African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.48K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
አካዳሚው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወነ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሱሉልታ ኢፋ ቦሩ ለገ ደቦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጊቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውኗል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ተቋሙ አገራዊ አጀንዳዎችን ለመፈፀም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አስታውሰው በት/ቤት ውስጥ ችግኝ መተከሉ የነገ ሃገር ተረካቢዎችን ተስፋ እንደሚያለመልም ገልፀዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አቡ ብርኪ በበኩላቸው አካዳሚው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የሚሰራቸውን ስራዎች አድንቀው የችግኝ ተከላው መርሃ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ፋይዳ አብራርተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና የትምህርት ቤቱ ሃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡
አካዳሚው የምስጋና መርሃ ግብር አከናወነ
በሃገር አቀፍ ደረጃ የተላለፈውን የምስጋና መርሃ ግብር ጥሪን ተከትሎ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች የምስጋና መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡
በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ (ዶ/ር) ማመስገን ለሚደረግልንና ለተደረገልን የምንሰጠው ምላሽ መሆኑን በማንሳት በእኛ ጉብዝና ብቻ ሳይሆን በፈጣሪ ድጋፍ ጭምር ለዚህ ደርሰናል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ከጨለማ ይልቅ ብርሃንን መምረጥ መልካም ጎኑ የሚጎላ በመሆኑ ሃገራችንና ህዝባችንን የጠበቀ ፈጣሪን በማመስገን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
የአካዳሚው ፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ህይወት አለማየሁ በበኩላቸው መመሰጋገን እንደ ባህል መወሰድ አለበት ለሃገር የለፉ፣ የደከሙና ውጤታማ የሆኑ አመራሮችን ማመስገን ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
የግል ዝና እና ሃብታቸውን ትተው ሃገር በማገልገል ላይ ያሉ አመራሮችን ማመስገን ለላቀ ውጤት ስለሚያበቃ ባህሉ ሊጎለብት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ሰራተኞች ለበላይ ኃላፊዎቻቸው እንዲሁም ኃላፊዎች ለሰራተኞች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ሃገራችንን በመወከል ከፍተኛ ድል ያስመሰገቡ አትሌቶቻችንንም የማመስገን ስነስርዓትም ተካሂዷል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት (ECSOC) በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ አካዳሚው እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጀምሮ ያከናወናቸውን ተግባራትና የጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም ሲጨርስ ሊሰሩ ስለታሰቡ ስራዎች ያብራሩ ሲሆን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመስራት በዘርፉ ያለውን የአመራር የክህሎትና የዕውቀት ክፍተት በመሙላት ብቁ አመራር ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አካዳሚው የድርሻውን ለመወጣት እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተወጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በበኩላቸው አካዳሚው እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን በማድነቅ ተቋሙ የሰነቀው ራዕይ ከሃገራችን አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ትልቅ ተቋም መሆኑን የሚያመላክት በመሆኑ በቀጣይ ከአካዳሚው ጋር በመስራት የዘርፉን አመራር አቅም ማብቃት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡
አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በወርክሾፕና በስልጠና ግንኙነቱን ወደ ላቀ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማሳደግ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት በስሩ 3700 የሚሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይገኛሉ፡፡
የደቡብ ሱዳን የደህንነትና የሲቪል ሹማምንት ከፍተኛ ልዑክ ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጉት እንዳለው ገለፀ
የደቡብ ሱዳን የደህንነትና የሲቪል ልዑክ አባላት እና የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የደቡብ ሱዳን ልዑክ አባላት የአካዳሚውን መሰረተ ልማት ከጎበኙ በኃላ እንደተናገሩት ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
የአካዳሚው የስራ አመራር ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሠ (ዶ/ር) የልዑካን ቡድኑ አባላት ወደ አካዳሚው በመምጣታቸው ደስተኛ እንደሆኑና ተቋሙ አፍሪካዊ ተልዕኮን ያነገበ በመሆኑ ከአፍሪካ አገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ በኢትዮጵያዊና በአፍሪካዊ መስተንግዶ የሚቀበሏቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው አካዳሚው እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን በማድነቅ በቀጣይ በተለይም በስልጠና ስራዎች አብሮ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጉት እንዳላቸውና በቅርቡ የቴክኒክ ልዑክ በመላክ በቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገቡ ስራዎች ዝርዝር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡