African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10ሺ ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በሰለሞን በረጋ አማካኝነት አገኘች: እንኳን ደስ አለን በአስር ሺ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ ወርቅ እንዲሁም በበሪሁን 4ኛ ደረጃን በማግኘታችን በጀግኖቻችን ኮርተናል🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ደንብ ቁጥር 484/2013

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዲሚን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሠላም፣ ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንዴፈ-ኃሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር የአመራር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ችግር ፈቺ ምርምር በማካሄድ ሳይንሳዊ የለውጥ ሀሳቦችን በማመንጨት የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ሁለንተናዊ ብልጽግና እና መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ የሚያስችል የአመራር ልህቀት አካዲሚ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የልማትና የመልካም አስተዳደር ፖሊሲዎችን ሥራ ላይ በማዋል ተቋማዊና ሀገራዊ ለውጥ በቀጣይነት ማረጋገጥ የሚችል፣ የአሁንና የመጪውን ጊዜ ፈተናና ለውጥ በመምራት የአፍሪካን ዘላቂ ልማትና ትስስር በማምጣት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ አመራር ማፍራት የሚችል ተቋም አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራሊዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 34 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከጀርመን ኬሄል ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ውይይት አደረገ፡፡
የጋራ ስምምነቱ በአጭር ስልጠናዎች፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በመማር ማስተማር ላይ ያተኮረ መሆኑን የአካዳሚው የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የአካዳሚክ ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት ተወካይ ዶ/ር ሰሜነህ ቤሴ አብራርተዋል፡፡
የጀርመን ሀገር ኬሄል ዩኒቨርሲቲን በመወከል በውይይቱ ላይ የተገኙት የዬኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኢንድሪያስ ፓተር በተደረገላቸው ገለፃና አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ የጋራ ስምምነቱ ለመምህራን እና ለአመራሩ የልምድ ልውውጥና የአቅም ግንባታ እድል በመፍጠር መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የውይይት ተሳታፊዎችና የጀርመን ኬሄል የዩኒቨርስቲ ተወካዮች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሱልሉታ ካምፓስ ጉብኝትም አድርገዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱም በቀጣይ በተያዘለት ጊዜ የሚደረግ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች ለሃገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ አደረጉ
በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ባለው የህልውና ዘመቻ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች ደም በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም ማዳሄዳቸውን የአካዳሚው የሴቶች፣ ወጣቶች ኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ ምህረት አስጨ ገልፀዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ትስስር ለማጠናከር የተዘጋጀ መርሀግብርን ለማስፈፀም በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ቃሉ ወረዳ ተገኝተው የአቅመ ደካማ ሰዎችን ቤቶች የማሳደስ ስራ አስጀምረዋል::