አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለመንግሥት ሰራተኞች የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ
==========================

የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 43 ላይ
እንደተመለከተው፣
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በሕመም ምክንያት ሥራ መሥራት ያልቻለ እንደሆነ ደመወዝ የሚከፈልበት የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሙከራ ጊዜውን ላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ ቢወስድም ሕመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው አስራ ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ከስምንት ወር
ወይም በአራት ዓመት ውስጥ ከአሥራ ሁለት ወር አይበልጥም፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከሙሉ ደመወዝ ጋር እና ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከግማሽ ደመወዝ ጋር ይሆናል፡፡
4. የሙከራ ጊዜውን ያላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ከታመመ የህክምና ማስረጃ የሚቀርብበት የአንድ ወር የሕመም ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
5.ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ሲታመም፣ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጠመው በስተቀር በተቻለ ፍጥነት መታመሙን ለመሥሪያ ቤቱ ማሳወቅ አለበት፣ በተከታታይ ከሦስት ቀናት ወይም በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ከስድስት ቀናት በላይ በሕመሙ ምክንያት ከሥራ የቀረ እንደሆነ ለመታመሙ የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
6. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት ሠራተኛ በዓመት ፈቃድ ላይ እያለ መታመሙን የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ካቀረበ የዓመት ፈቃዱ ተቋርጦ የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
7. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (6) መሠረት የተቋረጠው የዓመት ፈቃድ የሕመም ፈቃዱ እንደተጠናቀቀ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡

የህክምና ማስረጃ
“የሕክምና ማስረጃ” ማለት በሀገር ውስጥ አግባብ ባለው ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጠው የግልም ሆነ የመንግሥት የሕክምና ተቋም የሚሰጥ ወይም ከሀገር ውጭ የተገኘና ስለትክክለኛነቱ አግባብ ባለው ባለሥልጣን የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ነው፡፡
የምስክር ወረቀቱ ስለመንግሥት ሠራተኛ የጤና ሁኔታና ስለሚሰጠው የሕመም ፈቃድ መግለጽ አለበት፡፡

#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
244 ክፍት የሥራቦታዎች በ0አመት
at Metu University(For Fresh graduate)

Number of Positions: 244 -positions 0 EXP

Professions: Law, accounting,agribusiness-management,agricultural-economics,agro-forestry,algebra,amharic-teacher,animal-production,applied-mathematics,artificial-intelligence,automotive-engineering,basketball,biology-teacher,business-administration,chemical-engineering,ch emistry-teacher,civics,civil-engineering,clinical-nurse,computer-engineering,computer-science,construction-technology-and-management,control-enginegring,cooperative-accounting,data-base,development-economics,development-studies,earth-science,emergency-and-critical-care,english-teacher,finance-management,folklore-and-literature,food-engineering,forestry,geography,geophysics,gis,health-informatics,hematology,history,horticulture,hotel-management,human-anatomy,human-resource-management,industrial-economics,industrial-engineering,information-technology,irrigation-engineering,journalism,laboratory-technician,leather-engineering,linguistics,logistics,management-information-system-mis,manufacturing-engineering,marketing,mathematics-teacher,medical-doctor,medical-physiology,midwife-nurse,natural-resource-management,oromifa-language-teacher,pharmacist,physics-teacher,plant-breeding,power-engineering,psychiatry,psychology,public-administration,remote-sensing,reproductive-health,road-engineering,rural-development,sociology,software-engineering,soil-science,special-need-education,sport-medicine,sport-science,tourism,transport-engineering,urban-managment,veterinary-medicine,videography,water-engineering,water-resource-management

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇
👉Read Detail:- https://bit.ly/2UaUn8o

አዳዲስና ወቅታዊ የሆኑ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያዎችን ለመከታተል
=>See Detail:- https://ethioworks.com
Forwarded from Qualitymovbot
ጥቆማ ጠቃሚ የህግና ከህግ ጋር ተያያዥ መረጃዎችን እንዲሁም ስለ ህግ ጉዳይና የተለያዩ #ሕጎችን የሚያጋሩ የቴሌግራም ቻናሎችን❗️👇👇👇👇👇👇👇
Our Court - Give your verdict!
___
M
s. K bought a cow for 1,000 ETB then gave it to Mr. B in the form of a trust, and the cow eventually gave birth to three calves. After some time, Ms. K demanded that Mr. B return the cattle or pay her their value of 14,500 ETB. Mr. B, on the other hand, denied receiving any cattle in trust and added that if he is requested to return the cattle or their value, he should also be compensated for the day-to-day expenses incurred for the cattle, which he estimated to be 12,800 ETB.
👨‍⚖🧑‍⚖‍ If you were a judge for this case what would be your judgment, "Should Mr. B return the cattle or their value, and should Ms. K reimburse Mr. B for his cattle-care expenses?"
Feteh Activity in Ethiopia
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
#የቅጥር ውል

የስራ ማከናወኛ ውል ማለት አሰሪው በገባው ውለታ ለአንደኛው ወገን የስራውን ዋጋ ሊከፍለው ስራ ተቋራጩም በኃላፊነት የተሰጠውን አንድ ስራ በገባበት ውለታ ሊፈጽም በሁለቱ ወገኖች የተደረገ ውል እንደሆነ በፍትሐ ብሔር ህግ አንቀጽ 2610 ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ተገልጋዮች የቅጥር ውልን ለመዋዋል ወደመስሪያ ቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣

. ተዋዋይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፣

. የተዋዋይ ወገኖች የታደሰ መታወቂያ፣

. የተቀጣሪው የሙያ ፈቃድ እንደአስፈላጊነቱ፣

. የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረጃ ጽሁፍ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
#ጥንቃቄ ስለ ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 መሰረት፣

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፦
" ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን ይጠብቅ።

የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ ይደነግጋል።

በተጨማሪም በክፍያ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003 መሠረት በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም፡፡

ነገር ግን ከጥናት ለመረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ወቅት ከህግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ፣ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል።

በተጨማሪም ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።
............
ይህ እየተስተዋለ ያለው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል።

ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህንን ህገወጥ ተግባር የሚሠሩ አካላትን ሲመለከት ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን ። "
#የኢትዮጵያ_ብሄራዊ_ባንክ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
ለፈተናው ያለፉ አቃቢያን ህግ .docx
37.6 KB
ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በከተማ እና በስሩ ለሚገኙ ክ/ከተማዎች የዐቃብያነ ህግ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት የህግ ባለያዎችን በዝውውር ለማወዳደር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የተመዘገባችሁ የህግ ባለሞያዎች እንዳላችሁ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የወጣውን መመዘኛ መስፈርት ያሟላችሁ የህግ ባለሞያዎች ከዚህ በታች የስም ዝርዝራችሁ የተገለፀ መሆኑን እያሳወቅን የፈተናው ቀን የት እና መቼ እንደሆነ በዚሁ ገፅ የምናሳውቃችሁ በመሆኑ ለፈተና እየተዘጋጃችሁ እንድትጠብቁ እናሳውቃለን፡፡

Via ህግ ክሊኒክ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
2013 E_C CASSATION DECISIONS.pdf
56.3 MB
ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
ባንኮች የብድር ማመልከቻ ከመቀበል ጀምሮ ደንበኛ ወይም ተበዳሪ የሚፈልገውን የብድር መጠን ለመፍቀድ እንዲሟላ የሚፈልጉት፣ የጋራ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም መስፈርቶች አሉ፡፡ አነዚህን መስፈርቶችና ከጀርባ ያሉትን ምክንያቶች በሚገባ መገንዘብና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በሂደት ማሟላት የብድር ጥያቄ ውድቅ እንዳይሆን ከማገዝ ባለፈ፣ የሚፈለገውን የብድር መጠን ሳይቀናነስ ከባንኮች የማግኘት ዕድልን ያሰፋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://www.bankofabyssinia.com/loanr/

#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
የዳረጎት ውል
🔴።።።።።።።።።።።።።።።።።።።🔴
የገንዘብ መብትን ስለ ማስተላለፍ ስለ መዳረግ (ዳረጎት)በፍትሐ ብሔር ህግ አንቀጽ 1962 እስከ 1975 በዝርዝር ተቀምጧል፡፡

“የገንዘብ መብትን ማስተላለፍ በህግ ወይም በውል ካልተከለከለ ወይም የጉዳዩ ተፈጥሮ ካላገደው በቀር የባለእዳው ፈቃጅነት (ፈቃደኝነት) አስፈላጊ ሳይሆን ባለገንዘቡ መብቱን ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ይችላል፡፡” በማለት የፍ/ብ/ህ አንቀጽ 1962 ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ተገልጋዮች የዳረጎት ውልን ለመስጠት ወደመስሪያ ቤታችን ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣

. የዳረጎት ሰጪው ያገባ ወይም ያላገባ ከሆነ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት /ውክልና፣

. የክፍያው ጊዜ የደረሰ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ የገንዘብ መብት ያለው የውል ሰነድ፣

. የተዋዋይ ወገኖች የታደሰ መታወቂያ፣

. ተዋዋይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጫ ሰነድ፣

. በውሉ ላይ የተገለጸ ንብረት ካለ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ፣

. የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረጃ ጽሁፍ፣ የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፣

. በማንኛውም መልኩ ንብረቱ ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ፣

. ባንኮች ባለገንዘብ ሲሆኑ እዳው ከባለእዳው ወደ ዳረጎት ተደራጊው እንዲተላለፍ መፍቀዱን በዚህ ተቋም አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተገልጋዮች የተባሉትን ዝርዝር ነገሮች አሟልተው ሲቀርቡ ለዚህ አገልግሎት የሚወስደው ጊዜ 25 ደቂቃ ነው፡፡

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ share በማድረግ የሙስናን ወንጀልና ብልሹ አሰራርን ይከላከሉ::
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/Lawsocieties
።።።።።።።። #አለ_ህግ #Ale_Hig ።።።።።።
@Lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

በፌስቡክ Facebook
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም Telegram
https://t.me/lawsocieties

ሊክድን LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

በ ቲክቶክ Tiktok
tiktok.com/@lawsocieties

ትዊተር Twitter
https://twitter.com/Lawsocieties?t=VFQWzXMBnNQnXyZu7z52bQ&s=09

በዩቲዩብ YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw

Email address
lawsocieties@gmail.com

Telegram Bot
@LawsocietiesBot
👍👍👍👍👍👍👍👍❗️❗️❗️❗️❗️❗️


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።🙏
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ላይ ስላለው ተፈጻሚነት የሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም
በአሠሪና ሠራተኛ ህግ አፈጻጸም አስቸጋሪ ሆነው ከቆዩት ጉዳዮች አንዱ አዋጁ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ላይ ያለውን ተፈጻሚነት ይመለከራል። በእርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ አዋጁ ግልጽ ነው።
ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች አዋጁ ተፈጻሚ እንዳይሆን ካልተደረገ በቀር የአዋጁ ተፈጻሚነት ጥያቄ ውስጥ አይገባም
ሆኖም ትልቁ ችግር የአዋጁ የተፈጻሚነት ወሰን ሳይሆን እነዚህ ድርጅቶች ከዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች ወይም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከሚያደርጉት ስምምነት የመነጨ ያለ መከሰስ መብት ስለሚኖራቸው የስራ ክርክር ጉዳይ ሳይታይ ክሱ ወዲያው ውድቅ ይደረጋል።
በ ሰ/መ/ቁ 98541 ቅጽ 17 (አመልካች አቶ አለማየሁ ኦላና እና ተጠሪ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (UNDP) ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም.) ተጠሪ በዋናው ክርክር ሳይከራከር መዝገቡ አፈጻጸም ደረጃ ላይ እያለ ያለ መከሰስ መብቱ በምክንያትነት ተጠቅሶ አመልካች በፍርድ ያገኙትን መብት ተነጥቀዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም በተወሰነ መልኩ ይህንን ኢ-ፍትሐዊ የመብት መጣስ የሚያስቀር ይመስላል።
ምክር ቤቱ በውሳኔው ላይ ለሁለት መሰረታዊ ነጥቦች እልባት ሰጥቷል። ይኸውም

1. ያለ መከሰስ መብት ተፈጻሚነቱ ከዲፕሎማቲክ መብትና ድርጊት ጋር በተያያዘ እንጂ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ አይደለም።

2. ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገቡት ውል መሰረት ያለ መከሰስ መብት ሲያገኙ በውሉ የተመለከተው የአለመግባባት መፍቻ መንገድ ተግባራዊ መሆን ካልቻለ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን አይቶ የመዳኘት ስልጣን አላቸው። @Lawsocieties