ET Securities
655 subscribers
578 photos
7 videos
28 files
290 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር አተረፈ!
#CBE
*****************************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2023/24 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን እያበሰርን፤ ለውጤቱ መመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ላበረከታችሁ የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በበጀት ዓመቱ ብር 135.4 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13% ዕድገት አሳይቷል። በዚህ ዓመት ከታክስ በፊት የተገኘው ብር 25.6 ቢሊዮን ትርፍም በባንካችን ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። ለተገኘው ትርፍ ባንካችን የተገበራቸው የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂ እና የለውጥ ሥራዎች አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
የባንካችን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከብር 1.17 ትሪሊዮን የተሻገረ ሲሆን የደንበኞቻችን ቁጥር . . . ማንበብ ይቀጥሉ 👇👇
https://www.condoaddis.com/240712-1/
#CBE #USD
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ ጨመረ።

ባለፉት 5 ተከታታይ ቀናት ለውጥ የሌለበት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ነበር።

ዛሬ ግን በሁሉም የውጭ ምንዛሬ ዋጋዎች ላይ ጭማሪ አደርጓል።
የአሜሪካ ዶላር መግዣው 101 ብር ከ0041 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 111 ብር ከ1045 ሳንቲም ገብቷል።

#GBP
ፓውንድ ስተርሊግ መግዣው 122 ብር ከ6543 ሳንቲም ፤ መሸጫው 134 ብር ከ9197 ሳንቲም ሆኗል።

#Euro
ዩሮ መግዣው 110 ብር ከ2157 ሳንቲም ፤ መሸጫው ወደ 121 ብር ከ2372 ሳንቲም ጨምሯል።

#KWE
አንዱ የኩዌት ዲናር መግዣው 314 ብር ከ4020 ሳንቲም መሸጫው ደግሞ 345 ብር ከ8421 ሳንቲም ገብቷል።

Condoaddis.com/240809-2