አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለፌደራል ጠበቆች ማህበር አባላት በድጋሚ የቀረበ የእርዳታ ጥሪ ፣

የህግ ባለሙያ (ጠበቃ ) አቶ ኤፍሬም ተካ ሀ/የሱስ በፌደራል በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር አባል ናቸው ። ይሁንና ላለፉት 2አመታት ባደረባቸው Rectum Colon የተባለ ህመም በሀገር ውስጥና በህንድ ሀገር ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የህክምና ክትትል በማድረግ መቆየታቸው ገልፀው አሁንም በሀኪሞች ውሳኔ የመጨረሻ ዙር ህክምና ማከናወንና ይህንኑ ለመፈፀም 10,000ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፀው የሚወጣውን ከፍ ያለ ወጪ አቅማቸው መሸፈን የማይችል በመሆኑ በማህበሩ በኩል ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀው ድጋፍ የተሰባሰበላቸው ቢሆንም ህክምናውን ሊሸፍን አልቻለም::

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ድጋፍ ይደረጋችሁም ሆነ ያላደረጋችሁ የህግ ባለሙያውን ለማገዝ የምትችሉ የማህበሩ አባላት በስልክ ቁጥር
+251 911- 631118 ደዉላችሁ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን እንዲሁም በባንክ አካዉንታቸዉ ገቢ ለማድረግ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000037330756 ወይም በአዋሽ ባንክ አካውንት ቁጥር - 01320108358200 ላይ ድጋፍ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን ማህበሩ ይገልፃል ።

የማህበሩ ጽ/ቤት
ሰኔ 06 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
#ትግራይ

የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ ቢወስንም አልተተገበረም።

6 የVIP የጥበቃ አባላት የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚከካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " በመባል ተከሰዋል።

የመቐለ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤት ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሊቀመንበሩ ላፕቶፕ ኮምፒተር ስርቆት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወስኗል።

ስድስቱ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ቤተሰቦቻቸው ብር ቢያስይዙም " ከላይ የመጣ ትእዛዝ " በሚል ከእስር አልተለቀቁም ብለዋል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች።

ባለፈው የግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ሳምንት መጨረሻ የሊቀ-መንበሩ ላፕቶፕ ኮምፒተር " በጠባቂዎቻቸው ተዘርፏል " የሚል መረጃ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት ቢሰራጭም ደጋፊዎቻቸው " መረጃው የፈጠራ ወሬ ነው " በማለት ሲያጣጥሉ ቆይተዋል።

ሊቀ-መንበሩም በቅርቡ ከደጋፊዎቻቸው ጋር በነበራቸው ስብሰባ " አልተሰረቅኩም " የሚል እንደምታ ያለው በሚያሰመስል ሁኔታ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ይዘው ታይተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia