አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አሰሪዋን የገደለችው የቤት ሰራተኛ በፈፀመችው ወንጀል ጽኑ እስራት ተፈረደባት
________________
ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አሰሪዋን በመግደል እና በስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ሁለት ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣች፡፡

በ1ኛ ክስ ተከሳሽ መሰረት ነገሰ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ከምሽቱ 4 አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው ሉዋም ሱቅ ውስጥ ሟች እርግብ ገ/ክርስቶስ ቤት ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ እየሰራች በነበረችበት ወቅት ለጊዜው ያልተያዘው ግብረአበሯ በተደጋጋሚ ጊዜ ስልክ በመደወል ሟችን በተኛችበት ግደያት በማለት ሲነግራት እሷም በእለቱ ሟች ወደ ተኛችበት ክፍል በመሄድ በብርድ ልብስ አፍና የጉሮሮዋ ቧንቧ እንዲደፈን በማድረግ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ በፈጸመችው የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳለች፡፡

በ2ኛ ክስ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ለ) እና 669 (2) (መ) በመተላለፍ ተከሳሽ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ሟችን ከገደለቻት በኋላ ያልተያዘውን ግብረአበሯ ስልክ በመደወል ጠርታ ወደ ሟች ሱቅ በመግባት 6000 ብር እና ግምቱ ያልታወቀ ገንዘብ እንዲሁም የዋጋ ግምቱ ብር 1650 ብር የሆነ ስልክ ከወሰዱ በኋላ ግብረ አበሯ ለተከሳሽ 2000 እና የሟችን የእጅ ስልክ የሰጣት የወሰደች በመሆኑ በፈጸመችው የግድያና ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሳለች፡፡

ተከሳሽ የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ተነቦላት እንድትረዳው ከተደረገ በኃላ በ2ቱም ክስ ላይ የተጠቀሱትን ድርጊቶች አልፈፀምኩም በማለት የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታለች፡፡ዐቃቤ ሕግም እንደክሱ አቀራረብ የምስክሮች ቃል እንዲሳማ ለፍርድ ቤቱ ያመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ በቀረበባት 2 ክስ ጥፋተኛ ተባለች::

በመጨረሻም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን የዘወትር ፀባይ መልካም እንደነበር እና የቤተስብን የምትረዳ መሆኑን በማቅለያ በመያዝ በ2ቱ ክስ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡
ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
በመምህርነት ሙያ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ትምህርት ቤት የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
________________

ቀዳማዊ ሰለሞን የተባለ ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 669/2/መ/ ላይ የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ሰኔ 4 ቀን 2011 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ትራፊክ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በመምህርነት ሙያ ተቀጥሮ ከሚሰራበት 3A አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት ከተመራቂ ተማሪዎች የተሰበሰበውን የጋዋን እና የፎቶ ብር አምስት ሺህ ሰባት መቶ ብር የጠረጴዛውን መሳቢያ በመገንጠል የወሰደ እና የተሰወረ በመሆኑ በፈፀመው የከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሷል፡፡

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ተከሳሹ የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት እንደ ክሱ ሙሉ በሙሉ ያመኑ በመሆኑ ባመነው መሰረት በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ይሰጥልኝ ሲል አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር በዝርዝር ያመነ በመሆኑ ጥፋተኛ ነህ ብሏታል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በተከሳሹ ላይ የወንጀሉን ደረጃ በደረጃ 4 እርከን 19 መነሻ ቅጣት በመያዝ ተከሳሹ የወንጀል ሪከርድ የሌለበትና ወንጀሉን በዝርዝር ያመነ በመሆኑ በ2 የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት ዝቅ እንዲል በማድረግ በእርከን 17 ስር በማሳረፍ ተከሳሽን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራል ያለውን በ3 ዓመት ከ3 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡
ፌ.ጠ. አ .ህ
ሞባይል ሰርቆ ለማምለጥ የሞከረዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ ፡፡ ተከሳሹ ወርቁ አንዳርጌ ይባላል
________________
የ34 ዓመት ጎልማሳ ነዉ ካልተያዘዉ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን ከመኪና ዉስጥ ሞባይል ሰርቆ ለማምለጥ ሲሞክር ተይዟል፡፡

ዐቃቤ ህግም ፈጽሞታል ባለዉ የስርቆት ወንጀል ክስ መስርቶበት ሲከራከር ቆይቷል፡፡ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና 665/1/ ሥር የተደነገገዉን በመተላለፍ ነሐሴ 12 ቀን 2011ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ዲያስፖራ አደባባይ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከቀኑ 5፡30 ሲሆን ተከሳሹ የማይገባዉን ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት በማሰብ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ልዩነሽ በሀጋን የሆነ እና የዋጋ ግምቱ 25000(ሀያ አምስት ሺህ ብር)የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል ግብረ አበሩን አሰርቋል፡፡

የግል ተበዳይን የመኪና መስኮት ከፍቶ በማዘናጋት እጇን ይዞ እያወራት ባለበት ሁኔታ ያልተያዘዉ ግብረ አበሩ ሞባይሏን ከመኪና ዉስጥ አዉጥቶ ከአካባቢዉ ተሰዉሯል፡፡ እሱም አብሮ በመሮጥ ለማምለጥ ሲሞክር ተይዟል፡፡ በመሆኑም በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸመዉ የስርቆት ወንጀል ክሱ ተመስርቶበታል ሲል የዐቃቤ ህግ የክስ ሂደት ያስረዳል፡፡

ክሱ የተፈፀመዉ በየካ ክፍለ ከተማ የላምበረትና አካባቢዉ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን የተፈጸመዉ ወንጀልና የተመሰረተበት የክስ አይነት በመርማሪ ፖሊስ ካሳሁን በላይ አስረጅነት ተገልጾለት የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡ በእለቱ የግል ተበዳይ እግረኛ ለማሳለፍ መኪናዋን ስታቆም ተጠግተህ እጇን በመያዝ ያልተያዘዉ ግብረ አበርህ ሞባይሉን ነጥቆ እንዲያመልጥ አድርገሀል፡፡

አንተም ተከትለህ በመሮጥ ላይ ሳለህ በአካባቢዉ በነበሩ ሰዎች ተይዘሃል የሚል ሲሆን ተከሳሹ ግን የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምኩም ሲል ቃሉን ሰጥቷል፡፡ የፌደራሉ የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡለትን አራት ምስክሮች ዋቢ አድርጎ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነዉ ሲል ብይን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ህዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም ባስቻለዉ 1ኛ ወንጀል ችሎት የተከሳሽን የጤና ችግር በማቅለያነት ይዞ በአራት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
567..:
I'm Abush from Hu...if you have succession ppt prepared by Awet Lijalem unit 2 please share it!
Alemnew:
Call for paper to the International Conference on Investment Law and Policy to be organized by Debre Markos University School of Law
Abay:
I am Abayneh. Can you send me materials regarding corporal criminal liability in ethiopia?
UN Women Women's leadership and political participation.
Leave no one behind
Women's political participation and elections in Ethiopia: Envisioning 2020 and beyond for generation Equality.
Conference at Capital hotel 19-20 December 2019
https://telegram.me/TransparencyEthiopia
ቅፅ_23_የፌ_ጠ_ፍ_ቤት_ሠበር_ሰሚ_ችሎት_ውሳኔዎች.pdf
3.8 MB
የሰበር ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 23 ዲጂታል ቅጂ ይፋ ተደረገ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 23 የዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ተደራሽ መደረጉ ተገለጸ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸው የሰበር ውሳኔዎች ተደራሽነት ለማስፋት በፍርድ ቤቱ የጥናትና የህግ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በኩል ተዘጋጅቶና ታትሞ በስጦታ እና በሽያጭ እየተሰራጨ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የቅጾቹን ዲጂታል ቅጂ (Softcopy) በድረገጽ ላይ በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ ስርጭት መጠኑ እንዲያድግ እያደረገ ይገኛል፡፡
ዳሬክቶሬቱ ቀደም ሲል በድረገጽ ተደራሽ የተደረገውን ቅጽ ሃያ ሁለት (22) አሳትሞ በሜጋ ማተሚያ ድርጅት የመጽሃፍት መሸጫ መደብሮች እያሰራጨ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 23ን በቅርብ ጊዜ አሳትሞ ያሰራጫል ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ማየትና ማንበብ ለተሳናቻው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅጾቹን ተደራሽ ለማድረግ ከቅጽ 1 እስከ ቅጽ 18 የተካተቱ ውሳኔዎችን በድምጽ ተቀርጾ ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረገ ሲሆን የስርጭት ሁኔታና መንገዱን በተመለከተ ከፍርድ ቤቱ የበላይ አመራር በሚሰጥ አቅጣጫ መሰረት እንደሚሰራጭ ዳይሬክቶሬቱ አስታውቋል፡፡
የሰበር ውሳኔ ቅጽ 23 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረገጽ በመግባት የሰበር ውሳኔዎች የፌዴራል ተቅላይ ፍርድ ቤት ቴሌግራም አካውንት በዚህ መረጃ ላይ አባሪ ተደርጓል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ቤቱ አብሮት እንዲያድር በጋበዘዉ ጓደኛዉ ላይ ግብረሰዶም የፈጸመዉ ግለስብ በእስራት ተቀጣ
________________

ተከሳሹ ጉንፋ ጫጫ ይባላል፡፡የ46ዓመት ዕድሜ ጎልማሳ ነዉ፡፡በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፈረንሳይ ትምህርት ቤት አካባቢ ነዋሪ ነዉ፡፡ በእንግድነት ከቤቱ እንዲያድር በጋበዘዉ የወንድ ጓደኛዉ ላይ ፈጽሞታል ባለዉ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት በክርክር ላይ ቆይቷል፡፡

ግለሰቡ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 630/2/ሀ/ ሥር የተደነገገዉን ተላልፎ ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3፡40 ሲሆን ጉራራ ከሚገኘዉ መኖሪያ ቤቱ ጓደኛዉ የነበረዉን የግል ተበዳይ አቶ ገነቱ እያሱን ከእርሱ ጋር አብረዉ እንዲያድሩ ጋበዘዉ፡፡የግል ተበዳዩ አገር አማን ብሎ ከተከሳሹ መኖሪያ ቤት ከገባ በኋል ግን ያጋጠሙ ፈጽሞ ይሆናል ብሎ ያልጠበቀዉ ክስተት ነበር፡፡ የተከሳሽ ጓደኞች በድንገት በሀይል እጅና እግሮቹን ጠፍነገዉ ያዙት-ከዚያ በኋላ የሆነዉ ሁሉ ሌላ ነበር ፡፡ ተከሳሹ ለንጽህና ተቃራኒ እና ከባህላችን ያፈነገጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ድርጊት ባልገመተዉና አምኖት በቀረበዉ ጓደኛዉ ላይ ተፈጸመበት - ግብረሰዶም፡፡

ተከሳሽ በፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ በምርማሪ ፖሊስ ስጦታ ጌታሁን የእምነት ክህደት ቃሉን ተጠየቀ፡፡ መርማሪ ፖሊስ ስጦታ ጌታሁን በተጠቀሰዉ ቀንና ሰኣት የግል ተበዳይ በመኖሪያ ቤትህ አብሮ እንዲያድር ጠርተኸዉ በእለቱ የቤትህንና የበረንዳህን መብራት አጥፍተህ የግል ተበዳዩ ማንነታቸዉን የማያዉቃቸዉን ሁለት ግለሰቦች ጨለማን ተገን አድርገዉ ገብተዉ አፉን አፍነዉ እጅና እግሩን በሀይል እንድይዙልህ አድርገህ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽመህበታል ሲል አስርድቷል፡፡ ይሁን እንጂ ተከሳሹ በፍጹም ሀሰት ነዉ ድርጊቱን አልፈጸምኩም ወንጀለኛም አይደለሁም ሲል ክዷል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን አጠናክረዉ ቀጠሉ፡፡ ከየካቲት 12 ሆስፒታል የተገኘዉ የግል ተበዳይን የጉዳት መጠን የሚገልጸዉ የህክምና ማስረጃ የግል ተበዳዩ የተመሳሳይ ጾታዊ ጥቃት ሰለባ መሆኑን የምርመራ ዉጤቱ አረጋገጠ፡፡
ከምርመራዉ ሂደት ተጨማሪ ሶስት የሰዉ የምስክርነት ቃል ተጨምሮ ተከሳሹ ወንጀሉን መፈጸሙ ተረጋገጠ፡፡

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ወንጀል ችሎትም የቀረቡለትን የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎች ዋቢ አድርጎ በተከሳሽ ላይ የጥፋታኝነት ብይን ሰጠ፡፡

በዚህም መሰረት ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባስቻለዉ 5ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ በ5ዓመት ከ8 ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
የሰበር ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 23 ዲጂታል ቅጂ ይፋ ተደረገ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 23 የዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ በፍርድ ቤቱ ድረ ገጽ (www.fsc.gov.et) ላይ ተደራሽ መደረጉ ተገለጸ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠባቸው የሰበር ውሳኔዎች ተደራሽነት ለማስፋት በፍርድ ቤቱ የጥናትና የህግ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በኩል ተዘጋጅቶና ታትሞ በስጦታ እና በሽያጭ እየተሰራጨ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የቅጾቹን ዲጂታል ቅጂ (Softcopy) በድረገጽ ላይ በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ ስርጭት መጠኑ እንዲያድግ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዳሬክቶሬቱ ቀደም ሲል በድረገጽ ተደራሽ የተደረገውን ቅጽ ሃያ ሁለት (22) አሳትሞ በሜጋ ማተሚያ ድርጅት የመጽሃፍት መሸጫ መደብሮች እያሰራጨ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 23ን በቅርብ ጊዜ አሳትሞ ያሰራጫል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማየትና ማንበብ ለተሳናቻው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅጾቹን ተደራሽ ለማድረግ ከቅጽ 1 እስከ ቅጽ 18 የተካተቱ ውሳኔዎችን በድምጽ ተቀርጾ ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረገ ሲሆን የስርጭት ሁኔታና መንገዱን በተመለከተ ከፍርድ ቤቱ የበላይ አመራር በሚሰጥ አቅጣጫ መሰረት እንደሚሰራጭ ዳይሬክቶሬቱ አስታውቋል፡፡

የሰበር ውሳኔ ቅጽ 23 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረገጽ በመግባት የሰበር ውሳኔዎች /Cassation/ ተብሎ በተሰየመው ክፍል ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ወይም fsc.gov.et/Documents/GetPdf/36 መስፈንጠሪያ በመጠቀም ሊያገኙት ይችላሉ ተብሏል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
https://telegram.me/lawsocieties