ET Securities
665 subscribers
589 photos
7 videos
28 files
299 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ECMA's Fee Directive_ 996_2024.pdf
515.8 KB
የፀደቀው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አገልግሎት ክፍያ መመሪያ ቁጥር 996/2024

Approved directive 996/2024 of Ethiopian Capital Market Authority services fee.

https://www.condoaddis.com/catagory/etstocks
የኢትዮጵያ ሰነደ መዋለንዋይ ገበያ (ESX) የካፒታል ማሰባሰብያ ጅምር በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን አስታውቋል።

እ.ኤ.አ. ህዳር 2023 የተጀመረው እና በአዲስ አበባ፣ ናይሮቢ እና ለንደን ሰፊ የአስተዳደር ጥረቶች እና የመንገድ ትዕይንቶች የተደገፈው ጥረቱ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ባለሀብቶች ከፍተኛ ፍላጎት አግኝቷል።

ሰነደ መዋለንዋይ ግብይት ያሰባሰበው ብር 1.51 ቢሊዮን (26.6 ሚሊዮን ዶላር)፣ ከታሰበው የካፒታል ማሰባሰብ  ብር 631 ሚሊዮን (US$ 11.07 ሚሊዮን ዶላር) አንፃር 240% ሊሆን ችሏል። ኢንቨስተሮቹ ፋይናንሺያል እና ከገንዘብ ነክ ያልሆኑ ዘርፎች የተውጣጡ 48 ተቋማዊ ባለሃብቶች የሀገር ውስጥ እና የውጭ አካላትን ያቀፉ ናቸው።

እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2023 የተቋቋመው ኢስመገ (ESX) ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ፈር ቀዳጅ የመንግስት-የግል አጋርነት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ፣ የስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንዱ  ኤፍኤስዲ (FSD) አፍሪካ ፣ ንግድ እና ልማት ባንክ ቡድን (TBD) ጨምሮ ከተለያዩ ባለሀብቶች ከፍተኛ ፍላጎት አሳይቷል ። እነዚህም የናይጄሪያ ሰነደ መዋለንዋይ ገበያ ቡድን (NGX)፣ 16 የሀገር ውስጥ የግል የንግድ ባንኮች፣ 12 የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እና 17 ሌሎች የግል ባለሀብቶች ናቸው።

ያንብቡ👇
https://www.condoaddis.com/etstocks-240404-1/
የኢትዮጵያ ሰነደ መዋለንዋይ ገበያ(ኢሰመገ) የስራ ረቂቅ ደንብ ለህዝብ ውይይትና አስተያየት አቅርቧል።

ሠነዱ በመመልከት ሐሳብና አስተያየት ያላችሁ በኢሜል info@esx.et እንድታቀርቡ ጥሪ ተደርጓል።

ረቂቅ ደንቡን ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ያግኙ
👇👇
https://tinyurl.com/ywwesby4
Nigerian Exchange Group (NGX Group) CEO Temi Popoola is going to join board of Ethiopian Securities Exchange (ESX) as has been reported by the group.

Read more 👇
ET Securities
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1445ኛው ለዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰዎ!

በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እንዲሆንሎ ከመላው ቤተሰቦ ጋር ከልብ እንመኛለን!

ዒድ ሙባረክ!
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ባለአክሲዮኖች ምን አይነት መብት እንደሚኖራቸው የሚወስን ድልድል አያደረገ ነው

ከ48 የኢትዮጵያ እና የውጭ ሀገር ተቋማት 1.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የኢንቨስተሮቹን የድርሻ ድልድል በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ዶይቸ ቨለ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሰነደ-ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር ሚካኤል ሐብቴ “አሁን የድርሻ ድልድል እያደረግን ነው። ገና አልተጠናቀቀም” ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ሣምንት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሒደት በኩባንያው ድርሻ የገዙ ባለ አክሲዮኖች ምን አይነት መብት እንደሚኖራቸው የሚወስን ነው ተብሏል።

ከካፒታል ገበያው ድርሻ ከገዙ ሦስት የውጪ ሀገር ኢንቨስተሮች አንዱ የሆነው የናይጄሪያው ኤክስቼንጅ ግሩፕ፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ቴሚ ፖፖላ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የቦርድ አባል እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ 25 በመቶው ድርሻ የመንግሥት ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና 4 የመንግሥት ተቋማት ለ25 በመቶው ድርሻ 225 ሚሊዮን ብር ከፍለዋል። የተቀረው 75 በመቶ ድርሻ በሀገር ውስጥ የግል ዘርፍ እና የውጭ ባለሀብቶች መያዙ ነው የተገለፀው።

ለተጨማሪ 👇
ETStocks
Ethiopia Forms High-Level Trade Liberalization Committee

The Ethiopian government has established an inter-ministerial committee to spearhead the liberalization of its trade policies. In announcing its formation, Ethiopian Investment Commission (EIC) Commissioner Hana Arayaselassie reveals that the Trade Liberalization Committee will include representatives from key agencies.
Members are drawn from the EIC, the Ministry of Trade & Regional Integration, Ministry of Industry, Ministry of Revenues, Ethiopian Customs Commission, Ministry of Agriculture and the National Bank of Ethiopia.
Addressing a press briefing, EIC Commissioner Hana Arayaselassie says the previous approach of heavily protecting certain industries had not yielded the desired results of capital accumulation and sectoral transformation. Exports have remained stuck at around 3.5 billion dollars annually despite protection, while certain industries still face challenges in accessing markets.
A new directive approved last week by the Ethiopian Investment Board will now allow foreign investment in major export crops like coffee, oilseeds, pulses and hides & skins. It also permits foreign companies to import all goods except fertilizer and petroleum. Wholesale and retail trade is being opened to foreign ownership as well under the directive.
Investors will need to obtain permits as required by the new regulations, which take effect upon publication on the websites of the Ministry of Justice and EIC. For coffee exports, a minimum 10 million dollars annual procurement history or commitment to export 10 million dollars annually for the past three years is mandated. Oilseeds requires five million dollars annually.
Even smaller crops face thresholds of one million dollars for pulses and USD 500,000 for hides. Livestock is the only sector without an experience criterion. Companies new to Ethiopia face higher barriers of 12.5 million dollars for coffee and 7.5 million dollars for oilseeds.
Wholesale traders must commit to modern infrastructure and efficient logistics. The liberalization aims to attract greater foreign capital to boost Ethiopia's competitiveness and trade volumes.

www.condoaddis.com/category/etstocks
Introduction to Research in Capital Markets

Join for a free webinar on April 24, 2024, hosted by Tellimer in partnership with the Ethiopian Securities Exchange (ESX)!

Register here: https://bit.ly/3JeD7F5

@Etstocks
img247_copy-1.pdf
1.1 MB
የኢትዮጵያ ሰነደ መዋለንዋይ ገበያ ባለስልጣን ለባንኮች ባሰራጨው ደብዳቤ በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀፅ 70 መሰረት የአክሲዮን ሽያጭ በባለስልጣኑ ፍቃድ ከተሰጣቸው በኩል በስተቀር  የሚመጣ የአክሲዮን ሽያጭ እንይዳያስተናግዱ አሳስቧል።

ደብዳቤውን ይመልከቱ ከላይ
የተወሰነ ድርሻቸውን ለሕዝብ የሚሸጡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተለዩ!
*
#ሪፖርተር

»ባህር ትራንስፖርትና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በድርሻ ሽያጩ ተካተዋል።


በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ የተወሰ ድርሻቸውን ለሕዝብ የሚሸጡ ስድስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መለየታቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (Ethiopian Investment Holdings – EIH) ኃላፊዎች ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን መጀመር አስመልክቶ የተወሰኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprises) ውስን ድርሻዎቻቸውን በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ እንደሚሸጡ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት በፊት ይፋ እንደሆነውም መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ ለሕዝብ እንደሚሸጥ ገልጾ ነበር፡፡ ምን ያህል መጠናቸው እንደሆነ ውሳኔ ላይ ባይደረስም ሌሎች አምስት የልማት ድርጅቶች ድርሻዎቻቸው በገበያው ላይ እንዲሸጡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መወሰኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱረህማን ዒድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ድርሻቸው ለሽያጭ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (አባትሎአድ)፣ የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅት፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ የትምህርት ማምረቻና ማሠራጫ ድርጅትና የኢትዮጵያ የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ሲሆኑ፣ አምስቱ ተጨማሪ የልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ስድስት ድርጅቶች ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ላይ ድርሻቸውን ይሸጣሉ፡፡

ከትምህርት ማምረቻና ማሠራጫ ድርጅትና ከኢትዮጵያ የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ውጭ ያሉት አራቱ የልማት ድርጅቶች፣ በበላይ ከሚቆጣጠራቸው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር አምስት በመሆን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን (ESX) 25 በመቶ ድርሻ በመግዛት ገበያውን በዚህ ዓመት መስከረም ወር ላይ ማቋቋማቸው የሚታወስ ነው፡፡
እንደ አቶ አብዱረህማን ገለጻ፣ እነዚህን አራቱ ድርጅቶች የገበያውን አክሲዮን ገዝተው እንዲያቋቁሙ የተመረጡበት ምክንያትም በገበያው ላይ በኋላ ድርሻቸውን እንዲሸጡ በመወሰኑ ነው፡፡ በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአራቱ የልማት ድርጅቶችና ከሆልዲንጉ ጋር በመግባት ስድስተኛ ተቋም ሆኖ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይን 25 በመቶ ድርሻ በጋራ መግዛቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርሻቸውን እንደ ኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎቹ የልማት ድርጅቶች ለሕዝብ እንዲሸጥ አለመወሰኑን አቶ አብዱረህማን ተናግረዋል፡፡
‹‹የንግድ ባንክ አሁን አይሆንም፡፡ ምናልባት ወደፊት ከሆነ እንጂ አሁን አልተወሰነም፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹ኢትዮ ቴሌኮም በጣም ግዙፍ ድርጅት ነው፣ የእሱን ድርሻ በተወሰነ መጠን ከሸጥን የንግድ ባንክ አለመሸጥ ምንም አይደል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅትም ግዙፍ መሆኑንና ከ50 በመቶ በላይ የመድኅን ገበያውን የሚቆጣጠር መሆኑን፣ ኢባትሎአድም በጣም ትልቅ ድርጅት እንደሆነ፣ እንዲሁም ብርሃንና ሰላም በአገሪቱ ትልቁ የኅትመት ድርጅት እንደሆነ ያስታወሱት አቶ አብዱረህማን፣ የእነዚህ ድርጅቶች በገበያው ላይ መቅረብ ትልቅ ነገር እንደሆነ ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡
ድርጅቶቹ ምን ያህል የድርሻ መጠናቸውን ለሕዝብ እንደሚያቀርቡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ እንደሆነ ይታወቃል፣ ነገር ግን ሌሎቹ ምን ያህል መጠናቸውን እንደሆነ የሚሸጡት ገና አልወሰንም፤›› ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በውጭ አጋሮቹ ድጋፍ በቅርብ የድርጅቱን ዝግጁነት እያስጠና ሲሆን፣ በገበያው ላይ ለመሸጥ በጣም ጥብቅ የሆኑ መሟላት ያለባቸውን መሥፈርቶች ማሟላት ያለባቸው እንዳሉ ተገልጿል፡፡

የልማት ድርጅቶቹ በገበያው ለመቅረብ ምን መቀየር እንዳለባቸው ሐሳቡ ያላቸው መሆኑን፣ በዚህ ሳምንትም ጨምሮ በየጊዜው ጥልቅ ውይይት እንደሚያደርጉ አቶ አብዱረህማን ተናግረዋል፡፡
ሆልዲንጉ በካፒታል ገበያ ላይ ትኩረ አድርጎ የሚሠራ ልዩ ቡድን የሚያቋቁም ሲሆን፣ ቡድኑ የልማት ድርጅቶቹን ለገበያ ለማቅረብ እንዲዘጋጁ የሚያግዛቸው ይሆናል፡፡
#ESX #Stockmarket #ኢትዮጵያ #አክሲዮን
Safaricom has expressed openness to listing Safaricom Ethiopia on the Ethiopian Securities Exchange in the future.

Peter Ndegwa, CEO of Safaricom, who made the remark today, May 9, 2024, at a media briefing, stated Safaricom Ethiopia’s intention is to set up a business that is Ethiopian. And part of that in the future is to consider further integrating Ethiopian participation into their business model.

Read more
የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኑ።
#ሪፖርተር

በቅርቡ ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ያሰናበተው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን እመቤት መለሰ ዘለቀ (ዶ/ር)ን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሰየመ፡፡

ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው እመቤት (ዶ/ር) የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ሹመቱ ፀድቆላቸዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሥራ አስፈጻሚነት የሚመራ የባንክ ባለሙያ ሲያፈላልግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ካወዳደራቸው ሦስት የባንክ ባለሙያዎች መካከል እመቤት (ዶ/ር)ን ሊመርጥ ችሏል፡፡

አዲሷ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት (ዶ/ር) በባንክ ኢንዱስትሪ ውሰጥ ከ22 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ሲሆን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እስከ ተሰየሙበት ድረስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስትራቴጂክ ፕላኒንግ እና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ እንደ ነበር ታውቋል፡፡
www.condoaddis.com/etstocks
🔴 የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለምስራቅ አፍሪካ ኢንቨስትመንት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የናይሮቢ ሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍራንክ ሊዮድ ዊቲ ገለጹ።

የናይሮቢ ሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ በኬንያ የሚገኝ ከ60 ዓመታት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የአፍሪካ የሰነድ መዋዕለ-ነዋይ ገበያ ነው።
ገበያው በአፍሪካና በኬንያ ኢንቨስትመንት ለማሳለጥ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ኢንቨስተሮች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ተቋሙ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ጋር በትብብር የመሥራት ፍላጎት እንዳለውም ገልጿል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ፍራንክ ሊዮድ ዊቲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለኃብቶች ክፍት ለማድረግ እያከናወነች ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው።
ይህም እርምጃ ለሀገሪቱ ምጣኔ ኃብት እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው ያብራሩት።
በተለይም ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን በማቋቋምና የራሷ የሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ እንዲኖራት እያከናወነች ያለው ተግባር አዲስ የፋይናንስ ምህዳር እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ለውጥ በምስራቅ አፍሪካ በምጣኔ ኃብት ዘርፍ ያላትን የስበት ማዕከልነት የሚያጸናና ለቀጣናው እድገትም አዎንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል

ከዚህ ባለፈ በተለይም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ በቀጠናው ለሚሰሩ መሰረተ ልማቶች የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ተቋሙ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያና ከሌሎች ተዋናዮች ጋር ስትራቴጂክ አጋርነትን በመፍጠር የመሥራት ፍላጎት እንዳለው ጠቁመዋል።

ET securities