።።።።።። ቀለብ የመስጠት ግዴታ ።።።።
የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር ኑሮውን ለመግፋት በርካታ ነገሮች የሚያስፈልጉት እንደመሆኑ ሁሉም እንደአቅሙ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሰማራት የራሱን እና የቤተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ገቢ ለማግኘት ጥረት ማድረጉ የተለመደ ነው፡፡ ሆኖም ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች መሥራት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚያስችል ገቢ ማመንጨት የማይችሉበት ሁኔታ መኖሩ የነባራዊው አለም እውነታ ነው፡፡ በዚህ መልኩ መስራትና የእራሳቸውን ገቢ በማንጨት ኑሯቸውን መግፋት የማይችሉ ሰዎች ፈታኝ ሁኔታ እንደሚገጥማቸው ታሳቢ በማድረግ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቀለብ የመስጠት ግዴታን እንደመፍትሄ አካቷል። በዚህ አጭር ጽሁፍ የቀለብን ምንነት፣ ቀለብ የማግኘት መብትን እና የመስጠት ግዴታን ከተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንፃር በዝርዝር እንመለከታለን፡፡
።።።።።።።።።። የቀለብ ምንነት ።።።።።።
በዘልማድ ባለው የቃል አጠቃቀም “ቀለብ” የሚለው ቃል በአብዛኛው ከምግብ ጋር በተገናኘ ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላል፡፡ ሆኖም የቤተሰብ ህጉ ቀለብን የደነገገበት እሳቤ ከዚህ ሰፋ ያለ ነው፡፡ የቤተሰብ ህጉ ስለ ቀለብ ሲደነግግ የቀለብ ተቀባዩን ሁኔታና የአካባቢውን ልማድ መሰረት በማድረግ ለምግብ፣ ለመኖሪያ፣ ለልብስ፣ ለጤና መጠበቂያ እና እንደሁኔታው ለትምህርት የሚያስፈልገውን እንደሚያካትት ከአንቀፅ 197 ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ቀለብ የሚለው ቃል ምግብን ብቻ በመግለፅ የተወሰነ ሳይሆን እንደቀለብ ተቀባዩ ሁኔታ መሰረታዊ ፍላጎትን ያካተተ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ቀለብ የመስጠት ግዴታ በዋናነት የሚፈጸመው የቀለቡን ገንዘብ ለተቀባዩ በመስጠት ሲሆን መጠኑም ቀለብ ተቀባዩ ያለበትን ችግር እና የቀለብ ሰጪውን አቅም በማገናዘብ የሚወሰን ይሆናል፡፡
።።።።። ቀለብ የሚጠየቅበት ሁኔታ።።።።
ቀለብ አንድ ሰው ስለፈለገ ብቻ የሚጠይቀው አይደለም፡፡ ይልቁንም ቀለብ የመስጠት ግዴታ የሚኖረው ቀለብ ተቀባዩ ሰርቶ ለኑሮ አስፈላጊ የሆነ ገቢ ለማግኘት አቅም የሌለውና በችግር ላይ የወደቀ ሲሆን ብቻ እንደሆነ የተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 201 ደንግጓል፡፡
።።።። ቀለብ የመስጠት ግዴታ።።።።።።
ቀለብ የመስጠት ግዴታ በቀጥታ በወላጆችና በተወላጆች እንዲሁም በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ሲሆን በእህትና ወንድማማቾች መካከልም ቀለብ የመስጠት ግዴታ እንዳለ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 198 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ቀጥታ የጋብቻ ዝምድና የሚባለው ባል ከሚስቱ ወላጆችና ተወላጆች ወይም ሚስት ከባሏ ወላጆችና ተወላጆች ጋር ያላቸውን የጋብቻ ዝምድና ሲሆን ጋብቻው ከሞት ውጪ በሆነ ምክንያት ሲፈርስ ግን ይህ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ቀሪ ይሆናል፡፡ እነዚህ ዘመዶች ሁሉም በአንድ ጊዜ ለቀለብ ተቀባዩ ቀለብ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡ ይልቁንም ቀለብ የመስጠት ግዴታው በህጉ አንቀፅ 210 ሥር በተቀመጠው ቅድም ተከተል የሚፈፀም ነው፡፡ በዚህ መሰረት
1ኛ የቀለብ ተቀባዩ ባል ወይም ሚስት
2ኛ የቀለብ ተቀባዩ ተወላጆች እንደየደረጃቸው
3ኛ የቀለብ ተቀባዩ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደራጃቸው
4ኛ የቀለብ ተቀባዩ ወንድሞችና እህቶች
5ኛ የቀለብ ተቀባዩ የጋብቻ ተወላጆች እንደየደረጃቸው
6ኛ የቀለብ ተቀባዩ የጋብቻ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደረጃቸው
ባለው ቅደም ተከተል የሚፈፀም ይሆናል፡፡ በህጉ በተደነገገው ቅደም ተከተልም ቢሆን ቀለብ ሰጪዎች ቁጥራቸው ከአንድ በላይ ሊሆን የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ቀለብ ተቀባዩ አንዱን በመምረጥ ቀለብ ሊጠይቅ የሚችል ሲሆን የጋራ ቀለብ ሰጪዎችም መካከላቸው አንዱ ለቀለብ ተቀባዩ ቀለብ እንዲሰጥ የጋራ ስምምነት ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ ቀለብ ተቀባዩም ይህንን ስምምነት ከተቀበለ ከባድ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ከቀሪዎቹ ቀለብ ሰጪዎች መጠየቅ እንደማይችል በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 211 ተደንግጓል፡፡ በሌላ በኩል ከብዙ ቀለብ ሰጪዎች መካከል አንደኛው ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቀለብ ሲሰጡ የነበረ ከሆነ ሳይከፍሉ የቀሩት ድርሻቸውን እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡
ከጉዲፈቻ ጋር በተያያዘ ጉዲፈቻ አድራጊ ቤተዘመዶች ቀለብ ለመስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ካልሆኑ በስተቀር ጉዲፈቻ የተደረገ ልጅ፣ የጉዲፈቻ ተደራጊው ልጅ ባል ወይም ሚስት እንዲሁም የቀጥታ መስመር ተወላጆች ከጉዲፈቻ ተደራጊውን ልጅ የስር ወይም የቀደምት ወላጆች ቤተዘመዶች ቀለብ መጠየቅ የማይችሉ ሲሆን በተመሳሳይ የቀደምት ቤተሰቦች ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ከዘመዶቻቸው ቀለብ ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ጉዲፈቻ የሰጡትን ልጅ ቀለብ ሊጠይቁ አይችሉም፡፡
ሌላው ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ስጦታ ተቀባይ ሲሆን ስጦታ ሰጪው ሰርቶ ለማግኘት አቅም ሲያጣና ፍጹም ድህነት ላይ ሲወድቅ ስጦታ ተቀባይ ቀለብ የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት የፍትሐብሔር ህግ ስለ ስጦታ በሚደነግግበት ክፍል በቁጥር 2458 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የስጦታ ውሉ ላይ እንኳን ቀለብ የመስጠት ግዴታ ስምምነት ባይኖርም ይህ ግዴታ ቀሪ ሊሆን አይችልም፡፡ ስጦታ ሰጪ ቀለብ የመቀበል መብቱን ከሌሎች ግዴታ ካለባቸው ሰዎች መውሰድ የሚችል ሲሆን ይህ በሆነ ጊዜ ቀለቡን የሰጠው ሰው የሰጠውን ቀለብ ከስጦታ ተቀባዩ ሊቀበል እንደሚችል የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2458(3) ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
።።።።። የቀለብ ገንዘብ ሊተላለፍና ሊያዝ የማይችል ስለመሆኑ ።።።።።።
በመርህ ደረጃ ለቀለብ የሚከፈል ገንዘብ ሊተላለፍ ወይም በምንም ሁኔታ ሊያዝ አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ ቀለብ ተቀባዩ ላለበት ችግር አሳቢ ለሚሆኑ ለእርዳታ ለተቋቋሙ ድርጅቶች እንዲሁም ለቀለብ ተቀባዩ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ላበደሩ ሰዎች የቀለብ ገንዘቡ ሊተላለፍ እንደሚችል የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 205 ያሳያል፡፡ ሌላው ማንም ሰው ሊያውቀውና ሊገነዘበው የሚገባው የቀለብ ገንዘብ የማይጠራቀም መሆኑን ነው፡፡ በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 206 መሰረት ቀለብ ተቀባዩ ለኑሮ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ካላቀረበ በስተቀር ቀለቡን መቀበል ካለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሶስት ወራት ውስጥ ቀለቡን ያልተቀበለ ወይም ያልጠየቀ እንደሆነ የተጠራቀመውን ቀለብ መጠየቅ አይችልም፡፡
።።።። ቀለብ ተቀባይ መብቱን የሚያጣበት ሁኔታ።።።።።
በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 200 መሰረት ቀለብ ተቀባይ የሆነ ሰው በቀለብ ሰጪው ላይ ወይም በቀለብ ሰጪው ወደላይ እና ወደታች በሚቆጠሩ ወላጆች ወይም ተወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት ህይወት ወይም ንብረት ላይ የወንጀል ተግባር የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ እንደሆነ ቀለብ የማግኘት መብቱን የሚያጣ ይሆናል፡፡
።።።።። ቀለብ የመስጠት ግዴታን አለመወጣት የሚያስከትለው ተጠያቂነት።።።።።
ከላይ እንደተገለፀው ቀለብ የመስጠት ግዴት ከህግ የመነጨ ሲሆን ባለመብቱና ግዴታ ያለበት ወገን የቀለብ አሰጣጡን በተመለከተ በመስማማት ውል ሊፈጽሙ እንደሚችሉ በህጉ ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ከቀለብ አሰጣጥም ሆነ አቀባበል ጋር በተያያዘ በቤተሰብ ህጉ ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች በሚቃረን መልኩ ስምምነት ሊደረግ እንደማይችል በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 214 ላይ የተደነገገ እንደመሆኑ ይህን የሚቃረን ስምምነት ቢደረግም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

በሌላ በኩል በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀፅ 658 መሰረት ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው ያለ በቂ ምክንያት በህግ መሰረት ሊሰጥ የሚገባውን ቀለብ፡-
• ለባለመብቶቹ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ
• የፍቺ ውሳኔ እስከሚሰጥ ጊዜ ድረስ የፍቺ ጥያቄ ላቀረበ የትዳር ጓደኛ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ
• በህግ መሰረት ወይም በውል በገባው ግዴታ መሰረት ከጋብቻ ውጭ ላስረገዛት ሴት ወይም ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አብሮት ለኖረ ሰው ወይም ከጋብቻ ውጭ ለተወለደው ልጅ ሊያሟላ የሚገባውን የገንዘብ ግዴታ ያልተወጣ ከሆነ
የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን የግል አቤቱ ሲቀርብ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል፡፡
ማጠቃለያ
ቀለብ ሰርቶ ፍላጎቱን ለማሟላት የሚያስፈልገውን ገቢ ማግኘት የማይችል ሰው ከሥጋ ወይም ከቀጥታ የጋብቻ ዘመዶቹ መሰረታዊ ፍላጎቱ እንዲሟሉለት በህግ የተጣለ ግዴታ ሲሆን ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው ግዴታውን በአግባቡ የመወጣት የህግም የሞራልም ግዴታ እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
• ለባለመብቶቹ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ
• የፍቺ ውሳኔ እስከሚሰጥ ጊዜ ድረስ የፍቺ ጥያቄ ላቀረበ የትዳር ጓደኛ አልሰጥም ያለ ወይም መስጠትን ያስተጓጎለ
• በህግ መሰረት ወይም በውል በገባው ግዴታ መሰረት ከጋብቻ ውጭ ላስረገዛት ሴት ወይም ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አብሮት ለኖረ ሰው ወይም ከጋብቻ ውጭ ለተወለደው ልጅ ሊያሟላ የሚገባውን የገንዘብ ግዴታ ያልተወጣ ከሆነ
የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን የግል አቤቱ ሲቀርብ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል፡፡
ማጠቃለያ
ቀለብ ሰርቶ ፍላጎቱን ለማሟላት የሚያስፈልገውን ገቢ ማግኘት የማይችል ሰው ከሥጋ ወይም ከቀጥታ የጋብቻ ዘመዶቹ መሰረታዊ ፍላጎቱ እንዲሟሉለት በህግ የተጣለ ግዴታ ሲሆን ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው ግዴታውን በአግባቡ የመወጣት የህግም የሞራልም ግዴታ እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
Forwarded from ነገረሕግ NegereHig
አከራካሪ_የወንጀል_ሕግ_ድንጋጌዎች_ማብራሪያ_.pdf
1.1 MB
በወንጀል ጉዳዮች የአተረጓጎም ልዩነት ያለባቸው ድንጋጌዎች ላይ ወጥነት ያለው ትርጉም ለማምጣት እንዲቻል የተዘጋጀ የሕግ ማብራሪያ
አዘጋጅ፡- ፍትሕ ሚኒስቴር
አዘጋጅ፡- ፍትሕ ሚኒስቴር
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት
ምድብ ችሎት
አመሰራረት
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተደራሽ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት በአዲስ አበባ ከተማ ስተዳደር 1ዐ እና በድሬደዋ አስዳደር ምድብ ችሎቶች አዋቅሮ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ፍ/ቤቱ ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ 12 ኛ ምድብ ችሎት የሆነውን አዲስ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት በማቋቋም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡
የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት የጉዳዮችን ዓይነት መሠረት በማድረግ የተቋቋመ የመጀመሪያው ምድብ ችሎት ነው፡፡ ምድብ ችሎቱ ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ተያያዥነት ያላቸዉን የንግድ፣ የባንክ እና ኢንሹራንስ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ክርክሮች የሚታይበት ነዉ:
በሀገሪቱ ኢንቨስትመንት _ እንዲስፋፋ እና _ ኢንቨስተሮች ወደ ሀገሪቷ መጥተው በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ ከሚያደርጋቸው አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ከኮንትራት አፈፃጸም እና አጠቃላይ ከኢንቨስትምንት ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን የሚዳኝ ጠንካራ፣ እምነት የሚጣልበት፣ ገለልተኛ እና ፈጣን የፍትህ አካል ወይም ፍርድ ቤት መኖሩ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት መቋቋሙ ለንግድ እና ኢንቨስትምንት ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት በተቀላጠፈ መልኩ ጉዳዮች እንዲስተናገዱ ለማድረግ
በተጨማሪም በዚህ ምድብ የሚታዩ የንግድ እና ኢንቨስትምንት ጉዳዮች ልዩ እውቀት የሚጠይቁ በመሆኑ ባለሙያዎችን በዘርፉ በረጅም እና አጭር ስልጠና በመስጠት በዘርፉ ተገማች እና ውጤታማ ፍትህ አገልግሎት ለመስጠትም ይረዳል።
በመሆኑም የንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮችን በተቀላጠፈ መልኩ እልባት በመስጠት 3ተኛ የመንግስት አካል የሆነው የፍትህ አካሉ የራሱን የሆነ ጉልህ ሚና መጫወት እንዲችል ይህ ምድብ ችሎት ተቋቁሟል። ችሎቱ በጉዳዮች ዓይነት ሲቋቋምም የጉዳዮቹን የተለያ ባህሪ መኖር እና በፍርድ አሰጣጥ ረገድ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ እንዲኖር እንዲሁም በዘርፉ የሚሰጡ የፍትሕ አገልግሎቶች ማሳደግን ግብ በማድረግ ነዉ፡፡
ምድብ ችሎቱ በስሩ 5 የንግድ፣ 5 የባንክ እና ኢንሹራንስ እንዲሁም ] የኮንስትራክሽን ችሎቶችን በመያዝ በገ ችሎቶች የተዋቀረ ነው፡፡ በምድብ ችሎቱ 13 ዳኛ እና 5 ረዳት ዳኞች እንዲሁም አንድ አስተባባሪ ሬጅስትራር እና 2 ሬጅስትራሮች ያሉ ሲሆን በተጨማሪም 8 ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በስሩ ይዟል፡፡
በምድብ ችሎቱ የሚታዩ ጉዳዮች
ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ጋር በተገነኘ ዘርፉ ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት መሆኑ፣ ዘርፉ እንደ ሀገር ያለዉ ፋይዳ ከፍተኛ መሆን፣ የጉዳዩ ዉስብስብነት፣ በሂደቱ በርካታ ወገኖች የሚሳተፉ በመሆኑ የተለያዩ የክርክር ዓይነቶች ይቀርባሉ፡፡ በአብዛኛዉ፡
• በኮንስትራክሽን አሰሪ እና በአማካሪ መሀንዲሱ መካከል የሚደረጉ ከዉል ጋር የተያያዙ ክርክሮች፣
• በአሰሪና እና በዋና ስራ ተቋራጩ ወይም በተቋራጩ እና በንዑስ ተቋራጩ መካከል ከዉል ግዴታ መጣስ፣ ክፍያ፣የስራ መዘግየት፣ የዋጋ ልዩነት፣ የጉዳት ኪሳራ እና ጠቃሚ ነው፡፡ የመሳሰሉት ክርክሮች
በአሰሪዉ እና በፋይናንስ ተቋሞች (ባንክ፣ኢንሹራንስ መካከል) ከጨረታ ማስከበሪያ፣ቅድመ ክፍያ እና ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች፤
• በኮስትራክሽን ግብዓት አምራች ወይም አቅራቢ እና በተረካቢዉ መካከል የሚደረጉ እንደ ዉል አለመፈፀም፣ · የጥራት ችግር እና ክፍያ የመሰሰሉ ክርክሮች፤
. የኮንስትራክሽን ማሽን ኪራዮችን የሚመለከቱ ክርክሮች እና ሌሎች ከኮንስትራክሽን ጋር የተያያዙ ክርክሮች ይቀርባሉ፡፡
የንግድ ጉዳይ
በንግድ እና ኢንቨስትምንት ስር በተዋቀሩት 5 የንግድ ችሎቶች የተለያዩ ከንግድ ማህበራት እና ንግድ ነክ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የሚታይበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ • ማህበር ይፈረስ
• የማህበር ሂሳብ( ትርፍ እና ዕዳ) ይጣራልን፣ ትርፍ ክፍፍል ይደረግልን • አክሲዮን ሽያጭ ውል ይመዝገብብልኝ፣ በውሉ
መሰረት ይፈፀምልኝ • በማህበር አባልነት ልመዝገብ፣ ከማህበር አባልነት ልውጣ፣
• የባለአክሲዮን ምስክር ወረቀት ይሰጠኝ
• የማህበር ስራ አስኪያጅ ይነሳልን፣ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ጥፋት ወይም ኃላፊነት ይረጋገጥልን፣ ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ ወይም ማህበር የሚያስተዳድር ንብረት አስተዳዳሪ ይሾምልን
• ቃለ ጉባኤ ይሻርልን • የስብሰባ ጥሪ ይደረግልን የስብሰባ ጥሪ ይታገድልን
• በአጭር ስነስርዓት የሚቀርቡ ቼክ ክፍያ፣ የብድር ውል ገንዘብ ይከፈለኝ፣ የመተማመና ሰነድ ክፍያ እና የቃልኪዳን ሰነድ ክፍያ ጥያቄዎች
• ከማህበራት መመስረቻ ፅሁፍ እና ከተለያዩ ንግድ ክርክሮች ጋር ተያይዞ ገላጋይ ዳኛ ይሾምልን
• የንግድ ምልክት ምዝገባ ጥበቃ አዋጅ ጋር ተያይዞ ከንግድ ስያሜ አላግባብ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሚነሳ የካሳ እና የክልከላ ጥያቄ፣ አዋጁን በመተላለፍ የገቡ እቃዎች ይወገድልን እና ሌሎች ከአወጁ ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
የባንክ እና ኢንሹራንስ ጉዳይ
መድን ገቢው በመድን ውሉ በመድን ሰጪው ላይ የሚያቀርባቸው ክሶች
• መድን ሰጪው በመድን ውሉ መሰረት በመድን ገቢው ላይ የሚያቀርባቸው ክሶች እንደ አረቦን ይከፈለኝ ያሉ
የመድን ሰጪዎች የመዳረግ መብታቸውን ተጠቅመው የከፈሉት ካሳ ተመላሽ እንዲደረግ የሚያቀርቡት ክስ
• በ3ተኛ ወገን መድን ሽፋን አዋጅ ተገደው የከፈሉት ካሳ ተመላሽ እንዲደረግ የሚቀርብ ክስ
• የህይወት ኢንሹራንስ ካሳ ይከፈለኝ ክስ
• በመልቲሞዳል፣ በአየር በየብስ እንዲሁም በባህርና ትራንስፖርት የጉዞ ላይ ጉዳት ካሳ ከፈለኝ ክስ • ከመልካ ስራ አፈፃጸም ቦንድ ወይም የገንዘብ ዋስትና(financial bond) ጋር የተያያዙ ጉዳዮች • የባንክ ደንበኞች ባንኮች አላግባብ ክፍያ በመፈፀማቸው ወይም በመከልከላቸው ምክንያት ሚያቀርቡት ክስ እና መሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ፍርድ ቤት መር አስማሚ
የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ 1234/2013 መውጣትን ተከትሎ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በወጣው በፍርድ ቤት መር አስማሚ መመሪያ ቁጥር 12/2013 መሰረት ምድብ ችሎቱ የአስማሚ ማዕከል አቋቁሞ የንግድ እና የኮንስትራክሽን ጉዳዮች በመደበኛ ክርክር ከመታየታቸው በፊት በፍ/ቤት መር አስማሚ በኩል ጉዳዮች እየቀረቡ በስምምነት እንዲያልቁ እየተደረገ ይገኛል፡፡
• የአስማሚነት ስራዉም በረዳት ዳኞች አማካኝነት የሚሰራ ሲሆን አዎንታዊ ዉጤት እያስገኘ ይገኛል፡፡

የባለቤቱን እህት አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ . . .
በጉጂ ዞን ነገሌ ከተማ 03 ቀበሌ ውስጥ ታጀበ ከበበ የተባለው ግለሰብ የባለቤቱን ስራ መሄድ በመጠባበቅ ከ14 እስከ 16 ዓመት እድሜ ያላትን ታዳጊ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ይፈጽማል።
ከቀናት በኋላ የታዳጊዋ እህት ሁኔታዋን በመጠራጠር ደጋግማ ብትጠይም ምላሽ ታጣለች፡፡ ታዳጊዋ የደረሰባትን ሳትናገር ከምትኖርበት አካባቢ ብትጠፋም ፖሊስ ባደረገዉ ብርቱ ፍለጋ ወደ መኖሪያ ቤቷ እንድትመለሰ ይደረጋል፡፡
በመቀጠልም ምን እንዳጋጠማት ስትጠየቅ በእህቷ ባለቤት በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር እንደተፈፀመባት እና ነፍሰ ጡር እንደሆነች ቃልዋን ለፖሊስ ታሳውቃለች፡፡
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየዉ የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ አሳልፏል። (ለብስራት ሬድዮ)
#tikvahethmagazine

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንጻ መኖሪያ የሕብረት ስራ ማህበር
አሰራርና አደረጃጀት ደንብ ስራ ላይ ዋለ፡፡
መንግስት በከተማች የሚስተዋለውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስልቶችን ቀይሶ በተለያየ ጊዜ የጋራ መኖርያ ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚው ሲያስተላልፍ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በመንግስት ከተቀረፁት የቤት ልማት ፕሮግራሞች መካከል አንዱ የሆነው የመኖርያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ሲሆን በዚህ የቤት ስራ ልማት ፕሮግራም በተለያየ ጊዜ የከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚ በማድረግ የቤት ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ደረጃ አስተዋጽኦ ነበረው ፡፡
የከተማው አስተዳደር በከተማው ውስጥ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ሰራተኞችን በማደራጀት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስተዳደሩ ከሊዝ ነፃ የሆነ የመሬት ዝግጅት በማቅረብ ዕድሉን ያመቻቸ ሲሆን ይህንኑ ተግባር የሚመራበትን የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንፃ መኖርያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር የአደረጃጀትና አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 129 /2014 በከተማው ካቢኔ ፀድቆ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን የገለፁት የፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ መብራቴ ናቸው ፡፡
https://t.me/lawsocieties
አሰራርና አደረጃጀት ደንብ ስራ ላይ ዋለ፡፡
መንግስት በከተማች የሚስተዋለውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስልቶችን ቀይሶ በተለያየ ጊዜ የጋራ መኖርያ ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚው ሲያስተላልፍ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በመንግስት ከተቀረፁት የቤት ልማት ፕሮግራሞች መካከል አንዱ የሆነው የመኖርያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ሲሆን በዚህ የቤት ስራ ልማት ፕሮግራም በተለያየ ጊዜ የከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚ በማድረግ የቤት ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ደረጃ አስተዋጽኦ ነበረው ፡፡
የከተማው አስተዳደር በከተማው ውስጥ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ሰራተኞችን በማደራጀት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስተዳደሩ ከሊዝ ነፃ የሆነ የመሬት ዝግጅት በማቅረብ ዕድሉን ያመቻቸ ሲሆን ይህንኑ ተግባር የሚመራበትን የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንፃ መኖርያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር የአደረጃጀትና አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 129 /2014 በከተማው ካቢኔ ፀድቆ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን የገለፁት የፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ መብራቴ ናቸው ፡፡
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት 👈
የመወያያ እርዕስ፣
"የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር1156/2011''
እሁድ 👇👇👇👇👇👇
በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ
ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆
Live 🔘 Live on Telegram 👈👈
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Topic_“Labour Proclamation No.1156/2019”
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Topic of the discussion.
⏸Live🔴on Telegram
🔵 Ale_Hig / አለ ህግ
Starting Time: 8:30PM -
[Sunday evening]
Join us: https://t.me/lawsocieties
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
👉 https://t.me/lawsocieties
Subscribe our YouTube👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
.....

*ነጻ የጥብቅና አገልግሎት የመሰጠት ግዴታን*
በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ 943/2008 (የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁ 1262/2014 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 4(ሠ) እና (ረ) ዓቃቤ ሕግ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሃብሄር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕጻናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ እንደሚከራከር እንዲሁም የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዮች እንዲካሱ፣ መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳት ጋር የተያያዙ በፍትሃብሄር ጥቅማቸውን ለማሰጠበቅ እነሱን በመወከል የፍትሃብሄር ክስ እንደሚያቀርብ ተደግጓል።
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 (ሀ) ላይ ነጻ የሕግ ድጋፍን አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን የመቅረጽ፡ አፈጻጸሙን የመከታተልና፡ በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን የማስተባበር ሃላፊነት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ስለመሆኑ ተደንጎ ይገኛል።
በፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 31 ነጻ የጥብቅና አገልግሎት የመሰጠት ግዴታን በጥብቅና ድርጅት ውስጥ ሸሪክ ሆኖ ወይም ተቀጥሮ በሚሰራ ጠበቃ ወይም በግሉ በሚሰራ ጠበቃ ላይ ይጥላል።
ጠበቃው በነጻ የሚሰጠው አገልግሎትም እንደ ጉዳዩ ክብደት እና ቅለት እየታየ በዓመት ከሶስት ጉዳይ እንደማይበልጥ፤ አገልግሎቱ የሚሰጠውም፦ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሰዎች፣ ለበጎ አድራጎት እና ለሲቪክ ማህበራት እና የማህበረሰብ ተቋማት፣ ፍርድ ቤት የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ ለሚጠይቅላቸው ሰዎች እንዲሁም ሕግን፣ የሕግ ሙያን እና የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል ለሚሰሩ ኮሚቴዎችና ድርጅቶች እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 31 ላይ ተመልክቷል።
ይህ ሲሆን ጠበቃ በዓመት ቢያንስ ለሶስት ሰዎች በነጻ የሰጠውን አገልግሎት ለፍትህ ሚኒስቴር ለሚመለከተው ክፍል ካላሳወቀ የጥብቅና ፈቃዱን ሊያሳድስ ሲል ሊጠየቅ እንደሚችል እና በራሱ ተነሳሽነት አገልግሎቱን ለተቸገሩ ወገኖች ሙያውን በነፃ መስጠት እንዳለበት ነው።
ሙያን መሰረት ያደረገ የዜግነት ግዴታ ነው።
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

"ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል "
- ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት የወንጀል ችሎት ዳኛ የሆኑት ፦
1ኛ ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣
2ኛ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ
3ኛ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረዋል።
ይህን ተከትሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እስራቱ ፈጽሞ ሕገወጥ እና በዳኝነት ነጻነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት በመሆኑ በአስቸኳይ ከእስር ሊለቀቁና ድርጊቱ ተጣርቶ ተገቢው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ኢሰመኮ ስለጉዳዩ ባደረገው ማጣራት ዳኞቹ በሕግ የተሰጣቸው ልዩ ጥበቃ መብት በሕጋዊ መንገድ ሳይነሳ እና ዳኞች መሆናቸው ሳይገለጽ ከወረዳ ፍርድ ቤት ተሰጥቷል በተባለ የእስር ትእዛዝ ከሥራ ገበታቸው ላይ ተነስተው የታሰሩ መሆኑን ገልጿል።
የእስር ትእዛዙን የሰጠው የወረዳ ፍርድ ቤት ታሳሪዎቹ ዳኞች መሆናቸውን እንደተረዳ የእስር ትእዛዙን የሻረ መሆኑን አሳውቋል፡፡
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ዳኞቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀው አሳስበዋል።
ትላንት አርብ ኢሰመኮ እስሩን በተመለከተ መግለጫ እስካወጣበት አመሻሽ ድረስ ዳኞቹ በእስር ላይ ነበሩ ፤ ዛሬም ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።
ዛሬ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የዳኞቹ መታሰር " በጣም አሳሳቢ ነው " ብለዋል።
" በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት ሥስት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በአዳማ ከተማ መታሠራቸው በጣም አሳሳቢ ነው " ያሉት ወ/ሮ መአዛ ፥ " ዳኞች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ " ብለዋል።
ወ/ሮ መአዛ ፤ ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው " ስለተከሰተዉ ሁኔታ የበለጠ ለመረዳት እየሞከርን ነዉ። " ሲሉ ገልፀዋል።
" ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ ድርጊቶች በአንዳንድ ክልሎች በዳኞች ላይ ሲፈጸሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ፍርድ ቤቶች ፕሌነም አውግዘው ውሳኔ አስተላልፈው ነበር ። " ሲሉ ወ/ሮ መአዛ አስታውሰዋል።
#tikvahethiopia

የኢትዮጵያ የተረትና ምሳሌ እንዲሁም የልማድ ህግ ተሻረ🙏
ቻይ፣ ታጋሽ፣ ሰራተኛ የድሀ አለኝታ የሚስኪን ትራንስፖርት፣
በጣም በመቻል እና በአገልጋይነት የምትታወቀው አህያን ያከበረ እና በስሟ ዝናን ያተረፈ መልካም ወጣት ይህ ነው።
#አለ_ህግ Ale Hig አለ ህግ Law Societies

Forwarded from Beamlak Tadesse is typing...
የአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢኒስቲትዩት የ15ኛ ዙር ፕሮግራምን በዚህ መልኩ አሳውቋል! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖⚖
26/02/2015 ዓ/ም
ማስታወቂያ
ለ15ኛ ዙር የቅድመ -ሥራ ስልጠና ለመመልመል ለተመዘገባችሁ በሙሉ፣
በቅድመ -ሥራ ስልጠና ምልመላ ማስታወቂያ መሠረት ለምልመላው ከተመዘገቡት መካከል ለፈተና የሚቀርቡትን ለይተን ለጥቅምት 21/2015ዓ/ም እንደምናሳውቅ ና የመግቢያ ፈተናውንም ጥቅምት 30/2015ዓ/ም እንደምንሰጥ ገልጸን ነበር።
ይሁን እንጅ በስራ መደራረብ ምክንያት በተባለው ቀን ማሳወቅ ባለመቻላችን ምክንያት የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ወደ ህዳር 6 ቀን 2015ዓ/ም የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ ለፈተና የሚቀርቡ ተመዝጋቢዎችን ዝርዝር በየተመዘገባችሁበት ዞን ፍትህ መ ምሪዎች በኩል ጥቅምት 28/2015ዓ/ም የምናሳውቅ መሆኑ ን እንገልጻለን።
ኢንስቲትዩቱ
👇👇👇

Subscribe Now 👈👈👈👈
Subscribe Now 👈👈👈👈
በተለያዩ_ጊዜያት_የወጡ_የአብክመ_የህግ_ምርምር_ፈተናዎች.pdf
1.2 MB
የአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢኒስቲትዩት ካወጣቸው ፈተናዎች ለዝግጅት ይሆኑ ዘንድ።
👇👇👇
Via Click Ethiopia
👇👇👇
Via Click Ethiopia