#መከላከያ ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጠረ::
አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ህዳር 13/2013
መከላከያ ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጠረ::
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጥሯል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ ነው።
የመከላከያ ሠራዊቱ ከሰሞኑ ሽሬን፣ አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ከጁንታው ነጻ ማውጣቱ ይታወቃል።
#FBC

#መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነቱን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየፈፀመ መሆኑን አስታወቀ፣፣
ሰመራ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠባቂ በመሆኑ ሀገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነቱን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየፈፀመ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
መከላከያ ሠራዊት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ÷ አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱ፣ “እኔ እየመራሁ የማልዘርፋት ሀገር ትፍረስ” ከሚል እኩይ ተግባሩና ፀረ-ሕዝብ ባህሪው አንፃር የሚጠበቅ ነው ብሏል።
በተቃራኒው እኛ ግን የመላው ከ120 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵውያንን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ተቀብለን የምንፈፅም ሕዝባዊና ፕሮፌሽናል ብሔራዊ ኃይል ስለሆንን፥ መላውን ሕዝባችንና የትግራይን ጨቅላ ሕፃናት ከከንቱ እልቂት የመታደግ ሞራላዊና ሕጋዊ ግዴታ አለብን ነው ያለው መከላከያ በመግለጫው፡፡
ህወሓት ያኔ ጥንት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ስልጣኔና የዘመነ ጦር መሳሪያ ባልነበረበት ጊዜ ጦርነትን በሰው ማዕበል ገጥመህ ማሸነፍ ወረት በነረበት ወቅት እንደሚደረገው፥ ከግብረ-ገብ፣ ከሞራልና ሕጋዊነት በእጅጉ በተጣረሰ አኳኋን ገና በሰውነታቸው ያልጠነከሩ ጨቅላና ለጋ ሕፃናትን ከኋላ በኃይል እየገፋ፥ በሚገባ ሰልጥኖ እስከ አፍንጫው ከታጠቀ የመከላከያና ጥምር ኃይል ፊት እያሰለፈ የእሳት እራት አድርጎ በማስፈጀት የሞት ቀኑን ለማዘግየት ታሪክ ይቅር የማይለውን ጭካኔ በገዛ ወገኑ፣ ወገናችን የትግራይ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
መከላከያ ሠራዊት በሕግ የተቋቋመ፣ በሕግ የሚመራና በሕዝብ በተመረጠ መንግስት የሚታዘዝ፣ ሲያለማ እደሚሞገስና እንደሚሸለም ሁሉ የተሰጠውን ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮ በሚገባ ሳይፈፅም ሲቀርና ሲያበላሽ በሀገሪቱና ዓለም አቀፍ ሕጎች የሚጠየቅና የሚዳኝ ሀገራዊ ኃይል እንደሆነም በመግለጫው አስረድቷል፡፡
ስለሆነም መከላከያ ሠራዊት ሕግን ተከትሎ ወገኑን ከሰቆቃና እልቂት ለመታደግ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት በጀግንነት በመክፈል፥ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ያስከብራል ነው ያለው መከላከያ ሠራዊት፡፡
የሽብር ቡድኑ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ተከፋይ፣ ጉዳይ አስፈፃሚና በወንጀል የሚፈለግ ሕገ-ወጥ ሽፍታ መሆኑን ያመላከተው መከላከያ÷ ቡድኑ የኃላፊነትና የተጠያቂነት መንፈስ የማይሰማው መሆኑን ገልጾ፥ በባህሪው ምክንያት ሊሰማውም እንደማይችል አስረድቷል፡፡
በዚህ ሳቢያም የሽብር ቡድኑ እንደፈለገው የሚዋሽ እና የግፎች ሁሉ ጥግ የሆነ ተግባር በገዛ ወገኑ ላይ የሚፈጽም መሆኑንም ነው ያብራራው፡፡
ስለሆነም መከላከያ ሠራዊት ሕዝባችንን ከዚህ አረመኔ ቡድን ቀንበር ለማላቀቅና ከከንቱ ጭፍጨፋ ለማዳን ለሕዝባችንና ለሀገራችን ይጠቅማል የተባለውን ሁሉ በመስዋዕትነታችን እውን ለማድረግ በከፍተኛ ብቃትና የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ሕዝባችንን ከፍጅት ለመታደግ ሲባል፥ መሆን የሚገባውን ሁሉ አጠቃላይ ሁኔታን በማያበላሽ አግባብ ቀጣይም ሊኖር እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል ነው ያለው፡፡
እኛ ታላቅና ታሪካዊ ኃላፊነት ካለበት የመከላከያ ኃይል በሚጠበቅ አግባብ፣ ሁለንተናዊ በሆነና ነገን አሻግሮ በሚመለከት እሳቤ እንዲሁም በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የምናደርገው እና እናንተ በጋለ ጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ዛሬ፣ አሁን፣ እዚችው እዲሆን የምትፈልጉትን ሁሉ "አፍ በእጅ በሚያሲዝ" አስተማማኝና ዘላቂ በሆነ ድል ይታረቃል ሲልም አረጋግጧል፡፡
“ዛሬም ሆነ እስከ ወዲያኛው የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም ለመጉዳት የሚደረግ ከሰማይ በታች ባለ ፈተና ሁሉ እንደማንፈተን ታውቃላችሁ! ታምኑናላችሁም!” ሲል የገለጸው መከላከያ ሠራዊት፥ ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ደህንነት፣ የግዛት አንድነትና ለሀገረ መንግሥቱ ቀጣይነት በመቆም የምንከፍለው መስዋዕትነት ክብርና ኩራታችን ነው ብሏል በመግለጫው፡፡