African Leadership Excellence Academy
2.36K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት የተሰጠው ሹመት የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲመክሩበት ቆይተው የወሰኑት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ፓርቲው ከበርካታ እጩዎች ውስጥ ባላቸው ልምድ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚችሉ እጩዎችን ወደ ፊት ለማምጣት የወሰነበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም ከተሿሚዎች ውስጥ ሁለቱ ከብልጽግና ፓርቲ አባል ውጪ መሆናቸው ለኢትዮጵያ ቅድሚያ የተሰጠበት እና ልምድ እና እውቀት ብቻ መስፈርት የሆነበት መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከየትኛውም ፓርቲ ቢሆን ልምድና እውቀት ያላቸውን ወደፊት ማምጣቱ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ባለው የመተካካት ባህል የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሥራ አስፈፃሚነታቸው በክብር መሸኘታቸውን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን ሹመት መርምሮ አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
*********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን – የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
2. ትዕግስት ሃሚድ – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከ UN Women ለመጡ የስራ ሀላፊዎች ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር ሰፊ ገለጻ ተደረገላቸው።
ገለጻውን ያደረጉት የአፍሌክስ ፕሮግራም ዘርፍ ም/ል ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ አቶ ጥላሁን አረጋ ሲሆኑ አፍሌክስ አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ እና በሀገራችን የነበረውን የስልጠና ስርአት ወደ አመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳደግ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ቀርጾ እየሰራ ነው ብለዋል።
አካዳሚው የአፍሪካን እና የኢትዮጵያን አመራር ለማብቃት በሀገር ውስጥ ካሉ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየሰራ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ጥላሁን የሴቶችን አቅም በአመራር ልማት ፕሮግራም ለማጎልበትም ከሜሊንዳ እና ቢል ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከ UN Women ጋር በመስራትም የአካዳሚውን ስትራቴጂያዊ የግንኙነት አድማስ ማስፋት እንደሚያስፈልግ እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር ለመመስረት እንደሚፈልጉ የጠቆሙት አቶ ጥላሁን በቴክኒካል፤ በፕሮግራም እና በመሰረተ ልማት አብረው እንዲሰሩ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከ UN Women የመጡት የልፍኝ አበጋዝ በበኩላቸው አፍሌክስ በሶስት ዓመት ውስጥ ሊተገብራቸው ያቀዳቸውን ፕሮጀክቶች አድንቀው በገለጻው ያገኙትን ግንዛቤ ለ UN Women ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በማጋራት እና በመነጋገር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር የሚቻልበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል።
ከ UN Women የመጡት የስራ ሀላፊዎችም ለአፍሌክስ ግምታቸው ከሰባ ሺህ ብር በላይ የሆኑ መጽሀፍት በስጦታ ያበረከቱ ሲሆን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ፋሲሊቲም ጎብኝተዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ አብርሃ በአፍሌክስ ሪፎርም(Reform)፤ ማስፋት (Scaling Up) እና ሽግግር (Transformation) ለሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ አድርገዋል።
አፍሌክስ የጀመረውን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳካት የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ርዕሰ አካዳሚው ተናግረዋል።
አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም በመስራት ላይ እንደሆነም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመሆንም በአመራር ልማት ፕሮግራም፤ በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ እና በአፍሌክስ ሽልማት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለመፈራረም መስማማታቸውንም አቶ ዛዲግ አብርሃ ጠቅሰዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው አፍሌክስ ይዞ የተነሳውን ራዕይ ለማሳካት ተቋማቸው ዝግጁ እንደሆነ ጠቁመው፤ ባለስልጣኑ የሚቆጣጠራቸው ሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶችም ከአፍሌክስ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ አመራሮች ስለ አፍሌክስ ፕሮጀክቶች እና የአመራር ልማት ፕሮግራሞች በተደረገላቸው ማብራሪያ መደሰታቸውን ጠቅሰው፤ ለአካዳሚው የሚጠቅሙ ሀሳቦችን እና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን እንዲብራሩላቸው ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይም ርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው ከአፍሌክስ ጋር በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በመፈራረማቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸው፤ በተለይም ከዚህ ቀደም በተቋማቸው ተጀምሮ የነበረውን የአፍሪካ የሲቪል ሶሳይቲ ልህቀት ማዕከል በአፍሌክስ ውስጥ መገንባቱ የዘርፉ አመራሮች የሚሰባሰቡበት፤ ሀሳባቸውን የሚያንሸራሽሩበት፤ የጥናት እና ምርምር ስራዎቻቸውን የሚያጎለብቱበት እንደሚሆን ጠቅሰዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የተስማሙት በአመራር ልማት ፕሮግራም፤ በአፍሌክስ ሽልማት እና በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ ላይ ሲሆን የሲቪል ማህበረሰቡን አቅም ለመገንባት የሚያግዝ ትብብር እንደሆነም ተገልጿል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ሀሳብን እያመነጩ ለመመራመር እና ጥናት ለማድረግ የተሟላ መሰረተ ልማት ያለው የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመሆን የአፍሪካ ሲቪል ሶሳይቲ ልሕቀት ማዕከል ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ያሉትን ከፍተኛ አመራሮች አቅም ለመገንባትም በአፍሌክስ ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራም ውስጥ በማስገባት የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ እና ማህበራዊ ሃላፊነት እንዲወጡ የሚያግዙ ፕሮግራሞች መኖራቸውን ያስታወሱት ርዕሰ አካዳሚው በዚህም ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
የተሻለ አፈጸጸም ያስመዘገቡ እና በአርአያነታቸው ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆኑ የዘርፉን አመራሮች ለመሸለም የሚያስችል ስምምነት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር መኖሩንም አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናግረዋል።
"እድል እና ትግል ሲገናኙ መከናወን ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊነት የታደልነው ነው፤ ይህ መታሰቢያ ደግሞ ታግለን የሠራነው ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓድዋ ድል መታሰቢያን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በመርሃግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "እድል እና ትግል ሲገናኙ መከናወን ይሆናል። ኢትዮጵያዊነት የታደልነው ነው፤ ይህ መታሰቢያ ደግሞ ታግለን የሠራነው ነው ብለዋል።

መታሰቢያው ኢትዮጵያዊ በመሆናችን ታድለን የመስራት ጥረት ታክሎበት የተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከ128 ዓመት በኋላ ተከውኖ ለልጆች ማለፍ በሚችልበት መልኩ ከነግርማ ሞገሱ ኢትዮጵያን መስሎ ኢትዮጵያን አክሎ የታየበት መሆኑንም ገልጸዋል።

የዓድዋን ድል ማርከስ ማለት የአባቶቻችንን አጥንትና ደም ማርከስ መሆኑንም ገልጸዋል።

አባቶቻችን ዋጋ የከፈሉበት ነጻነትና ክብር እሴት መሆኑን ገልጸው ነጻነትን ለማግኘት የሄዱበት መንገድ እሳት መሆኑን ገልጸዋል።

ከአባቶቻችን ልንወርስ የሚገባው ነጻነቱን ክብሩንና አንድነቱን እንጂ እሳቱን መሆን አይጠበቅብንም ብለዋል።

በምረቃ መርሃግብ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሁለቱም ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተገኝተዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለአሁኑ ትውልድ ኩራትና መማሪያ እንዲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ አተማ አስተዳደር መገንባቱ ተገልጿል።
ከ 21 በላይ ተቋማት ለተውጣጡ 40 ሴት አመራሮች ሲሰጥ የነበረው አራተኛ ዙር የሴት አመራር ልማት ፕሮግራም ተጠናቀቀ።
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሴት አመራር ፕሮጀክት ማናጀር አቶ መስፍን በሐይሉ እንደገለጹት በስልጠናው ለተሳተፉት ሴት አመራሮች ለውጥን መተንበይ እና መተንተን እንዲሁም የፖሊሲ ተፅዕኖ ማድረግ እንዲችሉ የሚያግዝ ስልጠና ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደተሰጠ ጠቅሰው ሴት አመራሮቹ በቀጣይ ለሚሰሩት ፕሮጀክት እንደ ትልቅ ግብዓት ይሆናቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
አቶ መስፍን አያይዘውም ስልጠናው የተሰጠው ሀገር ውስጥ ባሉ ከፍተኛ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ባላቸው አሰልጣኞች እንደሆነ አስታውሰው በ Digital leadership, influencing policy making, Change Management & organizational Transformation, System thinking skills for leaders, እና Capstone project seminar ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል።
ይህን የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም በገንዘብ የሚደግፈው የሚሊንዳ እና ቢል ጌትስ ፋውንዴሽን እንደሆነም ተገልጿል።