ET Securities
661 subscribers
584 photos
7 videos
28 files
297 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ኦሮሚያ ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ ከ 68 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ኦሮሚያ ባንክ የተከፈለ ካፒታል 6.5 ቢሊየን ብር መድረሱን ያስታወቀ ሲሆን አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ ወደ 68 ቢሊዮን ብር ማደጉን በሪፖርቱ ገልጿል።

ዘንድሮ አለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች የባንኪንግ ዘርፉን በተለያየ መልኩ ቢፈትኑትም፣ ኦሮሚያ በንክ ይህን መቋቋም መቻሉን ነዉ በሪፖርቱ የገለፀዉ። ይህን ተከትሎ በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት ከወለድ ነፃ የባንክ ገቢ 56.4 ቢሊዮን ብር መድረጉን አመልከቷል ።

15ኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ያደረገው ባንኩ ኦሮዲጂታል የተሰኘ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ማፍራት መቻሉን አስታዉቋል።

በዚህም አጠቃላይ የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን ከባለፈው ተመሳሳይ የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ157 % እድገት አሳይቷል ብሏል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የሚፈቅደውን ታሪካዊ አዋጅ አፀደቀ።

Read more
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዋጅን አጸደቀ!!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  በመደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው የብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ሪፖርት ካቀረበ በኋላ  የውሳኔ ሀሳቡ ላይ ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ ተሰጥቷል።

ስለ ክሪፕቶ ከረንሲ ቁጥጥር ፣ የብድር ዋስትና ፣ ወንጀልን የማጣሪያ የጊዜ ገደብ እና ከመመሪያ ይልቅ ደንብ ቢሆን በሚል የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ አንስተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ የአዋጁን ጠቀሜታ አፅኖት ሰጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ የብሔራዊ ባንክን ዋና ስራ በቅደም ተከተል ያስቀመጠ መሆኑን ተናግረዋል ።

አክለውም የብሔራዊ ባንክ አደረጃጀት እና የአመራር ሁኔታ እንዲሁም ባንኩ ከመንግስት ጋር ያለውን ልዩነት በግልፅ ያሰፈር አዋጅ መሆኑን ጠቁመዋል።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ተግባር የዋጋ መረጋጋት እንዲኖር ማስቻል፣ የፋይናንስ ስርአቱን ጤናማ እንዲሆን ማድረግ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሆነ ገልፀዋል።

ረቂቁ አዋጅ ቁጥር 1359 /2017 በመሆን በሙሉ ድምጽ ጸደቋል፡፡
Siinqee Bank's shareholders voted to establish an investment bank as part of a wider plan to venture into the capital market ecosystem.

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ ዲጂታል አካዳሚ መጀመሩን በይፋ አብስሯል።

የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ "ESX Academy" የተሰኘውን የመማሪያ ፕላትፎርም ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም ከ FSD Ethiopia ጋር በመተባበር  የተሰራ ፕሮጀክት ነው።

መጪው ካፒታል ገበያ ሲጀመር ክፍተት ይሆናል ተብሎ የታሰበውን የፋይናንስ እውቀት ለመቅረፍ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ኢሰገ ገልጿል።

በኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ሰሚት ላይ አቶ ሚካኤል ሃብቴ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አካዳሚ እንጀምራለን ማለታቸው አይዘነጋም ነበር።

ፕላትፎርሙ የተለያዩ ኮርሶችን አንድላይ የያዘ ሲሆን ከነዚህም፡

1. ካፒታል ገበያ እንዴት ነው ሚሰራው
2. ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ
3. ሻሪያን ስላገናዘቡ ምርቶች
4. የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ላይ ስላለው ሚናና ያካትታል።

ኮርሶቹን ለመወሰድ esxacademy.com ላይ ገብተው መውሰድ ይችላሉ።
| YouTube | X | TikTok
አዲሱን የባንክ ስራ አዋጅ ከማብራሪያው ጋር እነሆ!!
ገዳ ባንክ ከታክስ በፊት 101 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተገለፀ!!

ገዳ ባንክ የባለ አክሲዮኖች ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤውን  ባካሄደበት ወቅት  በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 101 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

በ2016በጀት አመት ያገኘው ገቢ 790 ሚሊዮን ብር  ሲሆን ካለፈው አመት ጋር ሲነፃጸር የ609 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በ 2,88,174 ደንበኞች አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ 4 ቢሊዮን  መድረሱም ተጠቁሟል።

ካሉት ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ 42,930 መሆናቸውን ባንኩ አሳውቋል።

በበጀት አመቱ 2.9 ሚሊዮን ብር ብድር መስጠት መቻሉም ተገልጿል፡፡
ዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል

#Ethiopia  | ከብድሩ 90 በመቶው የንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጧል።

ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።

ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው፣ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው።

የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደኾነም ባንኩ ባሠራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።

https://t.me/etstocks
" የሂጅራ ባንክ አጠቅላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል " - የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል

ሂጅራ ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ታህሳስ 13 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል የ2023/2024 የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች ያቀረቡ ሲሆን ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 100 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ማጠናቀቁን ያበሰሩ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ334.78%  ብልጫ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ከምን ጊዜውም በላይ የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፍ ብዛቱን ወደ 100+ ከፍ ማድረጉን ገልጸው ይህም 40% እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል።

ባንኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የደንበኞች ብዛቱን በማሳደግ ከ700,000 በላይ ደንበኞችን ማፍራቱንም ገልጸዋል።

በዚሁ ረገድ ባንኩ ስኬታማ አፈፃፀም በማስመዝገብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ለባንኩ ባለአክሲዮኖች አብስረዋል።

ባንኩ ከፋይናንሺያል አፈፃፀም በተጨማሪ  የማህበረሳችንን እሴቶች ማእከል ያደረጉ ምርትና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ባንክ የመሆን ራዕዩን አጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል::

#HijraBank
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መዝጋት ዕቅድ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ700 ሚሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ የፋይናንሺያል ሴክተር ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ቅርንጫፎችን ከመዝጋቱ በፊት የማህበራዊ ስጋት ግምገማ ያካሂዳል። መልሶ ማዋቀሩ ቅልጥፍናን ለማሳደግ እና ከተማን ያማከለ ብድርን ለመፍታት ያለመ ቢሆንም ተቺዎች የገጠር የባንክ ተደራሽነትን ሊያባብስ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።

ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ፣ ንግድ ባንክ የስንብት ፓኬጆችን፣ የሥራ ሽግግር ፕሮግራሞችን እና አማራጭ የአገልግሎት ሞዴሎችን አቅዷል። የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ሜሪየም ሳሊም የፕሮጀክቱን የበለጠ ተቋቋሚ እና አካታች የፋይናንሺያል ስርዓት ለመገንባት ያለውን ግብ አፅንዖት ሰጥተዋል። የዘመናዊነት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ ቅነሳው ለገጠሩ ማህበረሰብ ስጋት ይፈጥራል።

Linkupbusiness
@Etstocks
ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ በአይፒኦ ወቅት 269,433 አክሲዮኖችን እያንዳንዳቸው በ750 ብር በመሸጥ የአክሲዮን ባለቤቶቹም ብዛት ከ7 ወደ 1,799 ከፍ ብሏል። በሐምሌ፣ 2016 የጀመረውይህ የመጀመሪያው የህዝብ አቅርቦት(IPO) 10 ሚሊዮን አክሲዮኖችን ለመሸጥ ያለመ ነበር።

በሪል እስቴት (80 በመቶው የፕሮጀክቶች) እና የመንግስት ኮንትራቶች (20%) ልዩ አቅም ያለው ፍሊንትስቶን እንደ የዋጋ ግሽበት እና የዋጋ ንረት ያሉ የሴክተሩን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ በቦጎሲያን፣ አዋሬ እና ካዛንቺስ ውስጥ ፕሮጄክቶችን አጠናቆ አስረክቧል።

በ2016 በጀት አመት የ829.2 ሚሊየን ብር ገቢ፣ የተጣራ 25 ሚሊየን ብር እና አጠቃላይ የሀብት መጠን 2.1 ቢሊዮን ብርጽቭ
በማስዝገብ የ24 በመቶ እድገት አሳይቷል። 18 ፕሮጀክቶችን ተረክቦ በመካሄድ ላይ ያለው ፍሊንትስቶን በኢትዮጵያ የግንባታ እና የሪል ስቴት ዘርፎች የማይበገር ተጫዋች ሆኖ ቀጥሏል።

linkupbusiness
@Etstocks