commission
https://t.me/lawsocieties
👍5🔥1
Gizachew.doc
1.8 MB
Bahir Dar University, Module on law of traders and Businesses
3👍1
Ministry of Finance Amended the new policy which ban importing of duty free capital goods after business license.

Please check the letter below from ministry of finance regarding importing a capital good duty free, even after business license, but the letter clearly stated that if they get business license and practically start to sell thier product and service, this amndement is not applicable.

EII.
👍4
👍2
ወንጀል ማለት ፡-
በወንጀል ህግ የተከለከሉ ድትጊቶችን መፈፀም ወይም እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ ወይም ግዴታ የተጣለበቸውን ድርጊቶች አለመፈፀም ነው፡፡


በዚህ መሠረት የወንጀል ህጉ ኃላፊነትን የማያስከትል ተግባር የፈፀሙ ሠዎች በወንጀል እንዳይጠቁ ማድረጊያና ወንጀል የፈፀሙ ቢሆንም እንኳን በህጉ ላይ ከተመለከተው ቅጣት ውጪ በዘፈቀደና ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንግድ እንዳይቀጡ መከላከያ መሣራያ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
👍2
የነፃነት መብት
 
በህገ መንግስስቱ አንቀፅ 17 መሠረት ማንኛውም ሰው የነፃነተ መብት እንዳለው ተቀምጧል፡፡ ይህ መብት የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

☑️ከቦታ ቦታ መዘዋወር
☑️በመረጡት ስፍራ መኖር
☑️በፈለጉት ጊዜ ወጥቶ በፈለጉት ጊዜ መግባት
☑️ከመረጡት ሰው፣ ቤተሠብ ወይም
☑️ህብረተሠብ ጋር መቀላቀል
☑️ቢፈልጉም በብቸኝነት መኖር
☑️በማናቸውም ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ተሣታፊ ለመሆን መቻል እና የመሣሠሉት ናቸው፡፡
እነዚህ እውቅና የተሠጣቸው መብቶች ፈፅሞ አይደሉም፡፡ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 17(1) መሠረት በህግ መሠረት ማንኛውም ሰው ነፃነቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ በወንጀል ህጉ ተለይተው ከተቀመጡት ቅጣቶች አንዱ ማገድና መለየት ነው፡፡ የዚህ ቅጣት አላማ ወንጀለኞችን ከህብረተሠቡ ነጥሎ በማስቀመጥ ሌሎች ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ መከላከል ነው፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ወንጀለኛ እሰራት ቢፈረድበት እስሩን እስኪጨረሰ ድረስ ሌላ ወንጀል በመፈፀም የህብረተሠቡን ሠላም አያናጋም የሚል ግምት ስላለ በህገ መንግስቱ እውቅና የተሠጠው የነፃነት መብት ሊያጣ ይችላል፡፡
በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጡትን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በወንጀል ህጉ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ሙሉ በሙሉ መዘርዘር የዚህ ፅሁፍ ዋና አላማ ባይሆንም ከላየ የተዳሰሱት የህገ መነግስቱ አንቀፆች ህገ መንግስቱ እና የወንጀል ህጉ በቀጥታ ትስስር እንዳላቸው ያመለክታሉ፡፡
መንግስት የህብረተሰብን ሠላምና ፀጥታ እንዲሁም የግለሰብን መብትና ነፃነት የማስከበር ሃላፊነት አለው፡፡ ይሄንን ሃላፊነት ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው እና በሚያዘው መሠረት ተገባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ ከእነዚህ እርምጃዎች አንዱ የወንጀል ህግ መደንገግ እና ይህንን ህግ የተላለፉ ሰዎች ወደ ህግ ማቅረብ ይጨምራል፡፡ በነዚህ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ንፁህ ግለሰቦች ሣይጐዱ የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ሣይስተጓሎል ጥፋተኞች እንዲቀጡና ከጥፋታቸው እንዲማሩ ማድረግ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የእነዚህ ህገ መንግስታዊ መርሆች ዋና አላማ መንግስት ከለይ የተገለፀውን ሃላፊነት ሲወጣ ሊያልፈ የማይችለውን ገደብ ማበጀት ነው፡፡ በአጠቃላይ ህገ መንግስት በባህሪው መብቶችና ግዴታዎችን በጥቅል መልኩ የሚያስቀምጥ ሰነድ ነው፡፡ የወንጀል ህግ ደግሞ በህገ መንግስቱ ውስጥ ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶችና ነፃነቶች ተግባራዊ ማድረጊያ መንገድ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
👍2
ውድ የተከበራችሁ #የአለ ህግ ቤተሰቦች የዛሬ ፕሮግራማችን በአለም ዋንጫ ምክንያት ለሚቀጥለው ሳምንት ተራዝሟል።

ሰላም ቆዩ


https://t.me/lawsocieties
👍2