ET Securities
675 subscribers
593 photos
7 videos
30 files
300 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባልስልጣን ስለ አክሲዮን ሽያጭ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ለበለጠ መረጃ 👇👇
https://www.condoaddis.com/etstocks-230822-1
በ2016 በጀት ዓመት ካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ይጀመራል

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የካፒታል ገበያ ተግባራዊ ከማይደረግባቸው ሀገራት መካከል አንዷ የነበረችው ኢትዮጵያ በቅርቡ ይህንን ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች።

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እንቅስቃሴን ለመጀመር የሚያስችል አዋጅ ከፀደቀ በኋላ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በ2016 በጀት ዓመት ወደ ተግባር ለመግባት መታቀዱን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር  ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በዚህም ባለሥልጣኑ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የግል ድርጅቶች የራሳቸውን የብድር ሰነድ ገበያ ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ከዚህ ቀደም መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ለሽያጭ የሚያወጣቸው ሰነዶች ቢኖሩም ሌሎች ትላልቅ የልማት ድርጅቶች የብድር ሰነድ ገበያ ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍና የአሠራር ሥርዓት አለመኖሩ በዚህ ወቅት ተገልጿል።

ይህ አዲስ የተፈረመዎ ስምምነት፥ የግል ድርጅቶች የራሳቸውን የብድር ሰነድ ገበያ ላይ እንዲያውሉ  የሚያስችል ነው ተብሏል።

ካፒታል ገበያ ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ በማቅረብ ሰዎችም ድርሻ ከገዙ በኋላ ተቋሙ ትርፋማ በሆነ መጠን ያላቸውን ድርሻ መልሰው በመሸጥ ከትርፍ ክፍፍል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ነው።

Source: Tikvah
የኢትዮጵያ የቦንድ ገበያ በአዲስ የግብይት መድረክ ሊቀየር ነው።

የአይኤፍሲ(IFC)- ኢትጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን( ECMA) ሽርክና እስከ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ የቦንድ ገበያ ዉልደት

ባለስልጣኑ አዲስ የሁለተኛ ደረጃ የግብይት መድረክን ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ የቦንድ ገበያ ለውጥ ላይ ይገኛል። ይህ ክስተት ...... ማንበብ ይቀጥሉ👇👇👇👇👇👇
Condoaddis.com/etstocks-230922-1
ለኢትዮጵያ የመዋዕለ ንዋይ ገበያ(ኢኤስኤክስ)( ESX) ወሳኝ ምዕራፍ!         

የኢትዮጵያ የሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ( Ethiopian Securities Exchange- ESX) እንዳስታወቀው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋገርኩ ብሏል። እውነትም ወሳኝ ምዕራፍ!

በዚህም መሠረት የኢኤስኤክስ(ESX) አክሲዮን ማህበር ማቋቋሚያ ሰነድ (MoA) በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (Ethiopia Investment Holding ) እንዲሁም በአራቱ በስሩ በሚገኙ ኩባንያዎች  ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ፣ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት እና የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት መካከል የተፈረመ መሆኑን ተገልጿልም። የኢኤስኤክስ ዋና የዳይሬክተሮች ቦርድም ተሹሟል! ቀጥሎ፡ ቦርዱ የሌሎች . . . . . .

ማንበብ ይቀጥሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
Condoaddis.com/etstocks-231005-1
ET Securities pinned «https://m.youtube.com/watch?v=ebyM1l9VGTk&feature=youtu.be»
DIRECTIVE ON THE PUBLIC.pdf
2 MB
ያንብቡ👆👆
ET Securities
DIRECTIVE ON THE PUBLIC.pdf
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን   የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (የአክሲዮን እና የብድር ሰነዶችን) ሽያጭ የሚተዳደርትበት ረቂቅ መመሪያ (The draft directive for public offer of securities (shares and bonds) ለህዝብ ውይይት ይፋ ያደረገ ሲሆን ። በሰነዱላይ በቅርቡ የህዝብ ውይይት መድረክ እንደሚዘጋጅ ጠቅሶ በዚህ መድረክ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አካላት በ communications@ecma.gov.et ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ በተለያዩ መንገዶች ያሳወቀ ሲሆን እኛም ከላይ የተጠቀሰውን መመሪያ ማለትም፤ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (የአክሲዮን እና የብድር ሰነዶችን) ሽያጭ የሚተዳደርትበት ረቂቅ መመሪያ (The draft directive for public offer of securities (shares and bonds) ያያያዝን መሆኑ ይታወቃል፡፡
( ምንጭ፤ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)  
⬇️⬇️
ኢ.ሜይል: girumyit@gmail.com
ድረ ገጽ: www.condoaddis.com/etstocks
ቴሌግራም  t.me/Etstocks
ፌስ ቡክ፡  https://www.facebook.com/Etstocks
Youtube:https://www.youtube.com/channel/UCYeq9Fbfyjp37w3dsjRNY7A
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/etstocks/
ET Securities pinned «የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን   የሰነደ ሙዓለ ንዋይ (የአክሲዮን እና የብድር ሰነዶችን) ሽያጭ የሚተዳደርትበት ረቂቅ መመሪያ (The draft directive for public offer of securities (shares and bonds) ለህዝብ ውይይት ይፋ ያደረገ ሲሆን ። በሰነዱላይ በቅርቡ የህዝብ ውይይት መድረክ እንደሚዘጋጅ ጠቅሶ በዚህ መድረክ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አካላት በ commu…»
ዳሸን ባንክ በ2015 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ተናገረ።

ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ31.9 በመቶ ብልጫ እንዳለው በዛሬው እለት የባንኩ የባለ አክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገልጿል።

የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ባንኩ በበጀት ዓመቱ 18 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዝግቧል ብለዋል።

ባንኩ ተጨማሪ 23.6 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ ችሏል ያሉት የቦርድ ሊቀመንበሩ ይህም ተቀማጩን 114.8 ቢሊዮን ብር አድርሶታል ብለዋል።  የባንኩ አጠቃላይ ሀብቱም 144.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል ሲሉ ለባለ አክሲዮኖች ተናግረዋል።

የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ካፒታሉ 19.3 ቢሊዮን ብር፤ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 9.3 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተነግሯል።

Source: Sheger FM
ዘመን ኢንሹራንስ በአስራ ሰባት እጥፍ የትርፍ ጭማሪ አሳይቷል።

ዘመን ኢንሹራንስ በ2009 በጀት ዓመት አመርቂ ዕድገት አስመዝግቧል፤ ይህም ለኢንሹራንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ ነው። በኢንዱስትሪው ውስጥ አዲሱ ተጫዋች እንደመሆኑ፣ ኩባንያው ከታክስ በፊት ከፍተኛ ትርፍ መጨመሩን ዘግቧል

ምንጭ፡ ካፒታል
የኢትዮጵያ ሴኪውሪቲስ ኤክስቼንጅ (ኢኤስኤክስ) የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥላሁን እስማኤል ካሳሁንን የኢኤስኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚነት አፀደቀ፡፡ ይህም የኢኤስኤክስ የመጀመሪያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ያደርገዋል፡፡
Ethiopian Securities Exchange (ESX)