Opening date: December 14, 2020 Closing date: December 23, 2020 • Application Tips • Interested applicants shall apply online through website address; https://www.ethiotelecom.et // and other way of application is not acceptable. • Applicants must have the required educational qualification and experience. • Applicants are required to print the application confirmation page for successful registration. Any complaints regarding registration will not be entertained otherwise. • Applicants who submit false or forged documents will be disqualified at any time confirmed. • Only short-listed applicants will be contacted. • Female applicants are strongly encouraged to apply
www.ethiotelecom.et
Ethio Telecom
Your Description
Forwarded from Burje Shade 🤔
pls can i get land proclamatins and regulations on lease and compensation .
በንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ላይ በህዝብ ተወካዮች በምክር ቤት ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ
________________________
ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የንግድ ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የንግድ ማህበራት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በውይይት መድረኩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሕግ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ በላይሁን ይርጋ የአዋጁን መነሻ እና አስፈላጊነት በማስመልከት ገላጻ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ የንግድ ሕጉ በ1952 ከወጣ በኃላ ከ60 አመታት በላይ ሳይሻሻል የቆየ በመሆኑን ጠቁመው አዋጁ አለም ከደረሰበት ዘመናዊ የኢኮኖሚ እና የንግድ አኳያ ተመጣጣኝ ያልሆነ፣ በወቅቱ ሕጉ ሲረቀቅ አገሪቱ ከነበረችበት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ፣ በሕጉ ውስጥ በተግባር ያልተፈተሸ ድንጋጌዎች መኖራቸው እና ጉድለቶች የታዩበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አቶ በላይሁን አክለውም ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት የኢኮኖሚ እንቅንስቃሴ እና ደረጃ ሕጉ የተሟላ እና በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ፤ አገሪቱን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማስፋፋት፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ በሚያስችል ደረጃ የንግድ ሕጉን ወቅቱን በሚመጥን ደረጃ ዘመናዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረው ነባሩ የንግድ ህግ ጥራዝ በአምስት መጽሐፍት የተደራጀ ሲሆን፣አዲሱ የንግድ ህግ በይዘትም ሆነ በቅርፅ መሰረታዊ የሚባሉ ለውጦችን የያዘ ሰነድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ተሳታፉ ባለድረሻ አካላትም በረቂቅ የንግድ ሕጉ በተመለከተ የሽርክና ማህበርን፣ ሂሳብ አያያዝ ስርዓት፣ አክስዮን ማኅበርን ፣ በንግድ ድርጅቶች መካከል የሚፈጠርን ዝምድና እና ከቼክ ጋር በተያያዘ ሊሻሻሊ፣ ሊታዩ፣ ሊካተቱ ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ያነሱ ሲሆን በውይይቱ በአካል ያልተገኙ ተሳታፊዎች ለቋሚ ምክር ቤቱ የተለያዩ ጥያቄቸውን እና አስተያየቶችን በላኩት መስረት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
አቶ በላይሁን እና የንግድ ሕጉን በማረቀቅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ ሙህራን በተሳታፊዎች ለተነሱት ዝርዝር ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ለሻሻሉ ይገባል የተባሉትን ጉዳዮች በመለየት በግብአትነት እንደሚካተቱ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችም የንግድ ሕጉ 20 እና 30 ዓመታት በላይ እንዲያገለግል ሁሉምን አካል አሳታፊ በሆነ መልኩ እየተሰራ ሲሆን በቀጣይም በ150 በላይ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ሙህራን፣ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የከፍትኛ ትምህርት ተቋመት አመራሮች በተገኘበት ውይይት እንደሚደረገ ፕሮገራም የተያዘ መሆኑ በመድረኩ ስብሳቢወች ተጠቁሟል፡፡የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

አማራጭ የግጭት መፍቻ ስርአትና ጠቀሜታው
-------------------------
በነባራዊው አለም ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ሁሉ የተለያየ ፍላጎት ካላቸው ሌሎች ሰዎች ጋር አብረው ይኖራሉ፡፡ በየትኛውም የአለማችን ክፍል እና ዘመን ሁሉም ሰው ፍጹም የተመሳሳለ ወይም አንድ አይነት ፍላጎት ኖሮት ሲንቀሳቀስ ታይቶ አይታወቅም፡፡ ለዚህ ብዙ ምክኒያትን ማንሳት ቢቻልም ዋንኛው ግን የአለማችን ሀብት ከሚኖርባት የሰው ብዛት አንጻር ሲታይ ውስን በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ውስን ሀብት በአንድ ጊዜ የሁሉንም ሰው ፍላጎት ማርካት እጅግ አዳጋች ነው፡፡
ስለዚህ ባለው አቅም እና ሀብት የሁሉንም ፍላጎት በማጣጣም መጓዝ ለሁሉም ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ነገሮች ሁሉ በሚጠበቀው መጠን ይከናወናሉ ማለት አይደለም፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን የሰዎች ፍላጎት ባለመጣጣሙ በመካከላቸው የጥቅም ግጭት ሲነሳ ማየት የተለመደ ነው፡፡
ሉላዊነት/Globalization/ አለምን ወደ አንድ መንደር ያመጣት ሲሆን በተለይ በንግዱ ዘርፍ ከተለያዩ የአለም ክፍል ሰዎች እና የንግድ ድርጅቶች የንግድ ልውውጥ በሚደርግበት ጊዜ እንዲሁም ባለሀብቶች ወደተለያዩ ሀገር በመሄድ ኢንቨስትመትን ለማስፋፋት ሀብታቸውን በሚያፉበት ወቅት የጥቅም ግጭት በነጋዴዎቹ መካከል፣በባለሀብት እና በመንግስታት መካከል ኢንዲሁም በቤተሰብ እና በጓደኛሞች መካከልም ጭምር የጥቅም ግጭት ሊነሳ ይችላል፡፡ በእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን ይሄን እውነታ መጋፈጥ የተለመደ ተግባር ነው፡፡
ከላይ እንዳየነው ግጭት የሰው ልጆች አንዱ የህይወት ገጽታ ከሆነ ይህ ግጭት በአግባቡ ተይዞ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል፡፡በአግባቡ ያልተዘ ግጭት(unmanaged conflict) ውጤቱ ጎጂ ነው፡፡ጉዳቱም ከንብረት ውድመት እስከ ክቡሩ የሰው ህይወት መጥፋት ሊደርስ ይችላል፡፡በተግባርም አገራችንን ጨምሮ በአለም ላይ እየሆነ ያለው ይሄው ሀቅ ነው፡፡
ስለዚህ ግጭት መኖሩን ካመንን የግጭት መፍቻ መንገዶቹንም ቀድሞ ማበጀት ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚሁም መሰረት በዋነኛነት ሁለት አይነት የግጭት መፍቻ መንገዶች ያሉ ሲሆን እነሱም መደበኛ እና ኢ-መደበና የግጭት መፍቻ መንገዶች ይባላሉ፡፡
መደበኛውን የግጭት መፍቻ መንገድ ካየን ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው ግጭቶች ሲነሱ ቀድመው በህግ በቀቋቋመ ፍርድ ቤት ወይም ከፊል የዳኝነት ስልጣን ባላቸው አካላት እና በህግ በተዘረጋ ስርአት ውስጥ በማለፍ ግራቀኙን ወገኖች ቀርበው አቤቱታቸውን እና ምላሻቸውን አሰምተው በመንግሰት በተሰየሙ ዳኞች ግራቀኙን አከራክረው ተገቢ ነው ያሉትን ውሳኔ የሚወስኑበት እና ይሄንኑ ውሳኔ የሚያስፈጽሙበት የግጭት አፈታት ስርአት ነው፡፡
በሌላ በኩል ኢ-መደበኛውን የግጭት አፈታት ስርአትን ያየን እንደሆነ ከስያሜው መረዳት እንደሚቻለው እላይ ካነሳነው መደነኛ የግጭት አፈታት ውጭ ያሉትን ሁሉንም የግጭት አፈታት ዘዴዎች የሚያካትት የግጭት አፈታት ዘዴ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በሌላ አገላለጽ አማራጭ የግጭት አፈታት ስርአትም ይባላል፡፡ ይህም ስያሜ የተሰጠው በነባራዊው ሁኔታ ብዙ ጊዜ ግጭቶች በዋነኛነት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች በሚደረግ ክርክር የሚፈቱ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህ መደበኛው የግጭት አፈታት ስርአት በብዙ ምክኒያቶች ተመራጭ የማይሆንባቸው አጋጣሞዎች አሉ፡፡ የዚህን ግዜ አማራጭ የግጭት መፍቻ መፈለጉ ምክኒያታዊ ነው፡፡ ለዚህም ነው አማራጭ የግጭት መፍቻ ስርአት የሚባለው፡፡
አማራጭ የግጭት መፍቻ ሲባል በዋነኛነት በሂደቱም ሆነ በውጤቱ ከመደበኛው የግጭት መፍቻ መንገዶች የሚለይባቸውን መሰረታዊ ነጥቦች ስናይ፡-
የሚዳኛቸውን አካል እና የመዳኛ ሂደቶችን ተከራካሪዎች እራሳቸው ቀድመው በስምምነት የሚመርጡ በመሆኑ
ወደ ግልግል ዳኝነቱ ለመምጣት የሁለቱም ወገን ተከራካሪዎች ነጻ ፈቃድ የሚያስፈልግ መሆኑ
በሂደቱም ሆነ በውጤቱ አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴ ሁለቱንም ተከራካሪ ወገን አሸናፊ የሚያደርግ መሆኑ
መደበናውን የፍርድ ቤት ረጅም ክርክር በማስቀረት ፈጣን እና እንደ ጉዳዩ አይነት ሞያተኛ የሆኑ ገላጋይ ዳኞችን በመምረጥ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው መፍትሄ ለመስጠት ማስቻሉ እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴ በመሰረታዊነት በአንድ አይነት ባህሪው የሚታወቅ ቢሆንም የተሳታፊዎቹን እና የአሸማጋዮቹን በሂደቱም ሆነ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ያላቸውን ሚና ማእከል በማድረ በጣም ጎልተው የሚታወቁ ሶስት አይነት አማራጭ የግጭት መፍቻ መንገዶች እንዳሉ የተለያዩ የመስኩ ባለሞዎች እና ጥናታዊ ጽሁፎች ይጠቁማሉ፡፡ቀጥለን እነዚህኑ አማራጭ የግጭት መፍቻ መንገዶች ባጭሩ እናያለን፡፡
የመጀመሪያውስ ስናይ ሽምግልና (mediation) ሲሆን በዚህ አይነቱ የግጭት መፍቻ ዘዴ የአሸማጋዮቹ ሚና ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን ሆነው ሚናቸውም ግራቀኙ ተከራካሪዎች በራሳቸው ስምምነት ላይ ደርሰው አለመግባባቱን እንዲፈቱ ምቹ መደላድል መፍጠር ነው፡፡
ተከራካሪዎቹን በጋራም ሆነ በተናትል በማነጋግ ትክክለኛ ፍለጎታቸውን እንዲለዩ እና ግራቀኙ ሳይገደዱ አለመግባባቱን በቋሚነት ለመፍታት የሚስችላቸው መፍትሄ ላይ እንዲደርሱ በራሳቸው ነጻ ፍቃድ እንዲስማሙ እና መፍትሄውንም እንዲተገብሩት መርዳት ነው፡፡
ከመርዳት ባለፈ ግን የውሳኔ ሀሳብ አያቀርቡም እንዲሁም አይወስኑም፡፡
ሁለተኛው አማራች የግጭት መፍቻ ዘዴ የግልግል ዳኝነት (Arbitration) ሲሆን የዚህ አይነቱ የግጭት መፍቻ መንገድ ከመደበኛው የፍርድቤት ስርአት ጋር የተቀራረበ ነው፡፡ በዚሁም መሰረት ገለልተኛ የሆነ ሶስተኛ ወገን በዳኝነት ተሰይሞ አለመግባባቱንም ለመፍታት በሙሉ ስልጣን እና ሀላፊነት የሚሰራበት ስርአት ነው፡፡ ዳኛው የሁለቱንም ወገን መከራከሪያ ነጥብ እና ማስረጃ ሰምቶ በመመዘን አስገዳጅ ውሳኔ የመስጠት ሀላፊነት አለበት፡፡ከመደበኛው ፍርድ ቤት የሚለየው ገላጋይ ዳኛው በተከራካሪዎች በነጻ ፍቃዳቸው የሚመርጡት መሆኑ እና በሚወሰነው ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማይጠየቅበት መሆኑ ነው፡፡በዚህም ጉልበት እና ሰአት ቆጣቢ የግጭት አፈታት ስርአት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ሌለኛው የግጭት አፈታት ዘዴ መግባባት ወይም ተነጋግሮ መግባባት (Negotiation) ሲሆን የሄንኛው ዘዴ እላይ ካነሳነው ሽምግልና ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡በዚህ ጊዜ ተከራካሪ ወገኖች በራሳቸው የግጭት መንስኤ የሆነው ጉዳይ ላይ በራሳቸው ተነጋግረው በመግባባት ግጭቱን የሚፈቱበት ዘዴ ነው፡፡በዚህኛው አይነት የግጭት አፈታት ዘዴ የሶስተኛ ወገን ተሳትፎ የለም፡፡
በአለማቀፍ ህግ ደረጃ አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴ በ1950 በጸደቀው የኒውዮርኩ ስምምነት እውቅና ያለው ሲሆን አገራችንም በቀርቡ ይሄንን አለማቀፍ ስምምነት በህገመንግሰቱ አንቀጽ 9 ንኡስ አንቀጽ 4 መሰረት ተቀብላ አጽድቃዋለች፡፡ በዚሁ ስምምነት መሰረት በሌላ ሀገር የተወሰነ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ የኢትዮጵን ህዝብ ሞራል ወይም ግብረገብነት እሴትን ማይጎዳ ከሆነ እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱም በህጉ መሰረት ተከራካሪ ወገኖች በፈቃዳቸው በመረጡት ስርአት የተሰጠ ውሳኔ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደተወሰነ ህጋዊ ውሳኔ ተቆጥሮ ተፈጻሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡የእትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ውሳኔውን እውቅና ሰጥተው የማስፈጸም ስልጣን እና ሀላፊነት አለባቸው፡፡
ከኒውዮርኩ ስምምነት በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት አለማቀፍ የንግድ ህግ ኮሚሽን (United nations commission on international trade law) በ1986

የተዘጋጀ በንግዱ አለም የግልግል ዳኝነቱ የሚመራባቸውን መርሆች ያካተቱ አለማቀፍ መርህ በዝርዝር የያዘ ሰነድ ያለ ሲሆን እሱም UNCITRAL model law on International commercial arbitration በመባል ይታወቃል፡፡እነዚህ መርሆች አስገዳጅ ሳይሆኑ በተከራካሪ ወገኖች ነጻ ፈቃድ ላይ ተመስርተው በግልግል ጉባኤው ተግባር ላይ የሚውሉ መርሆች ናቸው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከ በተመሳሳይ የግልግል ዳኝነት ወይም የሽምግልና አሰራርን የሚዘረጋ አካል የተዋቀረ ሲሆን እሱም አለማቀፍ የኢንቨስትመንት ግጭት መፍቻ ማእከል (international center for settlement of investment dispute(ICSID) በመባል ይታወቃል፡፡ይህ ማእከልም በአለም አቀፍ ቃልኪዳን የተቋቋመ ነው፡፡
የሚቋቋሙት የግልግል ዳኝነት አካለት ቋሚ(Permanent Arbitaration Tribunal ) ወይም ጊዜአዊ የግልግል ጋኝነት(Adhoc Arbitaration Tribunal) ሆነው ለየግጭቶቹ መፍትሄ ለመስጠት በየግዜው የሚዋቀሩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙት ይሄንኑ ጊዜአዊ የግልግል ዳኝነት ሰጢ አካል ነው፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የግልግል ዳኝነትን የሚመራበትን እና ውሉ የሚፈጸምበትን ህግ በ1952 የፍትሀ ብሄር ህግ ከአንቀጽ 3325 አና ቀጥሎ ባሉት አንቀጾች የደነገገ ሲሆን እና የግልግል ዳኝነቱ ስርአት የሚከተለውን ሂደት ደግሞ በ1957 በወጣው የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ ተደንግጓል፡፡
በግልግል ዳኝነት የሚታዩ ጉዳዮች በተለያዩ አዋጆችም ተደንግገው የገኛሉ፡፡ለምሳሌም በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1186/2016፣የማእድን ልማት አዋጅ ቁጥር 678/2002 እና በኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2007 መጥቀስ ይቻላል፡፡ በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1186/2012 አንቀጽ 28 መሰረት ከላይ ያነሳናቸውን የሽምግልና ወይም የግልግል ዳኝነት እንደ አማራጭ የግጭት መፍቻ ተደርጎ የተደነገገ ሲሆን በባለሀብቱ እና በመንግሰት መካከል የሚነሱ የኢንቨስትመት አለመግባባቶች የሚፈታበት አማራጭ መንገድ ነው፡፡
እንደ ባለሀብቱ ወይም መንግስት ነጻ ፈቃድ ጉዳዩ ወደመደበኛው ፍርድ ቤት ካልቀረበ በዚሁ የግጭት መፍቻ ዘዴ መፍትሄ የሚያገኝ ጉዳይ ነው፡፡
በ1957 የወታው የፍ/ስ/ስ/ህግ አንቀጽ 461 መሰረት በሌሎች አገራት የተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙበትን ሁኔታ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡በዚሁም መሰረት በውጭ አገር በግልግል/ሽምግልና ዳኝነት የተሰጡ ውሳኔዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚከተሉትን ቅድመሁኔታዎች ማሟላት አለባቸው፡-
ብይኑ በተሰጠበት አገር በኢትዮጵያ ውስጥ የተሰጠ የግልግል ወይም ሽምግልና ብይን የሚፈጸም ከሆነ(reciprocity principle)
ብይኑ የተሰጠው ተከራካሪ ወገኖች በስምምነት ለግልግል ዳኝት ጉባኤው ባቀረት ጥያቄ መሰረት ከሆነ
ብይኑ የተሰጠው በተወሰነበት አገር ህግ መሰረት ብቻ ከሆነ
የግልግል ዳኞች መረጣ ላይ እና በሂደቱ ሁለቱም ወገኖች እኩል ማስረጃ የማቅረብ እና የመደመጥ መብት የተሰጣቸው ከሆነ
የግልግል ዳኝነት ጉባኤው በተቋቋመበት አገር ህግ አግባብ የተቋቋመ ከሆነ
ዳኝነት የተሰጠበት ጉዳይ በኢትዮያም ህግ በግልግል ዳኝነት ሊታይ የሚችል ከሆነ እና
የፍርዱ አፈጻጸም የኢትዮጵያ ህዝብን ሞራል እና ጸጥታ የማይቃወም ከሆነ እና
የተሰጠው ብይን በኢትዮጵ ህግ መሰረት በተግባር ለፈጸም የሚችል ብይን ከሆነ
ባጠቃላይ በኢንቨስትመንት እና በንግዱ አለም ይህ የግልግል ዳኝነት የተለመደ አሰራር ቢሆንም አገራችን ይህን አማራጭ የግልግል ዳንነት የሚገዛ እራሱን የቻለ አገራዊ አዋጅ በማዘጋጀት ላይ ትገኛለች፡፡
ይህ አማራጭ የግጭት መፍቻ ስርአት ከባህላዊ የግጭት መፍቻ ስርአት አንጻር ምን አይነት አንድምታ እንደለው ስናይ በሀገራችን አማራጭ የግጭት መፍቻ ስርአት የነበረ ቢሆንም በዘመናዊ መልኩ በተቋም ተዋቅሮ መስራት የጀመረው በ1996 ዓ.ም.ሲሆን እሱም በእትየጵያ ግልግል ዳኝነት ማእከል መመስረት ተከትሎ የተፈጠረ አደረጃጀት ነው፡፡ይህ ተቋም እስካሁን ከተደራሽነት እንጻር ገና በጅምር ላይ ያለ እና በዙ መስራት የምጠበቅበት ዘርፍ ነው፡፡
በሌላ በኩል ሀገር በቀል የሆኑ ባህላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶችን ያየን እንደሆነ በአገራችን ሰፊ ሽፋን አላቸው፡፡በእትዮጵያ በጣም በርካታ ቋንቋዎች እና ባህሎች ያሉ ሲሆን እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል የራሱ የሆነ አንጋፋ የግጭት አፈታት ስርአት አለው፡፡ከተደራሽነት አንጻር ካየነው ግጭት ሲነሳ መፍትሄ ለማግኘት ከሚኬድባቸው ተቋማት ውስጥ መደበኛው ፍርድ ቤት ወይም ከፊል ዳኝነት ስልጣን ያላቸው አካላት፣ዘመናዊ አማራጭ የግጭት መፍቻ ማእከላት፣እና ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴን መጠቀም ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በመደበናው የዳኝነት ስርአትን ስናይ ተደራሽነቱ ብዙ ወጪ እና፣በመመላለስ ጊዜ እና ጉልበትን የሚፈጅ ሲሆን ለሰፊው ማህበረሰብ ተደራሽ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ዘመናዊው አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴንም ስናይ ከመደበኛው ፍርድ ቤት በባሰ መልኩ እጅግ ውስን በሆኑ ቦታዎች የሚሰጥ አገልግሎት ያለበት በመሆኑ በዚህ ስርአት ግጭትን ለመፍታት ለአብዛኛው ማህበረሰብ ክፍል በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡
ነገር ግን ባህላዊ አማራጭ የግጭት መፍቻ ስርአትን ካየን በማህበረሰብ እሴት ውስጥ በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች ሁሉም የአገራችን ህዝብ እንደ በጎ እሴት የሚጠቀምባቸው እና ጎልበተው ለዘመናት የዘለቁ በመሆናቸው ከተደራሽነት አንጻር እጅግ ሰፊ ሽፋን ያላቸው ናቸው፡፡ ይህ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርአት እጅግ የተከበሩ የአገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣አባ ገዳዎች ፣የየአካባቢው የጎሳ መሪዎች እና እንዲሁም በነዘዚሁ ሰዎች በሚመረጡ ሌሎች ሰዎች አሻማጋይነት ወይም ገላጋይነት ሁሉንም ወገን አሸናፊ በማድረግ አጥፊዎችን በማህበራዊ ቅጣት ለምሳሌ ከማህበራዊ ግንኙነት በማግለል በመቅጣት የአካባቢው ህዝብን ሰላም እና አብሮነት በቋሚነት ለማስጠበቅ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ማህበራዊ ትስስር(social synergy) ለማጠናከር የጎላ ሚና አለው፡፡
አጥፊዎችም ሊደርስባቸው የሚችለውን ማህበራ ቅጣጥ በማሰብ ለስርአቱ ታማኝ በሆን ሰላም ያወርዳሉ፡፡የህ ስርአት በተለይ በአገራችን ሩቅ አካባቢ በሚኖሩ ጎሳዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች እጅግ አስፈላጊ የማህበረሰቡ እሴት ነው፡፡ከማእከላዊው እና ዘመናዊው የዳኝነት ስርአት እና የግጭት አፈታት በአንድም በሌላም ምክኒያት የራቁ ሆነው በመቆየታቸው በምትኩ ባህላዊውን የግጭት አፈታት ስርአት እንደ አማራጭ ሳይሆን እንደ ዋና የግጭት መፍቻ መንገድ ሲጠቀሙ ማየት የተለመደ ነው፡ከላይ እንዳነሳነው ዘመናዊው አማራጭ የግጭት አፈታት ስርአት የመንግስትን ሀይል የመጠቀም ስልጣን(monopoly use of force) በመጠቀም ውሳኔዎቹን የሚያስፈጽም ሲሆን ባህላዊው የግጭት አፈታት ስርአት ግን ማህበራዊ ቅጣትን በመጠቀም ማህበረሰቡ እዛው በራሱ ውሳኔዎቹን ያስፈጽማል፡፡
ከህግ አንጻር የግልግል ዳኝነት ታይቶ ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ ዳግም በፍተሀብሄር ክስ ሊቀርብበት እንደማይችል ከቀረበም በፍ/ስ/ስ /ህ/አንቀጽ 144 (2)(ረ) እና 145(2) መሰረት እንደመጀመሪያ ክስ መቃወሚያ የሚቀርብ እና ክሱን የሚያዘጋ ሲሆን ይህም ያአገራችንን ህግ ለብዝሀነት(legal pluralism) የሰተውን ቦታ ያሳያል፡

፡ይህ የግጭት አፈታት ዘዴ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 34(5) መሰረት የጋብቻ እና የግል ጉዳዮችን በተመለከተ በተከራካሪ ወገኖች ስምምነት በባህላዊ ወይም በሃይማኖታዊ ህግጋት አለመግባበቶች ሊፈቱ እንደሚችሉ የተደነገገውን የህግ ብዝሀነት ይበልጥ ያጎለብታል፡፡
ሌላው በአማራጭ የግጭት አፈታት ስርአት የሚታዩ እና የማይታዩ ጉዳዮች ያሉ በመሆናቸው ከአገራችን ህግ እና ስርአት አንጻር ሲታይ ገና በአግባቡ ያልተለየ በመሆኑ አዲስ በሚወጣው አዋጅ የሚሸፈን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከወንጀል ህግ አንጻር ግን በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ክሶች በዚሁ አማራጭ የግጭት መፍቻ ሊታዩ የሚችሉ ሲሆን ህጉ በዓቃቤ ህግ ክስ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ናቸው ብሎ የደነገጋቸው ወንጀሎችን በተመለከተ በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ሊታዩ አይችሉም፡፡
ሆኖም በአገራችን እነዚህንም በአቃቤ ህግ ክስ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ወንጀሎችን ጨምሮ በባህላዊ የግጭት አፈታት በመጨረስ የህግ አካላት የክስ መዛግብትን እንዲዘጉላቸው መጠየቅ የተለመደ ነው፡፡ነገር ግን ይህ አሰራር ከህወንጀል ህጉ መሰረታዊ አላማ እና ግብ አንጻር ሲታይ የህጉን ፍላጎት መሰረት ደረገ ስላልሆነ ሊበረታታ አይገባም፡፡
https://t.me/lawsocieties
ሌላው በአማራጭ የግጭት አፈታት ስርአት የሚታዩ እና የማይታዩ ጉዳዮች ያሉ በመሆናቸው ከአገራችን ህግ እና ስርአት አንጻር ሲታይ ገና በአግባቡ ያልተለየ በመሆኑ አዲስ በሚወጣው አዋጅ የሚሸፈን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከወንጀል ህግ አንጻር ግን በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ክሶች በዚሁ አማራጭ የግጭት መፍቻ ሊታዩ የሚችሉ ሲሆን ህጉ በዓቃቤ ህግ ክስ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ናቸው ብሎ የደነገጋቸው ወንጀሎችን በተመለከተ በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ሊታዩ አይችሉም፡፡
ሆኖም በአገራችን እነዚህንም በአቃቤ ህግ ክስ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ወንጀሎችን ጨምሮ በባህላዊ የግጭት አፈታት በመጨረስ የህግ አካላት የክስ መዛግብትን እንዲዘጉላቸው መጠየቅ የተለመደ ነው፡፡ነገር ግን ይህ አሰራር ከህወንጀል ህጉ መሰረታዊ አላማ እና ግብ አንጻር ሲታይ የህጉን ፍላጎት መሰረት ደረገ ስላልሆነ ሊበረታታ አይገባም፡፡
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
Forwarded from Deleted Account
ፀበፍ/ብ/ህ/ቁ 418 እና 358 ሳይከራከር የቀረ መብት አለኝ የምል ሰው በ 421 ክስ ማቅረብ ይችላል ወይ?
Forwarded from Deleted Account
ሠላም ወንድሞች ፣ እባካችሁ አዲሡን የመውጫ ፈተና መመሪያ
Forwarded from Deleted Account
ሠላም ወንድሞች ፣እባካችሁ አዲሱ exit guide line ካላችሁ attach አድርጉልን።
Forwarded from Deleted Account
አዎ ይችላል! በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 41 መጀመሪያ በክርክሩ መግባት የነበረበት ሰው ሳይገባ ከቀረ በ358 መሰረት ፍርዱን ለፈረደው ፍ/ቤት ተቃውሞ ሊያቀርብ ይችላል። ሁለቱንም ያላደረገ ሰው ደግሞ በአፈጻጸሙ ክስ ላይ በ418 መሰረት አፈጻጸሙን ሊቃወም ይችላል። ሆኖም ግን ከዚህ በላይ ባለው መሰረት ተቃውሞ ያላቀረበ ወይም አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ራሱን ችሎ በአዲስ ክስ ከማቅረብ አያግደውም(የመጨረሻ አማራጩ ሊሆን ይችላል) ብየ አስባለሁ።
ለዐቃብያነ ሕግ የስብዕና ግንባታ እና የሙያ ብቃት ለማጎልበት ስልጠና ተሰጠ
--------------------------------------
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክተር ከጀስቲክስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ100 ለተቋሙ ለዐቃብያነ ሕግ ስብዕና ግንባታ እና የሙያ ብቃት ማጎልበቻ ዙሪያ ለ2 ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሕግ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ተሰፋዬ ደባ እንደተናገሩት ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 10 የለውጥ አጀንዳዎችን በመቅረፅ ተቋማዊ ለውጥን ለመፍጠር ከሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል የባለሙያዎች እና አመራሮች ሙያዊ ብቃት ማጎልበት መሆኑን ጠቁመው ተቋሙ ለ"ሕግ፣ ለፍትህ እና ለርትዕ!" የቆመ የሕዝብ አገልጋይ ተቋም እንዲሆን የተቋም ግንባታ እና ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ተስፋዬ አክለውም ስልጠናው ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ተአማኒነት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም የዐቃብያን ሕግ እና አመራሮች ተገቢ የሆነ የተሟላ ስብዕና፣ ሙያ ብቃት፣ ሥነ- ምግባር ፣ የስራ ተነሳሽነት እንዲኖራቸው የዐቃቤ ሕግ ስብዕና ከፍ ለማድረግ እና ፕሮፌሽናሊዝምን ለማስፈን የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኃለፊው አያይዘውም ሰልጣኞች በሚኖራቸው የስልጠና ቆይታ የዐቃቤ ሕግ ማንነትና ምንነት፣ስብዕና፣ ባህሪ፣ የዐቃቤ ሕግ ስነ-ምግባር፣ ነፃነትና ገለልተኝነት ፣ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የዐቃቤ ሕግ ሚና እና ሰብዓዊ መብትን በማስከበር ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና የሚሉትን ወሰኝ ሙያዊ ጉዳዮችን መሰራት ያደረገ ስልጠና ሲሆን በስልጠናውም ጠቃሚ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቋሟል።
በመጨረሻም የተቋሙን ባለሙያዎች ሙያዊ ብቃት እና ስነ- ምግባር ተላብሰው እንዲሰሩ የሰብዕና ግንባታ ስልጠና በቀጣይነት ተጠናክሮ እንደሚሰጥ የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ወርቁ በበኩለቸው ገልጸዋል።

Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ
ፍርድ ቤቶች በፀረ-ሙስና ትግሉ ተደራራቢ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለጸ
**********************************************************
በአገራችን ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ፍርድ ቤቶች ከሌሎች ተቋማት በተለየ ሁኔታ ተደራራቢ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ገለጹ፡፡
ክቡር ፕሬዚዳንቱ ይህን የገለጹት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ 16ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በፍርድ ቤት ደረጃ ለማክበር ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል ለግማሽ ቀን በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
ፍርድ ቤቶች ከሌሎች ተቋማት በተለየ ሁኔታ በአንድ በኩል በሕግ በተሰጣቸው የዳኝነት ሥልጣን የሙስና ወንጀሎችን የመዳኘት ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ውስጣዊ አገልግሎት አሠጣጣቸው ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዳ እንዲሆን የመከታተልና ይህንኑ የማረጋገጥ ኃላፊነትም ያለባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፍርድ ቤቱ የተከበረው «የትውልድ የሥነምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፒሊን በመምራት፣ ሌብነት እና ብልሹ አሠራርን በመታገል የሕዝብ አመኔታን ያተረፈ የዳኝነት ሥርዓት እንገነባለን» በሚል መሪ-ቃል ሲሆን በውይይት መድረኩ ላይ 150 ያህል የፍርድ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመድረኩ ላይ «የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሙስና መከላከል ሒደት የፍርድ ቤቶች ሚና» በሚል ርዕስ በፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት በክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን ይህን ተከትሎም የፍርድ ቤቱ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል የ2012 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ በፍርድ ቤቱ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኑሀሚን አለሙ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በፍርድ ቤቱ ተዘጋጅቶ ለሕትመት የበቃው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነምግባር መተዳደሪያ ደንብን የማስመረቂያ ሥነሥርዓትም በመድረኩ ላይ ተከናውኗል፡፡
አራት ክፍሎችና 30 አንቀጾች ያሉት የሥነምግባር መተዳደሪያ ደንብ የሥነምግባር ጥሰት የሚፈጽሙ ሠራተኞችን እና የሥራ ኃላፊዎችን ተጠያቂ በማድረግ ፍርድ ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የራሱ ድርሻ እንደሚኖረውም በወቅቱ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት በተጨማሪ የፍርድ ቤቱ ም/ፕሬዚዳንቶች፣ የየምድብ ችሎቶች ሬጅስትራሮች፣ አስተባባሪ ዳኞች እና የሥነምግባር አውታሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

proclamation-no-881-2015-corruption-crimes-proclamation.pdf
4.7 MB
proclamation-no-881-2015-corruption-crimes-proclamation.pdf
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Ethiopia - Investment Proclamation No1180_2020 (English).pdf
154.1 KB