African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.53K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ጠንካራ የተቋማት ግንባታ ወሳኝ ነው"

------ ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሐ -----

(ዜና ፓርላማ) ጥቅምት 09 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ጠንካራ የተቋማት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሐ አስገንዝበዋል።

ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሐ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመሮችና አባላት ዛሬ ለሶስተኛ ቀን በቀጠለው ስልጠና "ተቋማዊ ግንባታ፤ ለሀገር እመርታ" በሚል ርዕስ ገለፃ እያደረጉ ነው።

ክቡር አቶ ዛዲግ በገለፃቸው ሀገራችን ከብዙ አመታት በፊት የዲሞክራሲ መገለጫ የሆነውን የገዳ ስርዓትን እና ወታደራዊ መዋቅሮችን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትን የመገንባት ጅምሮ ቢኖራትም እስከመጨረሻው ድረስ ባለመዝለቁ ሀገራችንን ማሳደግ አልቻልንም ብለዋል።

ስለሆነም ይህ ትውልድ ኢትዮጵያን ለማሳደግ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት ረገድ ጀምሮ እስከ ማጠናቀቅ ድረስ ረጅም ርቀትን በቁርጠኝነት ሊሄድ እንደሚገባ አሳስበዋል።
👍15
ስለሆነም በቀጣይ ምክር ቤቱም ሆነ የምክር ቤት አባላት ከስልጠናው የሚገኘውን ዕውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ በመቅሰም፣ ከተቋማት ጋር በመቀናጀትና ተናቦ በመስራት፣ እንዲሁም የሚሰጡ ቀጣይ ሀገራዊ አቅጣጫዎችን በአግባቡ በመያዝ ሀገራችንን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች በማጠናከር ወደተሻለ ከፍታና ብልጽግና የማሸጋገር ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ‹‹የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት›› የሚለው አለማቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ጥቅል የሆነ ሀሳብን የያዘ በመሆኑ የነበራቸውን ግንዛቤ ይበልጥ እንዳሳደገላቸው ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ዛሬ ላይ አደጉ የሚባሉት ሀገሮች የራሳቸውን ህልም አስቀምጠው እንዳሳኩ ሁሉ ሀገራችንም ወደ ብልፅግና የሚሻግራት ህልም ማስቀመጥ በመቻሏ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ያገኙት ይህ ህልም ዕውን እንዲሆንም ለመራጭ ህዝባቸው በአግባቡ በማስገንዘብ ሀሳቡ እንዲሰርጽ ማድረግ እና በክትትልና ቁጥጥር ስራቸው ውስጥ በማካተት እንዲሰሩም ሰልጣኝ የምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል፡፡

የተሰጡንን ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በአግባቡ በመወጣት፣ ከግጭት እና ከፅንፈኝነት አመላከት በመውጣት፣ ችግሮቻችንን በጋራ በመፍታት እንዲሁም ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር ሀገራችንን ወደተሻለ ከፍታ ማሻገር ይጠበቅብናልም ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም ሰልጣኝ የምክር ቤት አባላት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በቀጣይም በሚሰጡ የስልጠና ርዕሶች ላይም በአግባቡ እንዲሳተፉና የተሻለ ዕውቀትና ግንዛቤ እንይዛለን ብለው እንደሚጠብቁም ገልጸዋል፡፡

(በኃይለሚካኤል አረጋኸኝ)
👍11
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ የሚሰጠው
ስልጠናው ምክር ቤቱ እና የምክር ቤት አባላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ትልቅ አቅምን እንደሚፈጥር ተመላከተ
--------------------
(ዜና ፓርላማ)ጥቅምት 09 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለምክር ቤቱ አመራሮችና አባላት እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ምክር ቤቱ እና የምክር ቤት አባላት የተጣለባቸውን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ትልቅ አቅምን እንደሚፈጥር የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አመላክተዋል፡፡

ስልጠናው ምክር ቤቱና የምክር ቤት አባላት ሀገራችንን ከወቅታዊ አለምዓቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ በህገ-መንግስቱ የተሰጠንን የህግ አወጣጥ፣ የክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የህዝብ ውክልና ስራችንን በሙሉ አቅምና ብቃት ለመወጣት ያስችላል ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አክለውም ስልጠናው ሀገራችን በተጨባጭ እያስመዘገበች ያለውን እመርታ፣ ያጋጠሟትን ተግዳሮቶችን እና እነዚህን ተግዳሮቶች በአንድነት በመቆምና በትብብር መንፈስ በጋራ በመስራት መወጣት እንደሚቻል ያሳየም ነው ብለዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ በሀገራችን ብዙ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፤ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እኛም እንደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና እንደ ምክር ቤት አባል ተሳትፏችን የጎላ ነበር ሲሉ አብራርተዋል፡፡
👍15
የጋራ ትርክት ሀገራዊ ህልምን ዕውን ለማድረግ አጋዥ መሆኑን አቶ #ዛዲግ_አብርሐ ገለፁ
--------------------------
(ዜና ፓርላማ) ጥቅምት 08 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ የኢትዮጵያን ህልም ዕውን ለማድረግ የጋራ ትርክት መፍጠር አስፈላጊና አጋዥ ነው ሲሉ #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሐ ገለፁ።

ክቡር አቶ ዛዲግ ይህን የገለፁት #"የትርክት_እመርታ_ከታሪካዊ_ስብራት_ወደ_ሀገራዊ_ምልአት" በሚል ርዕስ በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በተሰጠው የሥልጠና ርዕስ ጉዳይ ላይ ለኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች ማጠቃለያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ክቡር አቶ ዛዲግ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት #የኢትዮጵያ ታሪክ አጻጻፍ ላይ በሚነሱ አንዳንድ ክፍተቶች ምክንያት የጋራ ታሪክና የወል ትርክቶች መፍጠር አለመቻሉን ገልፀዋል ።

በመሆኑም እነዚህ አሉ የሚባሉ የታሪክ አተራረክ ክፍተቶችን በማረቅ ከነጠላ ትርክት ይልቅ አሰባሳቢና የጋራ የሆነ ትርክት መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
👍16
የታሪክ አለመግባባቶች አሉ ማለት ግን ሁሉንም ታሪኮች አሽቀንጥሮ መጣልና ትክክለኛ ያልሆኑ ታሪኮች መነሻ በማድረግ ወደ ግጭት መግባት ማለት አለመሆኑን የገለፁት ክቡር አቶ ዛዲግ ጥሩ ጥሩ ታሪኮችን መቀበልና ከተዛቡ ታሪኮች ደግሞ ትምህርት መውሰድ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

የታሪክ አለመግባባት በሚኖርበት ሁኔታ #የጋራ_ትርክትን ለመፍጠር እንደችግር የሚታይ እንደሆነ የገለፁት ክቡር አቶ ዛዲግ፤ ዋናው ጉዳይ ግን በእውነት ላይ ያልተመረኮዙና በምናብ በተፈጠሩ ታሪኮች ሳቢያ የሚፈጠሩ አለመግባባቶች ለመከላከል የጋራ እውነት ላይ የተመሠረተ ትርክት መገንባት ይገባል ብለዋል። በታሪክ የተነሳ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንም በቀጣይ ለመቅረፍ እንደ ሀገራዊ የምክክር መድረኮች የመሳሰሉ ዕድሎች መፍትሔ እንደሚሆኑም አመላክተዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህልም ዕውን ይሆን ዘንድም የጋራ እና አሰባሳቢ የሆነ ትርክትን መፍጠርና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሁሉም አካል የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበት እና የምክር ቤት አባላት በዚህ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

(በኃይለሚካኤል አረጋኸኝ)
👍15
የሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ የፖለቲካ እመርታን ማረጋገጥ ይገባል-አቶ አደም ፋራህ
****************
ሕዝብ የሚያነሳቸውን የዲሞክራሲ፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ወቅቱን የዋጀ ህዝብን ሁለንተናዊ ጥያቄዎችን የሚመልስ የፖለቲካ እመርታን ማረጋገጥ እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ገለፁ።

አቶ አደም ፋራህ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች " የፖለቲካ እመርታ፤ ከዲሞክራሲ መብት ወደ ሀገራዊ ኃላፊነት" በሚል ርዕስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ገለፃ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ጊዜያት በነበሩ የመንግስት ስርዓቶች የህዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠበት፣ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ምላሽ ያላገኙበት፣ ቁልፍ ፖለቲካዊ ተቃርኖዎችና ችግሮች ያልተፈቱበት እንደነበር አስታውሰዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የፖለቲካ ሪፎርም ማካሄድ ይገባል ብለዋል።

ይህ የፖለቲካ ሪፎርምም ተቃርኖዎችን ሊያስታርቅ የሚችል የመሀል ፖለቲካን የሚከተል፣ የህዝቦችን ሁለንተናዊ ጥያቄዎች የሚመልስ፣ የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ብልፅግናዋን ሊያረጋግጥ የሚችል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ይህ ዕውን እንዲሆን ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓትንና ተቋማትን መገንባት እንዲሁም ይህን መምራት የሚችል አመራር እንደሚያስፈልግ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ መግለፃቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓም
👍13