African Leadership Excellence Academy
2.36K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከፓን አፍሪካን ወጣቶች ህብረት ዋና ጸሀፊ ቤንኢንግ አህመድ BENING AHMED WIISICHONG SECRETARY-GENERAL, PAN AFRICA YOUTH UNION(PYU) ጋር ተወያዩ።
አፍሌክስ የአህጉሪቱን እና የሀገራችንን አመራሮች ለማብቃት ስልጠና ብቻውን በቂ እንዳልሆነ በማመኑ አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰምንት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ነድፎ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ ርዕሰ አካዳሚው ለዋና ጸሀፊው ገልጸዋል።
በተለይም በወጣቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ወጣቶች አቅም ለመገንባት ፕሮጀክት መቀረጹን የጠቀሱት አቶ ዛዲግ፤ በአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎች ውስጥም ወጣት አመራሮች አቅማቸውን እንዲገነቡ እና ሀሳብ እያፈለቁ የምርምር ስራዎችን እንደዲያበረክቱ አፍሌክስ እየሰራ ነው ብለዋል።
ሀያ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካውያን ብልጽግና የሚረጋገጥበት እንደሆነ ያስታወሱት ርዕሰ አካዳሚው፤ ቀደምት የአፍሪካ ወጣቶች አህጉሪቷን ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዳወጧት ሁሉ የዚህ ዘመን ትውልድም ከድህነት የምትላቀቅበትን መንገድ እንዲቀይስ የሚያግዙ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እንደተቀረጹ አቶ ዛዲግ ተናግረዋል።
አፍሪካን ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ባለቤትነት የሚያሸጋግሩ ፕሮጀክቶችም በአፍሌክስ ውስጥ እየተዘጋጁ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ፤ የአፍሪካ ወጣቶችም የአፍሪካውያንን አጀንዳ በመቅረጽ እና በማስፈጸም ረገድ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ አፍሌክስ ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አያይዘውም የፓን አፍሪካን ወጣቶች ህብረት ከአፍሌክስ ጋር በወጣቶች አመራር ልማት ፕሮግራም፤ በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ እና በአፍሌክስ አመራር ሽልማት ላይ አብረው እንዲሰሩ ግብዣ አቅርበዋል።
የፓን አፍሪካን ወጣቶች ህብረት ዋና ጸሀፊ ቤንኢንግ አህመድ BENING AHMED WIISICHONG SECRETARY-GENERAL, PAN AFRICA YOUTH UNION (PYU) በበኩላቸው አፍሌክስ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን አመራሮች አቅም ግንባታ የሚሰራውን ስራ አድንቀው ህብረቱ በቀረበለት ግብዣ መሰረት ከአካዳሚው ጋር ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ እና የጋራ መግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ወደ ተግባር ለመግባት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
አፍሪካ እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 484/2013 እንደ አዲስ የተቋቋመው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የተሰጠውን ሀገራዊ እና አህጉራዊ ተልዕኮ ለመወጣት እንዲችል፤ በቅርጽም ሆነ በይዘት አፍሪካዊ እንዲሆን የሚያስችሉ የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ሂደቶች ውስጥ ይገኛል።
አፍሪካዊ ተቋም እንዳይሆን ያደረጉትን ውስንነቶች በጥናት በመለየት፤ ችግሮቹን በመፍታት፤ ከአፍሪካውያን ወንድሞች እና እህቶች ጋር በአመራር ልማት ፕሮግራም እና በትምህርት መስክ ለመስራት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ፤ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ስራ ገብቷል።
ሱሉልታ የሚገኘው የተቋሙ የአመራር ልማት ማዕከል በቻይና መንግስት ድጋፍ እንደመሰራቱ፤ ሕንጻው እና በውስጡ የሚገኙ መገልገያዎች በሙሉ የቻይናን የስነ ህንጻ ጥበብ የሚያጎሉ እና የቻይናን የስልጠና ማዕከላት ቅርጽ የሚያንጸባርቁ ናቸው።
ይህ ደግሞ የአፍሪካን ስያሜ እና ተልዕኮ ይዞ ለሚሰራ አካዳሚ አፍሪካዊ ባህልን እና እሴትን አለማካተቱ በተልዕኮው አፈጻጸም ላይ የራሱን አሉታዊ ጫና እንደሚኖረው በጥናት ተለይቷል።
የአካዳሚው ሕንጻ እና መገልገያዎች አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት ተላብሰው ሁሉንም አፍሪካዊ የሚወክሉ ባህላዊ ዕሴቶች እንዲኖራቸው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር በመወያየት የህንጻውን የተለያዩ ክፍሎች እና መገልገያዎች አፍሪካዊ በሆኑ ቀለማት እና ባህላዊ እሴቶች ለመለወጥ የውስጥ ዲዛይን ስራው ተጀምሯል።
በአካዳሚው ቅጥር ውስጥ የሚገኙ መተላለፊያዎችን፤ አዳራሾችን፤ መኝታ ቤቶችን፤ ምግብ ቤቶችን፤ እንግዳ መቀበያዎችን፤ ካፍቴሪያዎችን፤ ላውንጆችን እና ሌሎችንም መገልገያዎች የአፍሪካ ህብረት ዕውቅና በሰጣቸው የአፍሪካ አንድነት መስራቾች እና የቀድሞ መሪዎች እንዲሁም ለአህጉሪቷ ውለታ በዋሉ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ እና የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ስም በመሰየም አፍሪካዊ ተቋም መሆኑን በተግባር ማሳየት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት ይህን ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች ተጀምረዋል።
አካዳሚው አፍሪካዊ ተቋም ለመሆን የጀመረውን ጉዞ የሚያሳዩ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በተከታታይ ማቅረባችንን እንቀጥላለን። ሀሳብ አስተያየታችሁን አጋሩን።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Ethiopia warmly welcomes you to the capital of the African Union_ ወደ አፍሪካ ኅብረት
"አፍሌክስ የሁሉም አፍሪካውያን ቤት እና አቅም መገንቢያ እንዲሆን እየሰራን ነው"
አቶ ዛዲግ አብርሃ በፓን አፍሪካን ወጣቶች ዩኒየን የመክፈቻ ጉባኤ ላይ የተናገሩት
#አሁን
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በፓን አፍሪካን ወጣቶች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
# አሁን
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ # የፓን አፍሪካ ወጣቶች ዩንየን ጉባኤ እየተካሄደ ነው::
'22ኛውን ክፍለ ዘመን ለአፍሪካውያን ለመዋጀት ከአፍሪካውያን ወጣቶች ብዙ ይጠበቃል። ወጣቱ አቅሙን ገንብቶ የአፍሪካን ህዳሴ የሚያረጋግጥበት ጊዜው ደርሷል።
አፍሌክስ በወጣቶች አመራር ልማት ከአፍሪካውያን ጋር አብሮ ይሰራል። '
አቶ ዛዲግ አብርሃ በፓን አፍሪካን ወጣቶች ዩኒየን ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ
'የቅኝ ግዛት አስተሳሰቦች አሁንም ድረስ በአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ውስጥ አሉታዊ ጥላቸውን እንዳጠሉ ነው። የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ከእጅ አዙር የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እና አመለካከት ነጻ እንዲወጣ ወጣቶች ዘመኑ የሚፈልገውን ጥናት እና ምርምር በማድረግ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ይኖርባቸዋል።'
አቶ ዛዲግ አብርሃ በፓን አፍሪካን ወጣቶች ዩኒየን የመክፈቻ ጉባኤ ላይ የተናገሩት
# አሁን
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን ( African Capacity Building Foundation) በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ነው::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ሪፎርም: ማስፋት እና ሽግግር ለተሳታፊዎቹ እንዲያብራሩም በአዘጋጁ አካል መድረኩ ተመቻቶላቸዋል::
የከተማ እና መሰረት ልማት ሚኒስቴር ለ 9ኛ ግዜ የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የከተሞች ፎረም በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄዷል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በመድረኩ ላይ ተገኝተው በከተማ አመራር ልማት ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል::