Pls check us whether federal justice institution begins to deliver judicial training for fresh law graduates.
pls Plsss Send Me Journal Article Review Of The Legal Protection Of Human Right In Africa. Written By Abdullahi Ahmed An-Na’im: On human right.Tnx In advance. thank you a Lot👍
via Baraki Belay The link for the paper is here https://www.abyssinialaw.com/online-resources/researches/
category/19-criminal-law
About the hate speech research paper by baraki belay
He may contact me in person
Abyssinialaw
Research Works | Abyssinia Law
Abyssinia Law Research is a digital collection of open access scholarly research publications from different Universities.

ሰላም Ale Hate speechን በተመለከተ የተጻፈ article, book or paper(research) ካላችሁ አካፍሉኝ linkም ቢሆን
Ĵų§ŧ Şïłęňţ:
Hey my ale, would you please sent me comments on the charitable organization proclamation

Hu No One Is Parfect:
Please share if you have contract law pp and tort law
Please help me my questions

እንደዋዛ!
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የኢፌድሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌስቡክ ገጽ ተከታዮቻችን "እንደዋዛ" በተሰኘው ፕሮግራማችን ብዙውን ጊዜ ችላ የምንላቸው፤ ነገር ግን ወንጀል ሆነው በህግ ማህደሮቻችን ላይ ሊያስጠይቁ እንደሚችሉ የተቀመጡ ጉዳዮችን የምናይበት ፕሮግራም ነው፡፡
ለዛሬ ያከራዩትን ሰው ማንነት አለማሳወቅ ከ3 እስከ 10 ዓመት ጽኑ እሥራት እንደሚያስቀጣ ያውቃሉ? በሚል አርዕስት ላይ ተከታዩን አጭር ጹሁፍ ልናስነብባችሁ ወደናል መልካም ንባብ፡፡ ማንኛውንም ቤት፣ ለንግድ ቢሆን ለመኖሪያ፣ ቦታ፣ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ የሚያከራዩ ከሆነ ይህንን የሕጉን አንቀጽ ከግምት ያስገቡ፡፡
በ2001 ዓ.ም የወጣው የጸረ-ሽብር አዋጅ አዋጅ ቁጥር 652/2001 በአንቀጽ 15 ማንኛውም ቤት፣ ቦታ፣ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ ወይም ተመሳሳይ መገልገያ አከራይ (ልብ ይበሉ አከራይ) የሆነ ሰው የተከራዩን ማንነት በዝርዝርና በጽሑፍ የመያዝ እንዲሁም በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ብሎ ደንግጓል፡፡
በዚህም መሠረት አከራይ ከሆኑ የሚያከራዩትን ሰው ማንነት ማለትም ስም፣ አደራሻ እንዲሁም መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ማንኛውም ዓይነት ማንነትን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒ በማድረግ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ በመሔድ የማሳወቅ ግዴታ አለበዎት፡፡
በተለይ የቤት ኪራይ በመኖሪያ ቤትዎ እያከራዩ ከሆነና ያከራዩት ሰው ማንነት የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ከሆነ የፓስፖርቱን ቅጂ የመያዝና ለፖሊስ የማቅረብ ግዴታ ያለበዎት መሆኑን ይኼው አዋጅ በአንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 2 ሥር ደንግጓል፡፡ ይህንን ግዴታ ያልተወጡ እንደሆነ ማለትም አከራይተው ስለአከራዩት ሰው ማንነት ለፖሊስ ያላሳወቁ እንደሆነ ከሦስት እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ሊያስቀጣዎት እንደሚችል የጸረ ሽብር ሕጉ አንቀጽ 35 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
እንዲህ ዓይነት የማከራየት ዕድል ሳይገጥምዎ ተከራይ የሆኑ እንደሆነ ወይም አከራይ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ያለዎት እንደሆነ ይህንን የሕጉን ግዴታ በማሳወቅ የድርሻዎን መወጣትዎን አይርሱ! ወይም አከራይዎት ስለማንነትዎ በጠየቀ ጊዜ ወይም መታወቂያዎትን ኮፒ እንዲያደርጉ ሲጠይቆዎት መተባበርን አይዘንጉ መልእክታችን ነው፡፡
ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን ጥንቅር በዚሁ አበቃን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካም ጊዜን ተመኘን፡፡መረጃውን ያገኘነው ከአቢሲኒያ ለው ድህረ-ገጽ ላይ ነው ሰላም፡፡
https://telegram.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመው የፖሊስ አባል በእስራት ተቀጣ
________________
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አካባቢ ከሌሊቱ 7፡00 ለአካል መጠን ባልደረስ ልጅ የግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመው የፖሊስ አባል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡
የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 631 (1) (ሀ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከእርሱ ጋር አንድ አይነት ፆታ ካለውና ለአካል መጠን ባልደረሰ ልጅ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት ለመፈፀም አስቦ መጋቢት 03 ቀን 2011 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቆጨ አካባቢ ከሚገኘው የወረዳ 9 ቀጠና 2 የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አግልገሎት መስጫ ቢሮ ውስጥ እድሜው ከ14-15 ዓመት የሚሆነውን የግል ተበዳይ ከተኛበት ቦታ እስረኛ ነህ በማለት ቀስቅሶ ወደ ቢሮው እንዲገባ ካደረገ በኃላ የለበሰውን ሱሪና ትሸርት አስወልቆ በግል ተበዳይ ላይ በፈፀመው አስነዋሪ የወንጅል ድርጊት ተከሷል፡፡
ዐቃቤ ሕግም የሰው እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የተላከውን የግል ተበዳይ የዕድሜና የጤና ሁኔታ የሚገልጽ ማስረጃ አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
ተከሳሽ ክሱ ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ መቃወሚያ የለኝም የወንጅል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ የሚያስረዱ ምስክሮች ቃል እንዲሰማ አድርጓል፡፡ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ብሎታል::
የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎትም መዝገቡን መርምሮ ተከሰሽ የፖሊስነት ስልጣኑን አላግባብ በመጠቀም፣ ጨካኝነቱን በሚያሳይ እና በሌሊት የተፈፀመ መሆኑን በማክበጃ በመያዝ በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል::

በፍርድ ቤቶች በሚተገበሩ የለውጥ ስራዎች ላይ ሴት ዳኞች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተገለጸ
በፌደራል ፍርድ ቤቶች በአዲስ መልክ እንዲተገበሩ በሚጠበቁ አዲስ ለውጦች ላይ ሴት ዳኞች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡
ክብርት ፕሬዜዳንትዋ ይህን የገለጹት "የሴት ዳኞች ዕድሎችና ፈተናዎች" በሚል ርዕስ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ሴት ዳኞች በአዜማን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ጥቅምት 22 ቀን 2012 ዓ.ም በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በሆኑት ወ/ሮ እትመት አሰፋ "በፍትሕ ተቋማት የሴቶች ተሳትፎ" በሚል ርዕስ እንዲሁም በዳኛ ሌሊሴ ደሳለኝ "ዳኝነትና ሴቶች" በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ወ/ሮ እትመት አሰፋ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ በሕገመንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ፣ በፌደራል ፍርድ ቤቶች፣ በፌደራል አቃቤ ሕግ፣ በፌደራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ የሴቶች ውክልና አነስተኛ መሆኑን በጥናታቸው አመላክተዋል፡፡
ሴቶች በፍትሕ ተቋማት ሲሰሩ ጉዳዮችን የመረዳት፣ ተረጋግቶና ጊዜ ሰጥቶ በትጋት ነገሮችን የማየት እንዲሁም በታማኝነት የመስራት ብቃት እንዳላቸውና ለተለያዩ ተጽዕኖ ፋጣሪ ነገሮች የመጋለጥ ዕድላቸው አነስተኛ እንደሆነ የሚታመን መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ዳኛዋ፣ ሴቶች በፍትሕ ተቋማት ያላቸው ቁጥር ግን አነስተኛ እንደሆነ በአኃዛዊ ማስረጃ በማስደገፍ አሳይተዋል፡፡
አሁን ያለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራር የሴቶችን ተሳትፎ እንደሚያሳድግ ያላቸውን እምነት የገለጹት ክብርት ዳኛ፤ በቅርቡ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስድስት ሴት ዳኞች መሾማቸው አመራሩ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለውን ፍላጎት ጠቋሚ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በፍትሕ ተቋማት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግም በዚህ ዙሪያ ፖሊሲና ሕጎችን ማውጣት፣ ሴቶችን በተመለከተ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖር ማሕበረሰቡ ላይ መሥራት፣ የሴቶችን ልዩ ፍላጎቶች መለየት፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ እንዲሁም ሴቶችን ማስተማር እና ማብቃት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሌሊሴ ደሳለኝ በበኩላቸው "ዳኝነትና ሴቶች" በሚል ርዕስ ባቀረቡት የመወያያ ጽሑፍ ሴቶች በዳኝነት ሥራ ላይ ሙሉና እኩል ተሳታፊ መሆናቸው የሕብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑ ሴቶች ሚዛናዊ ውክልና ያላቸው መሆኑን ለማረጋገጥና የፍርድ ቤት አመኔታን ለማሳደግ እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡
የሰው ሀብትን በአግባቡ ከመጠቀም አኳያም ሴቶች ከህብረተሰቡ ግማሽ ቁጥር የሚይዙ እንደመሆናቸው መጠን በፍርድ ቤቶች በሚገኙ የዳኝነት ቦታዎች ሴቶች የማይሳተፉ ከሆነ አገሪቱ ያላትን የሰው ሀብት በአግባቡ እየተጠቀመች እንዳልሆነ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በዳኝነት የሥራ ዘርፍ እና አመራር ሰጪነት የሴቶች ቁጥር አነስተኛ መሆኑ በሌሎች አገሮችም እንደሚስተዋል የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙ ገልጸው፣ ይህ ቁጥር ግን ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ቢመጣም ጭማሬው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በአገራችንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ሴቶች ወደ አመራርነት መምጣታቸው እንደ በጎ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰው፣ እስካሁን ድረስ ሴቶች ወደ ዳኝነት ሙያ እና ወደ አመራርነት እንዳይመጡ ካደረጓቸው ምክንያቶች መካከል በሕብረተሰቡ ውስጥ በሴቶች ላይ ያለው ባህል እና የሥራ ጫና እንዲሁም ሴቶችን የሚያበረታቱ አዋጆችና መመሪያዎች ያለመኖር፣ ሴቶች በዚህ ዙሪያ የሚያገኙዋቸውን ዕድሎች በአግባቡ ያለመጠቀም እንዲሁም ፍላጎት ማጣት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የቀረቡትን የመወያያ ጽሑፎች ተከትሎ በተደረገው አጠቃላይ ውይይት ሴት ዳኞች ከወንድ ዳኞች በተለየ ያሉባቸውን ጾታዊ፣ ቤተሰባዊ እና ማሕበራዊ ጫናዎች ተቋቁመው የዳኝነት ሥራቸውን በአግባቡ ሊያከናውኑ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 355 ዳኞች በዳኝነት ስራ ላይ ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 246 ወንድ 109 ደግሞ ሴት ዳኞች መሆናቸውን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት መረጃዎች ያሳያል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት https://telegram.me/lawsocieties

በቤተሰብ ችሎት በሚስተዋሉ አከራካሪ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሔደ
"በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ የታዩ ለውጦች፤ በቤተሰብ ችሎት ዳኝነት ላይ የሚስተዋሉ አከራካሪ ጉዳዮች እና ከቤተሰብ ችሎት ዳኞች በሚጠበቁ ተግባራት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ጥቅምት 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአዜማን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ተካሔደ፡፡
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሴት ዳኞች በተሳተፉበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተሻሻለው እና ነባሩ የቤተሰብ ሕግ ጉልህ ልዩነቶችን የሚዳስስ የመወያያ ጽሑፍ በፌዴራል ከፍተኛ ፍረድ ቤት ዳኛና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮርት ማናጀር በሆኑት በአቶ ጎሽዬ ዳምጠው ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የውይይቱ ዓላማ የህብረተሰብ መሠረት የሆነውን ጋብቻ ከመጠበቅ አንፃር በስራ ላይ የሚያጋጥሙ አከራካሪ ነጥቦችን በተመለከተ በዳኝነት ሥራ ላይ የተገኘ ልምድን ለማጋራት መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
ለውይይት የቀረበው ጽሑፍ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ የታዩ ለውጦች፣ በቤተሰብ ዳኝነት ላይ የሚስተዋሉ አከራካሪ ጉዳዮች እና ከቤተሰብ ችሎት ዳኞች የሚጠበቁ ተግባራት የተዳሰሱበት ሲሆን በመድረኩ ላይ የነበረው የሀሳብ ልውውጥ በጉዳዩ ላይ የዳኞችን ግንዛቤ በማዳበር የዳኝነት ሂደቱን ወጥ እና ተገማች ለማድረግ እንደሚረዳ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
በውይይቱ ላይ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ላይ መሠረታዊ ስህተት ስለሚባሉ ጉዳዮች፣ በፍቺ ክርክር ላይ ባለጉዳይ በአካል መቅረብ ይኖርበታል ወይስ በወኪሉ አማካይነት መከራከር ይችላልን?፣ ስለማሰላሰያ ጊዜ አሰጣጥ፣ ስለጋብቻ ማስረጃ፣ ስለንብረት ክፍፍል፣ የጋራ ንብረትን ለሌላ ወገን በስጦታ ማስተላለፍን በተመለከተ ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡
በሌላ በኩል ስለቀለብ አቆራረጥ፣ አባትነትን በመካድ ላይ ስለሚቀርብ ክስ፣ ስለተደራራቢ ጋብቻና ፍች፣ የቤተዘመድ ሽምግልና ጉባኤ የዳኝነት ስልጣን መነሳትን በተመለከተና በሌሎች ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡
ጽሑፍ አቅራቢው ከቤተስብ ችሎት ዳኞች ስለሚጠበቁ ተግባራት በሰጡት ማብራሪያ በጎ የተግባቦት መስተጋብር (good communication) ማዳበር እንደሚገባ፣ ባለጉዳይን በጥሞና (በትዕግስት) ማዳመጥ እንደሚያስፈልግና ባለጉዳዮችን ተረጋግቶ ማዳመጥ ወደ ትክክለኛ ፍትህ እንደሚያደርስ የራሱ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
ይህን ተከትሎም "የማሕበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ሚና በቤተሰብ ችሎት" በሚል ርዕስ በፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (Children Justice Project Office) አስተባባሪ የሆኑት ዳኛ ልዑለስላሴ ሊበን በቤተሰብ ችሎቶች የሕጻናትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለፍርድ ቤቶች እና ለዳኞች ስለሚደረገው ሙያዊ ድጋፍ ማብራሪያ ቀርቦ በተሳታፊዎቹ የሐሳብ ልውውጥ ተደርጎበታል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት