ET Securities
661 subscribers
584 photos
7 videos
28 files
297 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 282 ሚሊየን ዶላር አዘጋጅቼ 28% ብቻ ነው የተወሰደው!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ "ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአራት ዙር 282,459,436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች ቢደለድልም ካዘጋጀው የውጪ ምንዛሬ ውስጥ ደንበኞቹ የተጠቀሙት በአማካይ 28 በመቶ መሆኑን ገልጿል"፡፡

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳሰበ‼️

ብሔራዊ ባንኩ ይህንን በተመለከተ ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል።

አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት አስታውቋል።

አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።

ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ አዝዟል።

እስካሁን በነበረው አሰራርም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸውን ከኮሚሽኑ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር አስታውሶ፤ ንግድ ባንኮች ሁለቱን ጉዳዮች እስከነገ ባለው ባለው ጊዜ ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ብሏል።
ዳሸን ባንክ 6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዘገበ!!

የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ጉባኤ በሚሊንየም አዳራሽ ሲካሄድ የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ባለፈው በጀት ዓመት በአለም አቀፍ ደረጃ ሃገራት የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ያወጧቸው ፖሊሲዎች፣ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት፣ በቀይ ባህር አካባቢ የሚፈፀመው ጥቃት በአለም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደሯቸውን ተፅዕኖዎች አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የነበረው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ ግጭቶችና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩንም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ጥብቅ የገንዘብ ፓሊሲ ይፋ ማድረጉንም አስታውሰው እነዚህ ለውጦች ባንኮች በሚያቀርቡት የብድር መጠንና ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ዳሸን ባንክ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ 

በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡን፣ አጠቃላይ ተቀማጩ 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን አቶ ዱላ ተናግረዋል፡፡ ከወለድ ነፃ ዘርፍ ለባንኩ ተቀማጭ 11.1 ቢሊየን ብር ማበርከቱንም ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት የ27 በመቶ በማደግ 183.7 ቢሊየን ብር መደረሱን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘቱን፣ በአጠቃላይም ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተናግረዋል፡፡

ዳሸን ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት እና ከኔዘርላንድ የልማት ባንክ ጋር በፈጠረው አጋርነት የ40 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል፡፡
Job_Vacancy: Amen Institute በ9 ክፍት የስራ መደቦች ሰራተኛ ፈለገው ልከውልናል ስራው የሚምለከታችሁ ከታች Email adress ም የቢሮ ስልክም ተቀምጧል

Amen Institute Of Technology )are seeking a skilled and Energetic Trainer with over 6 years of experience to train professionals  for the follwing  positions.

#Qualifications:
↪️Bachelor’s degree  and above in related field with 6+ years of experience in retated fields.
↪️Strong public speaking and presentation skills.
↪️Level 4 CoC in relevant field are required for positins 1, 2 &  3
#Salary:
↪️Negotiable based on experience.

🔹Position_1: Electronics Trainer (Permanent/Part-Time)
↪️Fridge, washing Machine, Office machine, TV, Air conditioner etc Trainer.

🔹Position_2 : Industrial Machine Technology Trainer (Permanent/Part-Time)
↪️Emergency Generator istallation/Maintenance, Motor control System and Motor rewinding Trainer.

Position_3: Graphic Design Trainer
(Permanent/Part-Time)

We are hiring a talented Graphic
Design Trainer with over 6 years of professional experience.
Qualifications:
Bachelor’s degree in Computer science, ICT and related fields.

Position_4: AutoCAD & Revit Trainer (Permanent/Part-Time)
Qualifications:
Bachelor’s degree in  Engineering or Architecture. Profciency in AutoCAD and Revit.

Position_5 : Digital Marketing Trainer (Permanent/Part-Time)
We are looking for an experienced Digital Marketing Trainer with over 6 years of industry experience.
Qualifications:
Bachelor’s degree in Marketing.
Expertise in Google Ads, SEO, and social media platforms.

Position 6: Marketing and Sales Trainer (Permanent/Part-Time)

Position_7:  Leadership and Management Trainer (Permanent/Part-Time)

position_8: Video Interviewer / Digital Host
↪️We are seeking a dynamic and engaging Video Interviewer / Digital Host to join our creative team. The ideal candidate will have a passion for storytelling and the ability to connect with guests, making them feel comfortable on camera while engaging our audience.
#Qualifications:
↪️Bachelor’s degree in Media, Communications, or a related field (preferred).
2+ years of experience in video interviewing, hosting, or a similar role.
↪️Strong verbal communication and interpersonal skills.
Comfortable on camera with a natural ability to engage an audience.

Position_9: Commission-Based Sales Representative
↪️We are looking for 20 motivated and results-driven Sales Representatives to join our team on a commission-based structure. This is an exciting opportunity for individuals who thrive in a dynamic environment and are passionate about sales.
#Qualifications:
Proven experience in sales or customer service (preferred).
Excellent communication and interpersonal skills.
Self-motivated with the ability to work independently and manage time effectively.
Strong negotiation and persuasive skills.
Ability to build and maintain relationships with clients.

#Location:
Bole Michael, Addis Ababa, Ethiopia

#How_to_Apply:
Interested candidates should submit their CV and a link to their portfolio or sample interview videos via e-mail or in person.
Eimail: amengeneraltrading2008@gmail.com
Bole Michael Addis Ababa, the building infront of st. Michael church 2nd floor office No 218.
Phone No. 0118644716


Amen Trading-Amen institute of Technology
Forwarded from ET Securities
Forwarded from ET Securities
የአክሲዮን ዋጋ ምንድን ነው?

የአክሲዮን ዋጋ የሚለው ስያሜ የሚያመለክተው የአክሲዮን ድርሻ በገበያ ላይ የሚነግደውን የአሁኑን ዋጋ ነው።

የአክሲዮን ዋጋ

እያንዳንዱ የሕዝብ ንግድ ኩባንያ ድርሻው ሲወጣ ዋጋ ይሰጠዋል ፤ ይህም የኩባንያውን ዋጋ በሚገባ የሚያንጸባርቅ ነው ። በአጠቃላይ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚከሰቱ ለውጦችን፣ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚከሰቱ ለውጦችን፣ የፖለቲካ ክስተቶችን፣ ጦርነትን እና የአካባቢ ለውጥን ጨምሮ የአክሲዮን ዋጋ ከተለያየ ምክንያቶች ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ይላል።

የአንድ ኩባንያ የአክሲዮን ዋጋ መቀየር

ማንኛውም የአክሲዮን ዋጋ ለውጥ ከሚያደርጉ ሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በአንድ ኩባንያ ውስጥ የአክሲዮን ዋጋው ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እንዲቀየር የሚያደርጉ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ።

1. የአቅርቦትና የፍላጎት ሕግ

አንድ ኩባንያ ሌሎች ብዙ ምርታ ወይም ከፍተኛ ፍላጎት ወይም አስፈላጊ የሆነ ጥሩ ምርት የሚያመርት ከሆነ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ በመሆኑ የአክስዮን ዋጋ ይጨምራል። ጥሩው አቅርቦት ከተፈላጊነቱ ጋር በሚመጣጠንበት ጊዜ የአክሲዮን ዋጋ ከፍተኛ ይሆናል። አቅርቦቱ ከተፈላጊው በላይ ከሆነ የኩባንያው ድርሻ ዋጋ ሊቀንስ ይችላል።

በተጨማሪም ኩባንያው ጥሩውን ምርት ውጤታማና ልዩ በሆነ መንገድ በማምረት ላይ የተመካ ነው ። በአሮጌ መስፈርት ላይ ልዩነት ከፈጠሩ፣ የድርሻቸው ዋጋ ከፍ ያለ ቢሆንም እንኳ ተመሳሳይ ሆኖ ሊቆይ ወይም ሊጨምር ይችላል።

በመጨረሻም, በእርግጥ ስለ አቅርቦት እና ፍላጎት ሕግ ነው.

2. አስተዳደር ወይም የምርት ለውጥ

በአስተዳደር ወይም በምርት ላይ የሚከሰቱ ለውጦችም የአንድ ኩባንያ ድርሻ ዋጋ ከፍ እንዲል ወይም እንዲቀንስ ሊያደርጉ ይችላሉ። ኩባንያው ውጤታማና ውጤታማ በሆነ መንገድ በሚተዳደርበትና ሸቀጦችን በሚመረትበት መንገድ ላይ የተመካ ነው ። የአስተዳደር ቡድን፣ የአጻጻፍ ስልት ወይም ሸቀጦች እንዴት እንደሚመረቱ መለወጥ ውጤታማነትን እና አጠቃላይ ውጤታማነትን ሊጨምር ይችላል - ትርፍ መጨመር እና የሽያጭ ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል። ይሁን እንጂ አሉታዊ ለውጦች ፍጹም ተቃራኒ ውጤት ሊያስከትሉ ይችላሉ።


3. የኩባንያውን ስም መጥቀስ

በአክሲዮን ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ሌላው የማስታወሻ ነጥብ ደግሞ ኩባንያው ስም በዜና፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በቃል መጠቀሱ ነው። በተለይ ከሁለት ክንውኖች መካከል አንዱን ማለትም ቅሬታን ወይም ስኬትን በተመለከተ ነው ።

ቅሌቶች – እውነተኛ ወይም እውነት ያልሆኑ – ከአሉታዊ ነገር ጋር በመዛመድ ብቻ የአንድ ኩባንያ ድርሻ ዋጋ እንዲቀንስ ሊያደርጉ ይችላሉ. በተጨማሪም, በገበያ ወይም በየኢንዱስትሪው ውስጥ አንድ ግኝት ጋር መገናኘት, ወይም ተጠያቂ መሆን አብዛኛውን ጊዜ የአክሲዮን ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል.

የአክሲዮን ዋጋ፣ ገቢና ባለድርሻ አካላት

የአክሲዮን ዋጋ በመጀመሪያ የሚወሰነው አንድ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድርሻውን ወደ ገበያ በሚያስገባበት ጊዜ መጀመሪያ ላይ በሕዝብ ፊት በሚያቀርበው መዋጮ (IPO) ነው። የኢንቨስትመንት ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋ ምን መሆን እንዳለበት ለመወሰን የተለያዩ መለኪያዎችን ይጠቀማሉ። ከዚያ በኋላ ከላይ የተጠቀሱት በርካታ ምክንያቶች የድርሻው ዋጋ ከፍ እንዲልና እንዲወድቅ ያደርጋሉ። ይህ ደግሞ በአብዛኛው ከኩባንያው ሊጠበቅ የሚችለው ገቢ ነው።

ነጋዴዎች፣ ኩባንያው የሚያገኘውን ገቢ፣ በገበያ ላይ የሚከሰቱ ለውጦችንና የሚያስገኘውን ትርፍ ጨምሮ ያለውን ዋጋ በየጊዜው ለማወቅ የገንዘብ መለኪያዎችን ይጠቀማሉ። ነጋዴዎች የሽያጭ ዋጋ ከፍ እንዲሉና እንዲቀንሱ ያደርጋል።

ነጋዴዎች በኢንቨስትመንቶቻቸው ላይ ትርፍ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ። በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይከናወናል።
ዲቪደንድ– የኩባንያው አክሲዮን ትርፍ ከከፈለ ለባለድርሻ አካላት በየድርሻው ቋሚ ክፍያ ይደረጋል
በአነስተኛ ዋጋ ሲገዙ ና ዋጋው ከጨረሰ በኋላ መልሰው መሸጥ፡፡

በአጠቃላይ
አንድ የንግድ ድርጅት ለሚያወጣው ለእያንዳንዱ ድርሻ የአክሲዮን ዋጋ ይሰጣል ። ዋጋው የኩባንያው ዋጋ ነጸብራቅ ነው – ህዝብ ለአንድ ኩባንያ ለመክፈል ፈቃደኛ ነው። በዓለም አቀፉ መልክዓ ምድርና በኩባንያው ውስጥ ባሉት የተለያዩ ምክንያቶች ላይ ተመሥርቶ ሊነሳና ሊወድቅ ይችላል ፡፡

fb.me/Etstocks
የ ስቶክ/አክሲዮን ዋጋ እንዴት ማስላት ይቻላል?

የ አንድ አክሲዮን ዋጋን ለማወቅ በቀላሉ Market capitalization ÷ number of shares በማድረግ ማወቅ እንችላለን።
🔅MARKET CAPITALIZATION ማለት ተቋሙ / ድርጅቱ ያለው አሁናዊ ዋጋ ሲሆን
🔅NUMBER OF SHARES ማለት ደግሞ ለገበያ የወጣው የ አክሲዮን ብዛት ማለት ነው ::


ስለዚህ
የ ኢትዮቴሌኮም MARKET CAP = ወደ 119 ቢሊዮን ብር ሲሆን
የአክሲዮን ብዛት ግን አይታወቅም ስለዚህ ሊሆን ይችላል ተብሎ በሚገመት ቁጥር ስናሰላ
በግምት ለምሳሌ
📌 1 በመቶው 10,000 አክሲዎኖች ቢሆን
የ119 ቢሊዮን 1 በመቶ= 1.19 ቢሊዮን
    1.19 ቢልዮን ÷ 10,000 = 119,000 ብር

📌1 በመቶው 100,000 አክስዮን ቢሆን
የ119 ቢሊዮን 1 በመቶ = 1.19 ቢሊዮን
1.19 ቢሊዮን ÷100,000 = 11900 ብር

📌1 በመቶው 1,000,000 አክስዮን ቢሆን
የ119 ቢሊዮን= 1.19 ቢሊዮን
1.19 ቢሊዮን ÷ 1,000,000 = 1190 ብር

ይህ ለምሳሌ የተጠቀምንበት ነው :: ዋጋው እንደዚህ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል
ምክኒያቱም market evaluation(cap) እና የአክሲዮን ብዛት ሊለያይ ስለሚችል ትክክለኛ ቁጥሮቹን ስናገኝ የየትኛውንም ድርጅት አክሲዮን ለመግዛት ይህን አይነት አካሄድ መጠቀም እንኝላለን::

@Etstocks
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ አሽቆለቆለ።

ባለፉት በርካታ ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112 ብር ከ3957 ሳንቲም እየተገዛ በ123 ብር ከ6353 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።

ዛሬ ባንኩ ይፋ ባደረገው የዕለታዊ የምንዛሬ ተመን አንዱን የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበትን ዋጋ ወደ 113 ብር ከ1308 ሳንቲም አሳድጎ መሸጫውን ወደ 115 ብር ከ3934 ሳንቲም አውርዶታል።

እንደ ዛሬው የምንዛሬ ተመን ባንኩ ዶላር መግዣውን በ1 ብር ከፍ ያደረገው ሲሆን መሸጫው ላይ ካለፉት ቀናት የ8 ብር ቅናሽ አድርጎበታል።

ET Securities
ኢቲ ሴኩሪቲስ
Fb.me/Etstocks
#Ethiotelecom

መንግሥት ከኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የ10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ከ25 እስከ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚጠብቅ ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። አንድ ሰው ከኩባንያው ሊገዛ የሚችለው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የአክስዮን መጠንም እንደተወሰነ ዋዜማ ተረድታለች። ከኩባንያው ድርሻ ለመግዛት የተፈቀደላቸው፣ ኢትዮጵያዊያንና በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብቻ እንደኾኑ ምንጮች ገልጸዋል። ኩባንያው በቴሌብር አማካኝነት ነገ የ10 በመቶ ድርሻውን መሸጥ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እንዲመዘገቡ የሚደነግግ ረቂቅ መመርያ ለግምገማ ቀረበ!!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እንዲመዘግቡ በሚደነግግ ረቂቅ መመርያ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ለግምገማ አቀረበ።

አገልግሎቱን ቀልጣፋና ደኅንነቱ የተጠበቀ
እንዲሆን እና በሰነደ ሙዓለ ነዋይ ተዋንያን የሚደረጉ ግብይቶች መካከል ሙሉ እምነት እንዲኖር በማድረግ  የካፒታል ገበያ  አገልግሎቶች እንደሚያሻሽል በረቂቅ መመርያው ላይ መስፈሩን ሪፖርተር ዘግቧል።

ፈቃድ በተሰጣቸው ሰዎች ለሽያጭ የሚቀርቡ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ወይም አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚቀርቡበትን፣ የሚዳረሱበትንና እንዲሠራጩ በማድረግ ለብዙኃኑ ተጠቃሚዎች መረጃ እንዲዳረስ እንደሚያደርጉ የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ተደንግጓል።

አዋጁ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ አውጭው የሚይዛቸው የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ባለቤትነት መዝገቦች፣ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት በሚዘጋጅ ባለቤትነት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በሚመዘገብበት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት መተካት እንዳለበት ያስረዳል።

የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግብይት ተሳታፊዎች በአንድ ቦታ በአካል መገናኘት  ሳያስፈልጋቸው ግብይቶችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል ተብሏል፡፡
ET Securities pinned Deleted message
⭕️ LIVE

ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻውን ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለመሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ያበስራል።

ይህንን ዝግጅት Voice Chat በቀጥታ ይከታተሉ
https://t.me/tikvahethmagazine?livestream

@etstocks
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል።

የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ዝርዝር መረጃ ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ ➡️ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ➡️ 100 ሚሊዮን ብር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ ➡️ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ ➡️ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  ➡️ 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ ➡️999,900 ብር ይሆናል።

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።

- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

https://t.me/etstocks
➡️- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን   33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

➡️ ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።

➡️መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

➡️ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።