ET Securities
648 subscribers
572 photos
7 videos
26 files
287 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
" የሂጅራ ባንክ አጠቅላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል " - የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል

ሂጅራ ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ታህሳስ 13 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል የ2023/2024 የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች ያቀረቡ ሲሆን ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 100 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ማጠናቀቁን ያበሰሩ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ334.78%  ብልጫ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ከምን ጊዜውም በላይ የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፍ ብዛቱን ወደ 100+ ከፍ ማድረጉን ገልጸው ይህም 40% እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል።

ባንኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የደንበኞች ብዛቱን በማሳደግ ከ700,000 በላይ ደንበኞችን ማፍራቱንም ገልጸዋል።

በዚሁ ረገድ ባንኩ ስኬታማ አፈፃፀም በማስመዝገብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ለባንኩ ባለአክሲዮኖች አብስረዋል።

ባንኩ ከፋይናንሺያል አፈፃፀም በተጨማሪ  የማህበረሳችንን እሴቶች ማእከል ያደረጉ ምርትና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ባንክ የመሆን ራዕዩን አጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል::

#HijraBank
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መዝጋት ዕቅድ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ700 ሚሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ የፋይናንሺያል ሴክተር ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ቅርንጫፎችን ከመዝጋቱ በፊት የማህበራዊ ስጋት ግምገማ ያካሂዳል። መልሶ ማዋቀሩ ቅልጥፍናን ለማሳደግ እና ከተማን ያማከለ ብድርን ለመፍታት ያለመ ቢሆንም ተቺዎች የገጠር የባንክ ተደራሽነትን ሊያባብስ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።

ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ፣ ንግድ ባንክ የስንብት ፓኬጆችን፣ የሥራ ሽግግር ፕሮግራሞችን እና አማራጭ የአገልግሎት ሞዴሎችን አቅዷል። የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ሜሪየም ሳሊም የፕሮጀክቱን የበለጠ ተቋቋሚ እና አካታች የፋይናንሺያል ስርዓት ለመገንባት ያለውን ግብ አፅንዖት ሰጥተዋል። የዘመናዊነት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ ቅነሳው ለገጠሩ ማህበረሰብ ስጋት ይፈጥራል።

Linkupbusiness
@Etstocks
ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ በአይፒኦ ወቅት 269,433 አክሲዮኖችን እያንዳንዳቸው በ750 ብር በመሸጥ የአክሲዮን ባለቤቶቹም ብዛት ከ7 ወደ 1,799 ከፍ ብሏል። በሐምሌ፣ 2016 የጀመረውይህ የመጀመሪያው የህዝብ አቅርቦት(IPO) 10 ሚሊዮን አክሲዮኖችን ለመሸጥ ያለመ ነበር።

በሪል እስቴት (80 በመቶው የፕሮጀክቶች) እና የመንግስት ኮንትራቶች (20%) ልዩ አቅም ያለው ፍሊንትስቶን እንደ የዋጋ ግሽበት እና የዋጋ ንረት ያሉ የሴክተሩን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ በቦጎሲያን፣ አዋሬ እና ካዛንቺስ ውስጥ ፕሮጄክቶችን አጠናቆ አስረክቧል።

በ2016 በጀት አመት የ829.2 ሚሊየን ብር ገቢ፣ የተጣራ 25 ሚሊየን ብር እና አጠቃላይ የሀብት መጠን 2.1 ቢሊዮን ብርጽቭ
በማስዝገብ የ24 በመቶ እድገት አሳይቷል። 18 ፕሮጀክቶችን ተረክቦ በመካሄድ ላይ ያለው ፍሊንትስቶን በኢትዮጵያ የግንባታ እና የሪል ስቴት ዘርፎች የማይበገር ተጫዋች ሆኖ ቀጥሏል።

linkupbusiness
@Etstocks
አማራ ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ ሊያቋቋም መሆኑ ተሰማ!!

አማራ ባንክ የካፒታል ገበያና የኢንቨስትመንት ባንክ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ማቀዱን ካፒታል በዘገባው ገልጿል።

ባንኩ በፋይናንሺያል ኢንደስትሪ ውስጥ ካለው ወቅታዊ አካሄድ አንፃር የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ተጠቁሟል።

ባንኩ አሰራሩን እየለወጠ እና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ገልፀዋል፡፡

አክለውም ማህበራዊ ልማት ፕሮጀክቶችን እየደገፍን ግቦቻችንን ለማሳካት ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል፡፡

የካፒታል ማርኬት እና ኢንቨስትመንት ባንኪንግን ለመጀመር ማቀዱ በኢትዮጵያ ባንክ ዘርፍ ተጨማሪ ሚና እንዲሚኖረው እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
Abay Bank’s profit margin erosion emerged when its net profit dropped 3.2pc to 1.5 billion Br, accompanied by a 22pc fall in earnings per share (EPS), down from 360 Br, though it still is higher than many private banks.

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
የኢንሹራንስ ምርት እና አገልግሎት ሻጭ ለመሆን  ጥቂት ቁልፍ ነገሮችን ማስታወስ ያስፈልግዎታል።

ኢንሹራንስ ለመሸጥ ምን ማድረግ እንደሚችሉ አንዳንድ ምክሮች እነሆ፡-

1. የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪን በደንብ ይረዱ
* የተለያዩ የኢንሹራንስ አይነቶችን ይወቁ: የህይወት ኢንሹራንስ፣ የጤና ኢንሹራንስ፣ የመኪና ኢንሹራንስ፣ የንብረት ኢንሹራንስ እና ሌሎችም አይነቶች ምን እንደሚሸፍኑ እና ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ በደንብ ይረዱ።
* የኢንሹራንስ ውሎችን ይረዱ: ፖሊሲዎች ምን እንደሚሸፍኑ፣ ምን እንደማይሸፍኑ እና ምን ዓይነት ቅናሾች እንዳሉ በደንብ ይረዱ።
* የኢንሹራንስ ደንቦችን ይወቁ: ኢንሹራንስን የሚቆጣጠሩትን ደንቦች እና ደንቦችን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።

2. ጠንካራ የደንበኛ ግንኙነት ይገንቡ
* ደንበኞችን ያዳምጡ: ደንበኞችዎ ምን እንደሚፈልጉ እና ምን እንደሚያስፈልጋቸው ለማወቅ ጊዜ ይወስዱ።
* የደንበኞችን ፍላጎት ይረዱ: ደንበኞችዎ ምን አይነት ኢንሹራንስ እንደሚያስፈልጋቸው ለመወሰን ይረዱ።
* የደንበኞችን ጥያቄዎች በትዕግስት ይመልሱ: ደንበኞችዎ ጥያቄ ሲጠይቁ በትዕግስት እና በግልፅ ይመልሱ።

3. የሽያጭ ክህሎቶችዎን ያሻሽሉ
* የሽያጭ ቴክኒኮችን ይማሩ: እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቅረብ እንደሚችሉ፣ እንቅፋቶችን እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ እና ሽያጭን እንዴት መዝጋት እንደሚችሉ ይማሩ።
* በራስ መተማመን ይኑርዎት: በምርትዎ ላይ እምነት ይኑርዎት እና ለደንበኞችዎ እሴት እንደሚሰጡ ያሳዩ።
* የሽያጭ ግቦችን ያወጡ እና ይከታተሉ: ግልጽ የሆኑ የሽያጭ ግቦችን ያወጡ እና እድገትዎን ይከታተሉ።

4. ኔትወርኪንግ ያድርጉ
* በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ሰዎችን ያውቁ: ሌሎች የኢንሹራንስ ወኪሎች፣ ብሮከሮች እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን ያግኙ።
* የንግድ ክስተቶች ላይ ይሳተፉ: የኢንዱስትሪ ኮንፈረንሶች፣ ሴሚናሮች እና ሌሎች የኔትወርኪንግ ዝግጅቶች ላይ ይሳተፉ።
* የማህበራዊ ሚዲያን ይጠቀሙ: ሊንክዲን እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን በመጠቀም ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ይገናኙ።

5. የደንበኛ አገልግሎትዎን ያሻሽሉ

* ከደንበኞችዎ ጋር በመደበኛነት ይገናኙ: ደንበኞችዎ እንዴት እንደሚሰሩ ለማየት በመደበኛነት ያነጋግሩዋቸው።
* ለደንበኞችዎ ተደራሽ ይሁኑ: ደንበኞችዎ ጥያቄ ሲኖራቸው ወይም ችግር ሲያጋጥማቸው በፍጥነት እንዲደርሱባቸው ያድርጉ።
* ለደንበኞችዎ ተጨማሪ እሴት ይስጡ: ለደንበኞችዎ ጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ምክሮችን እና መረጃዎችን ይስጡ።
በተጨማሪም፣ እነዚህ ጥቂት ጠቃሚ ምክሮች ሊረዱዎት ይችላሉ፡-
* የግል ብራንድዎን ይገንቡ: በኢንዱስትሪው ውስጥ እንደ ባለሙያ እንዲታወቁ ያድርጉ።
* የደንበኛ ምስክርነቶችን ይሰብስቡ: ደስተኛ የሆኑ ደንበኞችዎ ስለእርስዎ ምን እንደሚሉ ለማሳየት የደንበኛ ምስክርነቶችን ይጠቀሙ።
* የማያቋምት ትምህርት ይኑርዎት: ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ በፍጥነት እየተለወጠ ነው፣ ስለዚህ እራስዎን ለማዘመን ጊዜ ይወስዱ።
ማስታወሻ: ኢንሹራንስ መሸጥ በጣም ውድድር የሚደረግበት ኢንዱስትሪ ነው። ስኬታማ ለመሆን ጠንካራ ሥራ፣ ቁርጠኝነት እና ትዕግስት ያስፈልግዎታል።


Financial Ethiopia
@Etstocks
ዘም ዘም ባንክ ሸሪዓን መሰረት ያደረገ "አንሳር" የተባለ የዲጅታል ፋይናንስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ።

ዘም ዘም ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውንና በሙሉ ሸሪዓን መሰረት ያደረገ "አንሳር" የተባለ የዲጅታል ፋይናንስ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ይህንን መተግበሪያ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ላይ አስመርቋል።

በዚህ ወቅት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ መሊካ በድሪ በሀገራችን ከተለመደው የፋይናንስ አሰጣጥ ተገልለው ለቆዮ በተለይም በአነስተኛ እና መካከለኛ የስራ ዘርፍ ለተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ለሴቶች መፍትሔ እንሚሆን ገልጸዋል።

"አንሳር  የፋይናንስ ተቋማት ዋስትና ሳያስፈልጋቸው ብድር የማግኘት ብቻ ሳይሆን ብድር የሚሰጥበትን ጊዜ ይቀንሳል ነው የተባለው።

አንሳር ሸሪአን መሰረት ያደረገ የፋይናንስ መርሆዎችን እና የዲጂታል ፈጠራ ኃይልን በመጠቀም ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እና እድሎችን በፍትሃዊነት እና በእኩልነት የሚያቀርብ ይሆናል ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የተናገሩት።

በክፊያ የፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ የጎለበተው አንሳር መተግበሪያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያካተተ እና አማራጭ ዳታን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው ተብሏል።

የክፍያ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀያት አብዱልመሊክ መተግበሪያው በኢትዮጵያ ያለውን የወደፊት ፍትሐዊነት እና የፋይናንሺያል አካታችነትን ከማረጋገጡም በላይ ከባንክ አገልግሎት ተገልለው የቆዩ ማህበረሰቦችን በቀላሉ ማገልገል እንደሚቻል ማሳያም ጭምር እንደሆነ በምርቃቱ ወቅት አብራርተዋል።
ግሎባል ባንክ ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2016 በጀት አመት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ አስታውቀዋል።

ከተገኘው ገቢም የባንኩ ትርፍ ታክስ ፤ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገልፀዋል።

ይህም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅሰዋል።

ባንኩ የተቀማጭ ሂሳቡን ወደ 4 ቢሊዮን ብር በማሳደግ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ ወደ 18.22 ቢሊዮን መድረሱን ተናግረዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉን 2.48 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ሀብት ደግሞ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አንስተዋል።

ግሎባል ባንክ የትርፍ ድርሻውን በ14 በመቶ በማሳደግ ለባለአክሲዮኖች 33.2 በመቶ የትርፍ ድርሻ መክፈሉን አስታውቋል።
ባንኮች የገዙት የመንግስት የብድር ሰነድ!!

የሀገሪቱ ንግድ ባንኮች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ 110 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ወጪ በማድረግ በብሔራዊ ባንክ የጸደቀውን የአምስት ዓመታት የመንግስት የብድር ሰነድ መግዛታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

ለትርፍ የተቋቋሙት የንግድ ባንኮቹ ይህንን ያህል መጠን ያለው የመንግስት ብድር ሰነድ (በእንግሊዝኛው ትሬዠሪ ቢል) የገዙት በፈረንጆቹ ኖቬምበር 2024 የመጣውን የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ድንጋጌን ተከትሎ ሲሆን መመሪያው ባንኮቹ ያበደሩትን ብድር 20 በመቶ የሚያክል መጠን ያለው ገንዘብን ለብድር ሰነዱ መግዣነት እንዲያውሉት ያዛል፡፡

ይህንን ተከሎም ባንኮቹ እስካለፈው ሴፕቴምበር 2024 ድረስ 109 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የሚደርስ የብድር ሰነድ መግዛታቸውን ነው የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት የሚያትተው፡፡

ይህ የብድር ሰነድ መንግስት ያለበትን የበጀት ጉድለቱን ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ መበደር ሳያስፈልገው የሚሞላበት አንዱ መላ ነው፡፡

በሌላም በኩል ይህ ሪፖርት እንደሚያሳየው የመንግስት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ብድር እስከሴፕቴምበር 30፣ 2024 ድረስ በ2 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡፡

ቅዳሜገበያ
NBE set to revise policy rate in early 2025

Early in the upcoming year, the National Bank of Ethiopia (NBE) is expected to revise the policy rate, commonly known as the National Bank Rate (NBR).

The initial policy rate, set at 15 percent, was established at the beginning of the fiscal year.

Read More

Source: capitalethiopia
@Etstocks
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ውስጥ አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መገኘት አስገዳጅ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ከዛሬ ታህሳስ 23 , 2017 ዓ.ም (Jan 1st 2025) ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ሆኗል።

በሌላ ተያያዥ መረጃ ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ " ፋይዳን ለባንክ አገልግሎት አስገዳጅነት " ትዕዛዝ ወደ ትግበራ መግባት ተከትሎ የተለያዩ ባንኮች የማርኬቲንግ እና ኮርፖሬት ህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ሀላፊዎች ያሳተፈ በጥምረት ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አሳውቆናል።

ከኃላፊዎች ጋር በነበረ ውይይት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ ፤ " የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ባንኮች በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን ልክ እንደ አንድ የባንክ አገልግሎት አጽንዖት ተሰጥቶት እንዲሰሩ " ሲሉ አሳስበዋል።
Oromia Bank shareholders’ patience appeared to have worn thin, while the Bank’s executives believe that the shift to technology and branch consolidation, combined with disciplined credit management, would help restore their confidence. Whether this recalibration is enough to propel Oromia Bank back to robust profitability remains open. But with a clear priority on cost control, digital expansion, and prudent lending, executives hope to steer the Bank toward a steadier path, aligning its founding ideals with the realities of a modern, increasingly tech-savvy market.

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ትርፍ 40 በመቶ ቀነሰ!!

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በተጠናቀቀው የ2016 ሒሳብ ዓመት 1.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ  ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ከቀዳሚ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በአንድ ቢሊዮን ብር ዝቅ ያለ መሆኑ አመታዊ ሪፖርቱ ያሳያል።

ባንኩ ለትርፉ መቀነስ ዓለም አቀፋዊና አገራዊ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝን እና የአገር ውስጥ የፀጥታ ችግር እንደ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ 903 ሚሊዮን አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 117.1 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ 

አጠቃላይ የባንኩ የብድር ክምችት መጠን 117.15 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የ19.03 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት አንፃር ሲታይ 7.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ 258.3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘ ሲሆን ይህም አፈጻጸሙ ከቀዳሚው ዓመት ቅናሽ ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይም የተከፈለ ካፒታሉን 11.16 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ ሀብት መጠን 139.7 ቢሊዮን ብር ሆኗል፡፡ 
በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ከቀናት በኋላ በነባሩም ሆነ አዳዲስ ውለታ የሚገቡትን ተበዳሪዎች የብድር ወለድ ምጣኔን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰማ‼️

ይህም #የብድር_የወለድ ምጣኔው እስከ 20 እና 22 በመቶ ይደርሳል እንደማለት ነው፡፡

ከዓመታት በፊት የነበረውን የገንዘብ የመግዛት አቅም እና የኢኮኖሚውን ሁኔታ እንዲሁም የገቢ መጠናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከባንክ በመበደር ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ሆኑ ቤት የገዙ ተበዳሪዎች በተበደሩት ወለድ ላይ ከ3 እስከ 5 በመቶ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

አንድ ተበዳሪ ከዓመታት በፊት ከባንክ በ17 በመቶ ወለድ ተበድሮ ከነበረ በአሁኑ ወቅት ባንኮች ወለዱን 5 በመቶ በመጨመር 22 በመቶ ሊያደርሱት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ታማኝ ምንጮች ነግረውናል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገበያው እራሱን እያረጋጋ ነበር ይሁንና ጥቂት ቁጥር ባላቸው #ባንኮች ምክንያት ተመልሶ ዋጋ ሊንር ነው የሚሉት ምንጫችን በተለይም ከውጭ እቃ ለማስገባት ከባንኮች ብድር አስቀድመው ውል ገብተው የተበደሩትም ሆኑ አዳዲስ ተበዳሪዎች ከፍተኛ በሆነው የብድር የወለድ ጭማሪ ምክንያት የሚስገቡት እቃ እጅግ ይንራል ይህም መልሶ ሸማቹ ላይ የሚወደቅ ይሆናል ብለዋል፡፡

አንድ ተበዳሪ ከባንክ ጋር የብድር ኮንትራት ሲገባ ባንኩ ወለድ እንዲጨምር ይሁንታውን ይሰጣል፡፡

ባንኮች ብድር ስለሚሰጡ እና በኮንትራቱ መሰረት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ በመመልከት የወለድ ምጣኔውን እንዲጨምሩ ስምምነት ተደረገ ማለት ግን እንደፈለጉት ህግንም እንዲተላለፉም ሆነ ሀገርን ወደ አደገኛ የኢኮኖሚ ችግር የማስገባት መብት አላቸው ማለት አይደለም ተብሏል፡፡

አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ1 በመቶ እስከ 2 በመቶ የብድር የወለድ ምጣኔን ሊያስጨምር የሚችል መሆኑን ማየት ይቻላል ይሁንና ከ3 - 5 በመቶ ግን በፍጹም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሊሸከመው የሚችል ዓይነት አይደለም ሲሉ ምንጫችን ነግረውናል፡፡
#ሸገርኤፍም