ET Securities
655 subscribers
578 photos
7 videos
28 files
290 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
#Daily_Tips

TelegramTips

ቴሌግራም በቅርቡ "ቴሌግራም ስታርስ/Telegram Stars" የተሰኘ አዲስ ምናባዊ ገንዘብ (virtual currency) ማስተዋወቁ ይታወሳል።

ይህን ሥርዓት በመጠቀም ቴሌግራም ለይዘት ፈጣሪዎች እና ለቻናል ባለቤቶች አዲስ ነገር አስተዋውቋል።

አንደኛው ቀጥታ ከቻናሉ አባላት የሚሰጥ የስታር ሥጦታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተከታዮች በክፍያ ይዘቶችን እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው።

1. ሥጦታ

የቻናል ባለቤቶች ሥጦታዎችን ከአባሎቻቸው መቀበል ከፈለጉ በመጀመሪያ የቻናላቸውን ገጽ ማስተካከያ ላይ በመግባት Reaction የሚለው ውስጥ Enable Paid Reaction የሚለውን መፍቀድ/ማብራት ይጠበቅባቸዋል።

ተጠቃሚዎች በበኩላቸው የሚፈልጉትን ይዘት ለመደገፍ ሲፈልጉ ወይም የወደዱት ልጥፍ ካለ የስታር ሥጦታ ልክ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ኢሞጂዎችን ሪአክት በሚያደርጉበት መንገድ የሚፈልጉትን ያክል መጠን መስጠት ይችላሉ።

2. በክፍያ የሚቀርብ ይዘት (Subscription)

ይዘት አቅራቢዎች በክፍያ ለሚያቀርቡት ይዘት ወርኃዊ ክፍያ ማስከፈል የሚያስችላቸው ሲሆን ይህንም ተጠቃሚዎች ለየት ያሉ ይዘቶችን ቀድመው ወይም በልዩነት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። (ይህ አገልግሎት አሁን ላይ አልጀመረም)

ቴሌግራም ለተጠቃሚዎች ከደረሰ 11 ዓመት ሞልቶታል። እስካሁን 950 ሚሊዮን ንቁ ተሳታፊዎች እንዳሉት የገለጸ ሲሆን በ2024 1 ቢሊዮን ለመገንባት እቅድ አለው።