ET Securities
691 subscribers
607 photos
7 videos
30 files
310 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ንብ ባንክ አቶ ሔኖክ ከበደን ዋና ሥራ አስፈጻሚነት መረጠ።
****
#ሪፖርተር
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የቀድሞውን የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደን፣ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ እንደገና መምረጡ ታወቀ፡፡

አቶ ሔኖክ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ከቦርዱ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቀበላቸው፣ የንብ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሹመቱ እንዲፀድቅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማመልከቱ ታውቋል፡፡

ንብ ባንክ ከስድስት ወራት በፊት አቶ ሔኖክን ለዋና ሥራ አስፈጻሚነት ዕጩ አድርጎ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ ብሔራዊ ባንክ ሹመቱን እንዳላፀደቀው ይታወሳል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸውን ያላፀደቀው ከአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸው እንዲነሱ የተደረጉበት ምክንያት ሊጣራ ይገባል ተብሎ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሆኖም አቶ ሔኖክ ከአማራ ባንክ የለቀቁበት ምክንያት አግባብ እንዳልነበር ከሥራ ሲሰናበቱ በአማራ ባንክ ቦርድ የተጻፈባቸው ደብዳቤ እሳቸውን የማይገልጽ መሆኑን በማመልከት ለብሔራዊ ባንክ ባቀረቡ አቤቱታ መሠረት፣ በአማራ ባንክ የተጻፈባቸውን ደብዳቤ መሠረት ያደረገው ዕግድ በብሔራዊ ባንክ ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክም ከዚህ ቀደም ጥሎባቸው የነበረውን ዕገዳ በማንሳቱ እንደገና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲያገለግሉ የቀረበውን ጥያቄ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የቀድሞዋ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት መለሰ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው ከለቀቁ በኋላ፣ ባንኩ አቶ በላይ ጎርፉን በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት መመደቡ ይታወሳል፡፡

የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት አቶ ሔኖክ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ በትምህርት ዝግጅታቸውም ከእንግሊዝ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በበዓለም አቀፍ ቢዝነስ የኤምቢኤ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው፡፡

በሥራው ዓለምም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ ኃላፊነቶች ከስድስት ዓመታት በላይ የሠሩ ሲሆን፣ የባንኩ የብራንች ኦፊሰር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በተለይም ለሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ማኔጀር በመሆንም ሠርተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከለቀቁ በኋላ ዳሸን ባንክን በመቀላቀል ከስድስት ዓመታት በላይ የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር (ምክትል ፕሬዚዳንት) በመሆን ሠርተዋል፡፡ ከዳሸን ባንክ የለቀቁት የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ነበር፡፡

የአማራ ባንክ የመጀመሪያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆንም ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ፣ ከአማራ ባንክ ቦርድ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸው አይዘነጋም፡፡ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እስከታጩበት ጊዜ ድረስም በአንድ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ በከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ነበር፡፡
👏1
Source~ Banks Ethiopia
@etstocks
The federal government is set to reform the franco valuta scheme due to concerns over market distortion, capital flight, and its impact on parallel market rates. Originally aimed at easing foreign currency flows for manufacturers and traders amid a forex shortage, the scheme allowed businesses to import goods without presenting foreign currency documentation. However, issues have arisen, with officials noting its impact on parallel market rates and concerns over capital flight.

Source: Addisfortune
@Etstocks
👍1
ሁለት የግል ባንኮች (አዋሽ ባንክ
እና ወጋገን ባንክ) የመጀመርያዎቹ የፋይናንስ ተቋማት በመሆን በኢትዮጵያ ሴኩሪቲስ ገበያ የሚተዳደረው እና በኢንፎ-ቴክ ግሩፕ በተሰራው የኤሌክትሮኒክስ መድረክ ግብይት የፈጸሙ።

Read More
@etstocks
#Ethiotelecom
#Telebirr

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ! ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።

መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል። የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው።

መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው!
@Etstocks
አዋሽ ኢንሹራንስ በሰፊ ልዩነት ገበያውን በአንደኝነት መምራት መቻሉን ገለፀ!!

አዋሽ ኢንሹራንስ በ2ዐ16 በጀት ዓመት ከ3.1 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ የአረቦን ገቢ አሰባስቦ ከግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የላቀ በመሆን የገበያውን መሪነት መያዙን ካፒታል ዘግቧል።

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ በጀነራል ኢንሹራንስ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል ተብሏል።

በዚህም ከ17ቱ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በሰፊ ልዩነት ገበያውን በአንደኝነት እየመራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ የ443.7 ሚሊዮን ብር አረቦን ገቢ አሰባስቦ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት 18ቱ ኩባንያዎች ቀዳሚ ሆኗል ተብሏል።

በ2016 ዓ.ም ብቻ በተለያዩ ኩባንያዎች ከ387.9 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በማድረግ በድምሩ የ1.25 ቢሊዮን ብር የአክሲዮን ባለድርሻ መሆን ችሏል።

2017 ከገባ እስካሁን አጠቃላይ ሀብቱ ከ7.7 ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ የተከፈለ ካፒታሉ ከ1.9 ቢሊዮን ብር መሻገሩን ተገልጿል።

ምንጭ_ ካፒታል
@Etsticks
የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያጤኑ መሆኑ ተሰማ‼️

መንግስት ሊበራላይዜሽን ሊያጠናቅቅ በተቃረበበት ወቅት ከኬንያ፣ ሞሮኮ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የተውጣጡ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ ሊገቡ መሆኑ ተሰምቷል።
በባለፈው በሰኔ ወር ብሄራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች "በጥሩ ሁኔታ የተቋቋመ፣ ታዋቂ እና በፋይናንሺያል ጤናማ የሆነ የውጭ ባንክ" ንዑስ ድርጅት/ቅርንጫፍ፣ ተወካይ ቢሮ ለመመስረት ወይም በአገር ውስጥ ባንኮች ውስጥ አክሲዮኖችን በመግዛት የሚሰማሩበትን ረቂቅ ማፅደቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ "ሕጉ በህዳር ወር መጨረሻ አካባቢ በሀገሪቱ ፓርላማ እንደሚፀድቅ" መናገራቸው ይታወሳል።
ማሞ የሞሮኮ፣ የኬንያ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ባንኮች ፍላጎት እንዳላቸው በወቅቱ መጠቆማቸው ይታወሳል።

@Etstocks
👍1
#InterbankLending The ESX platform is hailed as a transformative tool devised to streamline daily lending and borrowing among banks and create a more transparent, efficient financial ecosystem. It is a digital marketplace where banks can post their cash availability, interest rates, and maturity dates and others can respond within 24 hours.

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
Ahadu Bank to discuss mergers at upcoming general assembly

Ahadu Bank would be the first to bring up the merger and acquisition topic at the general assembly, which is scheduled for next week. According to the National Bank of Ethiopia (NBE), the merger case would be resolved by legislation.

Despite the unsuitable site, the bank, which started operations in July 2022, reported that it ended the previous fiscal year with favorable results.

Read More

Source: capitalethiopia
@Etstocks
NBE Set to Launch Interoperable QR Code Payments by December

In a significant move towards digital financial inclusion, Ethiopia is set to launch its interoperable QR code payment system by December 2024. This initiative aims to enhance the efficiency of cashless transactions and promote the widespread adoption of digital payments among merchants and consumers alike.

The new system, developed in alignment with global EMVCo standards, will allow merchants to generate QR codes that can be scanned by consumers using various banking applications. This interoperability means that consumers will be able to make payments seamlessly across different payment platforms, regardless of their financial service providers.

Source: capitalethiopia
@Etstocks
የካፒታል ገበያ ስብሰባ!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአይኤፍሲ - አለምአቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ጋር በመተባበር የመጀመርያው የካፒታል ገበያ ጉባኤ ይጋብዛችኋል!

ከህዳር 04 - 06፣ 2017 ዓ.ም ባሉት ሶስት ቀናት ይካሄዳል።

በዚህ አዲስ እና ተስፋ ሰጭ የድንበር ገበያ ላይ አዲስ የንግድ እድሎችን ሲከፍቱ የአለም አቀፍ ባለሙያዎችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችን እና ባለሀብቶችን ይቀላቀሉ።

አሁን ይመዝገቡ፡ https://pretix.eu/berryadvertising/CMS2024/

LinkedIn | Twitter |
Telegram | YouTube |
TickTok | Facebook
ሕብረት ኢንሹራንስ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማትረፉን አስታወቀ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ሕብረት ኢንሹራንስ በ2016 በጀት ዓመት 525.27 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማትረፉን አስታውቋል፡፡

ኩባኒያው ያተረፈው ትርፍ ከተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ በላይ ወይም የ60.62 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ሕብረት ኢንሹራንስ ይህንን ያስታወቀው ዓመታዊ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን በትላንትናው እለት ባካሄደበት ወቅት ነው።

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከሁለቱም ከሕይወት እና ሕይወት ነክ ካልሆነው) የሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን ገቢ ወደ 1.96 ቢሊዮን ብር  እንደሆነ ጠቅሷል።

ሕብረት ኢንሹራንስ ከሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን መጠን ብር 1.7 ቢሊዮን ብር የተገኘው ሕይወት ነክ ካልሆነ የኢንሹራንስ ስራ መሆኑን በሪፖርቱ አመላክቷል።

የሕብረት ኢንሹራንስ የተከፈለ ካፒታል አንድ ቢሊዮን ብር መድረሱንና የኩባንያው ካፒታል ከባለፈው ዓመት በ2 መቶ 21 ሚሊዮን ብር እድገት አሳይቷል፡፡

የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ባለፈው አመት በአማካይ 23.72 በመቶ እድገት ማሳየቱን ኩባንያው ጠቅሶ በዚህም የሕብረት ኢንሹራንስ እድገት 30.19 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ አክሎም በ2016 በጀት ዓመት  6 መቶ 93 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉን በሪፖርቱ አመላክቷል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@Etstocks
👍1
📊 Ethiopian Private Insurance Companies Financial Results 2022-23 FY

🏦 An overview of how Ethiopia’s private insurance companies performed at 2022-23 fiscal year.

Compiled by: Aksion
@Etstocks
ወጋገን ባንክ ባለፈው በ2016 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

ይህ የትርፍ መጠንም ከባለፈው ዓመት የ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ጋር ሲነፃፀር የ86 በመቶ ብልጫ
አለው ተብሏል።

ወጋገን ባንክ 31ኛ መደበኛ እና 15ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን በዚሁ ጊዜም ባለፈው በጀት ዓመት ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች 9.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ነው የገለፀው።

የባንኩ ባለአክስዮኖች ብዛት 12 ሺ መድረሱን የተናገሩት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አብዲሹ ሁሴን የተከፈለ ካፒታል መጠኑም የ27 በመቶ እድገት በማሳየት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱንና ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የባንኮች አነስተኛ ካፒታል መስፈርት በላይ ነው ብለዋል።

ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠ ብድር ደግሞ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ13 በመቶ እድገት በማሳየት 45 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱም ነው የተነገረው።

@Etstocks