African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.48K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ 3 ሚሊዬን ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሆስፒታሉ ከ3 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡ሆስፒታሉ በትግራይ ወራሪ ኃይል ዘረፋና ውድመት ደርሶበት ስለነበር የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ የሆስፒታሉን የግብአት ጉድለት የሚያጠና ቡድን በመላክ ባጠናው ጥናት መሰረት እጅግ አስፈላጊ ግብአቶችን ለግሷል ብለዋል፡፡ የእንግዳ ማረፊያ ወንበር ፣ የባለሙያዎች ወንበር ፣ ጠረንፔዛዎች ፣ አልጋዎች ፣ ፍራሾች ፣ ኮምፒውተር ፣ እስካነር ፣ ፋክስ ወ.ዘ.ተ እቃዎችን ድጋፍ መደረጋቸውን ስራ አስኪያጅ አብራርተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ /ዶ/ር/ የህውሀት አሸባሪው ቡድን ባደረሰው ጉዳት እጅግ ማዘናቸውንና ሆስፒታሉ የገጠመውን ችግር በመጋራት የአካዳሚው ማኔጅመት ኮሚቴ ሆስፒታሉን ለመደገፍ በመወሰኑ የመጀመሪያ ዙር ድጋፉን እና መልዕክት ልከዋል፡፡ ከቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ አካዳሚው ከሆስፒታሉ ጎን በመቆም በቀጣይ የአቅም ግንባታ እና ሙያዊ እገዛ እንደሚደረግ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር ሆስፒታሉ የአፋር ክልል ፣ ሰሜን ሸዋ ፣ ኦረሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉና አርጎባን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን በሪፈራል ሆስፒታልነት እያገለገለ በመሆኑ ፍሰቱ በርካታ ነው ብለዋል፡፡
ሆስፒታሉ በወራሪ ቡድኑ በደረሰበት ጉዳት የግብአት እጥረቱ እንዲቀርፍ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተከበረው የረመዳን ፆም ወቅት የከፍተኛ አመራር ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሙስሊም ሰልጣኞች በአካዳሚው የረመዳን ፆም ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚና መላው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋናና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡
በአመራር ብቃት ማዕቀፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዎርክሾፕ ተካሄደ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በቀጣይ ለሚሰጣቸው የአመራር ማብቃት ስራዎች ግብዓት ከሚሆኑ ስራዎች መካከል አንዱ በሆነው የአመራር ብቃት ማዕቀፍ ላይ ከአካዳሚው፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የተወጣጡ ምሁራን በተሳተፉበት በስካይ ላይት ሆቴል ነው ዎርክ ሾፑ የተካሄደው፡፡
በዎርክሾፑ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ አካዳሚው የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን በማከናወን አሁን ያለበት ደረጃ ላይ መድረሱን በማስታወስ አካዳሚው በቀጣይ ለሚሰጣቸው የአመራር ማብቃት ስራዎች የሚካሄደው ዎርክሾፕ ግብዓት የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአመራር ብቃት ማዕቀፍ በዶ/ር እሸቴ አበበ፣ የአመራር ብቃት ማዕቀፍ ካርኩሌም ዲዛይን በዶ/ር አሰፋ በየነ እንዲሁም የአመራር ብቃት ማዕቀፍ ጋይድላይን በዶ/ር ሞገስ ሎጋው ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡ ጽሁፎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመጨረሻም የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ በውይይት የተነሱት ሃሳቦች ጥሩ ግብዓቶች መሆናቸውን በማንሳት በቀጣይ ሰነዱ ዳብሮ ተግባራዊ እንዲሆን የዎርክሾፑ ተሳታፊዎች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስጋና ስጦታ ተበርክቶለታል፡፡👏🙏🤝
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓Dr. Wondeye Legese completed his doctoral studies at University of International Business and Economics, Beijing, China, with great achievements in the field of International Relations. His dissertation is titled On Factors Affecting Framing of National Interest. Congratulations!!!! 🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
ዜና ሹመት
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ በስልጠና ስራ ለጸጥታ ዘርፉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የማረሚያ ፖሊስ በጋራ በመሆን የተቋማቱ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር እንዲሆኑ ተሹመዋል፡፡
ሹመቱን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሲሆኑ ሁለቱን ተቋማት ወክለው ባደረጉት ንግግር ዶ/ር ምህረት ደበበ የፀጥታ ዘርፉ በህግ ማስከበር ወቅት ለሚኖረው ሚና የሚረዳ ስልጠና በመስጠታቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሹመቱ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ማልታ ሀገር ከሚገኝ ሜዲትራኔያን አካዳሚ ኦፍ ዲፐሎማቲክ ስተዲስ (The Mediterranean Academy of Diplomatic Studies at the University of Malta) ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የጋራ ስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ተቋማት በትብብር እንዲሰሩ የሚያስችል ሲሆን በተለይም በጥናትና ምርምር ተግባራት፤ በስልጠና ፕሮግራሞች፤ በጥናት ሰነዶች ልውውጥ እና በባለሙያዎች ስልጠና ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
በጋራ መግባቢያ ስምምነቱ ላይ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ (ዶ/ር) እና የማልታ ዩኒቨርስቲ ዲፕሎማቲክ አካዳሚ ዳይሬክተር prof. Stefen Calleya ተፈራርመው የስምምነት መርሀ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
አካዳሚው በአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት፤ በአረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ ተግባራትን አጠንክሮ መቀጠሉ ተገለፀ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጨምሮ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት በሻሸመኔ ከተማ 35 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት መርሃ ግብር አስጀምረዋል፡፡
ከተቋማቱ የተወጣጡ አመራሮችና ሰራተኞች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ በመሆን በምዕራብ አርሲ ዞን ሲራሮ ወረዳ በአረንጓደ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
በዞኑ ሁለት ወረዳዎች 11ሺህ ለሚሆኑ ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ተማሪዎች የ7 ሚሊዮን ብር የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍም ተደርጓል፡፡