#የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን መረጠ፣፣
ሰመራ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስፈጻሚ አባላትን መረጠ።
ጠቅላላ ጉባዔው ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዚዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲሁም ሸኽ ሀሚድ ሙሳን በዋና ፀሐፊነት መርጧል።
በጉባኤው እንደተገለፀው፥ ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት አገር አቀፍ ጉባዔ የተመረጠው ኮሚቴ በስድስት ወራት ውስጥ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ አመራሮችን እንዲያስመርጥ ኅላፊነት ቢሰጠውም ኅላፊነቱን ሳይወጣ ለሶስት ዓመት ከስድስት ወር ቆይቷል።
በወቅቱ የተመረጠው ኮሚቴ ኅላፊነቱን ባለመወጣቱ ጉዳዩ ወደ መደበኛው ጉባዔ እንዲመጣ በተወሰነው መሰረት ዛሬ ለሁለተኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች በተገኙበት መካሄዱ ነው የተገለፀው።
በጉባኤው ላይ በድምፅ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት 300 ተሳታፊዎች መካከል 261ዱ ተገኝተዋል።
ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ ከተሳተፉት መካከል 39ኙ በሞት፣ በህመም፣ ከሀጂ ጉዞ ባለመመለስና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በዛሬው ጉባኤ አለመገኘታቸውም ታውቋል።
ጉባዔውን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የኅይማኖት አባቶች ስለምርጫው ሂደቱ ማብራሪያና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በጉባዔው ምርጫ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የምርጫ መስፈርቶች ለጉባዔው በንባብ ቀርበዋል።
በዛሬው ጉባዔ መጂሊሱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫ ተካሂዶ የሚከተሉት 14 ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ተመርጠዋል።
1. ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
2. ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን
3. ሸኽ አልመርዲ ዐብዱላሂ
4. ሸኽ ሀሚድ ሙሳን
5. ሸኽ እድሪስ ዓሊይ ሁሴን
6. ሸኽ አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌ
7. ሸኽ መሀመድ አህመድ ያሲን
8. ሸኽ አሚን ኢብሮ
9. ኢንጂኔር አንዋር ሙስጠፋ
10. ሸኽ አብዱልሃሚድ አህመድ
11. ሀጂ ሙስጠፋ ናስር
12. ሸኽ ዛኪር ኢብራሂም
13. ሸኽ ሁሴን ሀሰን
14. ሸኽ መሀመድ አሚን ሰይድ
ከስራ አስፈጻሚ አባላቱ መካከልም ሸኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፕሬዚዳንትነት፣ ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲሁም ሸኽ ሀሚድ ሙሳን በዋና ፀሐፊነት መምረጡን ነው የኢዜአ ዘገባ የሚያመለክተው።
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሸኽ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫው ከየትኛውም አካል ጣልቃገብነት በጸዳ አግባብ በነጻነት ታሪካዊ ምርጫ እንደሆነ ተናግረዋል።
ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ታላቅ ኅላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት ሸኽ ኢብራሂም ቱፋ፥ በተለይም የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት በማስጠበቅ ረገድ በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋገጠዋል።
ህዝበ ሙስሊሙም ከጎናቸው እንዲቆም እና በጸሎት እንዲያግዛቸውም ነው ጥሪ ያቀረቡት።
የምርጫው ታዛቢዎች በበኩላችው ምርጫው ገለልተኛ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን የተከተለ ታሪካዊና ትክክለኛ ምርጫ ሂደት እንደነበር ገልጸዋል።
#FBC

#Gabbí Rasih Caddol Parti Kee Doolat Ekraaroh Kusaqay Awaash Subac Kiiloh Magaalal Gexsitak Suge Yumurruqe
Samara-Ditelik 12, 2014 (AFMMA)
Gabbí Rasih Caddol Parti Kee Doolat Ekraaroh Kusaqay Awaash Subac Kiiloh Magaalal Gexsitak Suge Yumuruqe
Sanat 2014 Ligidak Parti Kee Doolat Abnissoh Ekraaroh Kusaaqay Gabbí Rasih Caddol Rasu Kee Daqoorit Miraaciini Edde Yengele Qidi Kee amô qidi fanteena abeh yan baar le kusaqay Gexsitak Suge Yumurruqe.
Tá Kusaaqih Ellacabol "Qabala Yaceenim Rooci Wadu" itta itrol Miraaciini Qabala Yeceenimih taama Kee Agat Caddol Qimbinteh Tan Anxaxin Ratih Tadeera Arac Xagutuh Awash Subac Kiilok, Naama Lee-fanak Fayya Le Caddoh Barittoh Buxaal Coox Dabisen.
#QafárTV