African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ቃሉ ወረዳ ተገኝተው በሸብርተኛዉ ህወሃት ቡድን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የምግብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል:: ለወገን ደራሽነታቸውንም በተግባር አሳይተዋል::
እንኳን ለ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ!

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እውቀትና እውነትን የተላበሱ፣ ለሕዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችሉ፣ በሥራቸውና በምግባራቸው ብቁ አመራሮችን በየደረጃው በብዛት በመገንባት የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ብልጽግና በዘላቂነት ለማሳካት፤ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረተ፣ በንድፈ-ኃሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር፣ ሁለን አቀፍ እና ተደራሽ የአመራር ሥልጠና ሥርዓት መዘርጋትና ማጠናከር፤ ወቅታዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚነሱ ሀሳቦች ላይ ጥናትና ምርምር በማካኄድ፣ ሥጠናዎችን በመስጠት፣ የተለያዩ መድረኮችንና ፎረሞችን በማዘጋጀትና በማማከር የአመራር ልማትን ማሳደግ፤ የአመራር ስልጠናና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ለተሳካ ሀገራዊና ተቋማዊ ግንባታ እውን መሆን ኃላፊነቱን መወጣት የሚችል አመራር በማፍራት የብሔረ-መንግስትና ሀገረ-መንግስት ግንባታን ማሳለጥ፣ በሀገር ውስጥ በቀጠናውና በአፍሪካ የአመራር ልማት ፖሊሲ እና ብቃት ማዕቀፍን መሠረት ያደረገ የአመራር ሥልጠና በማካሄድ፣ ተወዳዳሪ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠርና በማጠናከር በዘርፉ የልህቀት ማዕከል መሆን፣ የመንግስትና የህዝብ የፖሊሲ ሪፎርሞችን በውጤታማነት መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል ብቃት ያለው አመራር መገንባትን አላማ አድርጎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 484/2013 መሰረት የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ ተጠሪነቱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማድረግ የተቋቋመ ተቋም ነው።

አካዳሚው መጪው ዘመን የሰላም፣የደስታና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ይመኛል!
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና በመከታተል ላይ ለሚገኙት ዲፕሎማቶች ባቢሎን በሳሎን ቲያትርን ተጋብዘው እየተመለከቱ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ለምናከናውነው የአመራር አቅም ግንባታ ስራ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡
በዛብህ ገ/የስ
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
‹‹አካዳሚውን ከጠበኩት በላይ ነው ያገኘሁት፤ ሁሉም ነገር የተሟላ ነው፡፡በሌሎች ሀገሮች የምናያቸውን አይነት ትልልቅ ተቋማት በሀገራችን ማየት ትልቅ ኩራት ነው›› ደጀኔ በቀለ
በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክተር
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰልጣኞችን ተቀብሎ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠቱ ምስጋና እና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ሽልማቱን ሲያበረክቱ እንደተናገሩት ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና መስተንግዶ በተቋማቸውና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ለአካዳሚው የተሰጠውን ሽልማትም የተቋሙ ፕሬዚደንት አቶ አወሉ አብዲ ተቀብለዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አፈወርቅ ካሱ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት አካደሚው የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አድንቀው የልህቀት ማዕከል በሆነ ተቋም ውስጥ ስለ ትምህርት ጥራት መወያየት ልዩ ስሜትን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡