African Leadership Excellence Academy
2.15K subscribers
2.38K photos
90 videos
6 files
107 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
💥የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ስለ ተቋም ግንባታ የአመራር ልማት ስልጠና ሲሰጡ ካነሷቸው ሀሳቦች ውስጥ የተወሰዱ፡-

👉የሀገራት የስልጣኔ መነሻ እና መድረሻ የተቋም ግንባታ ነው።

👉ጠንካራ እና ተሻጋሪ ተቋማትን የገነቡ ሀገራት ስልጣኔያቸውን አስጠብቀው ዘልቀዋል።

👉ተቋማት የስልጣኔ የማዕዘን ድንጋይ ናቸው። ይህ አዕማድ በአግባቡ ከተቀመጠ ትናንትን ይዘክራል፤ ዛሬን ይሰራል፤ ነገን ይተልማል።

👉የአንድ ሀገር የዕድገትት እና የብልጽግና መለኪያ ኒኩለር የማመንጨት እና የማስወንጨፍ፤ በማዕድን ሀብት መበልጸግ እና በነብስ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ መሆን አይደለም።

👉ተቋም ግንባታ እንደ ድልድይ ግንባታ ነው። ሲገነባ ጥንቃቄን ይፈልጋል። በደንብ ታስቦበትና በዕቅድ የሚገነባ ድልድይ በአገልግሎትም ይሁን በዕድሜ ለረጅም አመታት እንደሚቆየው ሁሉ ተቋምም እንዲሁ ነው።

👉ስኬታማ የሚሆኑ የተቋም መሪዎች ተቋማቸውን በህግ መሰረት የሚመሩ ናቸው። አንድ መሪ ተቋም ለመገንባት ዘመዱን፤ ሀይማኖቱን፤ ጾታውን፤ ዘሩን፤ ቀለሙን፤ እና ብሔሩን መርሳት ብቻ ሳይሆን መካድ አለበት። እነዚህን ነገሮች በጉያው የያዘ መሪ ተቋም መገንባት አይችልም።

👉ተቋማት የሚገነቡ መሪዎችን ከድንጋይ ጠራቢ ጋር ይመሳሰላሉ። ሁለቱም ገደብ አልባ ስልት እና ትዕግስት (strategic patience) ያስፈልጋቸዋል። ድንጋይ የሚጠርብ ጠራቢ በትዕግስት ድንጋዩን እንደሚጠርበው ሁሉ መሪም ተቋም ለመገንባት ሰፊ ትዕግስት ያስፈልገዋል።
👉መሪዎች ተቋም ግንባታ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ቀላል ግምት የሚሰጠው ባለመሆኑ ሲያበረታቱም ሆነ የሚመሯቸውን ለስራ ሲያነሳሱ የሚጠቀሟቸውን ቃላት እና ድርጊት በማስተዋል ማድረግ ይገባቸዋል።

👉ተቋም እና ስልጣኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ተቋማት የስልጣኔ ዘብ ናቸው። ስልጣኔን ያስቀጥላሉ። ተቋም ስትገነቡ ስልጣኔን እያዋቀራችሁ ነው። የተቋም ግንባታ ከአንድ ሰው እድሜ በላይ ነው። ተቋም የሚገነባ ሰው የብሔረ መንግስቱ አናጺ መሆኑን መርሳት የለበትም። “
“ ከአባቶቻችን በክብር የተቀበልናትን ሀገር ለወራሪ ሀይል አሳልፈን አንሰጥም ያሉ የኢትዮጵያ ልጆች፤ በሕብረት፤ በአንድነት እና በተባበረ ክንድ ወራሪውን ሃይል መክተዋል። “ አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

አዲስ አበባ- የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)፡- ትውልዱ የዓድዋን ድል በዓል ሲያከብር የተጀመረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ ለማስቀጠል ቃል በመግባት መሆን እንዳለበት ተገለጸ

ኢትዮጵያውያን ዓለምን ያስደነቀ ጀብድ ፈጽመው፤ ሀገራቸውን እና ታሪካቸውን ጠብቀው አቆይተው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳሻገሩ ሁሉ አሁን ያለው ትውልድም የተጀመረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ ለማስቀጠል ቃል በመግባት ድሉን ማክበርና መዘከር እንደሚገባው የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናግረዋል።

"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል’’ በሚል መሪ ሀሳብ 129ኛዉን የዓድዋ የድል በዓል ስናከብር የቀደሙ አባቶቻችንን ታሪክና ገድል ከመዘከር ባሻገር የሀገረ መንግስት ስራን የሚያጠናክሩ እና በዘላቂነት የሚያስቀጥሉ ተግባራትን በመከወን ሊሆን እንደሚገባ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ፤ የዚህን ትውልድ የቤት ስራ የሚሆነው ለሁላችንም የምትሆን ሀገር መገንባት ላይ መረባረብ ነው ብለዋል።

ሁሉም ትውልድ የየራሱ የቤት ስራ አለው ያሉት አቶ ዛዲግ፤ የዚህ ትውልድ አመራር ዋና ተግባር የሚሆነው የአሸናፊነት ሚናን ከቀደሙ አባቶቹ በመውረስና ተፈጥሮአዊና ሰብአዊ ሀብቶችን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለመቀየር በልዩ ትኩረት በመስራትና ድህነትን በመርታት የበለጸገች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የራሱን አሻራ ማኖር እንደሆነም ተናግረዋል።
አሰባሳቢ እና ገዥ ትርክቶች ለጋራ ጥቅምና ዓላማ በሕብረት የሚያቆሙ የሀገረ መንግሰት መገንቢያ መሳሪያዎች በመሆናቸው፤ ከሚከፋፍሉ እና ከሚነጣጥሉ ትርክቶች በመራቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በጊዜ የለንም መንፈስ በመስራት፤ የተጀመረውን የሀገረ መንግስት ግንባታ ማስቀጠልና ማጽናት እንዳለበትም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ችግር ምንድን ነበር?

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ስለ ሀገረ መንግስት ግንባታ የአመራር ልማት ስልጠና ሲሰጡ ካነሷቸው ሀሳቦች ውስጥ የተወሰዱ፡-

👉አፍርሶ መስራት፡- የተጀመረውን ከማስቀጠል ይልቅ አፍርሶ ከዜሮ መጀመር። ማፍረስ ካለብንም ለማፍረስ ብቻ ሳይሆን ከፈረሰው የተሻለ ለመገንባት መሆን አለበት።

👉የጀመሩትን አለመጨረስ፡- የጀመርነውን መጨረስ በአትሌቲክስ ብቻ የተሰጠን እስኪመስል ድረስ ጀምረን መጨረስ የተሳነን ሆነናል። ኢትዮጵያ የጀመረችውን መቋጨት እንድትችል ተቋማት ላይ መስራት ይገባል።

👉ተሻጋሪ ህልም አለመኖር፡- የምንኖረውም ሆነ የምናልመው ዛሬን ብቻ ነው። ዛሬ የምንተክለው ዛፍ ለእኛ ሳይሆን ለነገ ትውልድ ጥላ ይሆናል ብሎ አለማሰብ።

👉ከቀደመው ትውልድ አለመማር፡- የሚጻፉ መጽሀፍት እና ገድላት የቀደመውን ትውልድ የሚከሱና የሚወቅሱ እንጂ ትውልድን ለማስተማር የሚጻፉ አይደሉም።

👉የባህል ለውጥ አለመኖር፡- የሚጠቅመውንና የማይጠቅመውን ባህል አጃምሎ ከዘመን ዘመን መሻገር፤ ማራገፍ የሚገባንን ሳናራግፍ ለማደግ መጣር።
🌟 Unlocking Potential: The Power of a Leadership Academy for Senior Leaders🌟

At AFLEX, senior leaders are the backbone of any organization's success.

Our Leadership Academy is designed to elevate their skills, foster innovation, and drive impactful change.

By focusing on capacity building, we empower senior leaders to:

💡 Develop strategic thinking and vision

🤝 Enhance collaboration and influence

🚀 Navigate challenges with confidence

Invest in your leadership today because great leaders create great organizations! 🙌

Join AFLEX in shaping the future of leadership. Together, let’s build stronger, more resilient teams.

#LeadershipAcademy #SeniorLeaders #CapacityBuilding #AFLEX #Empowerment #LeadershipDevelopment
In Ethiopia, leadership has always been deeply tied to community.

The "Shimagile" system, for example, is a traditional form of governance where elders and community leaders solve conflicts and make decisions collectively, not through hierarchy but through dialogue and consensus.

🤝 it’s a reminder that leadership isn’t about one voice: it’s about creating harmony among many. 🌍

#AFLEX #EthiopianTraditions #CollectiveLeadership #CommunityEngagement
አፍሌክስ ትክክለኛ የአመራር ልማት ማዕከል ነው ስንልዎ በምክንያት ነው። የአመራር አቅምዎን የሚያሳድጉ፤ ክህሎትዎን የሚያበለጽጉ፤ የስልጠና ቪዲዮዎችን ወደ እናንተ ማድረሳችንን ቀጥለናል።
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለከፍተኛ አመራሮች በተቋም ግንባታ፤ በሀገረ-መንግስት ግንባታ እና በውጤታማ አመራር ዙሪያ የሰጧቸውን ሁለት የስልጠና ቪዲዮዎች ልናጋራችሁ የአንድ ሰዓት ዕድሜ ቀርቶናል።
የመጀመሪያው ቪዲዮ 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ የሚፈጅ ሲሆን ሁለተኛው ቪዲዮ ደግሞ 3 ሰዓት 20 ደቂቃ ነው። በቪዲዮዎቹ የአካዳሚያችን ፕሬዚደንት አስገራሚ ዕይታዎችን ከበቂ ማብራሪያ እና ማስረጃዎች ጋር ያገኛሉ። ይምጡ ከሰፊው የአመራር ልማት ማዕድ ይካፈሉ።
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ማንነት እና የአመራር ውጤታማነት ጥበብ !! በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የሰጡትን የአመራር ልማት ስልጠና ሙሉ ቪዲኦ በአካዳሚው ዩቱዩብ ቻናል ላይ ያገኙታል። ማስፈንጠሪያውን በመጫን እንዲመለከቱ ጋብዘናል፡- https://www.youtube.com/watch?v=X7HtiC4MDHE
#ክፍል_2 አፍሌክስ ትክክለኛ የአመራር ልማት ማዕከል ነው ስንልዎ በምክንያት ነው። የአመራር አቅምዎን የሚያሳድጉ፤ ክህሎትዎን የሚያበለጽጉ፤ የስልጠና ቪዲዮዎችን ወደ እናንተ ማድረሳችንን ቀጥለናል።

የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለከፍተኛ አመራሮች በተቋም ግንባታ፤ በሀገረ-መንግስት ግንባታ እና በውጤታማ አመራር ዙሪያ የተቋማት ግንባታ እና የሀገራት ዕጣ-ፈንታ በሚል ርዕስ የሰጡትን የስልጠና ቪዲዮ በአንድ ሰአት ውስጥ እናጋራችሁለን።

ሁለተኛው ቪዲዮ 3 ሰዓት 20 ደቂቃ ነው። በቪዲዮው የአካዳሚያችን ፕሬዚደንት አስገራሚ ዕይታዎችን ከበቂ ማብራሪያ እና ማስረጃዎች ጋር ያገኛሉ። ባሉበት ሆነው ከሰፊው የአመራር ልማት ማዕድ ይካፈሉ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እናመሰግናለን!!

በ12 ሰዓት ውስጥ 1መቶ ሺህ ዕይታ!!

ስላተጋችሁን እናመሰግናለን!!

የአካዳሚያችን የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮች የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ማንነት እና የአመራር ውጤታማነት ጥበብ !! በሚል ርዕስ የሰጡት ስልጠና በ12 ሰዓት ውስጥ 1መቶ ሺህ ዕይታ አግኝቷል!!

ተልዕኮአችንን እንድንወጣ የተጣለብን አደራ አድርገን እንወስደዋለን።

አፍሌክስን መርጣችሁ የአመራር ልማት ስራችንን ለምትደግፉ ሁሉ እናመሰግናለን!!

ስናመሰግናችሁ ትናንትን ብቻ ሳይሆን ዛሬንም፤ በዛሬ ሳትወሰኑ ነገንም ከእኛ ጋር እንደምትሆኑ ስላመንን ነው!!
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የተቋማት ግንባታ እና የሀገራት ዕጣ-ፈንታ!! በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የሰጡትን የአመራር ልማት ስልጠና ሙሉ ቪዲዮ በአካዳሚው ዩቱዩብ ቻናል ላይ ያገኙታል። ማስፈንጠሪያውን በመጫን እንዲመለከቱ ጋብዘናል፡-
https://www.youtube.com/watch?v=NHrRmhcKc6A&t=1s
ተቋማት የስልጣኔ ምሰሶዎች ናቸው! እንዴት
👉የሃገራት ታላቅነት የሚለካው በተቋማቶቻቸው ጥንካሬ ነው። ጠንካራ ተቋማት የዴሞክራሲ፣ የፍትህ እና የብልጽግና መሰረቶች ናቸውና!
👉ተቋም ለመገንባት ስትራቴጂያዊ ትዕግስት ይጠይቃል!
👉ተቋምን መገንባት ድልድይ እንደመገንባት ነው! ተቋም መሰረቱ እንዳማረ ዘመናትን ተሻግሮ እንዲያገለግል ከተፈለገ፣ በደንብ ማሰብ፣ ትክክለኛውን ባለሙያ ማሳተፍ እና በቂ ሃብት መመደብ ያስፈልጋል!
የተቋማት ግንባታ፣ የሃገረ መንግስት ግንባታ እና የብሄረ መንግስት ግንባታ ምንድናቸው
👉የብሄረ መንግስት ግንባታ ማለት የሚለያዩበትም የሚጋሩትም ማንነት ካላቸው ማህበረሰቦች የጋራ ህብረተሰብ መገንባት ነው።
👉የሃገረ መንግስት ግንባታ ማለት ስርዐት ማስፈን እና አገልግሎት አሰጣጥን መዘርጋት ነው።
👉እድገትን ለማስቀጠል አስተዳደርን ለማጽናት የሚሆን አሰራር ስናበጅ የተቋም ግንባታ ይባላል።
የተቋማት ግንባታ ስትራቴጂያዊ አንድምታው ምንድነው
የተቋማት ግንባታ ምን ምን አላማና ግቦች አሉት
የተቋማት ግንባታ ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ ነው! ታድያ ለምን አንገነባም ምንድነው ችግሩ
የተቋም ግንባታ ምን አይነት ሂደቶች አሉት
1️⃣ሁኔታዎችን እንገመግማለን፣ እቅድ እናወጣለን
2️⃣ለእቅዱ ማስፈጸሚያ መንገድ እንነድፋለን፣ ወደትግበራ እንገባለን
3️⃣ክፍተቶችን እያየን፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንሰራለን
4️⃣ለስራ ሂደቱ የክትትል እና የድጋፍ ስርዐት እናበጃለን
5️⃣የተቋም ግንባታውን ዘላቂ የሚያደርጉ እርምጃዎችን እንወስዳለን
የተቋማት የውድቀት መንስኤ ምንድነው
ውድቀቱ ምን ያስከትላል
የዴንማርኩ መንገድ ምን ያስተምረናል በኢትዮጵያ ለተቋም፣ ለሃገረ መንግስት እና ለብሄረ መንግስት ግንባታ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮች ምንድናቸው
አሁንስ ይህ ትውልድ ይህን ዘመን እንዴት ይጠቀምበት
አቶ ዛዲግ አብርሃ ለከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ሀሳቦች ያብራራሉ። ተገቢውንም መልስ ከበቂ ማብራሪያ ጋር ያቀርባሉ፡- የአካዳሚውን የዩቱዩብ ቻናል ላይ ሙሉውን ያገኙታል። ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ https://www.youtube.com/watch?v=NHrRmhcKc6A&t=1s
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ሱሉልታ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ. ም (አፍሌክስ) የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከ90 በላይ ለሚሆኑ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ለ 3 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ማሰልጠኛ አዳራሽ እየሰጠ ይገኛል።

መርሀ ግብሩ ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን፤ግንኙነት በማስፋት እንዲሁም የተጀመሩ የቢዝነስ ዩኒቶች(በመንገድ በሎጂስቲክስ፤በማማከር፤ በዲዛይንና ቁጥጥር) ስራዎች የአመራር ሚናን ለማጎልበት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች የአመራር እና የውሳኔ አሰጣጥ ፣ ስልታዊ እይታ ፣ ፋይናንሻል እና ተግባራዊ ችሎታቸውን የሚያጠናክሩበት እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ለመጨመር የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል።

በአፍሌክስ የጠቅላላ አመራር ልማት ፕሮግራም ተ/መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት እሸቴ አበበ ዶ/ር/ የአካዳሚውን የሪፎርም፣የማስፋትና የትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎉 MASSIVE THANK YOU! 🎉

We are absolutely thrilled to share that our latest video post reached 400,000 views in just TWO DAYS! 🚀

This milestone is a testament to the incredible support, engagement, and passion of our amazing community.
To every single person who watched, liked, shared, and commented—THANK YOU! 🙌

Your enthusiasm fuels our mission to inspire and connect leaders worldwide. Special shoutout to our dedicated team and partners who make impactful content possible.

This is just the beginning! 🌍 Stay tuned for more stories, collaborations, and initiatives that bridge borders and empower leaders. Together, we’re creating waves of positive change.

#Gratitude #LeadershipJourney #GlobalCommunity #AFLEXImpact #ThankYou
“ ይህ ትውልድ የቀደመው ትውልድ ያመለጠውን ዕድልና ጀምሮ ያለመጨረስ ታሪክ ዘግቶ፤ በመስፈንጠር ታሪክ ለመስራት መንገድ ጀምሯል። ታሪክ የመስራት መንገዱ በኮሙኒኬሽን ሀይልና ጥበብ ሊመራ ይገባል።"

አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት

ሱሉልታ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ. ም (አፍሌክስ)፡- ይህ ትውልድ እድለኛ ነው። ያለፈው ትውልድ ጀምሮ ያልጨረሰውን በተሻለ ጉልበትና ህብረት ለመስራት እድል በሩን እያናኳኳችለት ነው። የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ ጊዜውን ተጠቅሞ ከሰራ ትውልድን የሚሻገር ጸጋን ያወርሳል። በመሆኑም ሁለት ዕጣ ፈንታዎች በእጁ ይገኛሉ። አንደኛው የቀደመው ትውልድ ያመለጠውን ዕድል እና ጀምሮ ያለመጨረስ የታሪክ ምዕራፍ ዘግቶ፤ ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መሸጋገር አሊያም ከቀደመው በባሰ መልኩ ወደ አረንቋ መውረድ።

አቶ ዛዲግ የትውልዱን ምርጫ ሲጠቅሱ “የዚህ ትውልድ ምርጫ የቀደመው ትውልድ ያመለጠውን ዕድል እና ጀምሮ ያለመጨረስ የታሪክ ምዕራፍ እየዘጋ አዲስ የታሪክ አሻራ ለማኖር እየታተረ ያለ ትውልድ ነው " ይላሉ። ያለፈውን ዘግቶ አዲስ ለመጀመር የሚደረገው ጉዞ በተሟላ የኮሙኒኬሽን ሀይልና ጥበብ መመራት አለበት ሲሉም አጽንኦት ይሰጣሉ ፕሬዚደንቱ።

አቶ ዛዲግ ለከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልተና ላይ በአግባቡ የተመራ ኮሙኒኬሽን ሀገርን ለመገንባት እና የትውልድን የታሪክ ቅብብል ለማስቀጠል የሚኖረውን ሚና ከታሪካችን አውድ እና ማህደር እየመዘዙ፤ ከአለም አቀፍ እውነታዎችና ሳይንሳዊ መንገዶች ጋር እያዋሃዱ አቅርበዋል።
ኮሙኒኬሽንን በመጠቀም መሪዎች የሀገራትን እድገት ማፋጠን እንደሚችሉና የሚጠቀሟቸው ስልቶችና ቃላቶች የማሻገር ሀይላቸው ከፍተኛ እንደሆነ የአለም አቀፍ መሪዎችን ተሞክሮ በማካፈል ያብራሩት አቶ ዛዲግ፤ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተጠቀሙት ቃል የአሜሪካውያንን ቀልብ በመያዝ ለውጤት እንዳበቃቸው አስታውሰው፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጀመሪያ ቀን የፓርላማ ንግግራቸው የተጠቀሙት ቃል ‘ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ’ ምን ያህል የህዝብ ድጋፍ እንዳስገኘ እና ለውጡን ለማቀጣጠል ጥቅም ላይ እንደዋለ ተናግረዋል።

በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መልዕክቶች ተደራሹን ማእከል እንዲያደርጉ በጥንቃቄ መዘጋጀት አለባቸው የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ጥልቅ ብዝሀነት ባለባቸው ሀገራት የሚያሰባስቡ ሀገራዊ መልዕክቶችን መቅረጽ እንደሚገባ ጠቁመው፤ አንድነትን የሚያመጡ፤ መተማመንን የሚፈጥሩ፤ መተባበርን የሚያሳድጉ እና መከባበርን የሚያስተምሩ መልዕክቶችን ግልጽና ሳቢ በሆነ መንገድ በማዘጋጀት፤ በመጠቀም አካታች ይዘት ያለው ውጤታማ ኮሚኒኬሽን እንዲኖር መስራት እንደሚገባ በስልጠናው ላይ አንስተዋል።