African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.53K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ሚዲያዎች ኢትዮጵያዊያንን አንድ በሚያደርጉ ትርክቶች ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡

*********************

“የሚዲያ ሚና ለትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዘጋጅነት ለሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 18/2017 ዓ/ም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥተጀምራል፡፡

"ሚዲያ ለብሔራዊ ትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል ርዕስ ላይ ገለጻ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስተሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሚዲያዎች ኢትዮጵያዊያንን አንድ በሚያደርጉን ትርክቶች ላይ ትኩረት አድርገው መሥራት እንደሚጠበቅባቸውና ሃገር የሚገነባው በአዎንታዊ ትርክቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሥራ ትርክትን እንደሚቀይር የተናገሩት አማካሪ ሚኒስትሩ ባዶ ትርክት እንደማይጸናና ተግባራዊ ሥራ ሲሰራ ትርክቶች ይለወጣሉ ብለዋል። ትላንት የነበረው የአባይ ውሃ ዛሬ ህዳሴ ግድብን ሰርተን ስናጠናቅቅ ትርክቱ ተቀይሯል በማለት ሥራ ተግባርን እንደሚቀር አመላክተዋል፡፡

ትርክቶች አካታች መሆን እንዳለባቸው ፣ልሂቃን የሚገቡ ትርክቶች መቃናት እንዳለባቸው ያነሱት አማካሪ ሚኒስትሩ ትርክት ለነገ ሲባል የትላንቱን የሚተወውን ትተን፣ የዛሬንም ይቅር ብለን ነገን የምንገነባበት ሊሆን ይገባል ብለዋል በገለፃቸው፡፡

ትርክት የአብሮነት ታሪካዊ መሰረት እንደሆነ፣ ሰዎች ከየት ተነስተው እና ወደየት እንደሚሄዱ እና የት እንደሚደርሱ የሚመለከቱበት መሆኑንም ዲያቆን ዳንኤል አክለዋል፡፡

ለመገናኛ ብዙሃን "ሚዲያ ለብሔራዊ ትክርክትና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ስልጠና ለሶስት ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ይቀጥላል፡፡
👍12
በመንግሰት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት እና በአካዳሚው 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመንግሰት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት እና በአካዳሚው 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ውይይት አካሄደ፡፡

በአካዳሚው የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በአለም አቀፍ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አዝማሚያና ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው አንድምታ፣ የሪፎርሙ ተጠባቂ ፋይዳዎች የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ፤ የዘርፎች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት እና የመንግስስት አገልግሎትና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል:: ምክትል ርዕሰ አካዳሚው የዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይም ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በበኩላቸው፣ ተቋሙ እቅዱን በመፈተሸ፣ ተግዳሮትን በመለየት፣ የተቋቋመበት ተልዕኮ ላይ አተኩሮ መስራት እንዳለበትና መሪነት የሚታይበት እና መሪ ፈፃሚ መሆን እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡
👍17
የርዕሰ አካዳሚ ጽ/ቤት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ጫኔ በበኩላቸው የተቋሙን የመቶ ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም የሀብት አጠቃቀምና አገለልግሎት አሰጣጥ ፣በቁልፍ የውጤት አመላካቾች ላይ የተመሰረተ የዕቅድ አፈፃፀም ትንተና፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

በቀረቡት ገለፃዎች ላይ ከአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በምክትል ርዕሰ አካዳሚዎቹ ለጥያቄዎቹ ምላሽ ፣ ለአስተያየቶቹም ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያቶች ጥሩ መሆናቸውን የተጠቀሰ ሲሆን እንደግብአትም እንደሚያገለግሉ ተጠቁሟል፡፡

የአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ሆነው ለተሾሙት ወ/ሮ መሰረት ደስታ የእንኳን ደህና መጡ የመልካም ምኞት መልዕክትም ከአመራሩና ከሰራተኛው ተላልፏል::
👍22
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት !!
ክቡር የኢፌዴሪ #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ዐቢይ_አሕመድ (ዶ/ር) ስለ #አፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ምን አሉ?
የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት !! በሚል በቀረበው የከፍተኛ አመራር ስልጠና ላይ የስራ ቦታ፤ ኤርጎኖሚክስ፤ የተቋማት ግንባታና የመፈጸም ባህል በሚለው ገለጻ ስር ስለ ተሻጋሪ ተቋማት ይህን ብለዋል።
እንደ #አፍሌክስ ያሉ ተቋማት ለትውልድ የሚሻገሩ ናቸው። ጥርት ብለው፤ ትልቅ ሆነው፤ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ የተሰሩ ናቸው።
👍21
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው
*****************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄዎቹ ላይ የሚሰጡትን የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
👍11
ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዓመት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍13