ET Securities
646 subscribers
567 photos
7 videos
26 files
286 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ኢትዮጵያ በትራምፕ 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባታል!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ የታሪፍ እርምጃ ወሰዱ።

ረቡዕ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ነው፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

ለምሳሌ፡- ቻይና 67% ታሪፍ አሜሪካንን የምታስከፍል ሲሆን ትራምፕ በአዲሱ ታሪፍ 34% ያስከፍላሉ። ካምቦዲያ 97% ታሪፍ አሜሪካንን ታስከፍላለች አሜሪካ አሁን 49% የምታስከፍል ይሆናል።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ በርካታ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ታውቋል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአሜሪካ የአክሲዮን ገበያ ቅናሽ አሳየ

#Ethiopia | ዛሬ የሚጀምረው የትራምፕ የ10 በመቶ ዓለም አቀፍ ቀረጥ ዓለም አቀፉ የአክሲዮን ገበያ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ አስከትሏል።

ከሌሎች ሀገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ 10 በመቶውን ቀረጥ በምትሰበስበው አሜሪካም የትራምፕ የቀረጥ እርምጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳረፉ ነው የተሰማው።

የሀገሪቱ ትላልቅ የአክሲዮን ገበያዎች በአማካይ 5 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ ማሳየታቸውን ወልስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

ይህም በፈረንጆቹ 2020 በኮቪድ19 ወረርሽኝ ከተመዘገበው የአክሲዮን ገበያ መቀዛቀዝ በኋላ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

ሌሊቱን በተዘጋው የአክሲዮን ገበያ ድርሻ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ባደረሰው አዲሱ ቀረጥ አውስትራሊያ፣ ብሪታንያ፣ ኮሎምቢያ፣ አርጀንቲና፣ ግብጽ እና ሳዑዲ አረቢያ የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሽ ሀገራት ሆነዋል።

ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ዕቅዱን ይፋ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ ዓለም ላይ የሸቀጦች እና የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱም ነው የተነገረው።

በርካታ ሀገራት የገበያ አማራጭ እያፈላለጉ ሲሆን፥ አንዳንድ የብሪታንያ ምግብ አምራች ኩባንያዎች ከወዲሁ ከሌሎች ሀገራት ጋር ምርታቸውን ማቅረብ በሚችሉበት አግባብ ላይ ንግግር መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ገቢዎች እና የድንበር ቁጥጥር ባለስልጣንም በወደብ፣ ድንበር እና አውሮፕላን ማረፊያዎች የደረሱ ሸቀጦች ላይ አዲሱን የ10 በመቶ ቀረጥ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ወደ አሜሪካ መንገድ ከጀመሩ በኋላ በተዋወቀው ቀረጥ ለሚከፍሉ ኩባንያዎችም የ51 ቀናት የቀረጥ ክፍያ መክፈያና መግቢያ ሰነድ ማሟያ ጊዜ መስጠቱንም ነው የገለጸው።

በአዲሱ የትራምፕ ውሳኔ መሰረት ቻይና 34 በመቶ ቀረጥ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ምርቶች 20 በመቶ ቀረጥ በመክፈል ቀዳሚዎቹ ይሆናሉ።

ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ከፍተኛውን ቀረጥ እንደምትጥል የገለጸች ሲሆን፥ የአውሮፓ ህብረትም ተመጣጣኝ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።
"መንግስት አንድ ትሪሊየን ብር እዳ አለበት" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት፣ በአጠቃላይ ካለው የብድር ክምችት አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ የመንግሥት መሆኑን አስታውቋል ።

የባንኩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የባንኩ የብድር ክምችት 1.393 ትሪሊዮን ብር መድረሱንና ከዚህ መጠን ውስጥ 74.4 በመቶ ወይም አንድ ትሪሊዮን ብር የመንግሥት ዕዳ መሆኑን ገልጸዋል።

የባንኩ ጠቅላላ የብድርና ቦንድ ክምችት መጠን ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ የተሻገረ ሲሆን፣ ከዚህም ላይ የግል ተበዳሪዎች ድርሻ ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተጠቅሷል።

ከተገለጸው አጠቃላይ የብድር ክምችት መጠን በቦንድ የተወሰደ ብድር 66.7 በመቶ ያህሉን በመሸፈን የአብላጫውን ድርሻ ሲወስድ፣ 27.62 ቢሊዮን ብር የተጠራቀመ ወለድ መሆኑም ተገልጿል።


ባንኩ ከነበረው አጠቃላይ ብድር ለግል ዘርፉ የተሰጠው ብድር ስምንት በመቶ ብቻ ነበር። የተቀረው 92 በመቶ በመንግሥት የተወሰደ ነው። መንግሥት ከወሰደው ብድር 98 በመቶ የሚሆነው የተሰጠው በስምንት በመቶ የወለድ ምጣኔ ሲሆን፣ የተቀረው ሁለት በመቶ ብቻ በ11 እና በ12 በመቶ የወለድ ምጣኔ የተሰጠ ብድር ነው፤›› ብለዋል።


እንደሪፖርተር ዘገባ መንግሥት በወሰደው ብድር ላይ 173 ቢሊዮን ብር ወለድ መጠራቀሙንና መንግሥት ግን ብድሩን ባያቃልልም፣ ንግድ ባንክ ወለዱን መሰብሰቡ ታሳቢ ተደርጎ በየዓመቱ ግብር ሲከፍል መቆየቱ ታውቋል ።
𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮’𝘀 𝗜𝗻𝘁𝗲𝗿𝗯𝗮𝗻𝗸 𝗠𝗼𝗻𝗲𝘆 𝗠𝗮𝗿𝗸𝗲𝘁 𝗦𝘂𝗿𝗽𝗮𝘀𝘀𝗲𝘀 𝗘𝗧𝗕 𝟱𝟬𝟬 𝗕𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝗧𝗿𝗮𝗻𝘀𝗮𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻𝘀

The Ethiopian Securities Exchange (ESX)  has announced a major milestone in the country’s financial sector with the interbank money market (IMM surpassing ETB 500 billion in transaction volume within just six months. This achievement highlights the growing momentum and liquidity in Ethiopia's financial markets. Launched to improve efficiency and transparency in interbank lending, the IMM platform has quickly gained traction among financial institutions, enabling them to manage short-term liquidity needs more effectively.

Read More

Source: ethiopianbusinessreview
@Etstocks
ዛሬ ሰኞ ጠዋት የአሜሪካ ግብይት ሲጀመር አክሲዮኖች (ስቶክ) እንደገና ወድቀዋል። ትራምፕ ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ ባለፈው አርብ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሎ የነበረው የስቶክ ገበያ ዛሬም ወድቋል::

ጠዋት  በኒውዮርክ የአክሲዮን ልውውጥ ቦታ ደወሉ ተደውሎ፣ ንግድ  በመካሄድ ላይ ሲሆን፣  በመጀመሪያዎቹ የጠዋቱ ጥቂት የንግድ ጊዜያት
🔴S&P 500 በ 3.4% ቀንሷል፣
🔴ዶው ጆንስ በ 3.1% ዝቅ ያለ ነው፣
🔴በተጨማሪም ናስዳክ በ 4.1% ወድቋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የንግድ ጦርነታቸውን እንደማይተዉ በመግለጽ፣ የአለም የኢኮኖሚ ውድቀት ስጋትን አጠናክረዋል።
Equity and Fixed-Income Securities Research Officer Job.pdf
712.8 KB
Vacancy announcement

Vacancy announcement by CBE Capital S.C for the job of Equity and Fixed-Income securities offer.

Check the detail of the vacancy on the attached document above👆.
በቴሌ ብር በቀን 7 ቢሊየን ብር እየተነቀሳቀሰ ነው


ቴሌ ብር ለኢትዮጵያ ዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ፡፡


ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ እንዳሉት÷ቴሌ ብር በደንበኞች ቁጥር ብዛትም ሆነ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ነው፡፡

እንደ ኤፍ ኤም ሲ ዘገባ አሁን ላይ በቴሌ ብር በቀን 7 ቢሊየን ብር እንደሚንቀሳቀስ ገልጸው ይህም ለዲጂታል ኦኮኖሚ ግንባታ ሚናው ጉልህ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ቴሌ ብር አዳዲስ መተግበሪያዎችን እና አሰራሮችን በመፍጠር ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ቴሌ ብር ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥም ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ነው የገለጹት፡፡


#Etstocks
ስኬት ባንክ በራሱ ለመቀጠል የሚያስችል የፋይናንስ አቅም እንዳለው አስታወቀ

በቅርቡ ከተቋቋሙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አንዱ የሆነው ስኬት ባንክ ከሌሎች ባንኮች ጋር ሳይዋሃድ ሪሱን ችሎ ለመቀጠል የሚያስችል የፋይናንስ አቅም እንዳለው አስታውቋል።

ባንኩ የ2016 በጀት ዓመት ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡንና የተከፈለ ካፒታሉ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ዳምጤ አለማየሁ ገልጸዋል።

ባንኩ ከ600,000 በላይ ደንበኞችና በፍጥነት እየሰፋ የሚሄድ የቅርንጫፍ አውታረ መረብ ያለው ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ዘርፉን ለማጠናከር ውህደትን እያበረታታ ቢሆንም ስኬት ባንክ ዝቅተኛውን የ5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል መስፈርት ቀድሞውኑ አልፏል።

በተጨማሪም ስኬት ባንክ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የብድር አመልካቾችን የስነ ልቦና ፕሮፋይል በመገምገም የብድር ብቁነትን የሚወስን አዲስ ሳይኮሜትሪክ ሞዴል ይፋ አድርጓል።

ይህ ተነሳሽነት ዋስትና የሌላቸውን አነስተኛ የንግድ ሥራ ባለቤቶችን ለመደገፍ ያለመ ሲሆን ከሀገሪቱ "ኢትዮጵያ ታምርት" እንቅስቃሴ ጋር የሚጣጣም ነው ብሏል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መምጣት ለባንካቸው ዕድገት ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
የብሄራዊ ባንክ አዲሱ መመሪያ

ብሔራዊ ባንክ፣ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ቅርንጫፎችን መክፈት የሚፈልጉ ባንኮች ፍቃድ ለማግኘት እንዲያሟሉ የሚጠበቅባቸውን ልዩ ዝቅተኛ መሥፈርቶች የያዘ መመሪያ ሊያወጣ እንደሆነ ሪፖርተር ዘግቧል።

በረቂቅ መመሪያው ከሚካተቱት መሥፈርቶች መካከል፣ ማናቸውም ባንክ የፍቃድ ጥያቄውን ካቀረበበት ቀን አስቀድሞ በነበረው ዓመት ውስጥ ያለው አጠቃላይ ሃብት በዚያው ዓመት ከተመዘገበው አጠቃላይ የባንክ ዘርፍ ሀብት በትንሹ ሁለት በመቶ ድርሻ ሊኖረው ይገባል የሚለው እንደሚገኝበት ዘገባው ጠቅሷል።

በትንሹ 65 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብት መያዝ፣ ሥጋታቸው ለሚያመዝን ብድሮች የተያዘ መጠባበቂያ ካፒታል ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው 8 በመቶ ዝቅተኛ መሥፈርት የ2 በመቶ ብልጫ ያለው እንዲሆን፣ የባንኩ የገንዘብና የገንዘብ አከል ይዞታ ምጣኔ ማመልከቻውን ካስገባበት ጊዜ በፊት ለነበሩ ሦስት ወራት በብሔራዊ ባንክ ከተቀመጠው ዝቅተኛ መሥፈርት በ3 በመቶ ብልጫ ያለው መኾን እንደሚገባውም በመስፈርትነት እንደተካተቱ ዘገባው አመልክቷል።
================
East Africa Launches First Regional Stock Market Index – The EAE 20 Share Index
by
StockMarket.et 
April 12, 2025

east african stock exchange

The East African Securities Exchanges Association (EASEA) has launched a new tool called the EAE 20 Share Index to help track the performance of top companies listed on stock markets in East Africa.

This is the first regional index of its kind. It brings together the 20 biggest and most successful companies from stock exchanges in Kenya, Tanzania, Uganda, and Rwanda. These companies come from different industries, like banking, telecom, manufacturing, and consumer goods. Together, they represent over 85% of the total value of East Africa’s stock markets.


Source- stockmarket
@etstocks
EAE 20 Share Index is a market capitalization-weighted index, comprising a cross-section of the top 20 listed public companies from multiple sectors across Nairobi, Tanzania, Uganda and Rwanda stock exchanges. Collectively, these listed companies represent over 85% of the region’s equity market universe.

The companies included in the Index are:

1.  Safaricom Plc
2.  KCB Group Plc
3.  Equity Group Holdings Plc
4.  The Co-operative Bank of Kenya Limited
5.  Absa Bank Kenya Plc
6.  CRDB Bank Plc
7.  NMB Bank Plc
8.  Tanzania Breweries Limited
9.  Tanga Cement Company Limited
10.  Tanzania Cigarette Corporation
11.  Bralirwa Limited
12.  BK Group Plc
13.  I&M Bank (Rwanda) Plc
14.  Cimerwa Plc
15.  MTN Rwandacell Plc
16.  MTN Uganda Limited
17.  Stanbic Uganda Holdings
18.  Bank of Baroda (Uganda)
19.  Airtel Uganda Limited
20.  Quality Chemical Industries Limited.
To qualify for inclusion in the Index, companies must meet criterias.
𝗡𝗕𝗘 𝘁𝗼 𝗜𝗻𝗷𝗲𝗰𝘁 𝗨𝗦𝗗𝟳𝟬 𝗠𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝗨𝗽𝗰𝗼𝗺𝗶𝗻𝗴 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗔𝘂𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻


In a continued effort to steer the foreign exchange market toward greater transparency and efficiency, the National Bank of Ethiopia (NBE) has announced it will conduct its fourth foreign currency auction tomorrow, April 17, 2025, offering a total of $70 million to participating banks.

This move aligns with NBE’s recent policy shift to a more market-oriented foreign exchange system, aimed at easing chronic forex shortages, closing the gap between official and parallel market rates, and improving external sector stability.

The bi-weekly auctions are part of a broader monetary reform agenda launched in recent months to support price stability, encourage export competitiveness, and attract remittances through formal channels. Commercial banks are invited to submit their bids in accordance with NBE’s updated auction guidelines, which prioritize transparency and fair market pricing.

Source - EBR
@Etstocks
“የመምህራን የኅብረት ሥራ ባንክ” በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ሊጀምር እንደሚችል ተስፋ እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ተናገረዋል።

የኑሮ ውድነት የበረታባቸው የኢትዮጵያ አስተማሪዎችን ለመርዳት ይቋቋማል የተባለው “የመምህራን የኅብረት ሥራ ባንክ” በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ሊጀምር እንደሚችል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ፍንጭ ሰጡ።

መንግሥት ለአስተማሪዎች ለቤት መሥሪያ የሚሆን መሬት ቢያቀርብ የሚቋቋመው ባንክ በአነስተኛ ወለድ ብድር የሚሰጥ ይሆናል።

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ባንኩ በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ሊጀምር እደሚችል ተስፋቸውን የገለጹት ትላንት ማክሰኞ የትምህርት ሚኒስቴርን የ2017 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

"""""""""""***""""""""""
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@etstocks

ፌስቡክ ገጽ: https://fb.me/etstocks

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@etstocks

ኤክስ: https://x.com/etstocks1
NBE Foreign Exchange Auction: Weighted Average Rate at 131.4961 Birr per USD

The National Bank of Ethiopia (NBE) today announced the results of its latest Foreign Exchange Auction.

According to the NBE's official announcement, the weighted average rate of all successful bids in the auction was Birr 131.4961 per US Dollar.

The auction saw a total of 26 banks participate, submitting demands for foreign exchange allocations. Notably, the NBE reported that 96 percent of the banks' foreign exchange demand/request was successfully met through the auction, with a total allocation of USD 70 million.

The National Bank of Ethiopia also indicated its schedule for future foreign exchange auctions. The next Foreign Exchange Auction is planned to be held in two weeks. An announcement regarding the specific date and time of this upcoming auction will be made public prior to the auction date.