ET Securities
656 subscribers
579 photos
7 videos
28 files
291 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የአሜሪካ ዶላር ለመግዛት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነው።
በካፒታል ማርኬት ውስጥ የሚግኙ የግብይት መሣሪያዎች
፟ _ አክሲዮኖች
_ የዕዳ ሠነዶች
_ የግል ዘርፍ የዕዳ ሰነዶቸ
_ የግምጃ ቤት ሠነዶች
_ የጋራ ፈንዶች
_ የኪራይ ሰነዶች
_ የንብረት ባለቤትነት
#Daily_Tips

TelegramTips

ቴሌግራም በቅርቡ "ቴሌግራም ስታርስ/Telegram Stars" የተሰኘ አዲስ ምናባዊ ገንዘብ (virtual currency) ማስተዋወቁ ይታወሳል።

ይህን ሥርዓት በመጠቀም ቴሌግራም ለይዘት ፈጣሪዎች እና ለቻናል ባለቤቶች አዲስ ነገር አስተዋውቋል።

አንደኛው ቀጥታ ከቻናሉ አባላት የሚሰጥ የስታር ሥጦታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተከታዮች በክፍያ ይዘቶችን እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው።

1. ሥጦታ

የቻናል ባለቤቶች ሥጦታዎችን ከአባሎቻቸው መቀበል ከፈለጉ በመጀመሪያ የቻናላቸውን ገጽ ማስተካከያ ላይ በመግባት Reaction የሚለው ውስጥ Enable Paid Reaction የሚለውን መፍቀድ/ማብራት ይጠበቅባቸዋል።

ተጠቃሚዎች በበኩላቸው የሚፈልጉትን ይዘት ለመደገፍ ሲፈልጉ ወይም የወደዱት ልጥፍ ካለ የስታር ሥጦታ ልክ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ኢሞጂዎችን ሪአክት በሚያደርጉበት መንገድ የሚፈልጉትን ያክል መጠን መስጠት ይችላሉ።

2. በክፍያ የሚቀርብ ይዘት (Subscription)

ይዘት አቅራቢዎች በክፍያ ለሚያቀርቡት ይዘት ወርኃዊ ክፍያ ማስከፈል የሚያስችላቸው ሲሆን ይህንም ተጠቃሚዎች ለየት ያሉ ይዘቶችን ቀድመው ወይም በልዩነት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። (ይህ አገልግሎት አሁን ላይ አልጀመረም)

ቴሌግራም ለተጠቃሚዎች ከደረሰ 11 ዓመት ሞልቶታል። እስካሁን 950 ሚሊዮን ንቁ ተሳታፊዎች እንዳሉት የገለጸ ሲሆን በ2024 1 ቢሊዮን ለመገንባት እቅድ አለው።
The National Bank of Ethiopia NBE suspended the foreign exchange licenses of 12 banks for under invoicing.
ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቷል፡፡
መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሬ በገበያው አማካኝነት እንዲወስን ማድረጉ እና ይኸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ማሻሻያው ተከትሎ የገቢ ንግዱን በይበልጥ እንዲያሳልጥ ወደ አገር እንዳይገቡ በሕግ ክልከላ ከተደረገባቸው ፣ የነዳጅ አውቶሞቢሎች እና ከፀጥታና ከደህንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ አገር እንዲገቡ በመንግሥት ተወስኗል፡፡

ዕቃዎች በፍራንኮ ባሉታ በቀጥታ እንድገቡ መንግስት መፍቀዱ አሁን ላይ ያለውን ወቅታዊ የገበያና የንግድ እንቅስቃሴ ወደ መደበኛው የሚመልስ በመሆኑ ገበያውን የተረጋጋ እንደሆን አወንታዊ ሚና ይጫወታል፡፡

ET Securities
ድረ ገጽ: www.condoaddis.com/category/etstocks
ቴሌግራም: t.me/Etstocks1
ትዊተር፡ https://twitter.com/Etstocks
ፌስ ቡክ፡   https://www.facebook.com/Etstocks
ዩቲዩብ :https://www.youtube.com/@etstocks
Macroeconomic Reforms open new opportunities for renewable energy investment

Ethiopia’s recent macroeconomic reforms have created significant opportunities for renewable energy investment, a sector that has long faced challenges due to regulatory and financial constraints. Despite the government’s ongoing efforts to promote renewable energy development in the private sector, progress has been limited. However, the introduction of a floating exchange rate by the National Bank of Ethiopia (NBE) and the focus on convertibility guarantees are now seen as game-changers for foreign investors.



Source: capitalethiopia
#News አማራ ባንክ ከታክስ በፊት ከ 377 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን የገለፀ ሲሆን ተቀማጭ ገንዘብ ከ 25 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ሲል አስታዉቋል ።

ባንኩ በተጠናቀቀው የ2023/24 በጀት ዓመት የተሻለ ከታክስ በፊት ብር 377.2 ሚሊየን ትርፍ ያስመዘገበ መሆኑን እና ብር ተቀማጭ ገንዘብ ከ 25.1 ቢሊየን ብር ላይ መድረሱን ገሌጿል።

ከ1.8 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የሚነገርለት ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አጠቃላይ ብር 20.3 ቢሊየን ብድር መስጠቱን ገለጿል።

አማራ ባንክ የበጀት ዓመቱን አፈፃፀም በተመከለተ በሰጠዉ መግለጫ ከ 571 ሺ በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን እንዲሁም ከ50 ሺ በላይ የካርድ ተገልጋዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን በርካታ የኤቲኤም እና የፖስ ማሽኖችን በተለያዩ ቦታዎች በማኖር በዲጂታል ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችያለሁ ብሏል ።

ካፒታል
የኅብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ!
***
በኅብረት ባንክ በተለያዩ የኃለፊነት መደቦች ከ20 ዓመታት በላይ ሲያገለግሉ የቆዩት፣ ባለፉት 5 ዓመታት ደግሞ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ መላኩ ከበደ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት አቶ መላኩ ከኃላፊነታቸው የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው ሲሆን፣ ይህንንም በመልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩ ቢሆንም፣ ውሳኔያቸው ድንገተኛ ነው ተብሏል፡፡ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ደግሞ አቶ መላኩ ኃላፊነታቸውን የለቀቁት ከግል ምክንያት ጋር በተያያዘ ነው፡፡

ድንገተኛ የተባለውን የአቶ መላኩ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ የተቀበለው የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አዎንታዊ መልስ እንደሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቦርዱ በአቶ መላኩ ምትክ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ፣ የባንኩ ሲኒየር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ (ኦፕሬሽን) ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙትን ወ/ሮ ጽጌሬዳ ተስፋዬን መሰየሙ ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ልምድ አላቸው ተብለው ከሚጠቀሱ የባንክ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መላኩ፣ በኅብረት ባንክ ብቻ ከ20 ዓመታት በላይ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ከመሾማቸው በፊት፣ ከ11 ዓመታት በላይ በምክትል ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ነበር፡፡

አቶ መላኩ በኅብረት ባንክ ቆይታቸው በተለይ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የተከናወኑ ሥራዎችን በሙሉ በማስተባበርና በመምራት፣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ይጠቀሳል፡፡

ም/ፕሬዚዳንትና ዳይሬክተር በመሆን የዲጂታል የባንክ አገልግሎት ዘርፉን  ለ11 ዓመታት መምራታቸውን የተገኘው የባንኩ መረጃ ያስረዳል፡፡
Siket Bank registers 1.6 billion birr profit in first year after banking transition

Siket Bank, formerly known as Addis Credit and Saving S.C., has marked a significant milestone in its first year as a full-fledged bank, reporting an impressive profit of 1.6 billion birr for the 2023/24 financial year. This marks the end of a successful inaugural year since its transition from a microfinance institution to a commercial bank.

The bank, which became Ethiopia’s 32nd commercial bank after receiving approval from the National Bank of Ethiopia last year, earned more than 2.3 billion birr in revenue during the fiscal year. This represents a 42 percent increase in income compared to the previous year, when the institution was still operating as a microfinance entity.



Source: capitalethiopia
የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችለውን እንቅስቃሴ ጀመረ

የአሊባባ ግሩፕ (AliExpress) በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችለውን እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ።
የቻይናው አሊባባ ግሩፕ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማህበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን እንቅስቃሴ መጀመሩን ይፋ ያደረገበት መድረክ ዛሬ ተካሄዷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) የአሊባባ አሊ ኤክስፕረስ በኢትዮጵያ ስራ መጀመሩ
ኢትዮጵያውያን ሸማቾችና ነጋዴዎች በአዲሱ የዓለም ገበያ ምርትና አገልግሎትን ለመገበያየትና ኢትዮጵያን ወደ ዓለም አቀፍ ንግድ እንዲገቡ ማስቻሉን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢኮሜርስ ሎጂስቲክስ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ ቴዎድሮስ አያሌው አየር መንገዱ አሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚጀምረውን የኢኮሜርስ ስራ ለማሳለጥ የሚያስችል የኢኮሜርስ ሎጂስቲክስ አገልግሎትን የሚሰጥ ማዕከል(ሀብ) ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የአሊ ኤክስፕረስ ቢዝነስ ዳይሬክተር ጄፍሪ ጂያንግ ድርጅቱ በኢኮሜርስ ያለውን ዓለም አቀፍ ልምድ በመጠቀም የኢትዮጵያውያን ሸማቾችንና የንግድ ቦታዎችን እንቅስቃሴ ለማስተሳሰር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ምንጭ :ኢዜአ
Source ~ Banks Ethiopia
@etstocks
Highest Dollar offer DBE

@etstocks
ብሔራዊ ባንክ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን ገለፀ‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የዉጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አዉጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

የዉጪ ምንዛሪ ገበያ ዉስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ እንደተናገሩት " የዉጪ ምንዛሪ ዚሮዉን ለመክፈት ፍላጎት አሳይተዋል ያላቸዉን ሰዎች መቀበሉን " የገለፁ ሲሆን ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለዉ ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል ሲሉ ተደምጠዋል ።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለፃ "ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖሩ የዉጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል " ይህም በድፍረት የተደረገ ነዉ ማለት ይቻላል ሲሉም እርጃዉን አድንቀውታል።

ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ በ 100 ዶላር የዉጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።
#Capital
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 8.6 ቢሊዮን ብር የአርቦን ገቢ ማስመዝገብ መቻሉን እና የእቅዱን 92.4 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታወቀ

ብቸናዉ መንግስታዊ የኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነዉ ተቋሙ ካስመዘገበዉ የአረቦን መጠን ዉስጥ 8.3 ቢሊዮን ያህሉ ከመድን ዘርፍ የተመዘገበ ካለፈው በጀት ቀሪዉ 306.5 ሚሊዮን የሚሆነዉ ከረጅም ጊዜ መድን ዘርፍ የተመዘገበ መሆኑን በዓመታዊ ሪፖርቱ ገልጿል።

በበጀት አመቱ ከተመዘገበው አረቦን ውስጥ 85 በመቶውን ለመሰብሰብ እቀድ የተያዘ ቢሆንም የተሰበሰበው የአረቦን መጠን 89.7 በመቶውን ነው፡፡ ይህም ከተቀመጠው እቅድ አንጻር ሲገመገም አፈጻጸሙ 105.5 በመቶ መሆኑን ያስታወቀዉ ድርጅቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ግን አፈጻጸሙ የ9.3 በመቶ ብልጫ አለዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እንዳስታወቀው በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት ከታክስ በፊት ከ 1.66 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን እና ይህም ከተያዘው እቅድ ጋር ሲነፃፀር 7.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ሲል በሪፖርቱ ገልጿል ።

Source: ENA
Source _ Banks Ethiopia

@etstocks
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አተረፈ!

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በ2023/24 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን አብስሯል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ባሳለፍነው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡

ብር 232 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን

አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 1.8 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለ8250 ደንበኞች አቅርቧል፤ የተሰጡ ብድሮች ለግል ፍጆታ ብድር፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ፣ ለግብርና ብድር፣ ለቤት መስሪያና ማደሻ እና ለተሽከርካሪ ግዥ ብድር ለማኅበረሰባችን ተደራሽ አድጓል፡፡

የተከፈለ ካፒታል ብር 136 ሚሊዮን እንዲሁም ጠቅላላ የተቋሙ ሃብት ብር 1.9 ቢሊዮን ደርሷል፡፡
Wegagen Bank overtakes DBE offering the highest rate for buying of USD