የውጭ ሀገራት ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅደው የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተገለፀ፡፡
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ከተወያየ በኃላ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በነገው መደበኛ ስብሰባ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ሰኔ 18 ቀን ፣ 2ዐ16 ዓ/ም ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራ ሲሆን ምክር ቤቱ፤ ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ሲጸድቅ የውጭ ባንኮች በሃገር ውስጥ ተቀጥላ ወይም ሰብሲዲያሪ ጽህፈት ቤታቸውን እንዲከፍቱ ከመፍቀዱ በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ባንኮችን ድርሻ መግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድም ነው፡፡
ከዚህም ባሻገር የውጭ ባንኮች ቅርንጫፎቻቸውን እንዲከፍቱ፣ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገራት ዜጎችም በባንኮቻቸው የሥራ እድልን ማግኘትና የቦርድ ሊቀመንበር አባላት እንዲሆኑ መንገዱን የሚያቀናላቸው ነው ይኸው ረቂቅ አዋጅ፡፡
መንግስትም የአዋጁን መጽደቅ ተከትሎ ለአምስት የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት ያስችለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ገበያ ለመሥራት ፍላጎት ካሳዩ የውጭ ባንኮች ውስጥ የኬንያው ኬሲቢ እንዲሁም ስታንዳርድ ባንኮች ይጠቀሳሉ፡፡

❤1
ኦሮሚያ ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ ከ 68 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ
ኦሮሚያ ባንክ የተከፈለ ካፒታል 6.5 ቢሊየን ብር መድረሱን ያስታወቀ ሲሆን አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ ወደ 68 ቢሊዮን ብር ማደጉን በሪፖርቱ ገልጿል።
ዘንድሮ አለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች የባንኪንግ ዘርፉን በተለያየ መልኩ ቢፈትኑትም፣ ኦሮሚያ በንክ ይህን መቋቋም መቻሉን ነዉ በሪፖርቱ የገለፀዉ። ይህን ተከትሎ በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት ከወለድ ነፃ የባንክ ገቢ 56.4 ቢሊዮን ብር መድረጉን አመልከቷል ።
15ኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ያደረገው ባንኩ ኦሮዲጂታል የተሰኘ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ማፍራት መቻሉን አስታዉቋል።
በዚህም አጠቃላይ የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን ከባለፈው ተመሳሳይ የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ157 % እድገት አሳይቷል ብሏል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዋጅን አጸደቀ!!
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርጓል።
ቋሚ ኮሚቴው የብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ሪፖርት ካቀረበ በኋላ የውሳኔ ሀሳቡ ላይ ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ ተሰጥቷል።
ስለ ክሪፕቶ ከረንሲ ቁጥጥር ፣ የብድር ዋስትና ፣ ወንጀልን የማጣሪያ የጊዜ ገደብ እና ከመመሪያ ይልቅ ደንብ ቢሆን በሚል የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ አንስተዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ የአዋጁን ጠቀሜታ አፅኖት ሰጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ የብሔራዊ ባንክን ዋና ስራ በቅደም ተከተል ያስቀመጠ መሆኑን ተናግረዋል ።
አክለውም የብሔራዊ ባንክ አደረጃጀት እና የአመራር ሁኔታ እንዲሁም ባንኩ ከመንግስት ጋር ያለውን ልዩነት በግልፅ ያሰፈር አዋጅ መሆኑን ጠቁመዋል።
የብሔራዊ ባንክ ዋና ተግባር የዋጋ መረጋጋት እንዲኖር ማስቻል፣ የፋይናንስ ስርአቱን ጤናማ እንዲሆን ማድረግ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሆነ ገልፀዋል።
ረቂቁ አዋጅ ቁጥር 1359 /2017 በመሆን በሙሉ ድምጽ ጸደቋል፡፡

👍1
የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ ዲጂታል አካዳሚ መጀመሩን በይፋ አብስሯል።
የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ "ESX Academy" የተሰኘውን የመማሪያ ፕላትፎርም ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም ከ FSD Ethiopia ጋር በመተባበር የተሰራ ፕሮጀክት ነው።
መጪው ካፒታል ገበያ ሲጀመር ክፍተት ይሆናል ተብሎ የታሰበውን የፋይናንስ እውቀት ለመቅረፍ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ኢሰገ ገልጿል።
በኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ሰሚት ላይ አቶ ሚካኤል ሃብቴ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አካዳሚ እንጀምራለን ማለታቸው አይዘነጋም ነበር።
ፕላትፎርሙ የተለያዩ ኮርሶችን አንድላይ የያዘ ሲሆን ከነዚህም፡
1. ካፒታል ገበያ እንዴት ነው ሚሰራው
2. ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ
3. ሻሪያን ስላገናዘቡ ምርቶች
4. የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ላይ ስላለው ሚናና ያካትታል።
ኮርሶቹን ለመወሰድ esxacademy.com ላይ ገብተው መውሰድ ይችላሉ።
| YouTube | X | TikTok

ገዳ ባንክ ከታክስ በፊት 101 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተገለፀ!!
ገዳ ባንክ የባለ አክሲዮኖች ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 101 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።
በ2016በጀት አመት ያገኘው ገቢ 790 ሚሊዮን ብር ሲሆን ካለፈው አመት ጋር ሲነፃጸር የ609 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
በ 2,88,174 ደንበኞች አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ 4 ቢሊዮን መድረሱም ተጠቁሟል።
ካሉት ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ 42,930 መሆናቸውን ባንኩ አሳውቋል።
በበጀት አመቱ 2.9 ሚሊዮን ብር ብድር መስጠት መቻሉም ተገልጿል፡፡

😁1
ዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል
#Ethiopia | ከብድሩ 90 በመቶው የንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጧል።
ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።
ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው፣ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው።
የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደኾነም ባንኩ ባሠራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።
https://t.me/etstocks

" የሂጅራ ባንክ አጠቅላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል " - የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል
ሂጅራ ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ታህሳስ 13 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡
በጉባኤው ላይ የሂጅራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ከማል የ2023/2024 የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለ አክሲዮኖች ያቀረቡ ሲሆን ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 100 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ማጠናቀቁን ያበሰሩ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ334.78% ብልጫ ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ከምን ጊዜውም በላይ የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፍ ብዛቱን ወደ 100+ ከፍ ማድረጉን ገልጸው ይህም 40% እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል።
ባንኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የደንበኞች ብዛቱን በማሳደግ ከ700,000 በላይ ደንበኞችን ማፍራቱንም ገልጸዋል።
በዚሁ ረገድ ባንኩ ስኬታማ አፈፃፀም በማስመዝገብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 8.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ለባንኩ ባለአክሲዮኖች አብስረዋል።
ባንኩ ከፋይናንሺያል አፈፃፀም በተጨማሪ የማህበረሳችንን እሴቶች ማእከል ያደረጉ ምርትና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ባንክ የመሆን ራዕዩን አጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል::
#HijraBank

👍2
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መዝጋት ዕቅድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ700 ሚሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ የፋይናንሺያል ሴክተር ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ቅርንጫፎችን ከመዝጋቱ በፊት የማህበራዊ ስጋት ግምገማ ያካሂዳል። መልሶ ማዋቀሩ ቅልጥፍናን ለማሳደግ እና ከተማን ያማከለ ብድርን ለመፍታት ያለመ ቢሆንም ተቺዎች የገጠር የባንክ ተደራሽነትን ሊያባብስ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ፣ ንግድ ባንክ የስንብት ፓኬጆችን፣ የሥራ ሽግግር ፕሮግራሞችን እና አማራጭ የአገልግሎት ሞዴሎችን አቅዷል። የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ሜሪየም ሳሊም የፕሮጀክቱን የበለጠ ተቋቋሚ እና አካታች የፋይናንሺያል ስርዓት ለመገንባት ያለውን ግብ አፅንዖት ሰጥተዋል። የዘመናዊነት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ ቅነሳው ለገጠሩ ማህበረሰብ ስጋት ይፈጥራል።
Linkupbusiness
@Etstocks