ET Securities
647 subscribers
570 photos
7 videos
26 files
286 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
‎እንኳን ለ 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳቹ።

ET Securities
ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ዋጋን በማጭበርበር ተከሰሱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን በቅርበት መከታተል እንደሚያስፈልግ ገልጾ፣ ባለሙያዎች ባንኮች ያልተገባ ግምታዊ የውጭ ምንዛሪ ግዥ እንደሚፈጽሙ በመግለጽ ይህም በግዥና መሸጫ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት አባብሶታል።

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ​​ኮሚቴ (MPC) በቅርቡ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን ለመቆጣጠር ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት እና የተለካ ክትትል በገንዘብ ፍሰት ምክንያት በተዛማጅ የሚመጡትን ያልተፈለገ የገንዘብ ፖሊሲ ​ መላላት ያስወግዳል።

ተጨማሪ ያንብቡ

ካፒታል ጋዜጣ
@Etstocks
ET Securities
Photo
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ከባንክ ፕሬዝደንቶች ጋር መወያየቱን ገለፀ።
የውይይቱን ውጤት፣ አሉ ያሏቸውን ብዥታዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከማስተካከል አንፃር የማእከላዊ ባንኩ ገዥ አቶ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ያነሷቸው አበይት ነጥቦች
– በውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ረገድ በህብረተሰቡ በነጋዴ እንዲሁም ባንኮች ረገድ አልፎ አልፎ ብዥታ መኖሩን ባንኩ ተገንዝቧል።

–የባንኩ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ የለውጥ ትግበራ ከተጀመረበት ሀምሌ 2016 አንስቶ በ200 በመቶ ጨምሯል፤

–ይሄም በበጀት አመቱ መጨረሻ ይደረስበታል ተብሎ ከተቀመጠው እቅድ አንፃር ያለፈ ነው።

–ዛሬ ከባንክ መሪዎች ጋር በነበረው ውይይት በአፈፃፀም የሚታዩ ችግሮች እንዲታረሙ፣ የውጭ ምንዛሬ መመሪያ በጥብቅ እንዲተገበር  ብሄራዊ ባንክ አዟል።

–በተጨማሪ ባንኮች ለውጭ ምንዛሬ ግብይት የሚያስከፍሉት ኮሚሽን እና የአገልግሎት ክፍያ ተመጣጣኝ እንዲያደርጉ ታዘዋል።

–ብሄራዊ ባንኩ የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ቢያንስ እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ በየ 15 ቀኑ የውጭ ምንዛሬ ለባንኮች በጨረታ ይሸጣል።

–ባንኩ ቴክኖሎጂ እና አጋር ተቋማትን በመተቀም ጭምር በህገወጦች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ገዥው የጠቀሱት

–በተለይ ከባንክ ውጭ ያሉ ሀዋላ የሚሰሩ፣ ገንዘብ ወደ ውጭ የሚያሸሹ እና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር/ላውንደሪ የሚያረጉ ላይ ነው ማስጠንቀቂያ የተሰጠው

–የሀዋላ ኩባንያዎችም የባንኩን ህግ አክብረው እንዲሰሩ ነው ማሳሰቢያ የተሰጠው

ወደዚህ እንዴት ተደረሰ

የብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገው ግምገማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስቦ ነበር። ከሳምንታት በፊት ባንኩ 60 ሚሊየን ዶላር ለባንኮች ለመሸጥ ባወጣው ጨረታ ለአንድ ዶላር በአማካኝ 135 ብር ከ62 ሳንቲም ቀርቦ ነበር።
ይሄም በባንኮች ከሚሸጥበት ዋጋ በ10 ብር ገደማ የጨመረ በመሆኑ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። (የኮሚቴውን ውሳኔ ተከተወሎ በጉዳዩ ላይ ባሳለፍነው ረቡዕ መጋቢት 17/March 26 ቀን በቅዳሜ ገበያ የሬድዮ ቆይታ ሰፋ ያለ ሃሳብ ያቀረብን በመሆኑ ከማህበራዊ ገፆቻችን ውይይቱን ማድመጥ ይቻላል)

–ባንኮች የግምታዊ ገብይት ውስጥ መግባት፣ የአገልግሎት ክፍያን የማናር፣ የውጭ ምንዛሬውን ሌላ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ እና ሌሎች መላ ምቶች ለምንዛሬ መጠን መናር በባለሞያዎች በምክንያትነት የሚጠቀሱ ናቸው።

–በህገወጥ የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር ከ 150 ብር በላይ እንደሚመነዘር ነው ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች ለቅዳሜ ገበያ የገለፁት።

ማስታወሻ፥ በዚህ አበይት የወቅቱ ኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ በረቡዕ መጋቢት 24 የሬድዮ ጥንቅራችን ሰፋ ያለ ሃሳብ ይዘን የምንቀርብ በመሆኑ ከወዲሁ እንዲከታተሉን እንጋብዛለን።

ቅዳሜገበያ
ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ131.71 ብር ተመንዝሯል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (ብሔራዊ ባንክ) ዛሬ የተካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አደረገ። በባንኩ መረጃ መሰረት፣ ለተሳካላቸው ተጫራቾች የተመዘገበው አማካይ የምንዛሪ ዋጋ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ131.7095 ብር ሆኗል።

በጨረታው ሂደት በአጠቃላይ 12 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ተመድቦላቸዋል። የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትንና ፍላጎትን ለማስተዳደር በየጊዜው ጨረታዎችን ሲያካሂድ የቆየው ብሔራዊ ባንክ፣ ቀጣዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚካሄድ አረጋግጧል። ትክክለኛው ቀን እና ሰዓት ከዝግጅቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ይገለጻል።
Licensing_&_Renewal_of_Banking_Business_Draft_Directive.pdf
640.9 KB
የባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017 እና የብሔራዊ ባንክ  አዋጅ ቁ 1359/2017 መሠረት ብሔራዊ ባንክ የባንኮች ፈቃድ አሰጣጥ እና ዕድሳት ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል።

መመሪያው ስለ ውጪ ባንኮች...

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ባንኮች አምስት ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ሟሟላት እንደሚኖርባቸው፤

ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የወንጀል እና የታክስ ማጣራትን ጨምሮ ጥብቅ ምርምራ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው ፤

የውጭ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ ለማስቀመጥ እና ለመጠቀም እንደሚገደዱ ፤

ክፍያን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ለምርመራ 200 ሺህ፣ ለፈቃድ 400 ሺህ እና ለእድሳት 400 ሺህ ብር መክፈል እንዳለባቸው ፤

በባንኩ ዘርፍ የውጭ ሀገራት ተሳትፎን፡ የውጭ ባንክ ተቀጥላ፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ እና የእንደራሴ ቢሮ ብሎ ይከፍላቸዋል።

ረቂቅ መመሪያው ከዚህ ከላይ ተያይዟል
ኢትዮጵያ በትራምፕ 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባታል!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ የታሪፍ እርምጃ ወሰዱ።

ረቡዕ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ነው፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

ለምሳሌ፡- ቻይና 67% ታሪፍ አሜሪካንን የምታስከፍል ሲሆን ትራምፕ በአዲሱ ታሪፍ 34% ያስከፍላሉ። ካምቦዲያ 97% ታሪፍ አሜሪካንን ታስከፍላለች አሜሪካ አሁን 49% የምታስከፍል ይሆናል።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ በርካታ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ታውቋል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአሜሪካ የአክሲዮን ገበያ ቅናሽ አሳየ

#Ethiopia | ዛሬ የሚጀምረው የትራምፕ የ10 በመቶ ዓለም አቀፍ ቀረጥ ዓለም አቀፉ የአክሲዮን ገበያ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ አስከትሏል።

ከሌሎች ሀገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ 10 በመቶውን ቀረጥ በምትሰበስበው አሜሪካም የትራምፕ የቀረጥ እርምጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳረፉ ነው የተሰማው።

የሀገሪቱ ትላልቅ የአክሲዮን ገበያዎች በአማካይ 5 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ ማሳየታቸውን ወልስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

ይህም በፈረንጆቹ 2020 በኮቪድ19 ወረርሽኝ ከተመዘገበው የአክሲዮን ገበያ መቀዛቀዝ በኋላ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

ሌሊቱን በተዘጋው የአክሲዮን ገበያ ድርሻ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ባደረሰው አዲሱ ቀረጥ አውስትራሊያ፣ ብሪታንያ፣ ኮሎምቢያ፣ አርጀንቲና፣ ግብጽ እና ሳዑዲ አረቢያ የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሽ ሀገራት ሆነዋል።

ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ዕቅዱን ይፋ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ ዓለም ላይ የሸቀጦች እና የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱም ነው የተነገረው።

በርካታ ሀገራት የገበያ አማራጭ እያፈላለጉ ሲሆን፥ አንዳንድ የብሪታንያ ምግብ አምራች ኩባንያዎች ከወዲሁ ከሌሎች ሀገራት ጋር ምርታቸውን ማቅረብ በሚችሉበት አግባብ ላይ ንግግር መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ገቢዎች እና የድንበር ቁጥጥር ባለስልጣንም በወደብ፣ ድንበር እና አውሮፕላን ማረፊያዎች የደረሱ ሸቀጦች ላይ አዲሱን የ10 በመቶ ቀረጥ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ወደ አሜሪካ መንገድ ከጀመሩ በኋላ በተዋወቀው ቀረጥ ለሚከፍሉ ኩባንያዎችም የ51 ቀናት የቀረጥ ክፍያ መክፈያና መግቢያ ሰነድ ማሟያ ጊዜ መስጠቱንም ነው የገለጸው።

በአዲሱ የትራምፕ ውሳኔ መሰረት ቻይና 34 በመቶ ቀረጥ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ምርቶች 20 በመቶ ቀረጥ በመክፈል ቀዳሚዎቹ ይሆናሉ።

ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ከፍተኛውን ቀረጥ እንደምትጥል የገለጸች ሲሆን፥ የአውሮፓ ህብረትም ተመጣጣኝ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።
"መንግስት አንድ ትሪሊየን ብር እዳ አለበት" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት፣ በአጠቃላይ ካለው የብድር ክምችት አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ የመንግሥት መሆኑን አስታውቋል ።

የባንኩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የባንኩ የብድር ክምችት 1.393 ትሪሊዮን ብር መድረሱንና ከዚህ መጠን ውስጥ 74.4 በመቶ ወይም አንድ ትሪሊዮን ብር የመንግሥት ዕዳ መሆኑን ገልጸዋል።

የባንኩ ጠቅላላ የብድርና ቦንድ ክምችት መጠን ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ የተሻገረ ሲሆን፣ ከዚህም ላይ የግል ተበዳሪዎች ድርሻ ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተጠቅሷል።

ከተገለጸው አጠቃላይ የብድር ክምችት መጠን በቦንድ የተወሰደ ብድር 66.7 በመቶ ያህሉን በመሸፈን የአብላጫውን ድርሻ ሲወስድ፣ 27.62 ቢሊዮን ብር የተጠራቀመ ወለድ መሆኑም ተገልጿል።


ባንኩ ከነበረው አጠቃላይ ብድር ለግል ዘርፉ የተሰጠው ብድር ስምንት በመቶ ብቻ ነበር። የተቀረው 92 በመቶ በመንግሥት የተወሰደ ነው። መንግሥት ከወሰደው ብድር 98 በመቶ የሚሆነው የተሰጠው በስምንት በመቶ የወለድ ምጣኔ ሲሆን፣ የተቀረው ሁለት በመቶ ብቻ በ11 እና በ12 በመቶ የወለድ ምጣኔ የተሰጠ ብድር ነው፤›› ብለዋል።


እንደሪፖርተር ዘገባ መንግሥት በወሰደው ብድር ላይ 173 ቢሊዮን ብር ወለድ መጠራቀሙንና መንግሥት ግን ብድሩን ባያቃልልም፣ ንግድ ባንክ ወለዱን መሰብሰቡ ታሳቢ ተደርጎ በየዓመቱ ግብር ሲከፍል መቆየቱ ታውቋል ።
𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮’𝘀 𝗜𝗻𝘁𝗲𝗿𝗯𝗮𝗻𝗸 𝗠𝗼𝗻𝗲𝘆 𝗠𝗮𝗿𝗸𝗲𝘁 𝗦𝘂𝗿𝗽𝗮𝘀𝘀𝗲𝘀 𝗘𝗧𝗕 𝟱𝟬𝟬 𝗕𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻 𝗶𝗻 𝗧𝗿𝗮𝗻𝘀𝗮𝗰𝘁𝗶𝗼𝗻𝘀

The Ethiopian Securities Exchange (ESX)  has announced a major milestone in the country’s financial sector with the interbank money market (IMM surpassing ETB 500 billion in transaction volume within just six months. This achievement highlights the growing momentum and liquidity in Ethiopia's financial markets. Launched to improve efficiency and transparency in interbank lending, the IMM platform has quickly gained traction among financial institutions, enabling them to manage short-term liquidity needs more effectively.

Read More

Source: ethiopianbusinessreview
@Etstocks