African Leadership Excellence Academy
2.14K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአመራሩ የሥነ-ምግባር ጉድለት የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በመገንዘብ ተገቢውን ሥራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
ክቡር #ዶ/ር_ጌዲዮን "የስነ-ምግባራዊ እመርታ፤ ከሞራል ብልሹነት ወደ ግብረገባዊ አርኣያነት" በሚል የሥልጠና ርዕስ ላይ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች ገለፃ አቅርበዋል።
ክቡር ሚንስትሩ ሰለ #ሥነ-ምግባር፣ #ግብረገብ#ሞራል#ዲሲፒሊን ልዩነትን እና አንድነትን በተመለከተ ፍልስፍናዊ ዳራዎችንና አብነቶችን በመጥቀስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አብራርተዋል።
የሥነ-ምግባር ዋነኛ መገለጫዎችን በዝርዝር ያነሱት ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ሥነ-ምግባር #በግለሰብ#በቤተሰብ#በቡድን#በተቋም ደረጃ እንደሚገለፅ ጠቁመዋል።
በተቃራኒው የአመራሩ የሥነ-ምግባር ብልሹነት #የግል_ጥቅምን_ብቻ_መመልከትን#በዘር_መከፋፈልንና_ፅንፈኝነትን#ሙስናንና_ብልሹ_አሰራርን የሚያስፋፋ ከሆነ እና የመልካም አስተዳደር እጦት የሚኖር ከሆነ #በሕዝብና_በመንግሥት_መካከል_አሉታዊ_ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
ለዚህም እንደ ሊባኖስ ያሉ ሀገሮች ከውጭ ሀገሮች ጣልቃገብነት ይልቅ በሀገራቸው የተንሰራፋው ሙስናና በስልጣንን አለ አግባብ መጠቀም 80 በመቶ የሚሆነውን ሕዝብ ለከፋ ድህነት እና ሀገሪቱን ለአደጋ ማጋለጡን በአብነት አንስተዋል። በመሆኑም በአመራሩ ሥነ-ምግባር ላይ ብዙ መሥራት ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ክቡር ሚንስትር #ጌዲዮን_ጢሞቲዎስ ኢ- ሥነምግባራዊ በሆኑ መንገዶች የሚገኝ ጥቅምም ሆነ ማንኛውም ነገር ዘላቂነት እንደሌለው አስገንዝበው አመራሩ #መልካም_ሥነ-ምግባርን_በመላበስ እና #መርህን_በመከተል ሕዝቡንና ሀገሩን በማገልገል ኢትዮጵያን የማበልጸግ አደራ አለበት ብለዋል።
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም ለ7ኛ ቀን ቀጥሏል።