Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት: የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር ከSES ሳተላይት ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት በልዩነት ለኢትዮጵያውያን የቀረበው ኢትዮሳት የሃገራችን ብሮድካስተሮች የሚያሰራጩበት የሳተላይት መድረክ እንዲሆን ስምምነት መደረሱን ትናንት ታህሳስ 6, 2013ዓም. በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል::

በዚህም መሰረት የሃገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭታቸውን በልዩነት ለኢትዮጵያውያን ብቻ በቀረበው በኢትዮሳት የማስተላለፍ ጉዞ ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም እንደሚጀምሩ እያስታወቅን፤ ተመልካቾች ዲሻቸውን ወደ ኢትዮሳት በማዞር የሃገራችንን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና አለማቀፍ ቻናሎችን በከፍተኛ ጥራት እንድትመለከቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለዚህም በኢትዮሳት ስልጠና ያገኙ ወይም ባቅራቢያዎ የሚገኙ ሁነኛ ቴክኒሻኖችን በመጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ ዲሽዎን ወደ ኢትዮሳት አንዲያዞሩልዎ ይጠይቁ።
ኢትዮሳት ፡ የኢትዮጵያውያን!

#Ethiosat

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ታህሳስ 07/2013