“ ሁላችንም የውሳኔያችን ውጤቶች ነን፤ የሰው ልጅ የሚመስለው ውሳኔውን ነው፤ ማንነታችንን የሚዋቀረው በምንወስነው ውሳኔ ነው። " አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት
ሱሉልታ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ. ም (አፍሌክስ)፡- የሰው ልጅ ማንን ይመስላል ቢባል ውሳኔውን ነው ይላሉ አቶ ዛዲግ አብርሃ፤ ለከፍተኛ አመራሮች በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ስልጠና ሲሰጡ ከተናገሩት የተወሰደ ሀሳብ ነው። የሰው ልጅ የውሳኔው ውጤት በመሆኑ በህይወት ጉዞው ውስጥ የሚወስነው ውሳኔ ማንነቱን ከማዋቀር ባሻገር ልዩ ዕድልን ይፈጥርለታል፤ የተፈጠረለት ዕድል በተራው የህይወት መስመርን ውሰጥ ይከተውና ሀዲዱ ላይ ያሳፍረዋል፤ ሲሉም ያክላሉ ፕሬዚደንቱ።
ውሳኔ በባህርይው ግንኙነትን ይፈጥራል፤ ያሳድጋል፤ ያለመልማል፤ ያፈርሳልም። በመሆኑም ውሳኔያችን ዕጣ ፈንታችንን የመወሰን ዕድሉ እንዲሰፋ ያደርጋል፤ እነዚህ መነሻዎች የሰው ልጅ የውሳኔው ውጤት እንዲሆን ያስገድዱታል ብለዋል አቶ ዛዲግ በስልጠናው ላይ።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም ውሳኔ የተግባር ስረ-መሰረት ነው ይሉናል አመክንዮአቸውን በማስከተል። ከምንም ተግባር በፊት ውሳኔ ይቀድማል። በዓለማችን ካለ ውሳኔ የተፈጸመ ድርጊት አይገኝም የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ የሰው ልጆች በየዕለቱ ከ35,000-70,000 የሚደርሱ ውሳኔዎችን እንደሚወስኑ መረጃ ጠቅሰው ያብራራሉ።

ስለ ውሳኔ አሰጣጥ ሰፋ ያለ ስልጠና የሰጡት አቶ ዛዲግ፤ መወሰን ሲገባን ባለመወሰናችን የደረሰብንን ኪሳራ ከመወሰን ጥቅም ጋር መሳ ለመሳ አድርገውም አቅርበዋል። እንደ ምሳሌም ጥቂት ማሳያዎችን ያቀረቡት አቶ ዛዲግ በኮቪድ 19 ወቅት መንግስታት ማድረግ መወሰን የሚገባቸውን ውሳኔ ባለመወሰናቸው 6.9 ሚሊየን ሰዎች ሞተዋል።
የመሪዎች ውሳኔ በተገቢው ቦታ ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ መሆን አለበት የሚባለውም በምክንያት እንደሆነ ፕሬዚደንቱ ያስቀምጣሉ። በተሳሳተ ውሳኔ አሜሪካ በኢራቅ ጦርነት 2.4 ትሪሊየን ዶላር አጥታለች። ይህ የደካማ ውሳኔ ማሳያ ነው። ሌማን ብራዘርስ የተባለው ባንክ በተሳሳተ የብድር ውሳኔው 10 ትሪሊየን ዶላር ከስሯል። 8 ሚሊየን ሰዎችም ስራ አጥ እንዲሆኑ መንስኤ ሆኗል።
ከውሳኔ አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮች የሚፈጠሩት በተሳሳተ መልኩ በሚወሰን ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የውሳኔ አሰጣጥ ቅደም ተከተልን ተከትሎ ባለመስራት እንደሆነም አቶ ዛዲግ ጠቅሰዋል።

እ.ኤ.አ በ 1889 ደማስቆ ላይ የተጻፈው ታሪክ ዛሬም ደምቆ ይታያል። ዛሬ ላይ ፍቃዳችሁ ይሁንና አንዳቸው የሌላውን ህይወት ስለታደጉት "መሀመድ እና ሰሚር" ስለተባሉት ጓደኛማቾች ታሪከ እናውጋችሁ። መሀመድ በተፈጥሮው ዓይነ ስውር ሲሆን ሰሚር ደግሞ ሰውነቱ "ፓራላይዝ" ነው። ልዩነታቸው ከዚህ ይጀምራል። ስንቀጥል ደግሞ መሀመድ የእስልምና እምነት ተከታይ ነበር። ሰሚር ደግሞ የክርስትና ሀይማኖትን ተከታይ። ልዩነት ሁለት።
ከታች በፎቶው ላይ እንደሚታዩት ህይወታቸውን ሲገፉ የነበሩት ሰሚር የመሐመድ አይን ፤ መሐመድ ደግሞ የሰሚር እግር በመሆን ነበር። ዓይን አልባው እግር ሲሆን እግር አልባው ደግሞ አይን ሆነው ነበር። ሁለቱም ያላቸውን ነገር አክብረው የሌላቸውን በጸጋ ተቀብለውና አክብረው ዓመታትን ተሻግረዋል።
ህይወትን ለማሸነፍ ሲሉ መተጋገዝን እና መተሳሰብን ብቻ አማራጫቸው ሁኔታዎቻቸውንና እክሎቻቸውን አሸንፈዋል ። አንዱ ለሌላው ምን ማለት እንደሆነ በተግባር አሳይተዋል። መሀመድ ጉድለቱን ከሰሚር፤ ሰሚርም ክፍተቱን ከመሀመድ ሞልቷል።
ታሪካቸው የተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች አንድ ላይ ሆነው እርስ በርስ ሲረዳዱ ተአምር እንደሚፈጠር የሚያሳይ ድንቅ ምሳሌ ነው።
መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር ብለው እንዳቀነቀኑት የሀገራችን ድምጻውያን፤ ሰው ለሰው ቢፋቀር የት ይደረስ ነበር።ሁሉም ጣቶች እኩል ርዝመት የላቸውም። ሲረዳዱ ግን ሁሉም እኩል ይሆናሉ ነው ብሂሉ። ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው እየተረዳዳን ስናስተናግዳቸው ሕይወት የበለጠ ቀላል ትሆናለች።
ነገሩን ወደ ኢትዮጵያ ስንመልሰው ምን ትርጉም ይሰጠናል? የጥልቅ ብዝሀነት ባለቤትና ባለጸጋ የሆነቸው ሀገራችን ህዝቦቿ ቢረዳዱ እና ቢተባበሩ የት ትደርስ ነበር? የአንዳችን የተፈጥሮም ሆነ የባህል ጸጋ ለሌላኛችን ያለውን ዋጋ ተረድተን ልዩነቶቻችን ወደ ጎን ትተን፤ ትልቁን ምስል አብልጠን አይተን፤ ብንደመር የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ ከጫፍ ለማድረስ ጉልበት ይሆነናል።
መረዳዳት፤ መከባበር፤ አንዱ የሌላውን ጉድለት መሙላት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ምርጫችን ሳይሆን ብልጫችን ነው። ተደምረን አንዳችን የሌላችንን ጉድለት ብንሞላ ምን እንሆናለን?
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የመሀመድን እና የሰሚርን ታሪክ ከሀገራችን የእስካሁን ጉዞ ጋር እያገናኙ፤ የወደፊቱን ዕጣ-ፈንታችንን ፍንትው አድርገው ያሳዩናል። በቀጣይ የምንለቀው “የኮሙኒኬሽን ሀይል እና የአመራር ጥበብ” በሚለው ሙሉ የስልጠና ቪዲዮ ላይ በሰፊው ያገኙታል።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) በ አፍሌክስ ዋና መሥሪያ ቤት ተከበረ
አዲስ አበባ - መጋቢት 1/2017 (አፍሌክስ) - በአለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በሃገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፉ የሴቶች ቀን በ አፍሌክስ ዋና መ/ቤት መላውን ሰራተኛ ያሳተፍ ዝግጅት በማካሄድ ተከብሯል።
ዝግጅቱ የልምድ ልውውጥ፣ የጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ እና በሴቶች መብትና ተጠቃሚነት፣ በጾታ እኩልነት እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተካሄዱ ውይይቶችን ያካተተ ነበር።
የአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎችና ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች የዳሰሰ ንግግር አድርገዋል።
በንንግራቸው መንግስት እንደ መንግስት፣ አፍሌክስ እንደ ተቋም የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማስፈን በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ መሻሻል ቢታይም ጉዳዩ ገና ብዙ የሚቀረው የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።
"የምናመጣው ለውጥ ዘላቂ እንዲሆን ከተፈለገ የሴቶችን ተሳትፎ በእጅጉ ማሳደግ ይኖርብናል" ሲሉ የተናገሩት ወ/ሮ መሰረት "የፆታ እኩልነት ሙሉ በሙሉ እውን እስኪሆን ድረስ ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን፣ እናም እኛ ሴቶች በቤት ውስጥም ሆነ በሥራ ቦታ ሃላፊነቶቻችንን ሳንዘነጋ ከወንዶች ጋር በትብብር ሁሉንም ተግባራት በእኩልነት እንወጣለን " ሲሉ አክለዋል።
አፍሌክስ በአመራር መስክ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ሲሆን የሴቶችን የመሪነት ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ ውጥኖችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ከነዚህ ውጥኖች መካከል አንዱ የሆነው የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም ለአንድ አመት ያህል ያሰለጠናቸውን 50 ሴት መካከለኛ አመራሮች በቅርቡ ማስመረቁ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ 'ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል' በሚል መረ ቃል እየተከበረ የሚገገኘው የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአፍሌክስ ሲከበር መላው አመራር እና ሰራተኛ የጾታ እኩልነት በአመራር መስኩ እንዲረጋገጥ የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ አደራ በማስያዝ እንደሆነ ተገልጿል።

የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ
#የኮሙኒኬሽን_ኃይል_እና_የአመራር_ጥበብ በሚል ርዕሥ ለከፍተኛ አመራሮች የሰጡትን የስልጠና ሙሉ ቪዲዮ ወደ እናንተ ለማድረስ የአንድ ሰዓት ጊዜ ብቻ ቀርቶናል። በፌስቡክ ገጻችን እና እና በዩቱዩብ ቻናላችን ይጠብቁን!!

Strategic Meeting Enhances Collaboration Between AFLEX and Armenian Leadership Academy
Sululta - 11 March, 2025 (AFLEX) – A pivotal strategic meeting held between AFLEX and the Public Leadership Excellence Academy of Armenia, aimed at enhancing collaboration in the field of leadership development.
The meeting brought together key figures from both institutions, including AFLEX's Leadership Development, Vice Chief Mrs. Meseret Desta, other management representatives from AFLEX, and a delegation from Armenia led by Khachatur Ghazeyan, Rector at Armenian Academy and H.E Sahak Sargsyan, Armenian Ambassador to Ethiopia.
During the meeting, participants discussed AFLEX's recent reforms, scaling initiatives, and transformative approaches in leadership training. The Armenian delegates also had the opportunity to visit the AFLEX Leadership Development and Training Center located in Sululta, where the meeting was held.