አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
38 የተለያዩ ዕቃዎች ከውጭ እንዳይገቡ ዕገዳ ተጣለባቸው

38 የተለያዩ ዕቃዎች ከውጭ እንዳይገቡ ዕገዳ መጣሉን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ፍቃዱ ድጋፌ በሰጡት መግለጫ፣ የተለዩት ዝርዝር ዕቃዎች ጉምሩክ ኮሚሽን በጥናት የለያቸው ሲሆን ባንኮች ከነገ ጀምሮ “ኤልሲ' መክፈት አይችሉም ብለዋል።

የተለዩት ዕቃዎች ከሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ዝውውር ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በጥናት የተለዩ እና መሠረታዊ ቁሳቁስ እንዳልሆኑም ገልጸዋል።

በዕገዳው ከተለዩት ቁሳቁሶች መካከልም ተሽከርካሪዎች የተካተቱ ሲሆን አሁን ላይ የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ ላይ 2ኛ ደረጃ ላይ መሆኑን አስታውሰዋል።

የቁሳቁሶቹ ዕገዳ መተግበር በአማካኝ ግማሽ ያህል የውጭ ምንዛሪ ሊያስቀር እንደሚችልም ምክትል ገዥው አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል።
https://t.me/lawsocieties
#Dashen Bank Sc#🚩For Fresh & Exp

▪️1 - Customer Service Officer (Maker) – IFB
▪️2 - Attorney Legal Research & Advisory
▪️3 - Senior Attorney, Litigation

▪️4 -Quality Assurance Officer-Contact Center
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3EJe3VJ

▪️Deadline: October 14/22
Vacancy
=======
Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following positions:

1. Bank Trainee
2. Graduate Trainee
3. IS Trainee
4. IS Graduate Trainee
5. Legal Trainee👈👈👈
6. Legal Graduate Trainee
👈👈
7. Engineer Trainee

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website
https://vacancy.cbe.com.et from October 17, 2022 – October 27, 2022.

For requirements and other detail information, please use the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/External_Vacancy_6a87ddb632.pdf
" የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑ እና በህግ እንደሚያስጠይቅ፣

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል።

የማህበረሰብ የጋራ ሀብት በሆነው ፈተና ላይ ሚፈጸም ማንኛውንም አይነት ወንጀል በጋራ መከላከል ይገባል ይላል አገልግሎቱ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።
#tikvahethiopia
https://t.me/lawsocieties
በፍርድ ቤት ተጠርቶ አለመቅረብ

1. ክርክሩን ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ግራ ቀኙ ወገኖች ካልቀረቡ የክስ መዝገቡ ይዘጋል ፡፡ የክስ መዝገብ ከተዘጋ ከሳሹ ተገቢውን ዳኝነት በድጋሚ ከፍሎ መዝገቡን ለማስከፈት ይችላል፡፡፡ ከሳሹ የቀረው በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ካስረዳ ድጋሚ ዳኝነት ላይከፍል የተዘጋው መዝገብ እንዲንቀሳቀስ ዳኛው ሊወስን ይችላል፡፡ ሳሙኤል ግርማ የሕግ አማካሪና ጠበቃ

ተከሳሽ ካልቀረበ እንደ ሁኔታው ተከሳሹ በሌለበት 2. ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ እንዲቀጥል ወይም ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክለት ሊታዘዝ ይችላል፡፡ እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው መጥሪያው ለተከሳሽ ያልደረሰው በከሳሽ ጥፋት ከሆነ ባልደረሳቸው ተከሳሾች ላይ የክስ መዝገቡ ይዘጋል ፡፡ ተከሳሹ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ከታዘዘ ደግሞ በሚቀጥለው ቀጠሮ ቀርቦ በባለፈው ቀጠሮ ያልቀረበው በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ካስረዳ መከላከያውን አቅርቦ እንዲከራከር ሊፈቀድለት ይችላል ፡፡

ተከሳሽ ቀርቦ ከሳሽ ካልቀረበስ ?

ተከሳሹ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ ከሆነ ፍርድ ቤቱ በታመነው መጠን ውሳኔ መስጠት ይችላል ፡፡ ሳሙኤል ግርማ

ተከሳሹ ከካደ መዝገቡ ይዘጋል ሆኖም ከሳሹ የተዘጋው መዝገብ እንዲከፈትለት መጠየቅ ይችላል፡፡ ጥያቄው ተቀባይነት የሚያገኘው ከሳሹ በመጀመሪያው ቀጠሮ የቀረው በቂ በሆነ ችግር መሆኑን ካስረዳ ነው፡፡ ፍረድ ቤቱ ጥያቄውን ከተቀበለ ስለኪሣራውና ስለማናቸውም ወጪ አከፋፈል ተስማሚ መስሎ የታየውን ውሳኔ ከሰጠ በኃላ የተዘጋው መዝገብ እንደገና ተከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል ፡፡

የፍትሐብሄር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር ከ 65 እስከ 75 ያሉት አንቀጾች ይመለከተዋል ፡፡
https://t.me/lawsocieties
የጠበቆች የግብር አከፋፈልን በተመለከተ ከጠበቆች ማህበር ፣ ከፍትህ ሚ/ር እና ከገንዘብ ሚ/ር የተወጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ጥናት እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለዚሁ
ጥናት ይረዳ ዘንድ ለጠበቆች መጠይቅ / questionnaire/ ተበትኖ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተበተነውን መጠይቅ የሞሉት ጠበቆች ቁጥር እጅግ አነስተኛ የሚባል በመሆኑ መጠይቁን ለተጨማሪ ሶስት ቀናት ለጠበቆች ለመበተን የጥናት ቡድኑ ወስኗል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከተውን መጠይቅ በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት ውስጥ በሚመቻችሁ አማራጮች ጎግል ፎርም ወይም በጽሁፍ በመሙላት ለጠበቆች ማህበር ቢሮ/የፍትህ ሚ/ር የጠበቆች ፍቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ገቢ እንድታደርጉልን በማክበር እንጠይቃለን፡፡

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSePvYyBMs9-pbHnd-yd3yXpNwHk6ToOCGI-AuNjeyEj7yLjyg/viewform?usp=sf_link



https://t.me/lawsocieties
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚዎች

ተከራካሪ ወገኖች በተለይ የክስ መልስ እንዲያቀርብ የተዘዘ ወገን የክስ መልሱን በሚያቀርብበት ጊዜ በቅድሚያ መቃወሚያ ካለው መመርመር አለበት ።መቃወሚያዎቹን መቼ መቅረብ አለባቸው ?ለሚለው ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት መቅረብ አለባቸው።

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚባሉት የሚከተሉት ሲሆኑ የተጠቃለሉ

አይደሉም።ሌሎችም አሉ። እነዚህም

1.ክሱ በሌላ ፍርድ ቤት እየታየ ነው

2.ክሱን ያቀረበው ሰው በህግ ችሎታ የለውም

3.በክሱ ውስጥ መግባት የሚገባቸው ወገኖች ሳይገቡ ቀርተዋል


4.የማይገባቸው ወገኖች በክሱ ተካፋይ ሆነዋል

5.ከዚህ በፊት በከሰሰው ክስ ላይ ሊከስባቸው ሲችል ሆን ብሎ የተዋቸው ሀብት ሲሆኑ 6.ፍ/ቤቱ ነገሩን ለመስማት ስልጣን የለውም

7.ክስ የቀረበበት ጉዳይ ከዚህ በፊት በፍርድ የተወሰነ ነው

8.ክሱ በይርጋ የታገደ ነው

9.ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሽምግልና ታይቶ የተፈፀመ እና በእርቅ የተቀጠረ ነው

1ዐ.የወል ሰነዱ ህጋዊነቱን የጠበቀ አይደለም

11.ክሱ ተጣምሮ የቀረበው ያላአግባብ ነው።


የመሳሰሉት ሲሆኑ ተከራካሪ ወገኖች እነዚህን መቃወሚያውን በክስ መልሳቸው ላይ

ካለቀረቡ ና ከተዋቸው ማስረጃ ከተሰማ ወይም ክሱ ከተጀመረ በኃላ እነዚህን መቃወሚያ ማንሳት አይቻልም ፍ/ቤቱ ስልጣን የሌለው ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊያነሳው ይችላል።
Source legal service
A giant ship's engine broke down and no one could repair it, so they hired a Mechanical Engineer with over 40 years of experience.

He inspected the engine very carefully, from top to bottom. After seeing everything, the engineer unloaded the bag and pulled out a small hammer.

He knocked something gently. Soon, the engine

came to life again. The engine has been fixed!

7 days later the engineer mentioned that the total cost of repairing the giant ship was $20,000 to the ship owner.

"What?!" said the owner.

"You did almost nothing. Give us a detailed bill."

The answer is simple: Tap with a hammer: $2

Know where to knock and how much to knock: $19,998

The importance of appreciating one's expertise and experience...because those are the results of struggles, experiments and even tears.

If I do a job in 30 minutes it's because I spent 20 years learning how to do that in 30 minutes. You owe me for the years, not the minutes.

https://t.me/lawsocieties
ክስ መመስረቻ ጊዜ
---------_-__🛑
በሕገመንግሥቱ መሠረት ሰውን ከ48 ሰዓት በላይ ለ1 ሰዓትም እንኳን ማቆየት አይቻልም። በዚህ መሠረት በወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እስኪጣራ በእስር የሚገኝን ሰው፣ ምርመራው ካለቀ በኋላ ክስ እስኪመሠረት ድረስ በእስር ለማቆየት የተፈለገ እንደሆነ ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ ግድ ይላል። ምክንያቱም ከ48 ሰዓት በላይ አልፎም ለቀናት በእስር የነበረውን ሰው ክስ እስከሚመሠረትበት ድረስ በሚል ለተጨማሪ ጊዜ ማቆየት የተፈለገ እንደሆነ ፍርድ ቤት ሳይፈቅድ ማቆየት ጨርሶ ስለማይቻል ነው። የወመሕሥሥቁ 109 ዐቃቤ ሕግን በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲያዘጋጅ ከሚያስገድድ ውጪ ክሱ እስከሚመሠረት ድረስ ግን ተጠርጣሪው በእስር እንዲቆይ አያዝዝም። ስለዚህ ተከሣሹን በእስር ማቆየት ከተፈለገ ፍርድ ቤትን ማስፈቀድ የግድ ነው።

በተጨማሪም ሕጉ ለዐቃቤ ሕግ የሚሰጠው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ ጣሪያው ነው እንጂ ለእያንዳንዱ ጉዳይ እስከ 15 ቀን መቆየት ይችላል ማለት አይደለም ። ስለዚህ ጉዳዩ ግልጽና ብዛት የሌለው ወይም ውስብስብ ካልሆነ ዐቃቤ ሕግ ከ15 ቀንም ቀደም ብሎ ክስ መመሥረት ወይም መወሰን ይጠበቅበታል ማለት ነው። ስለዚህ ፍርድ ቤት ስንት ቀን እንደሚበቃው ጭምር ይወስናል፤ ከተጠየቀው 15 ቀን ውስጥ የሚበቃውን ያህል ብቻ በመፍቀድ ተከሳሹ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 37 መሠረት የተፋጠነ ፍትሕ እንዲያገኝ ያደርጋል ማለት ነው።
በጠበቃ ታምራት ኪዳነማርያም
https://t.me/lawsocieties
Live stream started
Live stream finished (2 hours)
እሁድ እሁድ ሁሌ ማታ ማታ በሳምንት አንድ ቀን የህግ ባለሙያዎች የሚመሩት የውይይት ጊዜ ስንት ስዓት ይመቸወታል?
Anonymous Poll
27%
2:00 ስዓት
41%
3:00 ስዓት
12%
3:30 ስዓት
20%
4:00 ስዓት