አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
February 12, 2022
February 12, 2022
February 12, 2022
February 14, 2022
February 14, 2022
February 15, 2022
February 15, 2022
የጡረታ ዕድሜን ጣራ ወደ 60 ዓመት ከፍ ያደረገው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ!!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የመንግሥት እና የግል ሠራተኞች ጡረታን ለመደንገግ በቀረበው አዋጅ ላይ በመወያየት አፀደቀ።

በዚህም መሰረት የጡረታ ዐዋጅ የጡረታ ዕድሜን ጣራ 60 ዓመት እንዲሆን እንዲሁም ጡረተኛው በሕይወት ሳለ የሚያገኘው የጡረታ መጠን ሲያልፍ ለትዳር አጋር 50 በመቶ የጡረታው ተጠቃሚ እንዲሆን ይፈቅዳል።

የፖሊስና መከላከያ መዋጮ ከግለሰቡ የሚደረገው ሌሎች የግልና የመንግሥት ሠራተኞች እንደሚያዋጡት 7 በመቶ ሆኖ ከመንግሥት አካል የሚደረግለት መዋጮ ግን ወደ 33 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል።

በተመሳሳይ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ዛሬ በምክር ቤቱ የጸደቀ ሲሆን፥ ይኸውም በድርጅቶች ምክንያት ሳይዋጣ የቀረን ገንዘብ በሦስት ወር ውስጥ ገቢ ካልተደረገ በቀጥታ ድርጅቱ ካለው ማንኛውም የባንክ አካውንት ገቢ እንዲደረግበት የሚያስገድድ ነው።

የግል ድርጅት ባለቤቶች በድርጅቱ ሠራተኛ ሆነው በጡረታ ማዕቀፉ ውስጥ እንዳይገቡም አዋጁ አግዷል። ከ10 ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ዕድሜው ለጡረታ በሚደርስበት ጊዜ የዕድሜ ልክ ጡረታ ተከፋይ እንዲሆንም አዋጁ ይፈቅዳል።

የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮም ወደ ኢንቨስትመንት በማስገባት ገቢን ማሳደግ ለጡረተኞች የክፍያ ማሻሻያ የሚያደርግበትን እድልም የሚፈጥር ነው ተብሏል፡፡ አንድ አሰሪ የግል ድርጅት ፍቃዱን በሚያድስበት ጊዜ የሠራተኞቹን መዋጮ ካላስገባ ፍቃዱ የማይታደስበት አስገዳጅ አንቀጽም ተካቷል።
https://t.me/lawsocieties
ኢትዮ-መረጃ
February 15, 2022
February 15, 2022