አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from የሕግ መረጃ
#AddisAbaba

የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን  ደንብ መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።

ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ነው።

ደንቡ " በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው " ብሏል።

ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ፦

ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤

የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤

ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡

ቢሮው " ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም  በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው " ብሏል።

ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል ይደረጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል ነው የተባለው።

መረጃው ከየአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱ_የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_መመሪያ_.pdf
2.5 MB
#የታክስ_ደረሰኝ_አጠቃቀም_እና_አስተዳደር_መመሪያ_/ማሻሻያ/_ቁጥር_188/2017

ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ እና በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል፡፡

የመመሪያውን ሙሉ ክፍል ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡- https://t.me/AleHig/10068
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ከነማሻሻያ አዋጁ ትላንትና ፀድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ረቂቅ አዋጁንና ማሻሻያ ሪፖርቱን አስመልከተው የተለያዩ የድጋፍና የተቃውሞ ሐሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ 
የምክር ቤት አባልት ምን አሉ ?

- ማሻሻያው ከአሁን ቀደም ከሥራ ባህሪያቸው አንፃር ለየት ባለ የአደረጃጀትና የአሠራር መዋቅር ተደራጅተው የነበሩ የፍርድ ቤቶችን መሰል አዋጆችን መሻሩን የወቀሱ ነበሩ፡፡

- ማሻሻያ አዋጁ ልክ ለገቢዎችና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች እንደሰጠው ሁሉ፣ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባ እንደነበርም ተገልጿል።

- ሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በየትኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎች በእኩልነትና በፍትሐዊነት ሊወዳደሩ የሚችሉበት አስገዳጅ ሁኔታ በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ አለመቅረቡ ተነስቷል።

- የውስጥ ዝውውርን በተመለከተ አንድ የተቋም ኃላፊ ለውጤታማነት በሚል ሠራተኞችን ወደ የሚፈልግበት ቦታ አዛውሮ ማሠራት፣ ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች ደግሞ መልቀቅ ይችላሉ መባሉም ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ የአሠራር ክፍተቶችን የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል።

የአብን የምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፦

" እንዲህ ዓይነት አዋጆች ሲዘጋጁ ሰፊ ዝግጅትና ውይይት ይፈልጋሉ። እንዲሁም የሠራተኞችን ሥጋት ማካተት ይገባል።

የረቂቅ አዋጁ መንደርደሪያ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሠራተኞች ስብጥር እንዲኖር ነው በሚል መገለጹ ችግር አለበት።

' ሲቪል ሰርቪሱ በአንድ ብሔር የበላይነት ተይዟል ' በሚል የቀረበ ነው። ያን ለማለት ደግሞ በሚያስችል መንገድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ሲቪል ሰርቪሱ ብቃትንና አቅምን መሠረት አድርጎ ሊገነባ ይገባል። ኮታን ወደ ማከፋፈል አይወስደንም ወይ ? ሥራን በኮታ ማደላደሉ ማቆሚያው የት ነው ?

አንድ ሠራተኛ አፈጻጸሙ ምንም ይሁን ምን ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እስከፈለገ ድረስ አንስቶ ሌላ ተቋም ላይ በተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ መመደብ ይችላል። ያን የማይፈልግ ከሆነ ሠራተኛው መልቀቅ ይችላል መባሉ የሠራተኞችን መብት የሚጋፋና ዕጣ ፋንታቸውን በአለቆቻቸው እንዲወሰን የሚያደርግ ነው።

እንዲሁም ከሥራ እንዲለቁ የሚገፋፋ ነው።

የሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከ39 ወደ 48 ሰዓታት እንዲያድግ መደረጉም አግባብነት የሌለው ነው " ብለዋል።


የኢዜማ አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በረቂቅ አዋጁ ' ዘመናዊና ኢትዮጵያን የሚመስል ' መባሉ በዘወርዋራው የኮታ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

' ዘመናዊ አገርና ዘመናዊ ቢሮክራሲ እንፈጥራለን ' እያልን የመንግሥት ሠራተኞችን ከችሎታና አቅም ይልቅ በብሔር ኮታ እንቅጠር ማለት እርስ በርሱ የሚቃረን ሐሳብ ነው።

ማይክሮሶፍትን መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት በአሜሪካውያን ሳይሆን በህንዳውያንና በቻይናውያን የሚመሩና የሚተዳደሩ ናቸው።

የመንግሥት ተቋማት የሃይማኖት የስብከት ቦታዎች እየሆኑ ነው። ይህ በጥብቅ ሕግ ጭምር ሊከለከል ይገባል።

አንድን ሠራተኛ መሥሪያ ቤቱ ወይም የበላይ ኃላፊው በፈለገው ቦታ መድቦ ማሠራት ይችላል የሚለው ሰው በሙያ (ፕሮፌሽን) እንዳያድግና የካበተ ልምድ እንዳይኖረው እንደሚያደርግ፣ ይህ ደግሞ በተቃራኒው ቢሮክራሲውን የበለጠ የሚጎዳ ነው።

የበላይ አመራሩ የመጨረሻ ወሳኝ መሆኑ ከሕግና ከሥርዓት የሚፃረርና ሰብዓዊ መብትንም የሚጋፋ ነው።

ይህ ከሆነ ባርነትን እንደገና በሕግ እያፀደቅን ነው ማለት ነው ? ውሳኔውን ፍርድ ቤት መስጠት አለበት " ብለዋል።


የምክር ቤት አባል አቶ ለማ ተሰማ ምን አሉ ?

" ረቂቅ አዋጁ ሠራተኞች በትምህርት መስክና ደረጃቸው እንዲሁም በልምዳቸው እንጂ፣ ከዚያ ውጪ የሚመደቡበትን አሠራር አይፈጥርም።

የሚነሱ ሥጋቶች ቀጥለው ሊወጡ በሚችሉ ደንቦች ሊመለሱ ይችላሉ።

በረቂቅ አዋጁ የተካተቱ አንዳንድ ጽንሰ ሐሳቦች በጥርጣሬ ሊታዩ አይገባም። ሲቪል ሰርቪሱ መለወጥ አለበት። ትናንት የነበረው አግላይ ነበር። ዕድልንም አይሰጥም ነበር።

ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም ጠርጎ የሚያስወጣ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በብቃቱ ተወዳድሮ ሠራተኛ መሆን የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር ነው። "


ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

🔴 ብዙዎቹ ጥያቄዎች በውይይት ወቅት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው ነበር።

🔴 ፍርድ ቤቶች በልዩ ሁኔታ መታየት ነበረባቸው መባሉ በረቂቅ አዋጁ በሚቋቋመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የሜሪትና የደመወዝ ቦርድ በኩል ራሱን ችሎ ምላሽ ሊያገኝ ይችላል።

🔴 በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ኮታ የሚል ነገር የለም። ኮታ ተቀባይነት እንደሌለው በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ተቀምጧል።

🔴 ረቂቅ አዋጁ የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩትን እንደ አዲስ የብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት በሚል ስያሜ አቋቁሞ ሠራተኞችን በብቃታቸውን ለመመዘን ያስችላል።

🔴 ሠራተኞችን የማዘዋወሩ ኃላፊነት በማኔጅመንት እንጂ በበላይ ኃላፊዎች ብቻ አይወሰንም። የሠራተኛው ምክንያት የሚደመጥበትና መብቱ የሚጠበቅበት አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተካቷል።

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት ይህ ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ሆኖ በ3 ተቃውሞ በአራት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 3- ክፍል 2
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋና ዋና ማሳያዎች

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. ህዳር 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሙስና በተለያዩ መንገዶች ሊገለፅ የሚችል፣ በባህሪው ተለዋዋጭና ውስብስብ ነው፡፡ ሆኖም ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋና ዋና ማሳያዎች የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

1. የግልፀኝነት ጉድለት
👉 ግልፅ ያልሆነ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ሲኖሩ እና መረጃዎችን ለህዝብ ወይም ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ያለማድረግ ችግሮች ሲበራከቱ፣

2. የጥቅም ግጭት ሲፈጠር
👉 የግል ፍላጎት ከተቋም ፍላጎት ጋር የሚጋጭበት ሁኔታዎች ሲፈጠር፣

3. ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም
👉 ውሳኔ ሰጪ አካላት ከተቋማቸው ጥቅም አንጻር ውሳኔዎችን ከመወሰን ይልቅ ለግል ጥቅማቸውና ለሌሎች ግለሰቦችና ድርጅቶች በሚያመች መንገድ በመወሰን ስልጣናቸውን አለአግባብ ሲጠቀሙ፣

4. መመሪያዎችን ችላ ማለት
👉 ከመመሪያ ውጪ የሚሰሩ ስራዎች ሲበራከቱ፣

5. ከመጠን ያለፈ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ወይም ያልተለመደ ቅናሽ ሲያጋጥም
👉 ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪ ወይም ከገበያ ዋጋ ጋር የማይጣጣሙ ግዥዎች መፈፀም፣

6. ሙስና ጠቋሚዎችን ችላ ማለት
👉 ሪፖርት የተደረጉ ስጋቶችን አለመፈተሽና ሙስና ጠቋሚዎችን ችላ ማለት፣

7. የተጠያቂነት ማነስ
👉 ደካማ የተጠያቂነት ስርዓት ሲኖርና ተመጣጣኝ የእርምት እርምጃ መውሰድ አለመቻል፣

8. የክትትል ማነስ
👉 ደካማ የውስጥና የውጪ ክትትልና ቁጥጥር ሲኖር ነው፡፡

በመሆኑም የሙስና ምልክቶችን ለይቶ በማወቅ ራሳችንን፣ የሥራ ክፍላችንን ብሎም ተቋማችንን በመጠበቅ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በማድረግ የሙስና መከላከል ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id6593662319
የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ.pdf
744.5 KB
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግሥት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 10/64/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
አማራጭ የሕግ እውቀት
https://linktr.ee/alehig
Alternative legal enlightenment/ALE
Telegram👉 @MikiasMelak
WhatsApp👉 #+251920666595
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

https://t.me/AleHig

alehig.com
ወድቆ ካገኘችው የሞባይል ስልክ ላይ በሞባይል ባንኪንግ 85 ሺህ ብር የሠረቀችው ግለሰብ.......

ወድቆ ካገኘችው የእጅ ስልክ ላይ የሞባይል ባንኪንግ ምሥጢራዊ ቁጥር በመጠቀም ወደ እራሷ አካውንት ብር ያዘዋወረችው ግለሰብ በእሥራት ተቀጥታለች።

በምዕራብ አርሲ ዞን ተከሳሽ ዝናሽ ሃጎስ የተባለችው ግለሰብ ወድቆ ከተገኘ ስልክ ገንዘብ መሥረቋን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ ተናግረዋል።

ግለሰቧ የስልኩን ባለቤት የሞባይል ባንኪንግ የምሥጢር ቁጥር ከፍታ በፍተሻ ማግኘቷ የታወቀ ሲሆን የእጅ ስልካቸው የጠፋባቸው ግለሰብ ...የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጄ ቅርንጫፍ በመሄድ የባንክ አካውንታቸውን ሲያስፈትሹ 85 ሺህ ብር በሞባይል ባንኪንግ እንደተላለፈ አረጋግጠዋል።

ተከሳሿ ገንዘቡን ወደ ራሷ ከወሰደች በኋላ ለሌሎች ሁለት ሰዎች ማስተላለፏም ታውቋል።

በዚህም ገንዘቡ የተላለፈላቸው ሁለት ሰዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር እንዳልዋሉ ተነግሯል።

ተከሳሽ ዝናሽ ሃጎስ የተባለችው ግለሰብ የፈጸመችው ወንጀል ሙሉ በሙሉ በዓቃቤ ሕግ ማሥረጃ በመረጋገጡ ...የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ዝናሽ ሃጎስ በ4 ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር እንድትቀጣ ወስኖባታል።
(ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን)
እንደዚህ አይነት ክስተት ቢያጋጥሞ ምን ያደርጋሉ??
አማራጭ የሕግ እውቀት
https://linktr.ee/alehig
Alternative legal enlightenment/ALE
Telegram👉 @MikiasMelak
WhatsApp👉 #+251920666595
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR.pdf
494.2 KB
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን
ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ DRAFT
መንግሥት ካርድ የተሰኘዉን የሰብአዊ መብት ድርጅትን ጨምሮ ሌላ አንድ ተቋምን ከስራቸዉ አገደ‼️

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰብአዊ መብት ሥራዎች ታዋቂ የሆኑ ድርጅቶችን በደብዳቤ ማሸጉን ዋዜማ አረጋግጣለች። ከታገዱት ድርጅቶች መካከልም “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል” (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ “CARD” እና “ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” (AHRE) ይገኙበታል። 

ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል።  

ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ ከባድ የህግ ጥሰት መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል” የሚል ነው። ዋዜማ የደረሳት መረጃ የታገዱት ድርጅቶች ቁጥር ከሁለት እንደሚበልጥ ቢጠቁምም፣ ለጊዜው ማረጋገጥ አልቻልንም። 

ይህ እርምጃ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በሚሠሩ ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። የእግድ እርምጃው በድርጅቶቹ መሪዎች አካባቢ የተጠበቀ እንዳልነበር ለመረዳት ችለናል።

የሲቪል ማህበረስበ ድርጅቶች ባለስልጣን መያዶችን የማገድ ስልጣን ቢኖረውም “የአሁኑ እርምጃ በሕጉ የተዘረዘረውን ቅደም ተከተልና ቅድመ ሁኔታ የሚጥስ ነው” ብለዋል ሌላ የሕግ ባለሞያ። ድርጅቶቹ እግዱን በሕግ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል። ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ የዋዜማ ምንጮች እገዳው የተላለፈበት ሂደት ለእርሱም ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
ከሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ | A Timely Statement Issued by Lawyers for Human Rights
#Ethiopia #LHR # Statement

ድርጅታችን "የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች" በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ዓ.ም. መሠረት በምዝገባ ቁጥር 4113 መስከረም 09 2012 ዓ.ም. ዳግም ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ሀገር በቀል ሲቪል ማህበር ሲሆን:
ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ በሀገራችን የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ዓላማው አድርጎ በርካታ ሥራዎችን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከፌደራልና ክልል አስፈጻሚ አካላት እና ከሌሎች ሲቪል ማህበራት ጋር በመተባበር ሲያከናውን ቆይቷል።

ሆኖም ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ሕዳር 12/2017 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ድርጅቱ “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መስራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዳ ተግባራት ላይ በመሰማራቱ..." በሚል ከማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ የታገደ መሆኑን ገልጾልናል።

ባለሥልጣኑ ማህበራችን ተሰማራበት በማለት በደብዳቤው ላይ የጠቀሰው አባባል ማህበራችንን የማይገልጽ እና የማይመለከት መሆኑን በአፅንኦት እየገለፅን የተጣለብን ዕግድ እንዲነሳ ለማድረግና ወደ መደበኛ ሥራችን ለመመለስ ሕጋዊ ሂደቶችን የምንከተል መሆኑን እናሳውቃለን።

Our organization, Lawyers for Human Rights, is a civil society entity duly re-registered under Proclamation No. 1113/2011 on September 20, 2019. Since its inception, we have maintained our independence and political neutrality, actively collaborating with the Ethiopian Human Rights Commission, federal and regional government bodies, and other civil society organizations to promote human rights in our country.

However, on November 21, 2024, the FDRE Authority for Civil Society Organizations issued a letter stating that our organization had been suspended from all activities for allegedly 'acting without political neutrality and beyond its purpose and engaging in actions harmful to the country’s interests and public welfare.’

We wish to clarify that the claims outlined in the letter do not accurately reflect our organization's activities. We are committed to following the legal process to challenge the suspension and resume our normal operations.

https://drive.google.com/file/d/1n28sWS4Lig2efcsXW7s6pH5k8Zn-NKYe/view?usp=sharing
ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተገልጋዮች ጥራቱን የጠበቀ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ (Online) Registration) ከሕግ ቢሮ የጽሑፍ አገልግሎት ያገኛሉ።
በየትኛውም ቦታና ስዓት ሁነው ሰነዶች ማረጋገጫ(ውልና ማስረጃ) የሚሄዱበት ጉዳይ ሲኖራችሁ ለተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት እና ማሟላት ስላለባቸው ሰነዶች ነፃ የሕግ ምክር እና የሕግ ድጋፍ እንሰጣለን።
👉 #ውክልና_ለመስጠት
👉 #ብድር_ውል ለመፈፀም
👉 #የሺያጭ ውል
👉 #ቃለ_ጉባዔ ለማጽደቅ
👉 #ሼር መግዛት /መሸጥ........ወ.ዘ.ተ
ሌሎችንም አገልግሎት በአካል መገኘት ሳይጠበቅብዎት በአሉበት ቦታ ሁነው በተመጣጣኝ ክፍያ በሕግ ባለሙያ ተፅፎ በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ ወይም በኢሜል ከሕግ ቢሮ ይላክላችኋል።
ከእናንተ የሚጠበቀው ፕሪንት አድርጎ ወደ አቅራቢያ ሰነዶች ማረጋገጫ በመሄድ ምንም ጊዜ ሳያባክኑ አገልግሎት ማግኘት ብቻ።
ይደውሉ:- 👉 0920666595
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልገሎት
Alternative legal enlightenment and Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

https://t.me/AleHig

alehig.com