አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አንድ ሚስት ባሌ እወድሻለሁ አይለኝም ብላ ከሰሰችው።
ከዚያም ባል፣ ያገባሁሽ እኮ ስለምወድሽ ነው። ባልወድሽ እኮ አላገባሸም ነበር።
ነገር ግን ሀሳቤን ስቀይር እነግርሻለሁ።አለ_ህግ @Lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
#Abay Insurance Sc#4 - Positions

▪️1 - Attorney I
▪️2 - Accountant II
▪️3 - Auditor II
▪️4 - Manager, Recovery Division (Legal)
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/39227Rg

▪️Deadline - May 15/2022
392_2016_commercial_registration_and_licensing_council_of_ministers.pdf
964.6 KB
የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ደንብ
Cassation 1-24.pdf
72.6 MB
ሁሉም የሰበር ውሳኔዎች በአንድ ከቅፅ 1-24
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
አለ_ህግ ✳️ Law Societies✳️
@lawsocieties
#አለ_ህግ#Ale_Hig, ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉንም ሕጎችና ባለሙያዎች እዚሁ ያገኛሉ🔴 All in one, for All. መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
#Share

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #አለ_ስራ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties
6ቱ መሰረታዊ የዳኝነት የስነ ምግባር መርሆች
The 6 Basic Principles of Judicial Ethics:

1. የዳኝነት ነፃነት/Independence/

2. ገለልተኝነት/Impartiality/

3. ቅንነት/Integrity/

4. ስነ ምግባር አክባሪነት/Propriety/

5. እኩልነት/Eqality/

6. ሙያዊ ብቃት እና ታታሪነት /Competence and Diligence/

👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
12ቱ መሰረታዊ (ሥነ ምገባር መርሆች)

➢ቅንነት /Integrity/

➢ታማኝነት / Loyality/

➢ግልፅነት /Transparency/

➢ሚስጢር ጠባቂነት/Confidentiality/

➢ሐቀኝነት/Honesty/

➢ ተጠያቂነት/Accountability/

➢የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም/Serving Public Interest/

➢ሥልጣንን በአግባቡ መጠቀም/Exercising Legitimate Authority/

➢አለማዳላት/Impartiality/

➢ሕግ ማክበር/Respecting the Law/

➢ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት /Responsiveness/
አርዓያ መሆን /Leadership/

👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

#አለ_ህግ . #Ale_Hig
Forwarded from ..?
ሰላም አለ ህጎች እንዴት ናችሁ ነፃ የህግ ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን የሚል ማስታወቂያ አይቼ ነው ፍቃደኛ ከሆናችሁ .... ፍቺ በንብረት ላይ ስላለው consequence ነው! እንደሚታወቀው በእኛ ህግ መሰረት personal property ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በፍቺ ግዜ የባለ ንብረቱ እንደሚሆን ያስቀምጣል! ነገር ግን የኔ ጥያቄ personal property ላይ በጋራ እያሉ ተጨማሪ ነገር add ቢያደርጉበት ውጤቱ ምን ይሆናል? መለትም ለምሳሌ ሚስት ባዶ መሬት ከቤተሰቦቿ ብትወርስና በትዳር ዘመኗ በጋራ ቤት ቢሰሩበት በፍቺ ጊዜ እንዴት ይሆናል?
Forwarded from ሕግ ቤት
The Ethiopian Law Schools Association (ELSA) has joined the International Association of Law Schools (IALS).
______________________
IALS is an association of more than 230 law schools and departments from over 70 countries representing more than 10,500 law faculty members.

By joining this association ELSA will have an open and independent forum for sharing experiences and discussing diverse ideas about legal education throughout the world.

It is to be recalled that ELSA was established in August, 2021 with the support of Feteh.
Via Feteh Activity Ethiopia
የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ይዟቸዉ የመጣ አዳዲስ ነገሮች
-----------------------------------------------

እንደሚታወቀዉ የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 (ካሁን በዉሀላ አዲሱ የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ተብሎ የሚጠራዉ) ፀድቆ ወደተግባር ገብቷል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አዋጁ ይዛቸዉ የመጣዉን አዳዲስ ነገሮች በሁለት ከፍል ለመቃኘት አንሞክራለን፡፡ የመጀመሪያዉ ክፍል ከፍ/ቤት የለት ተለት ስራ ጋር የተያያዙ ድንጋጌዎችን የምንቃኝ ሲሆን ሁለተኛዉ ክፍል ደግሞ አስተዳደራዊ እንድምታ ያላቸዉን አንቀፆችን ለመቃኝት እንሞከራለን፡፡

“መሰረታዊ የህግ ስህተት” ለሚለዉ ፅንስ ሐሳብ ትርጉም የተሰጠዉ ስለመሆኑ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት የፌደራልና የክልል የፍርድ ቤት መዋቅር እንደሚቋቋም በመደንገግ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት “መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት” ያለባቸዉን ማናቸዉንም ዉሳኔዎች የማየት ስልጣን የሰጠዉ ቢሆንም “መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት” ለሚለዉ ፅንስ ሐሳብ በቀደሙት ህጎች ትርጉም ያልተሰጠዉ ወይም በዚህ ፅንስ ሐሳብ ስር ሊሸፈኑ የሚችሉ የህግ ስህተቶችን ለመለየት የሚያስችል መስፈርት ያልተቀመጠ በመሆኑ በፍትህ ስርአቱ ወጥነትና ተገማችነት ላይ የራሱን የሆነ ጥቁር ጥላ አሳርፏል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ተመሳሳይ ጭብጥ የያዙ ጉዳዮችን አንዱን መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለበት ብሎ ሲቀበል ሌላኛዉን ደግሞ መሰረታዊ የሆነ የህግ ግድፈት የለበትም በማለት መዝገቡን ዘግቶ ባለጉዳዮዎችን ማሰናበቱ ነዉ፡፡ በርግጥ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምኛዉንም መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያበትን ጉዳይ ሰበር እንዲያይና ዉሳኔዉም አስገዳጅ እንዲሆን መደረጉ በመላ ሀገሪቷ ወጥነት ያለዉ የህግ ትርጉም እንዲኖር የሚያደርግ ቢሆንም “መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት” ማለት ምን ማለት ነዉ? ለሚለዉ ጥያቄ በህግ ምላሽ ያልተሰጠዉ በመሆኑ በጠቅላይ ፍ/ቤት የሚታዩ ጉዳዮች ወጥነትና ተገማችነት እንዳይኖረዉ ከማድረጉም በሻገር ዜጎች ላልተገባ ወጪና እንግልት እንዲዳረጉ እድል ፈጥሯል፡፡

ይህንን ችግ በሚቀርፍ መልኩ አዲሱ የፍ/ቤቶች አዋጅ በአንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 4 ስር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ማለት ምን ማለት እንደሆነና በዚህ ፅንስ ሀሳብ ስር ሊሸፈኑ የሚችሉ የህግ ስህተቶችን ለመለየት የሚያስትል መለያ መስፈርት አስቀምጣል፡፡ መዚህ አንቀፅ መሰረት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ማለት ቀጥሎ ከተዘረዘሩት መካከል አንዱ እና ፈትህን የሚያዛባ ጉልህ የህግ ስህተት ያለበትን በዚህ አዋጅ አንቀፅ 10 መሰረት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሊታዩ የሚችሉ የመጨረሻ ዉሳኔ፣ ፍርድ፣ ብይን፣ ትእዛዝ ናቸዉ፡-

ሀ. የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌዎች የሚቃረን፣
ለ. ሕግን አላግባብ የሚተረጉም ወይም ለጉዳዩ አግባብነት የሌለዉን ሕግ የሚጠቅስ፣
ሐ. ለክርክሩ አግባብነት ያለዉ ጭብጥ ሳይያዝ ወይም ከክርክሩ ጋር የማይዛመድ አግባብነት የሌለዉ ጭንጥ ተይዞ የተወሰነ፣
መ. በዳኝነት ታይቶ ሊወሰን የሚገባዉን ጉዳይ ውድቅ በማድረግ የተወሰነ፤
ሠ. በፍርድ አፈጻጸም ሂደት ከዋናዉ ፍርድ ጋር የማይገኛኝ ጥእዛዝ የተሰጠበት፣
ረ. ጉዳዩን አይቶ የመወሰን የዳኝነት ሥልጣን ሳይኖር የተወሰነ፣
ሰ. የአስተዳደር አካል ወይም ተቋም ከህግ ዉጭ የሰጠዉ ዉሳኔ፣
ሸ. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ ዉሳኔ በመቃረን የተወሰነ፡፡ በማለት ትርጉም ሰጥቶታል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የታዩ ጉዳዮችን በሰበር የማየት ስልጣን የጠበበ ስለመሆኑ

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 78 መሰረት የፌዴራልና የክልል ፍ/ቤት እራሳቸዉን በቻሉ መልኩ የተቋቋሙ ሲሆን በአንቀፅ 80 ንዑስ አንቀፅ 3(ሀ ና ለ) መሰረት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የታዩ ጉዳዮችን ጨምሮ ማንኛዉንም መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ወሳኔ የማየት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ስልጣን መሰረት በማድረግ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ማንኛዉንም ወሳኔ እያየ የቆየ ቢሆንም እዲሱ የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ይህንን ስልጣን አጥብቦታል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልሎች ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጡ ዉሳኔዎችን በሰበር ማየት የሚችለዉ ዉሳኔዎቹ የህገ-መንግስቱን ድንጋጌዎች ወይም አስገዳጅ የሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ዉሳኔዎችን በመቃረን የተሰጡ ዉሳኔዎች እንደሆኑ ወይም ክፍተኛ የህዝብ ጥቅም ወይም ሐገራዊ ፍይዳ ባለዉ ጉዳይ ላይ የክልሉን ህግ ያለ አግባብ በመተርጎም ወይም አግባብነት የሌለዉን ህግ በመጥቀስ የተሰጠ ዉሳኔ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 10 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ይህ ድንጋጌ የሰበር ችሎቱን የመዝገብ ፍሰት በመቀነስ የተፋጠነ ፍትን ለመስጠት የሚያስችል ቢሆንም ወጥነት ያለዉን የህግ ትርጉም በመላ ሀገሪቷ እንዲኖር ከማስቻል አንፃር ዉስንነት ሊኖረዉ ይችላል፡፡
የፍታብሔር ፍ/ቤቶች የስረነገር ስልጣን ስለመሻሻሉ
በቀድሞ የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 መሰረት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እስከ አምስት መቶ ሺ ብር(500‚000.00) የሚደርሱ ክፍተኛዉ ፍ/ቤት ደግሞ ከአምስ መቶ ሺ ብር በላይ የሆኑ የፍታብሔር ጉዳዮችን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የነበረዉ ቢሆንም በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 11(1) አና 14 መሰረት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እስከ አስር ሚሊዮን ብር(10‚000‚000.00) የሚደርሱ ክፍተኛዉ ፍ/ቤት ደግሞ ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የፍታብሔር ጉዳዮችን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

የሰብአዊ መብጥ ጥሰትን የሚመለከቱ አቤቱታዎች ተቀብሎ ተገቢ የሆነ ዉሳኔ የመስጠት ስልጣን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠ ስለመሆኑ
የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ አንቀፅ 11(3) ላይ እንደተደነገገዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማንኛዉም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት ምዕራፍ ሶስት ስር የሰፈሩትን መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶቸችን ለማስከበር የሚያስችል ተገቢ የሚለዉን ፍርድ፣ ትዕዛዝ ወይም ዉሳኔ የመስጠት ስልጣን የተሰጠዉ ሲሆን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 4 ስር ማንኛዉም በጉዳዩ ላይ መብት ወይም ጥቅም ወይም በቂ ምክንያት ያለዉ ሰዉ የመሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች ጥሰትን በሚመለከት አቤቱታ የማቀረብ መብት ያለዉ ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ የኢትዮጲያ መንግስት ሶስት መሰረታዊ ግዴታዎች የተጣለበት ሲሆን ከነዚህ መካከል ሰብአዊ መብቶችን የማክበር፣ የማስከበር ግዴታዎች ይገኙበታል፡፡ ይህ ድንጋጌ መንግስት በህገ-መንግስቱና በአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግጋት የተጣለበትን የማክበርና የማስከበር ግዴታ እንዲወጣ ከማስቻሉም ባሻገር በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጎጂ የሆኑ ፣ ያላግባብ በእስርላይ ያሉ ወይም አቤቱታ ማቀረብ በማይቻልበት ሁኔታ ዉስጥ ያሉ ግለሰቦች በአፋጣኝ ፍትህ እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል፡፡

ለአዲስ አበባና ድሬዳዋ የአስተዳደር ወይም ከተማ ነክ ፍ/ቤቶች የተሰጡ የፍታብሔር የዳኝነት ስልጣን
የአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደር ፍ/ቤቶች በከተማዉ ቻርተር መሰረት የተሰጣቸዉ የዳኝነት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 5 ንዑስ አንቀፅ 1(ደ) መሰረት በከተማዎቹ በሚኖሩ ግለሰቦች መሀከል የሚደረጉ እስከ አምስት መቶ ሺ ብር /500‚000/ ድረስ የሚደርሱ የገንዘብ ፣ ዉልና የብድር ጉዳዮችን የማከራከርና ዉሳኔ የመስጠት ስልጣን ተሰጥታቸዋል፡፡
Source:- FDRE Attorney General የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
#አለ_ህግ #Ale_Hig
አለሕግAleHig ️ pinned «ሰላም አለ ህጎች እንዴት ናችሁ ነፃ የህግ ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን የሚል ማስታወቂያ አይቼ ነው ፍቃደኛ ከሆናችሁ .... ፍቺ በንብረት ላይ ስላለው consequence ነው! እንደሚታወቀው በእኛ ህግ መሰረት personal property ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በፍቺ ግዜ የባለ ንብረቱ እንደሚሆን ያስቀምጣል! ነገር ግን የኔ ጥያቄ personal property ላይ በጋራ እያሉ ተጨማሪ…»
ማስታወቂያ ለጥብቅና ፈቃድ ተፈታኞች❗️🙏
ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት ለፈተና የተቀመጣችሁ የህግ ባለሙያዎች የፈተና ውጤት ለመሳወቅ የተዘጋጀውን ማስታወቂያ ከዚህ በታች አጋርተናል፡፡

በፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ ያላችሁ ከዛሬ ግንቦት 05 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑም በማስታወቂያው ተገልጿል፡፡

ላልደረሳቸው በማጋራት እንድታግዙን እንጠይቃለን
#አለ_ህግ #Ale_Hig
🔴Exit Exam🙏የሕግ መዉጫ ፈተና

ሠላም እንዴት ናችሁ ዉድ የ2014 የሕግ መዉጫ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ፣
ፈተናው 🔴 ከግንቦት 29 እስከ ሠኔ 5 የሚሠጠዉ ፈተና እስካሁን ምንም ለዉጥ ያልተደረገ መሆኑን አዉቃችሁ ዝግታችሁን እንድትቀጥሉ እየገለጽን ለውጥ የሚኖር ከሆነ የምናሳዉቅ መሆናችንን እንገልፃለን።

መሥፍን እሸቱ የ ሕግ ት/ ቤቶች አስተባባሪ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
#Update
.
የ2014አም መውጫ ፈተና አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግንቦት ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ይታመናል።ከዚህ በፊት በፃፍኩት ፅሁፍ ላይም ተፈታኞች መዘናጋት እንደሌለባችሁና ጥናታችሁን በአግባቡ ልታጠኑ እንደሚገባ አሳውቄ ነበር።በግል መስመር እጅግ በጣም ብዙ ተፈታኞች በእርግጥም ፈተናው ግንቦት ወር ላይ ይሰጣል ወይ እያላችሁኝ ነው።እኔም በተደጋጋሚ እንደምገልፀው አድስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስና ባለድርሻ አካላቱ ተራዝሟል እስካላሉ ድረስ ሳትዘናጉ ጥናታችሁን ተከታተሉ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታም ፈተናው ግንቦት ወር እንደሚሰጥ እናምናለን ብለዋል የELSA ፕሬዝደንትና የኮንሰርቲየሙ ዋና ፀሃፊ።
.
.
#Ahmed.M