Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አሸባሪው ሕወሓት ህፃናትን ለጦርነት መጠቀም ቀጥሏል::
#አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን ትንኮሳ ያደረገባቸውን ስትራቴጂክ ቦታዎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አስለቀቀ

ሰመራ-ነሐሴ 11፣ 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን ትንኮሳ ያደረገባቸውን ስትራቴጂክ ቦታዎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አስለቀቀ

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ቆቦ ከተማን በመቆጣጠር ወደ ሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች በቀላሉ ለማለፍ በተለምዶ የአርሴማ ተራሮች የተባሉ አራት ተራሮችን እስከ ሀምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ተቆጣጥሮ ለቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ነበር።
ሆኖም የፌዴራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን አራት ፈጥኖ ደራሽ አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አነስተኛ የሰው ሃይልና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብቻ በመጠቀም በርካታ የጁንታውን ሃይል በመደምሰስ አራቱንም ተራሮች በአንድ ቀን በማስለቀቅ ለአካባቢው ሚሊሺያ ማስረከብ መቻላቸው ተገልጿል፡፡
የጠላትን ግብዓተ መሬት ሳንፈጽም አንመለስም ያሉት የሰሜን ዳይሬክቶሬት ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ኢ/ር ሀሰን አብዱ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ቡድን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት፣ የተማመነባቸውን ስትራቴጂክ ቦታዎች በማስለቀቅና ጀሌዎቹን በመደምሰስ ለአካባቢው ማህበረሰብ መረጋጋትን ፈጥረዋል ብለዋል፡፡
አባላቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ሌላ ግዳጅ ለመሰማራት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ትእዛዝ እየተጠባበቁ መሆናቸውንም የሰሜን ዳይሬክቶሬት ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ሻለቃ ምክትል አዛዡ ኢ/ር ሀሰን አብዱ ተናግረዋል።
በቀጣይም አሸባሪውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ዝግጁ ነን ሲሉ አንዳንድ ያነጋገርናቸው የፈጥኖ ደራሽ አባላቱ ተናግረዋል።
ጦርነት የገጠምነው ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ እንደገና ወረራ ከፈፀመ ሃይል ጋር በመሆኑ ተራራ ሲይዝ ተስፋ ባለመቁረጥ፤ ተራራ ሲለቅ "ተሸነፈ" ብለን ሳንዘናጋና ሳንደናገጥ ተልዕኮአችንን በብቃት መወጣት ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ለሀገር ሉዓላዊነት ሲባል ህዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍና ጁንታውን እስከመጨረሻው ለማጥፋት መስዋትነትም ጭምር ለመክፈል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

#Federal Police
#አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ ራስወዳድ ቡድን ነው፡- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ፣፣

ሰመራ-ነሃሴ 29, 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ ራስወዳድ ቡድን ነው፡- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ፣፣

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያውያንን የሚጠላ እና ራሱን ብቻ ከሌሎች ነጥሎ የሚወድ ስግብግብ ቡድን መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላት ምረቃ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታል፡፡

ይህን ፈተና ለማለፍ ብልሃት፣ አንድነት እና ቆራጥነት ያስፈልጋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ባለፉት ወራቶች በተደረጉ ኦፕሬሽኖች አሁንም ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር መሆኗን አይተናል ብለዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን አስቦ እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡

#EBC
#አሸባሪው ህውሀት በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ (ዞን) በወረራ በቆየባቸው ወረዳዎች የሞት እና የንብረት ውድመት ማስከተሉ ተገለጸ ፡፡

መስከረም 02/2014 ዓ.ም (አፋ.ብ.መ.ድ ) አሸባሪው የህውሀት ጁንታ ቡድን በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ (ዞን) በወረራ በቆየባቸው አውራ፣ ከለዋን እና ያሎ ወረዳዎች በንጽሀን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ላይ የሞት እና የንብረት ውድመት ማስከተሉን ጉዳቱ የደረሰባቸው እና የአካባቢው የአመራር አካላት ገልጸዋል ፡፡

የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት በአውራ፣ከለዋን እና ያሎ ወረዳዎች ተገኝቶ የዘገባ ስራ ለመስራት ባደረገው ምልከታ የህውሀት ጁንታ በወረዳዎቹ ላይ ከዚህ በፊት በጋሊኮማ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ባሻገር ሊሎች የንጽሀን ሞት መፈጸማቸውን እና እንዲሁም የግለሰብ እና የመንግስት ተቋማት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጁንታው አውድሞ መሄዱን ከማህበረሰቡ ካገኝነው መረጃ እና ማስረጃ በተጨማሪ እኛም በአይናችን አረጋግጠናል ፡፡

ጉዳቱ የደረሰባቸው የማህበረሰብ ከፍሎች እንደተናገሩት የህውሀት ጁንታ ባደረገው ወረራ ወቅት በሞት ቤተሰቦቻቸውን ያጡ መሆናቸውን እና የቤት ንብረታቸው እና የንግድ ሱቃቸው ተዘርፎ እና ወድሞ ባዶ ቤት ያገኙ መሆናቸውን ቁጪት ፣ ንዴትእና ሀዘን በተቀላቀለበት ስሜት ገልጸዋል ፡፡

ጉዳቱ የደረሰባቸው ግለሰቦች ወደ ቀድሞው የኑሮም ሆነ የንግድ ስራቸው ለመመለስ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል ፡፡

የፈንቲ ረሱ (ዞን) አስተዳድር አቶ መሀመድ አሚን እና የወረዳዎቹ አመረር አካላትን ባናገርናቸው ወቅት እንደገለጹልን ደግሞ በንጹሀን የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ከደረሰው የሞት እና የንብረት ውድመት በተጨማሪ በመንግስት ተቋማት ላይ በጤና፣በትምህርት፣በውሀ እና በአርብቶ አደር በመሳሰሉት የህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ያየነውን ለማመን በተቸገርንበት ደረጃ የሚችሉትን ዘርፈው የልቻሉትን አውድመው ነው የሄዱት ብለዋል ፡፡

በጁንታው ወደ ሁለት ወር የሚጠጋ የተደረገብንን ወረራ ግን በአፋር ክልል ጀግና ልዩ ሀይል ፣በአፋር ሚኒሻ ፣ በአፋር ህዝብ እና በመከላከያ ሰራዊት ተጠራርግው እንዲወጡ ተደርጎ ወደወረዳችን በመመለስ ላይ እንገኛለን፡፡

ይሁን እና በአሁን ጊዜ ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰባችን የምንሰጠው ምንም አይነት አግልግሎት የለም ህዝባችን በከፍተኛ ችግር እና እንግልት ውስጥ በመሆኑ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲደርጉላቸው መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡

ከዚህ በፊት በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ ከጁንታው ወረራው ነጻ የወጣችውን የእዋ ወረዳ አጠቃላይ የደረሰበትን ጉዳት መዘገባችን የሚታወስ ነው ፡፡

በሁሴን በያን
#አሸባሪው የህውሀት ጁንታ የአፋርን መሬት የሚረግጥበት ሞራልም አቅምም የለውም ሲል የአፋር ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሰታወቀ ።

ሰመራ-ጥቅምት 7/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው የህውሀት ጁንታ ከርቀት ወደ ጭፍራ ከተማ በመተኮስ ህዝብን በማሸበር የአፋርን መሬት የሚረግጥበት ሞራልም ፣ አቅምም የለውም ሲሉ የአፋር ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢላይ አህመድ አሰታውቀዋል ።

ከጭፍራ ከተማ ወጣ ብለው በሰራ ላይ ያገኝናቸው አቶ ቢላይ አህመድ እንደገለፁት ጁንታው ከዚህ በፊት በአፋር ለመውረር ባደረገው ሙከራ በአፋር ልዩ ሀይልና ሚንሻ ፣ በአፋር ህዝብ እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ተደምስሶ እና ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ጥቂት የተራረፈው የጁንታው ሀይል ወደ መጣበት ፈርጥጦ መመለሱ የሚታወቅ ነው ።

ይሁን እና ጁንታው በአሁን ጊዜ ከዚህ በፊት የደረሰበትን ከፍተኛ ኪሳራ የረሳው በሚመስል መልኩ የተረፈውን እና የተሸራረፈውን ሀይል ይዞ የተካነበትን ውሸት ከፊት አሰልፎ ፣ ጭንቀት እና ፍርሀቱን ደግሞ ታጥቆ ኢላማና አላማ ለሊለው ከንቱ ተግባር ለማሳካት ከርቀት በከባድ መሳሪያ ወደ ጭፍራ ከተማ በመተኮስ የመሳሪያ ድምፅ ሲሰማ የሚበረግግ የአፋር ማህበረሰቡ ያለ ይመሰል የመጨረሻ ተሰፋ የቆረጠ ተግባሩን ፈፅሞል ሲሉ አቶ ቢላይ ገልፀዋል ።

በተጨማሪም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ቢላይ አህመድ በአብዛሀኛው የጭፍራ ወረዳ ማህበረሰብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከአፋር ልዩ ሀይል ጋር በመቀናጀት ጁንታውን እየቀጠቀጡ ሲሆን አዛውንቶች፣ ህፃናት እና የተለያዩ የጤና ችግር ያለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እና ሊሎች የከተማው ኗሪ ከከተማው በመውጣት ሁኔታውን በቅርብ እርቀት እየተከታተሉ ሲሆን ሊሎች ደግሞ ወደ ተለያዩ ቦታ ለጊዜው ተጠልለዋል ብለዋል ።

በመጨረሻም አቶ ቢላይ አህመድ የጁንታው ሀይሎች ጭፍራን ተቆጣጥረናል ብለው የሚያናፍሱት ወሬ ከእውነት የራቀ ነጭ ውሸት ነው ጭፍራ በራሳችን እጅ ናት ። ከዚህ በኃላ ጁንታው አፋርም መቀሌም አይገባም በያለበት ይቀበራል ይህን ደግሞ በእርግጠኝነት አሁን በቅርቡ የምናየው ይሆናል በማለት ተናግረዋል ።

በሊላ በኩል ደግሞ በግምት ከከተማው ከ2 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ሁነው በእለቱ ሁኔታውን ሲከታተሉ ያገኝናቸው የጭፍራ ወረዳ ኗሪዎች ባደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ እንደገለፁት ጁንታው በርቀት የሚተኩሰው ከባድ መሳሪያ እንዳያርፍብን ለጊዜው በቅርብ እርቀት የከተማውን ሁኔታ እተከታተልን እንገኛለን ።

ሊሎች የጭፍራ ወረዳ ማህበረሰብ ደግሞ በዛው ከከተማው በላይ ባሉ ተራራዎች ላይ ከጀግናው የአፋር ልዩ ሀይል ፣ሚንሻ እና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመመተባበር እየተደመሰሰ ስለሆነ ጁንታው ጭፍራን መቆጣጠር አይደለም በርቀት በአይኑ አያያትም በፍርሀት እና በጭንቀት ከርቀት ከባድ መሳሪያውን በመተኮስ የአፋር ህዝብ ለማሸበር የሚያደርገው መቼም አይሳካለትም ሲሉ ኗሪዎቹ ተናግረዋል ።
#አሸባሪው የህወሓት ቡድን በደሴ ከተማ የመብራት መስመሮችን ለማቋረጥና በከተማዋ በሚገኘው የፀጥታ ሃይል ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማሳደር ማቀዱ ተደረሰበት፣፣

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በደሴ ከተማ የመብራት መስመሮችን ለማቋረጥና በከተማዋ በሚገኘው የፀጥታ ሃይል ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማሳደር ማቀዱ እንደተደረሰበት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች አስታወቁ።

አሸባሪው ጁንታ ደሴ ከተማን ኢላማው አድርጎ የሚያቅዳቸው በርካታ የጥፋት ስራዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው ያሉት ምንጮቻችን፤ በሁሉም ግንባሮች በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ በአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እንዲሁም ለህልውናቸው በተሰለፉት የክልሉ ወጣቶች የሚደርስበት ከባድ ኪሳራ ሩቅ እንደማያስኬደው ግልጽ ስልሆነለት የተለያዩ የሽብር ተግባሮችን አቅዶ ለመፈጸም እይተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ ላይ ያቀደው ጥፋትም ይህንኑ ሽንፈቱን በጥፋት ስራ ለመሸፈን ማቀዱን ያሳያል ያሉት ምንጮቻችን፤ ህብረተሰቡም የዚህን ሽብር ቡድን እኩይ አላማና እቅድ በመረዳት ሃገርን ለመበታተን አቅዶ የተነሳውን የጥፋት ሃይል ሴራ ማክሸፍ ይገባዋል ተብሏል።

የሽንፈት ገፈትን እየቀመሰ የሚገኘው የሽብርተኛው ቡድን በደሴ ብዙ ሰራዊት ሊኖር ይችላል በሚል በተጨማሪም ፋኖ የከተማ የውጊያ ስልትን ለማካሄድ ሊዘጋጅ ይችላል የሚል ግምትን በማሳደር ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም በከተማዋ የመብራት መስመሮችን ለማቋረጥ እና በደሴ የሚገኘው የፀጥታ ሃይል ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማሳደር ማቀዱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደወጡ ምንጮቻችነ አረጋግጠዋል።

በከተማዋ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትም ሆነ የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ከመረጃ እንዲርቅ ማድረግንም በእቅዱ ይዟል ያሉት ምንጮቻችን፤ ሃሰተኛ መረጃዎችንና ምስሎችን በስፋት በማሰራጨትም የሰራዊቱንና አጠቃላይ የፀጥታ ሃይሉን ሞራል ለማዳከም ያስችሉኛል በሚል የያዛቸው እቅዶች መኖራቸው ተደርሶበታል ብለዋል።

ይህ የጥፋት ቡድን ሃገርን ማሸበር ዋና አላማው መሆኑን የሚያሳይ ነው ሲሉም አክለዋል።

የአማራ ክልል ህዝብና መላው ኢትዮጵያውያን የሽብር ቡድኑ ህወሃት ያቀዳቸውን የማወናበጃና የህብረተሰቡን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ተግባራት የማወክ እንቅስቃሴን ቀድሞ በመረዳት ሰርጎ ገቦችን በማጋለጥና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ እንደስካሁኑ ጠንካራ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን

👇
(ኢ ፕ ድ)
#አሸባሪው ህወሓት በቅርቡ ተፈጥሯዊ ሞቱን ይሞታል!

በክብር ኖሮ በክብር መሞትን ብዙዎች ይመኙታል፤ ግን የተመኙትን ኖረው የተመኙትን ዓይነት አሟሟት የሚያገኙት ጥቂቶችና የታደሉቱ ናቸው። ለዚህም ነው ሰዎች በተለይም በዕድሜ ገፋ ያሉ አዛውንቶች በነጋ በጠባ ቁጥር “አሟሟቴን አሳምርልኝ” ሲሉ የሚደመጡት።

ይህ የሚያሳየን ሰዎች በክብር መኖርን የሚሹት በስጋ በሚኖሩበት ዘመናቸው ብቻ ሳይሆን፤ የስጋ ሞትን በሚሞቱበት ወቅትም የኖሩበትን ዘመን ክብርና ዝና በማያጎድፍ ሁኔታ እንዲሆን የጸና ምኞት እንዳላቸው ነው።

በክብር መኖርን በማሰብ ብቻ የሰውነትን ክብር እያጡ፤ በክብር መሞትን እየናፈቁ ሲያልፉ እያየናቸው ያለነው የአሸባሪው ህወሓት ዕድሜ ጠገብ አሸባሪዎች ግን ይህ ምስጢር የገባቸው አይመስልም። ምክንያቱም አሸባሪው ህወሓት እንደ ድርጅት፤ አሸባሪዎቹ ዕድሜ ጠገብ አመራሮቹም እንደ ግለሰብ በክብር መኖርን ያልቻሉና ክብር የራቃቸው መሆኑን ብቻ ሳይሆን፤ በክብር መሞት ቀርቶ ሞት እንኳን ያለ እስከማይመስላቸው ደርሰው ታይተዋልና። ሆኖም ዛሬ ላይ የረሱት ሞት ተፈጥሯዊ ሞታቸውን ሊለግሳቸው ቀርቧል።

👇
(ኢ ፕ ድ)
#አሸባሪው ሕወሐት መሣሪያዎቹን ሲጨርስ ምላሱን መተኮስ ጀምሯል!

ሰሞኑን በደረሰበት ከባድ ምት ከተበታተነው ወራሪ ኃይል መካከል በጣት የሚቆጠረው በቦሩ ሜዳ አቅጣጫ በየወንዙ፣ በየጢሻውና በየሸለቆው ተደብቆ ከርሞ ነበር። ለቀናት ከተደበቀ በኋላ ርሃብና ውኃ ጥም ሲከብደው የእሩምታ ተኩስ በመክፈት ከጉድጓድ እየወጣ የአካባቢውን ሕዝብ ለማደናገር ሞክሯል። አይጥ ከጉድጓዷ በራቀች ቁጥር እንደምትመታው፣ ይሄም የተቆረጠ አሸባሪ ወዲያው ተመትቷል።

የተቆረጠው ኃይል ወደ ሲኦል እየተሸኘ ባለበት፣ በውስጥ ያሠረጓቸው ኃይሎች ጁንታው ወሎ ዩኒቨርስቲ አካባቢን እንደተቆጣጠረ በማስመል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ይገኛሉ። ጀግናው መከላከያና መላው የጸጥታ ኃይላችን እነዚህን ባንዳዎች በመልቀም ርምጃ እየወሰደ ነው። ቦሩ ሜዳም ሆነ ከቦሩ ሜዳ ራቅ ያሉት አካባቢዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን እጅ ላይ ይገኛሉ።

ኅብረተሰቡ የሐሰተኛ ወሬ ፈጣሪዎችንም ሆነ አስተላላፊዎችን ለሕግ እያቀረበ አካባቢውንና ቀዬውን አሁንም በንቃት መጠበቅ ይኖርበታል።
የደሴ ከተማ ሕዝብ የሽብር ቡድኑን የሚያሸንፈው በጽናትና በትግል ብቻ ነው።

በወሬ የተገነባ ከተማ ስለሌለ፣ በወሬ የሚያዝ ከተማ አይኖርም! ሊኖርም አይችልም!

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
#አሸባሪው ሕወሃት በህዝብ ማዕበል ስም ለሞት የዳረገውን ወጣት ለሌላ የፈጠራ ክስ “የሁመራ እልቂት” በሚል አሰናድቶቷል

ሰመራ-ህዳር 13/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው ሕወሃት ከግበረ አበሮቹ ሚዲያዎችና ተቋማት ጋር “የሁመራ እልቂት” ለሚል የፈጠራ ክስ ተሰናድቷል።

አሸባሪው ህወሃት ለዚህ የፈጠራ ክሱ ያሰናዳው በህዝብ ማዕበል ስም መስዋዕት ያደረገውን ህዝብ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የተመድ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ያደረጉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊት ምርመራ አሸባሪው ህወሃት “የአክሱም እልቂት” ሲል ያቀረበው ክስ ሀሰተኛ እና ፈጠራ መሆን መገለጹ ይታወሳል።

ይልቁንም አሸባሪው በወረራቸው አካባቢዎች በዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ማድረጉና በመከላያ ሠራዊት አባላት ላይ ግድያ መፈጸሙ ነው የተየተረጋገጠው።

ኢዜአ ከምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በፈጠራ ስራና ሐሰተኛ ትርክት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር አሸባሪው ህወሃት ከአጋሮቹ ጋር በመሆን “የሁመራ እልቂት” በሚል ክስ ብቅ ሊል መሆኑ ተሰምቷል።

ለዚህ የፈጠራ ክሱ የተዘጋጁት የሳይበር ሰራዊቶቹ ጉዳዩን በስፋት በማራገብ ነጭ ውሸታቸው እውነት እስኪመስል ድረስ ዘመቻ ለማካሄድ መዘጋጀታቸውም ተነግሯል።

ቡድኑ ለዚህ የፈጠራ ክሱ እንዲሆነው ለጥይት ማብረጃነት የተጠቀማቸውን ሰዎች አስከሬን ማሰናዳቱም ተገልጿል።

ለዚህ የፈጠራ ክስ ከዚህ ቀደም የአሸባሪውን የፈጠራ ተውኔቶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩት እንደ ሲኤንኤን ያሉ ሚዲያዎች እየተዘጋጁ መሆኑም ተሰምቷል።

በተለይም አሸባሪው በህዝብ ማዕበል በመላክ ለሞት የተዳረገውን ወጣት ሬሳ በተከዜ ወንዝ አካባቢ በመሰብሰብ “የሁመራ እልቂት በማለት” የፈጠራ ክሱንና ድራማውን ሊሰራ መሆኑ ታውቋል።

ለዚህ ክስ በጎረቤት ሃገር ሱዳን የተሰባሰቡ ጋዜጠኞች ጉዳዩን ለማራገብና እውነት መስሎ እንዲታይ ለማድረግ ከሽብር ቡድኑ ጋር ዝግጅት ላይ ናቸው።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።

#ENA
#አሸባሪው ህወሃት የአፋርን መሬት በመያዝ ለመደራደሪያ ለማቅረብ ማሰቡ መቀበሪያውን አፋጥኗል - አቶ አወል አርባ

ሰመራ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው ህወሃት የአፋርን መሬት በመያዝ ለመደራደሪያ ለማቅረብ ማሰቡ መቀበሪያውን አፋጥኗል - አቶ አወል አርባ

አሸባሪው ህወሃት የአፋርን መሬት በመያዝ ለመደራደሪያ ለማቅረብ ማሰቡ መቀበሪያውን አፋጥኗል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተናገሩ፡፡

የደቡብ ክልል ለአፋር ክልል 52 ሚሊየን ብር የአይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በዚህ ወቅት የሽብር ቡድኑ የአፋር አርብቶ አደርና የአማራ አርሶ አደሮችን መጉዳቱን፣ ሴቶች እናቶችን መድፈሩንና መግደሉ ተገልጿል፡፡

የሽብር ቡድኑ በማጥፋት የሚደሰት በመሆኑ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚገመት ሀብትን በክልሉ በማውደም በርካቶች እንዲፈናቀሉ አድርጓል ነው ያሉት አቶ አወል አርባ።

በደቡብ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት አሰተባባሪ እና የመንገድ እና ትራንሰፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አበባየው ታደሰ ÷ ድጋፋን ሲያስረክቡ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የነበረው እቅድ የአፋር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን በከፈሉት መስዋዕትነት መና ቀርቷል ብለዋል።

ክልሉ ያደረገው የአይነት ድጋፍም በሽብር ቡድኑ የጥፋት እጅ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማገዝ እንደሚያስችል ተናግረው በቀጣይም ክልሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የአይነት ድጋፉ አልባስት፣ የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እና ለማብሰያ እና ለመመገቢያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ይገኝበታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!
#አሸባሪው ሕወሓት በፈጸመው ዳግም ወረራ ከ300 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአፋር ክልል አስታወቀ፣፣

ሰመራ-የካቲት 08, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው ሕወሓት በፈጸመው ዳግም ወረራ ከ300 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአፋር ክልል አስታወቀ፣፣

አሸባሪው ሕወሓት በሰሜናዊ የአፋር ክልል ዞን ሁለት በአምስት ወረዳዎች ላይ በፈጸመው ዳግም ወረራ ከ300 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ከሎይታ አስኑም በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው ሕወሓት ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል በሁለት ዙር በፈጸመው ወረራ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን በላይ ዜጎች ለተለያዩ ጉዳቶች ተዳርገው ነበር፡፡

ቡድኑም ይህንን ሽንፈት ለማካካስ እና የአፋር ጅቡቲ መንገድን ለመዝጋት ካለው ጉጉት የተነሳ ዳግም በሰሜናዊ የአፋር አካባቢ ለሶስተኛ ጊዜ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ጥቃት መሰንዘሩን እና በዚህም በመጋሌ፤ አብአላ፤ በርሃሌ፣ ኩናባር እና አረርቲ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን አቶ አህመድ ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም ይህ ተግባሩ ለጊዜው በዜጎች ላይ ጉዳት ቢያስከትልም ዓላማው የማይሳካ ቅዠት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

ይህ ቡድን እየፈፀመ ያለው ተግባር ከበረሃ አንበጣ በላይ የከፋ ነው የሚሉት አቶ አህመድ፤ “የበረሃ አንበጣ አረንጓዴና እርጥብ ነገር ይፈልጋል፤ ይህ ቡድን ግን ህይወት ያለውም ሆነ የሌለው ነገር ሁሉ ነው የሚያጠፋው፤ የዚህን ቡድን የጥፋት መጠን ለመግለፅ ከባድ ነው” ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል ሁለት ጊዜ በፈፀመው ወረራ ያወደመው የመንግስት ንብረት የህብረተሰቡን ሳይጨምር ከ10 ነጥብ ሶስት ቢሊየን ብር በላይ እንደነበር እና አሁን ደግሞ በዞን ሁለት በአምስት ወረዳዎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እየተጠና እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የዞን ሁለት ነዋሪዎች በአብዛኛው አርብቶ አደር መሆናቸውንና የኑሮ መሰረታቸውም ፍየል፤ ከብት፣ ግመልና መሰል የቤት አንስሳት ናቸው ያሉት አቶ አህመድ፤ አሸባሪው ቡድን ደግሞ እንስሳቱን ስለዘረፈባቸው የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

አቶ አህመድ እንደገለፁት አሁን የተወረሩት አካባቢዎች በአንድ በኩል ከትግራይ ማህበረሰብ ጋር ከፍተኛ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ያላቸው ሲሆን፤ በአብዛኛው የአካባቢው ነዋሪዎችም አርብቶ አደር በመሆናቸው አሸባሪው ቡድን ወረራ ይፈጽምበታል ተብሎ አልታሰበም፡፡ በሌላ በኩል አብዛኛው ህዝብ ትጥቅ የሌለውና ሰላማዊ ህይወት የነበረው ነው፡፡

አካባቢው ከሌላው የአፋር አካባቢ በተለየ ተራራማ በመሆኑ አሸባሪው ቡድን ከተራራ ላይ በመሆን በከባድ መሳርያ ህዝቡን ጨፍጭፏል ያሉት አቶ አህመድ፤ በዚህም በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸውንና ከዚህም አልፎ በደረሰው ጥቃት እና መፈናቀል የደረሰው የስነልቦና ቀውስ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

መንግስት ቀደም ሲል የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ በነበረበት ሁኔታ አሸባሪው ሕወሓት ሌላ ጥቃት በመሰንዘሩ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እንዲፈጠር ቢያደርግም፣ አሁንም የተፈናቀሉ ዜጎችን በአንድ ቦታ በማስፈር ድጋፍ ለማድረግና መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ እንደሆነ አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ ከዚህ አልፎ ወደሌሎች ቀበሌዎች እንዳይስፋፋ የፀጥታና የሰላም ኮማንድ ፖስቱ ስራውን እየሰራ መሆኑንና ኅብረተሰቡም ራሱን ለመከላከል ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አዲስ ዘመን