የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች በአካዳሚው ሪፎርም: ማስፋት እና ሽግግር ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ ነው:: ስልጠናውን የሰጡት እሸቴ አበበ (ዶ/ር) ሲሆኑ በአፍሌክስ ውስጥ ሊሰሩ ስለታቀዱ ፕሮጀክቶች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል::
የተቋም እና የግል ልማት በሚል ርዕስም በሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ስልጠና ተስጥቷል::

የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ የአካዳሚውን የአገልግሎት አፈፃፀም ልህቀት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ::
ይህ የተገለጸው ለአካዳሚው አመራሮችና ባለሙያዎች ስለ ተገልጋዮች አገልግሎት አሰጣጥ (Customer Service Delivery, Etiquette and Protocol) ስልጠና በተሰጠበት መድረክ ነው::
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ሲሳይ ዘሪሁን እንደጠቀሱት የአካዳሚውን የአገልግሎት አሰጣጥና የእንግዳ አቀባበል በማሳደግና ዘመናዊ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል::
የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በእቅድ: ክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም የአፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት አቶ ምትኩ ጫኔ ናቸው::
በስልጠናው ላይም ስለ እቅድ እና ሪፖርት ምንነት እና አዘገጃጀት: ስለ ክትትል እና ግምገማ ስርዓት በሰፊው የቀረበ ሲሆን ስለ ተቋማዊ መዋቅርም ማብራሪያ ቀርቦበታል::

የአካዳሚውን የለውጥ: የማስፋት እና የሽግግር ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግ ለውጥን የሚረዳ: የሚያግዝና የሚያስተዳድር የተቋም ማህብረሰብ ለመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ተገለጸ::
ለአካዳሚው አመራር እና ሰራተኞች በተዘጋጀው የለውጥ አስተዳደር (Change Management) ስልጠና ላይ እንደተጠቀሰው የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ከጫፍ ለማድረስ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ጥላሁን አረጋ ተናግረዋል::
አፍሌክስ የሰነቀው ራዕይ ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ምድር ሚና እንዲኖረው የሚያስችለው በመሆኑ የተቋሙ ማህበረሰብ ለተልዕኮው መሳካት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ከመድረኩ ተገልጿል::
የአካዳሚው አመራር እና ሰራተኞች በፐብሊክ ሰርቪስ ስነ ምግባር እና ፕሮፌሽናሊዝም (Public Service Ethics and Professionalism) ላይም ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በተቋሙ የሚያጋጥሙ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የአካዳሚውን ግብ እንዲያሳኩ ጥሪ ቀርቧል:: ስልጠናውን የሰጡት አቶ መስፍን በሃይሉ እንደጠቀሱት ለሙያዊ ስነ ምግባር እና ለህግ ተገዥ በመሆን የተቋሙን ተልእኮ ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል::