African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.51K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
“የቻይና መንግስት፤ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን የሰው ሀብት ልማት እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ለማገዝ ዝግጁ ነው” Guan Zhiyong የCIDAC ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የልዑክ ቡድኑ መሪ

“የቻይና መንግስት ለአካዳሚው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እና እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛል” ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) የአፍሌክስ የአስተዳደር እና የቢዝነስ ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ

ታሕሣሥ 16፣ 2017 (አፍሌክስ-ሱሉሉታ)- የቻይና መንግስት የአፍሌክስን የሰው ሀብት ልማት እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ለማገዝ ዝግጁ እንደሆነ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው ዛሬ በአካዳሚው የአመራር ልማት ውስጥ በተደረገ ውይይት ላይ ነው። የቻይናን መንግስት ወክለው ከአካዳሚው ጋር ውይይት ያደረጉት ከአራት የቻይና መንግስት ተቋማት የተውጣጡ የልዑክ ቡድን አባላት ናቸው።

ከCIDAC፤ ከChinese Embassy in Ethiopia፤ ከChinese Mission to the African Union እና ከNational Academy of Governance የመጡ ልዑካን ከአፍሌክስ የአስተዳደር እና የቢዝነስ ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ የCIDAC ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የልዑክ ቡድኑ መሪ ጉዋን ዢዮንግ Guan Zhiyong የቻይና መንግስት፤ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን የሰው ሀብት ልማት እና የመሰረተ ልማት ግንባታ ለማገዝ ዝግጁ እንደሆነ ጠቁመው፤ ለዚህም የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን እና ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የልዑክ ቡድኑ መሪ ጉዋን ዢዮንግ Guan Zhiyong አያይዘውም የአካዳሚውን የሰው ሀይል አቅም ለመገንባት በትምህርት እና ስልጠና መስክ እንዲሁም በልምድ ልውውጥ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአፍሌክስ የአስተዳደር እና የቢዝነስ ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቻይና መንግስት ለአካዳሚው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እና እገዛ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረው፤ የአካዳሚውን እና የሀገራችንን አመራር አቅም ለመገንባት በርካታ መዋዕለ ንዋይን መድበው እየሰሩ በመሆኑ አመስግነዋል።

ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አያይዘውም የቻይና መንግስት በብሪክስ ጥላ ስር ለሀገራች እና ለአካዳሚው የሰው ሀብት ልማት እና መሰረተ ልማት ግንባታ ሰፋፊ ስራዎች በመስራቱ ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ የሚያግዝ እንደሆነም ተናግረዋል።

የልዑክ ቡድኑ በቻይና መንግሰት ቻይና ኤይድ የተሰራውን የአካዳሚውን መሰረተ ልማትም ጎብኝቷል።
በመጪው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት የተቀናጀ የኮሚኒኬሽን ሥራ ያስፈልጋል-ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ !

ከወራት በኋላ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት የተቀናጀ የኮሚኒኬሽን ሥራ እንደሚያስፈልግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን የገለፁት በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነባር ዲፕሎማቶችና በጎ ፍቃደኛ ካዴቶች #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ተገኝተው በውጤታማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና በሰጡበት ወቅት ነው።

በስልጠናው የተቀናጀ፣ የተደራጀ፣ ስትራቴጅክ እና አጀንዳ ሰጪ የኮሙኒኬሽን ስልትን በመከተል ውጤታማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን እንዲኖር ሁሉም ዜጎች በብሄራዊ ስሜትና አገራዊ ሀላፊነት እንዲሰሩ ሚኒስትር ዴኤታው አበክረው ተናግረዋል።

በመጪው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ኢትዮጵያን በሚገባ ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው ሰልጣኞቹ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በተገቢው በመረዳት በሁሉም ዘርፍ እየታዩ ያሉ እምርታዎችን ለእንግዶቹ በማስገንዘብ አገራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ የሚያጠለሹና ብሄራዊ ክብርን ዝቅ የሚያደርጉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በሚገባ በመለየት ብሔራዊ ጥቅምን ሊያስጠብቁ የሚችሉ የተግባቦት ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው
ከዚህ በተጨማሪም አዎንታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ መልዕክቶችን በመቅረጽ ተሳታፊዎች ስለኢትዮጵያ በጎ መረጃ ይዘው እንዲመለሱ የሚያስችል የመረጃ ስራ በቅንጅት እንደሚዘጋጅ አሳውቀዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ ሰልጣኞች በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት በሁሉም የኮሙኒኬሽን ስልቶች አገራቸውን ለማስተዋወቅ ያላቸውን ዝግጁነት ያሳወቁ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ላነሱት ጥያቄም ሚኒስትር ዴኤታው ምላሽ ሰጥተውበታል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና ኢጋድ በጋራ ለመስራት የተፈራረሙትን ስምምነት NBC ETHIOPIA እንዲህ ዘግቦታል፡-
Consultative Discussion between AFLEX and Chinese Delegates

Dec 25, 2025 / ADDIS ABABA / AFLEX / A consultative discussion was held between AFLEX President, Mr. Zadig Abreha, and the Chinese delegates from CIDAC, the China Embassy in Ethiopia, the Chinese Mission to the African Union, and the National Academy of Governance at the AFLEX Head Office.
The discussion aimed to strengthen collaboration and explore potential partnerships between the two parties. It highlighted two key areas of focus: human resource development and capacity building, and infrastructural development.

Mr. Zadig Abreha shared the academy’s recent initiatives, detailing its progress and successes. The Chinese delegates were briefed on AFLEX’s ongoing and future projects, especially its ambition to expand its influence in national and African training programs.

There was a notable emphasis on forming partnerships with prestigious Chinese universities, such as Peking University and Tsinghua University, for experience-sharing and collaborative research.

Additionally, the president emphasized the importance of China’s support in expanding AFLEX’s infrastructure.
This included potential collaboration on building new facilities and enhancing existing structures to accommodate the growing demand for training and capacity-building programs.

In response, Deputy Director-General Guan Zhiyoung of CIDAC expressed a strong willingness to collaborate with AFLEX. He shared the Chinese delegation's intent to develop a comprehensive training project plan with AFLEX.

Moreover, he referenced President Xi Jinping’s leadership development initiatives across Africa. He also confirmed that China was eager to engage with AFLEX as part of the BRICS partnership, highlighting the importance of focusing on human resource development as a primary goal.

The discussion concluded with both parties expressing a shared commitment to strengthening ties and creating sustainable collaborations.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና ኢጋድ በጋራ ለመስራት የተፈራረሙትን ስምምነት ፋና 90 በምሽት ዜናው እንዲህ ዘግቦታል፡-