#ጠ/ ሚ ዐቢይ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ፣፣
ሰመራ-ሰነ 10፣ 2013 (ኤ ኤፍ ኤም ኤም)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ የጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም።
የዘንድሮ ምርጫ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍትሃዊ፣ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ቁርጠኝነቱን ያሳየበት ነው ያሉት አቶ መሀመድ ÷ ቃለ መጠይቁ ከምርጫ ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ብዥታ እንዳይፈጠር ሲባል የመገናኛ ብዙሃኑ ከምርጫው በፊት እንዳያስተላልፉና ማስተዋወቃቸውንም እንዲያቆሙ አሳስበዋል።
በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ የሚገኙ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል።
#FBC

#ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በበዓለ ሲመታቸው ያደረጉት ንግግር
መስከረም 24/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር በርከት ያሉ ጉዳዮችን አንስተዋል።
ጥቂቶቹም፦
ሕዝባችን ጥቃት የሚያንገበግበውና ልዩነቱን ትቶ ለአገሩ የሚሰለፍ ነው፤ ይህም እንድኮራ ከሚያደርጉኝ መካከል ነው።
ኢትዮጵያ ድጋፍ በፈለገች ጊዜ ለደረሳችሁላት ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ።
ኢትዮጵያ በአቃፊነቷ በመርከብ ትመሰላለች።
ኢትዮጵያ ካዘመመችበት ቀና የምትልበት ጊዜው አሁን ነው ይህን ለማሳካት ኃላፊነት ተጥሎብናል።
ኢትዮጵያ አያሌ ውጣውረዶችን ተሻግራ እዚህ ደርሳለች።
6ኛው ምርጫ የምኞታችንን ያህል እንከን የሌሽና የተሳካ ነው ባይባልም የዘመናት የዴሞክራሲ መሻታችንን ለመጀመር መነሻ ሆኗል።
በምርጫው የተመዘገበው ድል የአንድ ፓርቲ ወይም መንግሥት ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደአገርና ኢትዮጵያዊያን እንደ ሕዝብ በአንድነት ያሸነፍንበት ነው።
ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ አካታች ብሔራዊ የምክክር መድረክን እንፈጥራለን።
የሰሜኑ ጦርነት ጥቂት ግለሰቦች እኛ ያልመራናት አገር አታስፈልግም ብለው በግፍ የከፈቱት ነው፤ በዚህም ህፃናት ለጦርነት እያሰለፈና እንስሳትን ሳይቀር እየገደለ ይገኛል።
ፀባችን ከኢትዮጵያ ጠልኃይሎች ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
ኢትዮጵያ ጠንካራ የደኅንነትና የፀጥታ ኃይል ትገነባለች።
ማንኛውም ወዳጅነት የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም የሚነካ አይሆንም ሊሆንም አይገባም።
ዓባይ ማለት የመነሳታችን ምሳሌ በራሳችን የመቆም ማሳያና መተሳሰሪያችን ነው፤ ግድቡም ይጠናቀቃል።
መንግሥት የኑሮ ውድነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል።
ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር አበክረን እንሰራለን።
ሌብነትን እንደ ትልቅ ፈተና ወስደን ለመሻገር እንሰራለን።
ለመጪው ትውልድ የተሻለ አገር ለማስረከብ ተደምረን ቀን ከሌት እንሰራለን።
እንደኅዳር አህያ ያለው ሁሉ ካልጫንኳችሁ እንዲለን ያደረገውን ድህነታችንን ለማሸነፍ እንተጋለን።
መጪዎቹ ዓመታት ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከአይበገሬነት ማሳያ ጋር የሚተሳሰርበት እንደሚሆንም እናምናለን።
ኢትዮጵያ ትናንት ነበረች ዛሬም አለች ነገ አቧራዋን አራግፋ ስትነሳ ደግሞ ከፊቷ የሚቆም ምድራዊ ኃይል አይኖርም።
#Walta