ET Securities
663 subscribers
588 photos
7 videos
28 files
298 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ET Securities
Photo
Requirements to buy shares አክሲዮን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ነገሮች

የባንኮችን የኢንሹራንሶችንና ሌሎች አትራፊ ድርጅቶችን የአክሲዮን ድርሻዎችን ለመግዛት ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት አስፈላጊ ነው።

1. ኢትዮጵያዊ ዜግነትን የሚያረጋግጥ በዘመኑ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ

2. በልጆች ስም ለመግዛት የልጆች የልደት ካርድ፣ የአባት/እናት/ወይም የአሳዳጊ  በዘመኑ የታደሠ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ

3. በድርጅት ሥም አክሲዮን ለመግዛት
👉🏼3.1. የድርጅቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
👉🏼3.2. አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል በህጋዊ አካል የተሠጠ ውክልና
👉🏼3.3. ድርጅቱ ማህበራትና ዕድሮች ከሆኑ የተመሰረቱበት የፈቃድ ሰርተፊኬት እና እድሩን የሚመሩ አመራሮች ውክልና

4. በውጭ ሐገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት

4.1. ዜግነታቸው የኢትዮጵያ ከሆነ በዘመኑ የታደሠ ፓሥፖርት/መታዎቂያ/መንጃ ፈቃድ

4.2. የውጭ ሐገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን የታደሰ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታዎቂያ(ቢጫ ካርድ)
    ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሐገር ዜጎች የፋይናንስ ተቋም አክሲዮን መግዛት የሚችሉት በሚኖሩበት ሐገር ገንዘብ ነው፡፡(ለምሣሌ የአሜሪካ ዜግነት ያለው በዶላር፣ የጀርመን በዩሮ፣ የእንግሊዝ በፓውንድ........

ለመረጃ ይፃፉልን/ይደውሉልን!
📲ሥልክ፡ 
0901166128


ስለ አክሲዮንና ተያያዥ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይከተሉ!

Follow our Pages:
https://www.facebook.com/etstocks
https://t.me/etstocks
https://condoaddis.com/catagory/etstocks
https://www.youtube.com/@etstocks
https://www.linkedin.com/company/etstock
https://www.tiktok.com/@Et_Securities_Market

#Bank #Stock #Investment #Finance #capitalmarkets
Safaricom PLC is planning to raise up to $150 million (Sh19.6 billion) in local currency debt in Ethiopia once the country's securities exchange (ESX) becomes operational in the third quarter of 2024. This amount translates to approximately 8.6 billion Ethiopian Birr at the current exchange rate, which the company intends to raise through the issuance of local currency-denominated bonds starting from September.

Read more👇
https://www.condoaddis.com/240522-1/
የድርጅታቸውን የተወሰነ ድርሻ በአክሲዮን ለመሸጥ የሚያስቡ ድርጅቶች የሚከተሉት 3 አማራጮች አሏቸው!

አንደኛ
ድርጅቶች ለመሸጥ የወሰኗቸውን አክሲዮናቸውን #ለህዝብ መሸጥ ከፍተኛ ካፒታል ለማሰባሰብ ጥሩ ዘዴ ቢሆንም ሂደቱ ውድ እና አድካሚ ነው! ምክንያቱም ድርጅቶቹ አክሲዮኖችን ለማሻሻጥ ፍቃድ ለተሰጣቸው ድርጅቶች ሃላፊነት ስለሚሰጡ የሚጠየቁት የአገልግሎት ክፍያ ውድ ሊሆን ይችላል እንዲሁም የሚፈልጉት ያህል አክሲዮን ተሸጦ እስከሚያልቅ ረጅም ጊዜ ለመፈጅ ይችላል።

ሁለተኛ
ድርጅቶች ለመሸጥ የወሰኗቸውን የተወሰኑ አክሲዮኖቻቸውን ለትልልቅ #የቢዝነስ_ተቋማት አውጥቶ መሸጥ! ከፍተኛ ካፒታል ለማሰባሰብ ጥሩ ዘዴ ሆኖ ሂደቱ እርካሽ እና ቀላል ነው! ምክንያቱም ተቋማት ትልልቅ ድርሻ የመግዛት አቅም ስለሚኖራቸው በጥቂት ተቋማት እና በአጭር ጊዜ አክሲዮኖቻቸውን ሸጠው ሊጨርሱ ይችላሉ።

ሶስተኛ
ድርጅቶች ለመሸጥ የወሰኗቸውን አክሲዮኖቻቸውን #ለውስጥ_ሰራተኞች መሸጥ! ሰራተኞች ከቁጠባቸው አልያም ከደሞዛቸው ላይ ከፍተኛ ካፒታል ሊኖራቸው ስለማይችል ትልቅ ካፒታል ከአክሲዮን ሽያጭ ለማሰባሰብ አስቸጋሪ ሲሆን (የሰራተኛ ተነሳሽነት ለመጨመር ጥሩ ዘዴ ነው!) የአክሲዮን ድርሻዎችን ለውስጥ ሰራተኞች የመሸጥ ሂደቱ ግን ቀላል ነው!

Source: The Ethiopian Economist View
@etstocks
The Ethiopian Securities Exchange signed a contract with the Information Network Security Administration INSA to enhance cybersecurity governance, security, performance and quality assurance activities for ESX. This collaboration also aims to build institutional and human capacity at ESX to ensure the highest standards of security and performance for our market. The agreement was signed by H.E. Mrs. Tigist Hamid, Director General of INSA, and Dr. Tilahun E. Kassahun, CEO of ESX.

Source: Ethiopiansecurtiesexchange
@Etstocks
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በሕገወጥ ሰነድ የባለቤትነትን ድርሻ አሳጥቷል በሚል ክስ ተመሠረተበት።

ለ23 ዓመታት ያልተከፈለ የትርፍ ድርሻ ከእነ ወለዱ ተሠልቶ እንዲከፈል የዳኝነት ጥያቄ ቀርቧል

በ1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካን የ‹‹ካስቴል ግሩፕ›› ዋና ባለድርሻ ለሆኑት ሚስተር ካስትል ሲሸጥ፣ . . .

Read more
Ethiopia Opens Doors to foreign Banks in Major Banking Reform

The Central Bank of Ethiopia is introducing significant changes in the banking sector to let foreign banks enter the market. In a recent meeting with banking executives, the regulators discussed proposed reforms regarding the entry of foreign banks into Ethiopia.

One crucial aspect of the reforms is . . . . Read more
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
መግለጫው በአጭሩ  !

🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ ማድረጉን የባንኩ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉት የተደረጉ ማሻሻያዎች ናቸው፦🔴

1ኛ. ‼️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ በወለድ ተመን ላይ ወደተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይሸጋገራል፡፡

2ኛ. ‼️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንኩ ፖሊሲ-ነክ የወለድ መጣኔ ለመጀመሪያ ጊዜ 15በመቶ ይሆናል፡፡

3ኛ. ‼️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከገንዘብ ፖሊሲ ጋር
የተያያዙ ጨረታዎችን በየሁለት ሳምንቱ ያካሂዳል፡፡

4ኛ. ‼️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility)ይሰጣል፡፡

5ኛ. ‼️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርስ የሚበዳደሩበትን የተነቃቃ የገንዘብ ገበያ ለመመሥረት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት በቅርቡ ለመዘርጋት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

6ኛ. ‼️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ቢሸጋገርም፣ በሽግግሩ ወቅት ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው የነበሩ ቀጥታ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎች በጊዜያዊነት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ይቀጥላሉ፡፡
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
Fb.me/etstocks
ኢትዮ ቴሌኮም 21.79 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

ገቢው ካለፈ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ21 በመቶ ወይም 16 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

በበጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘት መቻሉም ተነግሯል።

የተቋሙ ደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊዮን መድረሱን የተነገረ ሲሆን ካለፈው ዓመት በ8 ነጥብ 9 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉ ተጠቁሟል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ አንድ ነጥብ 81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር መከናወኑም ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር አተረፈ!
#CBE
*****************************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2023/24 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን እያበሰርን፤ ለውጤቱ መመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ላበረከታችሁ የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በበጀት ዓመቱ ብር 135.4 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13% ዕድገት አሳይቷል። በዚህ ዓመት ከታክስ በፊት የተገኘው ብር 25.6 ቢሊዮን ትርፍም በባንካችን ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። ለተገኘው ትርፍ ባንካችን የተገበራቸው የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂ እና የለውጥ ሥራዎች አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
የባንካችን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከብር 1.17 ትሪሊዮን የተሻገረ ሲሆን የደንበኞቻችን ቁጥር . . . ማንበብ ይቀጥሉ 👇👇
https://www.condoaddis.com/240712-1/
<<የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ሲደረግ የነበረው ዝግጅት ተጠናቋል።የኩባንያው አጠቃላይ ሀብት ግመታ በአንድ የውጭ ኩባንያ ተሠርቷል። በጣም በቅርብ ጊዜ ውስጥ አሥር በመቶ ድርሻው ለሽያጭ ይቀርባል፡፡>>ይህን ቃል ለሪፖርተር ጋዜጣ የተናገሩት ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው።

ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) አማካይነት አሥር በመቶ ድርሻውን ለኢትዮጵያውያን እንደሚሸጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።

መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በአገር ውስጥ እንዲሸጥ ያሳለፈውን ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ በአክሲዮን ተዋቅሮ በድጋሚ እንደሚቋቋም ተሰምቷል።

በተጨማሪ👇በዚህ ይከታተሉን

https://www.youtube.com/channel/etstocks

https://fb.me/etstocks
ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ ለምን ይበደራሉ?

የባንኮች ዋናው የገንዘብ ምንጭ ከቁጠባ የሚሰበስቡት ነው። ከቆጣቢ ሰብስበው (ለቆጣቢ ወለድ እያሰቡ) ለተበዳሪ ያበድራሉ (ከተበዳሪው ወለድ እየተቀበሉ) ገንዘብን ያንቀሳቅሳሉ።

የንግድ ባንኮች ከቆጣቢ የሰበሰቡትን ገንዘብ በሙሉ ሊያበድሩ አይችሉም! ምክንያቱም ቆጣቢ ገንዘቡን ለማውጣት ስለሚፈልግ የተወሰነ ጥሬ ገንዘብ ይዘው መቆየታቸው አይቀርም!

ብሔራዊ ባንክ የቆጣቢዎችን እና የባንክ ባለአክስዮኖች ዋስትና ለመጠበቅ የባንኮች የካፒታል ዋስትና እንዲቀመጥ ያዛል! ከሚያበድሩት ብር መጠን አንፃር የዋስትና ቦንድ ከብሔራዊ ባንክ እንዲገዙ ያስገድዳል (ያበደሩትን መቀበል ባይችሉ ቆጣቢ ብሩን ማጣት የለበትም የሚለው ስጋት ዋና ነው!)

#ለምሳሌ፦ በነባሩ አሰራር ማንኛውም ንግድ ባንክ ከሚያበድረው ገንዘብ ድርሻ 27% ከብሔራዊ ባንክ ቦንድ እንዲገዛ ይገደድ ነበር (1 ሚሊየን ለማበደር የ270 ሺ ብር ቦንድ ከብሔራዊ ባንክ መግዛት አለበት ማለት ነው)።

#ለምሳሌ፦ 1 ቢሊዮን ብር ቁጠባ የሰበሰበ ባንክ 1 ቢሊየኑን በሙሉ ሊያበድር አይችልም (በደንበኛ 2 ሚሊየን ብር ወጪ ቢጠየቅ መመለስ ላይችል ነው!) ስለዚህ የካሽ እጥረት እንዳይፈጠር የመስጋት እና የብሔራዊ ባንክ የአሰራር ሁኔታ ክልከላ ይሆንበታል!

አሰራሩ ይህ ሆኖ ሳለ ባንኮች በቁጠባ የሰበሰቡን በቂ ካሽ ሳያስቀሩ የማበደር እና ያበደሩትን ካሽ በበቂ ያለማስመለስ ችግር የመፈጠር እድል አለ።

#ለምሳሌ፦ በባንኮች ብድር ሲጠየቅ ያለማግኘት እና ጥሬ ብር ለማውጣት አለመቻል (Liquidity Criss) የሚስተዋለው ከላይ ከተጠቀሰው ምክንያት ጋር ይያያዛል።

ንግድ ባንኮች በምሳሌ የተቀመጠው ችግር በገጠማቸው ቁጥር ከብሔራዊ ባንክ ብድር ይጠይቃሉ።

የብሔራዊ ባንክ ገንዘቡን ከየት ያመጣል?

የሃገሪቱ የገቢ ገንዘብ፤ የባንኮች የካፒታል ተቀማጭ፤ በቦንድ እና በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ የተሰበሰበ (በተለይ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የጡረታ ዋስትና ተቀማጭች)፤ አዲስ የሚታተም ገንዘብ፤ ወዘተ መከማቻው ብሔራዊ ባንክ ነው።

የንግድ ባንኮች የብር እጥረት ሲገጥማቸው እና ተጨማሪ ገንዘብ በፈለጉ ጊዜ ከብሔራዊ ባንክ በብድር ይወስዳሉ (በአዲሱ ፖሊሲ በ15% ወለድ ይበደራሉ) ጊዜውን ጠብቀው ከነወለዱ እዳቸውን ይከፍላሉ።
*በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል መመሪያ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወደ ትግበራ እንዲገባ ተደረገ።*

ባለሥልጣኑ ለሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ ለተዛማጅ ውሎች እና ለያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች ፈቃድ የሚሰጥበትና የሚቆጣጠርበትን “የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ የተዛማጅ ውሎች እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች የፊቃድ አሰጣጥ፣ የአሰራር እና የቁጥጥር መመሪያ አዘጋጅቶ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር አስመዝግቧል።

በመሆኑም “የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ የተዛማጅ ውሎች እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች የፈቃድ አሰጣጥ፣ የአሰራር እና የቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1009/2016 ከሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ውሏል።

መመሪያው በባለሥልጣኑ እንዲዘጋጅ እና እንዲወጣ በካፒታል ገበያ አዋጅ ከተመለከቱት ውስጥ አንዱ ሲሆን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ የተዛማጅ ውሎች እና ያልተማለከ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ ፈቃድ ለማውጣት መሟላት ስለሚገባቸው መስፈርቶች፣ ገበያው አባላቱን እንዴት እንደሚቆጣጠር፣ ገበያው አባለቱን መቆጣጠር የሚያስችለው የውስጥ ደንብ በባለሥልጣኑ አጸድቆ ማውጣት እንደሚገባው፣ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዴት እንደሚያቀርብ እና በአጠቃላይ አሰራሩ ምን መምሰል እንዳለበት የተለያዩ ደረጃዎችን ያስቀምጣል፡፡

መመሪያው በመቋቋም ላይ ለሚገኘው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመመሪያው መሠረት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟላ ፈቃድ በመስጠት ሥራ ለማስጀመር የሚያስችል ነው፡፡
መመሪያው ከታችተያይዟል

ድረ ገጽ: condoadis.com/etstocks
ቴሌግራም      t.me/etstocks
ትዊተር       X.com/etstocks
ፌስ ቡክ፡   https://www.facebook.com/etstocks