አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ፍርድ ቤትን መድፈር ምን ማለት ነው?
ፍርድ ቤት መድፈርን የተመለከተው የኢትዮጵያ ሕግ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉና በወንጀል ሕጉ ላይ ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ዘጠነኛ መጽሐፍ ከአንቀጽ 480-482 ፍርድ ቤትን ለማስከበር ፍርድ ቤቶች የተሰጣቸውን ሥልጣን በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ በዚህ ሕግ መሠረት የማንኛውም ፍርድ ቤት ችሎት ዳኛ ፍርድ ቤቱንና የዳኝነት ሥራ አካሄድ ሥነ ሥርዓትን ለማስከበር ማናቸውንም አስፈላጊ መስሎ የታየውን ዕርምጃ እንዲወስድ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ለማስፈጸም ለፍርድ ቤቱ ችሎት ክብር ወይም ለዳኝነቱ ሥነ ሥርዓት መልካም አመራር ተቃራኒ የሆነ ጠባይ የሚያሳየውን ማንኛውንም ተከራካሪ ወገን ወይም ጠበቃ ወይም በችሎት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም ሰው ተቃራኒ ተግባር በሚሠራበት ጊዜ በያዘው መዝገብ ላይ የገንዘብ መቀጮ ሊወስንበት ይችላል፡፡ 
የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 481 እና የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 449 ለፍርድ ቤት መድፈር ዝርዝር ትርጉም የሚሰጡ ሲሆን፣ የአፈጻጸሙ ሥርዓትና ቅጣቶቹንም ደንግገዋል፡፡
የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 449 ላይ የተደነገገውን ስንመለከት ፍርድ ቤትን መድፈር በፍርድ ቤት ውስጥ ወይም ከፍርድ ቤት ውጪ ሊሆን የሚችል ሲሆን፤ ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት ምርመራ በሚደረግበት ወይም የፍርድ ሥራ በሚከናወንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱን ወይም የዳኝነት ሥራ በማከናወን ላይ ያለውን ዳኛ በማናቸውም መንገድ ከሰደበ፣ ካወከ ወይም በነዚሁ ላይ ካፌዘ ወይም ከዛተ ወይም የፍርድ ቤቱን ሥራ በማናቸውም ሌላ መንገድ ካወከ፤ ወይም ደግሞ ፍርድ ቤቶች አከራካሪ የሆነ ቦታን ለመመልከት በአካል ከፍርድ ቤት ውጭ ሥራቸውን ሲያከናውኑ፣ በተዘዋዋሪ ችሎት ወይም ከያዙት መዝገብ ጋር በተያያዘ ከፍርድ ቤቱ ውጭ የተፈጸሙ ድርጊቶች በሙሉ የፍርድ ቤቱን ሥራ የሚያውኩ ከሆነ በፍርድ ቤት መድፈር ሊያስጠይቁ ይችላሉ፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው በችሎት ውስጥ ከሆነ ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት ወይም ከሶስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጥፋት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሳያደርግ ወዲያውኑ በጥፋተኛው ላይ ቅጣት ሊወስን ይችላል፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው ከችሎት ውጭ ሆኖ ዳኛው ሥራውን እያከናወነ ባለበት ጊዜ ከሆነ፣ ቅጣቱ ከስድስት ወር የማይበልጥ ቀላል እሥራት ወይም ከአንድ ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይሆናል፡፡
ሌላው ሊዘነጋ የማይገባው ቁምነገር ወንጀሉ የተፈጸመው በችሎት ወይም በማናቸውም ቦታ የዳኝነት ሥርዓት በሚካሄድበት ጊዜ ሆኖ በኃይል ወይም በማስገደድ ከሆነ፤ አግባብ ያለው ድንጋጌ /አንቀጽ 441/ በተደራቢነት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ማንም ሰው አንድ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ ግዴታው የሆነውን ተግባር እንዳያከናውን በዛቻ፣ በማስገደድ ወይም በኃይል ድርጊት ካሰናከለ ወይም ይህን ግዴታውን እንዲያከናውን ወይም ማድረግ የሌለበትን እንዲያደርግ ካስገደደ ወይም የመንግሥት ሠራተኛን ወይም በስራው የሚረዳውን ሰው የደበደበ ወይም የኃይል ወይም የማስገደድ ድርጊት ወይም ማናቸውንም ሌላ የማስገደድ ድርጊት ከፈፀመ
ከሶስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ ተደንግጓል። እንደጥፋቱ ከባድነት መጠንና እንደ ተበዳዩም የሥራ ደረጃ ተበዳዩ በጦር መሣሪያ ወይም በሌላ መሣሪያ አማካይነት ተዝቶበት፣ ተገድዶ ወይም ተደብድቦ ከሆነ፤ ቅጣቱ ከአምስት ዓመት የማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይሆናል፡፡
የእጅ እልፊቱ ወይም የኃይል ተግባሩ በተበዳዩ ላይ የአካል ጉዳት ወይም የጤንነት ጉድለት ካስከተለ፤ በተጨማሪነት በሌሎች ድንጋጌዎች ይታያል።
የሕጉ ዓላማ
በአብዛኛው ፍርድ ቤት መድፈር ዳኞች ለራሳቸው የግል ጥቅም ሲሉ ግለሰቦችን የሚቀጡ እንደሆነ ማሰብ በኅብረተሰቡ የተለመደ ነው፡፡ ሆኖም ዳኛው በግለሰብ ማንነቱ ላይ ብቻ የተቃጣን ድርጊት እንደማንኛውም ሰው ክስ አቅርቦ ሊጠይቀው የሚገባ እንጂ ከዳኛው ጋር የተያያዘ ተግባር ሁሉ ፍርድ ቤትን መድፈር ላይሆን ይችላል፡፡ ፍርድ ቤትን መድፈር በሕግ የተካተተበት ዓላማ የፍርድ ቤቱን ክብር ለመጠበቅ፣ የፍትሕ ሥርዓቱን ሕልውና ለመጠበቅ እንዲሁም ኅብረተሰቡ በዳኝነት አካሉ (በፍርድ ቤት) ላይ ያለውን መተማመን ለመጠበቅ ታስቦ ነው፡፡ የዳኝነት አካሉ ከሕግ አውጪውና ከሕግ አስፈጻሚው ጋር በፖለቲካ፣ በሕዝብ ገንዘብ አስተዳደርና በወታደራዊ አመራር እንደማይወዳደር ግልጽ ነው፡፡ ለፍርድ ቤት ህልውና መሠረት በሕዝብ መታመን ሲሆን ሥራውን በአግባቡ እንዲያከናውን ሕዝቡ እገዛ ያደርግለታል፡፡ በዚህ መነሻነት ፍርድ ቤቱ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለውን መተማመን የሚቀንስ ተግባር በሙሉ በሕግ ሊቀጣ ይገባል፡፡ ፍርድ ቤትን የመድፈር ድርጊቶች በዚህ ሥር የሚወድቁ ናቸው።
ምንጭ (Abisinia law.com)፣ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ እና የፍትሃብሄር ስነ-ስርአት ህግ
ለሌሎች ህግ-ነክ መረጃዎች (የሀመር ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት) የሚለውን የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ…..።
የሐመር ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት
የህ/ጥ/ማ/ማ/ዋና ስራ ሂደት አቃቤ ህግ ህ/መ
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል ስልጠና ተሰጠ

በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ሀሰተኛ ሰነዶችን በመለየት ለመከላከል ያስችል ዘንድ ከአሜሪካ ኢምባሲ በመጡ አሰልጣኞች ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ አዳራሽ ከአስራ አራቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለመጡ ዋና ስራ አስኪጆች እና ለሌሎች ዳይሬክተሮች ለግማሽ ቀን ስጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ሀሰተኛ ሰነዶችን በተለያዩ ስልቶች መለየት እንደሚቻል በተለያዩ መተግበሪያዎች የታገዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከኦሪጅናል ሰነዶችን በተለያዩ በእይታና የተለያዩ መሳሪዎችን ማለትም (ultraviolet light) በመጠቀም መለየት እንደሚቻል ገለፃ ተደርጓል፡፡

ግለሰቦች ለተለያዩ ጉዳዮች ሲሉ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት እና በመጠቀም በግለሰብ እና በተቋም ብሎም በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ አሰልጣኙ ያብራሩ ሲሆን በስልጠናው ለተሳተፉ ኃላፊዎች ስራቸውን የሚያግዝ (MAGNIFYING GLASS) ተበርክቶላቸዋል፡፡

በስልጠናውም ጥሩ የሆነ የግንዛቤና የክህሎት አቅም እንዳገኙ ሰልጣኞች ገልጸዋል።

ስልጠናው ሰነዶችን የመለየት አቅምን የሚያጎለብት ሲሆን በተቋሙ ሀሰተኛ ሰነድ ይዘው የሚቀርቡ ግለሰቦች መበራከታቸው በስራው ላይ ተግዳሮት እንደፈጠረበት መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

Message Guday Asfetsami on Facebook.
https://www.facebook.com/GudayAsfetsami/

Message Guday Asfetsami on Telegram.
https://t.me/GudayAsfetsami

Message Guday Asfetsami on WhatsApp. https://wa.me/message/QW6PO22A2KXBN1
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከኢንተር ሚኒስትሪያል ታስክ ፎርስ ሴክሬተሪያት (Inter ministrial task force secretariat) ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ባጠኑት ጥናት የተመላከቱ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ መንግስት እየወሰደ ያለውን ርምጃ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማብራሪያ እያቀረበ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለጹት መንግስት ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በተለይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማሳተፍ በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል በማለት የሰብዓዊ መብት አያያዝን በማሻሻል ረገድ ሀገራችን ምን ላይ ነች በሚለው ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሀሳብ መስጠትና መስራት የሚጠበቅባቸው በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡
መንግስት በሁሉም ዘርፍ ለመድረስ ውስንነት ይገጥመዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ውስንነት ለመቅረፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከግሉ ሴክተር ጋር በመቀናጀት መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የኢንተር ሚኒስትሪያል ታስክ ፎርስ ሴክሬተሪያት (Inter ministrial task force secretariat) ዶ/ር ታደሰ ካሳ በመንግስት በኩል ጥናቱን መሰረት በማድረግ መንግስት እየወሰደ ያለውን ርምጃ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ተወካዮች ያብራሩ ሲሆን የታስክ ፎርሱ አወቃቀርና የስራ እንቅስቃሴ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የውይይት መድረኩን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ካውንስል በተገኘ የፋይናንስ ድጋፍ ያዘጋጀው ነው፡፡
@lawsocieties
ቼክ እና አራጣ. Cheque And Usury
ውሣኔዎቻችን የአራጣ አበዳሪዎች ዱላ ሆነዋል.


1. ማንኛውም ቼክ የሚወጣው በውል መነሻነት ነው. በሽያጭ ወይም ክፍያ በሚያስከትል ሌላ ውል መነሻ የሚሰጥ ቼክ የክፍያ ቼክ ነው. በዋስትና ውል መነሻ የሚሰጠው የዋስትና ቼክ ነው. በመሆኑም በአገራችን በኢትዮጵያ ሕግ ቼክ የክፍያ ሰነድ ብቻ ሳይሆን የዋስትና ሰነድም ነው. የንግድ ሕጉ አንቀጽ 827-886 ያሉት አብዛኛዎቹ ድንጋጌዎች የክፍያ ቼክ ሕግ ናቸው. የንግድ ሕጉ አንቀጽ 950-958 ያሉት የዋስትና መያዣ ቼክ ሕግ ናቸው. በንግድ ሕጉ አንቀጽ 950-958 እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2866 ቼክ በመያዣነት እንደሚሰጥ በግልጽ ተደንግጓል.
ይህ በኢትዮጵያ ሕግ ቼክ የክፍያ ሰነድ ብቻ ሳይሆን የዋስትና ሰነድ መሆኑን በግልጽ ያረጋግጣል.

2. ባጭሩ ቼክን በዋስትና መያዣነት ማውጣት ወይም መስጠት በአገሪቱ ሕግ የተፈቀደ ተግባር ነው.

3. በሕግ የተፈቀደ ተግባር ሕገወጥ ተግባር ባለመሆኑ መቼም ሆነ የትም በወንጀል አያስከስስም.

4. የዋስትና ቼክ (Security Cheque) ለግዴታ መፈፀም መተማመኛ ብቻ የሚወጣ በመሆኑ ለክፍያ የማይቀርብ ቼክ መሆኑን እነዚህ ሕጎች ያመለክታሉ. እንደ ንግድ ሕግ ቁጥር 952 (1) ቼኩ ከዋስትና ውሉ ቀን ጀምሮ መያዣ እንደሆነ በሕግ ይገመታል.

5. Black’s Law Dictionary Seventh Edition ገጽ 230 ላይም ተከታይ ትርጉም ተሰጥቷል.

Memorandum Check is a check a borrower gives to a lender for the amount of a loan, with the understanding that it is not to be presented for payment but will be redeemed by the borrower when the loan falls due.
የዋስትና ቼክ ማለት ተበዳሪ በብድሩ መጠን ለክፍያ አይቀርብም የብድሩ መክፈያ ጊዜ ሲደርስም ይመለሳል በሚል መግባባት ለአበዳሪ የሚሰጠው ቼክ ነው.

6. በወንጀል ሕግ ቁጥር 693 ሥር ወንጀል ነው ተብሎ የተደነገገው የክፍያ ቼክ መስጠት ብቻ ነው.

ይህንን ለክፍያ ቼኩ ለባንክ በሚቀርብበት ጊዜ ከሚለው የአንቀጽ 693 ሐረግ ማወቅ ይቻላል.

7. የዋስትና መያዣ ቼክ ማውጣት ወይም መስጠት ወንጀል ነው ተብሎ በወንጀል ሕጉ ስላልተደነገገ በወንጀል አያስከስስም አያስቀጣም.

8. በአሁኑ ጊዜ ብዙ ቼኮች ለአራጣ ብድር መያዣነት እየተሰጡ ናቸው. ነገር ግን ሁሉም ቼኮች እንደ ክፍያ ቼኮች በመቆጠራቸው ውሣኔዎቻችን የአራጣ አበዳሪዎች ዱላ ሆነዋል. በዱላውም ምስኪን ተበዳሪዎች አየተገረፉ አራጣ እየጨመረ ነው. የቼክ ፍትሕም ጠፍቷል.

ስለዚህ አራጣን ለማጥፋትና የቼክ ፍትሕን ለማስፈን ከሳሾቻችን እና ፈራጆቻችን የዋስትና ቼክ እና የክፍያ ቼክ ለይተው መወሰን አለባቸው.
የሐረር ጠቅላይ አቃቤ ህግ

https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የትራፊክ ቅጣት መክፈያ 👇👇👇👇
#6050

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የቅጣት ክፍያ ስርዓትን የሚያቀላጥፍ እና የሚያዘምን አዲስ አሰራርን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የትራፊክ ህግ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ቅጣት ክፍያን ለመፈፀም በኢትዮ-ቴሎኮም የተዘጋጀው 6050 አጭር ቁጥር መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

አዲስ ይፋ የተደረገው የትራፊክ ቅጣት ክፍያ ስርዓት በ6050 አጭር ቁጥር በመጠቀም ትራፊክ ፖሊሶች እና የኤጀንሲው የቁጥጥር ባለሙያዎች በወረቀት ይደረግ የነበረውን አሰራር እንደሚያስቀር ተገልጿል።

ቅጣቱን በሞባይል ስልክ ለተቀጪው በማድረስም መንጃ ፈቃዱ ሳይያዝበት ወይም ታርጋው ሳይፈታበት ጥፋቱን በፈፀመበት ቦታ ክፍያውን መፈፀም ያስችለዋል ተብሏል።

የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያን በቴሌብር አማካኝነት መክፈል የሚያስችለው ይህ አገልግሎት ወይም አሰራር ለዘመናት አድካሚ የነበረውን በወረቀት ላይ ያተኮረ የቅጣት ክፍያ አፈጻጸምን የሚያስቀር ነው ተብሎለታል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
#tikvahethiopia
ኢ ሕገ መንግሥታዊ አንቀጾች ከክልሎች ሕገ መንግሥት ውስጥ እንዲሻሩ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥያቄ ቀረበ🙏❗️❗️🙏

አማኑኤል ይልቃል

በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ህዳጣን ብሔረሰቦችን ‹‹መብት የሚጥሱና ከፌዴራሉ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረኑ›› የተባሉ በስምንት ክልሎች ሕገ መንግሥቶች ውስጥ የሚገኙ አንቀጽና ንዑስ አንቀጾች እንዲሻሩ፣ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ጥያቄ የተነሳባቸው በሶማሌ፣ በአፋር፣ በሐረሪ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በጋምቤላ ክልሎች ሕገ መንግሥቶች ውስጥ የሚገኙ አንቀጾችና ንዑስ አንቀጾች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ከሱማሌ፣ ከደቡብና ከጋምቤላ ክልሎች ውጪ ያሉት ሌሎች የተጠቀሱ ክልሎች ሕገ መንግሥት መግቢያም አቤቱታ ቀርቦበታል፡፡

ጥያቄውን ያቀረበው የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰኘ አገር በቀል የሲቪል ማኅበር፣ በአቤቱታው ላይ የተጠቀሱ የሕገ መንግሥቶቹ ክፍሎች በክልሎቹ ውስጥ የሚኖሩ ህዳጣን ማኅበረሰቦችን የፖለቲካ ተሳትፎ መብቶች የሚገድቡ ስለመሆናቸው በጥር ወር ለጉባዔው ባስገባው የ15 ገጽ ማመልከቻ አብራርቷል፡፡

የፌዴራሉን ሕገ መንግሥት አንቀጽ ዘጠኝ ንዑስ አንቀጽ አንድ የሚጠቅሰው አቤቱታው፣ ሕገ መንግሥቱ የበላይ ሕግ መሆኑንና ማናቸውም ሕጎች፣ ልማዳዊ አሠራሮችና ውሳኔዎች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚቃረኑ ከሆነ ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው መደንገጉን ያስረዳል፡፡ ይሁንና ማመልከቻው፣ አብዛኛዎቹ የክልል ሕገ መንግሥታት በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ ጥበቃ የተደረገላቸውን ሰብዓዊ መብቶች “እንዲሸራርፉ” እና “እንዲጣሱ” ምክንያት ሆነዋል የሚል ወቀሳውን አቅርቧል፡፡

ወቀሳው ከቀረበባቸው የሕገ መንግሥታቱ ክፍሎች ውስጥ አንዱ የሆነው የክልሎቹ ሕገ መንግሥት መግቢያዎች አግላይ እንደሆኑና የፌዴራሉን ሕገ መንግሥት አንቀጽ 25፣ 32፣ 38፣ እና 40ን እንደሚቃረኑ እንደሆኑ አቤቱታው አስረድቷል፡፡ ‹‹መግቢያዎቹ የክልሉን ባለቤትነት ጭምር በስም ለተጠቀሰው/ሱት ብሔርና ብሔረሰቦች ብቻ የሚሰጡና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩ ዜጎችን (ብሔር ብሔረሰቦችን) ዕውቅና የማይሰጡ፣ የሚያገሉና እንደ ሌላ አገር ዜጋ የሚቆጥሩ ናቸው፤›› የሚል ገለጻ በአቤቱታው ተገልጿል፡፡

በዚህም ምክንያት የሕገ መንግሥቶቹ መግቢያዎች በፌዴራሉ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን የእኩልነት፣ የመዘዋወርና በመረጡት የአገሪቱ ክፍል የመኖር፣ የመምረጥና የመመረጥ እንዲሁም የንብረት መብቶች “የሚቃረኑ” በመሆናቸው፣ ጉባዔው “ሕገ መንግሥታዊ አይደሉም” በማለት የውሳኔ ሐሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲልክ ተጠይቋል፡፡

የትግራይ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች ሕገ መንግሥቶች “ኢሕገ መንግሥታዊ” ተብለው ከተጠቀሱት ክልሎች በተቃራኒ አግላይ የሆነ አገላለጽን የማይጠቀሙና በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ሁሉ የሕገ መንግሥቱ መሥራቾች አድርገው የሚቆጥሩ ስለመሆናቸው በማመልከቻው ላይ ተጠቅሷል፡፡

በሕገ መንግሥቶቹ ላይ የተነሳው ሌላው ቅሬታ፣ ‹‹የሕዝብ ወሳኝነትን ሥልጣን የየክልሉ ባለቤት ሆነው ለተጠቀሱ ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ የሚሰጡ፣ በየክልሉ የሚኖሩ የሌሎች ዜጎችን ወይም ብሔር ብሔረሰቦችን ፖለቲካዊ መብቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ሰብዓዊ መብቶቻቸውን የሚገድቡና የሚጥሱ ናቸው፤›› የሚል ነው፡፡

የክልል ሕገ መንግሥታት ለሁሉም በክልላቸው ለሚኖሩ ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት የሚሰጡ ድንጋጌዎች ቢኖሯቸውም፣ የክልል የመንግሥት ሥልጣን ምንጭ በስም የተጠቀሱት ብሔርና ብሔረሰቦች ብቻ በመሆኑ በክልሎቹ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ብሔረሰቦች ትክክለኛ (Genuine) የፖለቲካ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደማይችሉ በአቤቱታው ውስጥ ተካቷል፡፡

የክልል ሕገ መንግሥታቱ በክልላቸው ላለው ብዝኃነት “ዕውቅና አይሰጡም” የሚለው አቤቱታው የክልል ነዋሪዎችን “ባለቤት” እና “ባለቤት ያልሆኑ” ተብለው መከፋፈላቸውን ያስረዳል፡፡ ‹‹አሁን በየዕለቱ ለምናየው የዜጎች ሕይወት መጥፋት፣ መደፈር፣ መፈናቀል፣ የንብረት መውደም፣ ብሎም በአጠቃላይ የሰላም ዕጦትና የሰብዓዊ መብት ቀውስ ምክንያት ሆኗል ብለን እናምናለን፤›› የሚል ሐሳብ ለአጣሪ ጉባዔው በቀረበው አቤቱታ ላይ ሠፍሯል፡፡

እነዚህንና ሌሎች ምክንያቶችን ያቀረበው አቤቱታው ጉባዔው የተጠቀሱት የሕገ መንግሥቶች መግቢያዎችና አንቀጾች ሕገ መንግሥታዊነት ተጣርተው ኢሕገ መንግሥታዊ እንዲባሉ ጠይቋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ጉባዔው፣ ‹‹የሚመለከታቸው የክልል መንግሥታት ኢሕገ መንግሥታዊ የተባሉትን ድንጋጌዎች በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ መሠረት ማስተካከያ እንዲያደርጉባቸው እንዲታዘዝ የውሳኔ ሐሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲልክልን፤›› የሚል ሐሳብ በአቤቱታው ተመልክቷ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢ ሕገ መንግሥታዊ እንዲባሉ የተጠየቁ የክልል ሕገ መንግሥታትን መሠረት አድርገው የወጡ ሌሎች የክልል ሕጎች፣ ፖሊሲዎችና አሠራሮች ሕገ መንግሥታዊነትን መርምሮ ውጤቱን በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርብ የባለሙያዎች ኮሚቴ እንዲቋቋም እንዲታዘዝ፣ አጣሪ ጉባዔው የውሳኔ ሐሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲልክ ተጠይቋል፡፡

ክልሎች ሕገ መንግሥት በሚያወጡበት ወቅት ከግምት ሊያስገቧቸው የሚገባቸውን ሕገ መንግሥታዊ መርሆች በግልጽ አለመቀመጣቸው ያስረዳው አቤቱታው፣ በዚህም የተነሳ የክልል ሕግ መንግሥታት አረቃቅ ‹‹ግልጽነት የጎደለውና ለተለያዩ ፖለቲካዊ ጫናዎች የተጋለጠ›› እንደሆነ ገልጿል፡፡ ስለዚህም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክልሎች ሕገ መንግሥት በሚያወጡበት ወይም በሚያሻሽሉበት ወቅት፣ ከግምት ሊያስገቡት የሚገባ ግልጽ የሆኑ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎችን እንዲቀመጡ ተጠይቋል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሰብሳቢነት የሚመራው የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ፣ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትን ለመተርጎም ሥልጣን ለተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን እያጣራ የሚያቀርብ ነው፡፡ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አዋጅ አንቀጽ አምስት ንዑስ አንቀጽ ሦስት በፌዴራሉም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጎች ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳ፣ ጉዳዩ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም ባለጉዳይ ለአጣሪ ጉባዔው ሊያቀርብ እንደሚችል ደንግጓል፡፡

አሥራ አንድ አባላት ያሉት ጉባዔው የሕግ ባለሙያ የሆኑ ስድስት አባላቱን ታኅሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሾመ በኋላ፣ አዲስ የተሾሙት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አባላት የተገኙበት የመጀመርያው ጉባዔ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡ በዕለቱም አጣሪ ጉባዔው በሦስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የጉባዔው ጽሕፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክተር ይርጋለም ጥላሁን ጉዳዮች ወረፋ ይዘው በቅደም ተከተላቸው እንደሚታዩ ገልጸው፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኘ የሲቪል ማኅበር የቀረበ ጥያቄ ለጉባዔው አለመቅረቡን ተናግረዋል፡፡

https://www.ethiopianreporter.com/article/24863

https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Legal and Policy Specialist

Chemonics International

Addis Ababa


Contractor

Chemonics International, a Washington D.C.-based international development organization, seeks to fill the position of Legal and Policy Specialist for the anticipated USAID Strengthening Ethiopian Civic Voice and Agency (SECVA) project in Ethiopia. The $10-25 million, five-year project will aim to strengthen sub-national government, increase citizen engagement, and strengthen civil society oversight using locally led, problem-driven, adaptive approaches. The Legal and Policy Specialist will be based in Addis and be responsible for leading all policy activities on the project. Candidates should possess extensive knowledge of effective legal and policy activities in Ethiopia. We are looking for individuals who have a passion for making a difference in the lives of people around the world. Responsibilities • Lead implementation of the project’s policy review, reform, and design activities in support of a strengthened and more effective local government. • Support all initiatives related to policy reform, an enabling environment for private investment, and public-private partnerships. • Ensure productive relationships with other donors, government counterparts, local organizations, and other stakeholders related to all policy activities. Qualifications • At least 8 years’ experience working in development, preferably in the area of public policy, public administration or law. • Advanced degree in a relevant field; J.D. or L.L.M. preferred • Experience interacting with host-government agencies and the private sector • Strong understanding of business enabling environment improvement programs, including with respect to enforcement of contracts • Previous experience working on a USAID or similar donor-funded projects in judicial and legal reform preferred • Demonstrated leadership, versatility, and integrity • Oral and written fluency in English required How To Apply To apply visit this link . No telephone inquiries, please. Finalists will be contacted. Applications will be accepted until March 15, 2022. Chemonics is an equal opportunity employer and does not discriminate in its selection and employment practices on the basis of race, color, religion, sex, national origin, political affiliation, sexual orientation, gender identity, marital status, disability, genetic information, age, membership in an employee organization, or other non-merit factors. COVID-19 Recruitment Information Chemonics International is monitoring COVID-19 activity around the world. The health and wellbeing of our staff is of the utmost importance to us, and we continue to hire for all open roles with interviewing and on-boarding done virtually
https://t.me/LawyerEthiopia
Forwarded from L @ 2022
ሰላም እንዴት ናችሁ አንተ ሀሳብ መጠየቅ ፈልጌ ነበረ እኔ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ እናም በእግ ተመርቄለሁ ነገር ግን ስራ ለማግኘት በጣም አሳሳቢ ሆኖብናል እኔ እና መሰሎቼ ምክንያቱም ከአማርኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ ስለማንችል በቅርቡ አማራ ክልል ስልጠና አውጥቶ ተመዘገብን እንዲሁም ተፈተንን ነገር ግን የፈተናችንን ወረቀት እንኳን ሳያዪ ከሌላ ክልል የሄድነውን ልጆች እንዳለ ጥለውናል እንዲሁም ሌላ ክልልም በተመሳሳይ የስራ ማስታወቂያ እየወጣ ነገር ግን የክልሉን ቋንቋ ይላሉ ከትንሽ ወራት በኃላም ደቡብም ሆነ ኦሮሚያ judicial training ቢያወጣ እኛ አሁንም ከውድድሩ ውጪ ነው የምንሆነው ስለዚህ አ.አ መስተዳድር ለእኛ ምንም መፋትሄ የለውም ማለት ነው ? ምታውቁት ነገር ካለ ብታሳውቁን ወይም የት ሄደን መጠየቅ እንዳለብን አቅጣጫዎችን ብታሳዪን። አመሰግናለሁ።
Legal Officer at Bank of Abyssinia

Bank of Abyssinia

Ethiopia

Full–time

Job Objective: Ensure the legal feasibility of purchasing contracts by devising/reviewing flawless contracts, advising procurement officials and performers and defending the Bank's interest at the court of law. Duties and Responsibilities: • Design/prepare purchasing and other related contracts; • Review contracts, ensure their completeness and cosign with responsible organ; • Review amendment to contracts (when needs arise) and ensure all concerned parties have got amended version of the contract documents; • Render legal advice and opinion, • Represent the Bank before the court of law, other judicial tribunals and organs; • Track legal defects and loopholes and take appropriate corrective measures; • Appeal on court decisions made against the Bank (if so required); • Work collaboratively with Procurement Department performers; • Conduct legal environment assessment to determine legal feasibility/admissibility of contracts; • Prepare periodic reports; • Perform other related duties given by the supervisor.
Qualifications/Skills Education:- LLB Degree in Law. Experience:- Minimum of 6 years banking experience, of which 3 years in the area of Law.
Method of Application Closing Date :
5 March. 2022
https://t.me/LawyerEthiopia
# Africa Insurance Company Sc#

▪️1: Assistant Lawyer
▪️2: HRM & P/Administration Assistant
▪️▪️How To Apply▪️
👇👇👇👇
https://bit.ly/3sJkRwa

▪️Deadline: march 11/2022

https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
#Dashen Bank#

▪️1-District Legal Officer
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3INb4uD

https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
#Danish Reefugee Council#NGO Jobs

▪️1- Protection Specialist - Legal
▪️https://bit.ly/3Mr330F

▪️2- Emergency Coordinator
▪️https://bit.ly/3MlbP0d

▪️3- Emergency Manager
▪️https://bit.ly/3HMEmrK

▪️Deadline - March 18/22

https://t.me/LawyerEthiopia
ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ(2) (1).pdf
1.3 MB
በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ
በወንጀል_ጉዳዮች_የዓቃቤ_ህግ_የህግ_ትርጉም_ማብራሪያ.pdf
1.1 MB
በወንጀል ጉዳዮች የአተረጓጎም ልዩነት ያለባቸውን ድንጋጌዎች ላይ ወጥነት ያለው ትርጉም ለማምጣት እንዲቻል የተዘጋጀ የሕግ ማብራሪያ
ስለ ቅጣት መገደብ የተሰጠ ዉሳኔ
#henoktaye law office
#ከቅፅ 23 የሰ/መ/ቁ142594 የተወሰደ!
የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ አላግባብ ተሰርዞብኛል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ጉዳዩ በቀጥታ ከመሬት ይዞታ ባለመብትነት ጋር ተያያዣነት ያለው በመሆኑ የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ ነዋሪነታቸው ወይም የተከራካሪው ወገን የፌደራል መንግሥቱ ተመዛጋቢ መሆን ግምት ውስጥ ሳይገባ የክርክሩን ልዩ ባህሪ በማየትና የጉዳዩን ዓይነት
መሠረት በማድረግ ንብረቱ የሚገኝበት የከተማ አሥተዳደር ፍ/ቤት የቀረበውን ክስ ተቀብሎ
የመወሰን የሥረ-ነገር ሥልጣን አለው፡፡