ET Securities
692 subscribers
614 photos
7 videos
30 files
314 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
October 16, 2024
October 16, 2024
October 16, 2024
October 16, 2024
Ethio Telecom Prospectus.pdf
14.5 MB
October 17, 2024
October 18, 2024
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ5 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን አገበያይቷል
***
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አራት የግብርና ምርቶች ወደ ዘመናዊ የገበያ ስርአት እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከአምስት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ማገበያየቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከጸደይ ባንክ ጋር የክፍያ አጋርነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ስምምነቱም አርሶ አደሮችና ኤክስፖርተሮች በመጋዘን የሚኖራቸዉን ምርቶች በማስያዝ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችላቸዉ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የግብርና ምርታና ምርታማነት ለማሳደግ ተጨማሪ የግብርና አይነቶች በብዙ አካባቢ እንዲመረቱ እንዲሁም ወደ ዘመናዊ ግብይት እንዲሸጋገሩ እየሰራ ይገኛል።

በመስከረም ሰይፉ

ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓም
@etstocks
October 18, 2024
ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ 2.39 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን አስታዉቋል።


- የባንክ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀለ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ዘመን ባንክ  2.39 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን እና ባለፈዉ ዓመት ካገኘዉ ትርፍ 579 ሚሊዮን ወይም 32 በመቶ ጭማሪ ማድረጉን ገልጿል።

- የባንኩን እጠቃላይ ሀብት በ23.9 በመቶ በማሳደግ ወደ 59.2 ቢሊየን ብር ያደረሰዉ ባንኩ በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ 43.61 ቢሊየን ብር ደርሷል ብሏል።

- የባንኩ 16ኛዉ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀዉ የተከፈለ ካፒታሉን 7.5 ቢሊዮን ብር ማድረሱንና ከቀደመው በጀት ዓመት በ2.45 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ መሆኑ ተመላክቷል በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የባንኩ የተፈረመ ከፒታል 14.97 ቢሊየን ብር መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

- የዘመን ባንክ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ በሪፖርቱ ወቅት እንዳስታወቀዉ በ2016 በጀት ዓመት ፈታኝ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በመቋቋም በተለያዩ የሥራ አፈጻጸም መመዘኛዎች አስደናቂ ውጤት እንዳገኘ ተገልጿል ።

#Capital

LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
October 19, 2024
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የሚገጥማቸውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ለመፍታት አሻሽሎ ያወጣውን መመሪያ ይፋ አድርጓል።

መመሪያው ያስፈለገው፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሚገጥማቸው ንግድ ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ሲበደሩ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው አሠራር በማስፈለጉ እንደኾነ ባንኩ ገልጧል። ከባንኩ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚችሉት ባንኮች፣ ጊዜያዊ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የገጠማቸው፣ በቀጣይነት አስተማማኝ ካፒታል መያዝ የሚችሉ፣ ችግራቸውን ለመፍታት ኹሉንም አማራጮች አሟጠው ስለመጠቀማቸው የሚያስረዱ፣ የመጠባበቂያ እቅዳቸውን ተግባራዊ አድርገው ችግሩን መቅረፍ እንዳልቻሉ ማስረጃ የሚያቀርቡና ተቀባይነት ያለው የእዳ ማስመያዣ ያላቸው እንደኾኑ አስታውቋል።


[ዋዜማ]
October 21, 2024
October 21, 2024
October 23, 2024
October 28, 2024
የኢትዮ ቴሌኮምን አክሲዮን ገዝተዋል??
Anonymous Poll
16%
አዎ ገዝቻለሁ
84%
አይ አልገዛሁም
October 28, 2024
October 28, 2024
October 29, 2024
የባንኮች የብድር ወለድ ምጣኔ አለመቀነስ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ የባንኮች የወለድ ምጣኔ ዝቅ እንደማይደረግ ተናግረዋል፡፡

የባንኩ ገዢ ይህንን ለብሉምበርግ የተናገሩት በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ባንክና የገንዘብ ተቋም የጸደይ ጉባዔ ላይ ሲሆን ውሳኔም በገበያው ያለውን ገንዘብ መጠን በመቀነስ ተበዳሪዎች ብዙ እንዳይበደሩ ለማድረግና የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ታስቦ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም የዋጋ ንረት ከዓመት በፊት ከነበረበት ከ29 በመቶ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ መቀነስ መቻሉን ብሔራዊ ባንክ መግለጹ አይዘነጋም፡፡

በሚቀጥለው 2018 ዓ.ም ይህንን የዋጋ ንረት ከ10 በመቶ በታች ወደ ነጠላ አሃዝ የማውረድ ዕቅድ ተቀምጧል፡፡

ይሁንና የዓለም ገንዘብ ድርጅት (IMF) የዚህ ዓመት የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት 25 በመቶ እንደሚሆንና ወደ ነጠላ አሃዝ የሚወርደው በፈረንጆቹ 2028/29 እንደሚሆን ትንበያውን አስቀምጧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም ብሔራዊ ባንኩ ተግባራዊ ባደረገው በወለድ ተመን በሚመራ የገንዘብ ፖሊስ ሲሆን በዚህም ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ የብድር ወለድ ምጣኔ 15 በመቶ  መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

የብድር ወለድ ምጣኔው ወቅታዊ የዋጋ ንረትን፣ ዝቅተኛ የመሰረታዊ ገንዘብ እድገትና ካለፉት ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እየወረደ የመጣውን የባንክ ብድር ዕድገትን እንዲሁም ሌሎችንም የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያሰገባ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የፖሊሲ አውጪ ባንኩ የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲወሰን ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በዚህም የመንግስት በጀትንና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወጪዎችን በጥብቅ መቆጣጠርን ገቢራዊ ያደርጋል፡፡

ለዚህ ማሳያ የሚሆነውም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ባለመሆናቸው የሚያጠፏቸውን ብድሮች መቀነስና አጠቃላይ ኢኮኖሚው ውስጥ የጥሬ ገንዘብ (Broad Money) እንዳይበዛ የመከላከል ሥራዎች እንደሚሰሩም ነው የሚጠበቀው፡፡

@Etstocks
October 29, 2024