የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.42K subscribers
183 photos
7 videos
867 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
Audio
በስልክ ንስሐ መግባት ይቻላልን?🛑"ቀኖና እና ሱታፌ ክርስቶስ" ወቅታዊ ትምህርት

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/ayPTHt4gYfs


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
"ልባቸውም ከንቱ ነው፥ጉሮሮአቸውም እንደተከፈተ መቃብር ነው" የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት ክፍል 30

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/qjpBqj9LWdg


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
"አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ በመዓትህም አትገስጸኝ"
የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት #ክፍል_31

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/qGLtoBwFNbs


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
👍1
ወደ እኔ ብረሪ

በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።

ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርር በደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።

ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን የኀያላን ጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይን ያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።

የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።

ነውር የሌለብሽ መልካም ጽጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።

👉በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ

🛑የቴሌግራም ሊንክ @AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዩቲዩብ ሊንክ
https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑ለጓደኛዎ ያጋሩ/ ቻናላችንን ያስፋፉ
ሰላም ለሁላችን። ከዚህ በፊት በ #ዩቲዩብ እና በ #ቴሌግራም የምታውቁት የ "ዕንቈ ሥላሴ tube" አሁን ደግሞ በ #ዋትሳፕ መጥቶላችኋልና ለወዳጅ ዘመዶት ሊንኩን በማጋራት ትምህርተ ወንጌልን በማስፋፋት የነፍስን ምግብ ይመገቡ ይመግቡ !
🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
መበሥር አብሣሪ ተበሣሪ
"እመቤታችን ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል፥ ነውር ነቀፋ የሌለባት ድንግል፥ ፍጽምተ ሃይማኖት የታመነች ድንግል፥ ትሕትናን የተመላችና ታዛዥ ድንግል ናት። የባሕርያችን መመኪያ የነገዳችን ክብር(the honor of our nature) ፥የሕይወታችን በርና የድኅነታችን ምንጭ ድኅነትን ያመጣችልን አንዲት ድንግል(the one who won salvation for us) ናት።

የመጀመሪያቱ ሴት ሔዋን የኃጢአትን በር ከፈተች ዳግሚት ሔዋን ግን የምሕረትና የጽድቅ መንገድ መራችን። ቀዳማዊቷ ምክረ ከይሲን ተከተለች። ደግሚት ሐዋን ግን የእባቡን መርዝ የሚሽረውን ጥልን አጥፍቶ መርዘኛውን እባብ ገድሎ ወደ ውጭ የጣለውን አመጣችልን። ብርሃንን አመጣች፥ ሊቀ ብርሃናቱንም ወለደችው። "the former introduced sin through the tree, the latter brings in grace through tree of the cross= ቀዳማዊቷ ሴት ኃጢአትን በእንጨት አመጣች። ዳግማዊቷ ሒዋን ድንግል ማርያም ግን ጸጋን ሞገስን ባለሟልነት በዕፀ መስቀሉ አመጣችልን"
ቅደስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ(on the Life of virgin Mary)

እንኩዋን ሽንገላ እባብ ተሽሮ ብሥራ መልአክ ለሰማንበት ፥ ሐዘነ ማርያም ተወግዶ ሙሐዘ ፍሥሐ የደስታ መፍሰሻ ወላዲተ አምላክ የዓለሙን ደስታ ለሰማችበት ግርማ ዲያብሎስ ተደምስሶ ጸሐያችን ክርስቶስ ለእኛ ይገለጥ ዘንድ ለመጣበት ለበዓለ መበሥር አብሣሪ ና ተበሣሪ ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ።

ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ያበሠራት መጋቢት ፳፱ ቀን ነው። ለምን ቢሉ ዓለም በዚህ ቀን መፈጠር እንደጀመረ በዚህ ቀንም እንደገና እኛን መፍጠር የጀመረባት ቀን ናትና። በመጀመሪያቱ እሑድ ዓለምን መፍጠር እንደ ጀመረ በአንዲቱ ድንግል ዓለምን እንደገና ይፈጥረው ዘንድ ጀመረ። "ወብኪ ተሐደሰ ቀዳሜ ኩሉ ፍጥረት=የፍጥረት መጀመሪያ በአንቺ ታደሰ" እንዲል አባ ሕርያቆስ

መጋቢት ፳፱ ማለት ዓለም በድንግል
ማርያም ደስታውን የሰማበት እንደገና መፈጠር የተጀመረበት ነው። ሊቃውንቱ መቼም አምላካቸውን የመሰሉ ጠቢባን ናቸውና ትንቢተ ነቢያት ሲፈጸም መልአክ እመቤታችንን እንዳበሠራት ለእኛም የጾመ ነቢያቱ መጨረሻ ላይ ይህን የብሥራቱን በዓል ደግመን እንድናከብረው አደረጉ። በጾመ ነቢያት መጨረሻ ይህን በዓል ማክበራችን የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ የአበው የቃል ኪዳን ምድር እመቤታችን ስለሆነች ነው። በጾመ ነቢያት የመጨረሻው ሳምንት ከታኅሣሥ ፳፪-፳፰ ይህን በዓል እናከብራለን። ይህን ቢቆጥሩት ሰባት ይሆናል።ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው ይላል ቅዱስ ሳዊሮስ። የነቢያትን ጾም ጹመን ነገረ ብሥራቱን ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ የመባሏን በዓል ማክበራችን የነቢያት የእንባቸው ፍሬ የሐዘናቸው መጽናናት የተጋድሏቸው ሽልማት መሆኗን ለማመልከት ነው። ለእኛም የጾማችን መሻጋሪያ
የክብራችን አክሊል ፍጹም ስጦታችን ናትና ሰባት ቀን እናከብራላታለን። ታኅሣሥ ሞገሥና ክብራችን በክርስቶስ ልደት አክሊልነት ይገለጣል።

እስከዚያ ሰባቱን ቀን የምናከብረው ግን የሦስት አካላትን ውለታ እያሰብን ነው። ደስታን የላከልንን እግዚአብሔርን፥ ደስታውን ይዞልን የመጣውን ብሩሕ ደመና ገብርኤልን፥ የደስታችን ማረፊያና መፍሰሻ የድንግል ማርያምን። ስለዚህ በዓሉ በዓለ መበሥር፥ በዓለ አብሣሪ በዓለ ተበሣሪ ተብሎ ይጠራል። እኛም ከቅዱስ ገብርኤል ጋር እንደተገኘን ከቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ጋር እንዲህ እያልን እናመሰግናት፦

አባቶቻችን ምሥጢርን መናገር ልማዳቸው ነውና ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይንን ምሥጢር እንዲህ ሲል በተመስጦ ያመሰጥረዋል።"ተፈሥሒ ኦ ማርያም ምድር ቅድስት ዘበጸሐኪ እግዚአብሔር እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ብሩሕ ወቦአ ውስቴትኪ=እግዚአብሔር በብሩሕ ደመና ሆኖ ወደ አንቺ የመጣ በአንቺም ያደረ ምድሮ ቅድስት እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ" ሃይማኖተ አበው፷፰፥፴፯

እመቤታችን እጅግ ከምትወዳቸው ጸሎታት አንዱና ዋናው"ተፈሥሒ ፍሥሕት=ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ" የሚለው ነው። የሰው ኀዘኑ ኃጢአት ነው። እርስዋ ግን ከዚህ ንጹሕ ናትና ደስተኛይቱ ሆይ አላት። መልአኩ ሲያበሥራት ጌታ ሲፀነስ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያነጻት ሳይሆን ቀድሞውኑ በኃጢአት ያልተከዘች ንጽሕት፥በትንቢተ ነቢያት በድኅነተ ዓለም ተስፋ ያሸበረቀች ፍሥሕት ናትና ደስተኛይቱ ሆይ ብሎ ጀመረ። እግዚአብሔር ቸርነትና ጥበቃ በእርስዋ ትጋትና ትሕትና ተጠብቆ የነበረው ንጽሕናዋ እጥፍ ድርብ ለሆነው አምላክን ለመውለድ አብቅቷታልና "ደስ ይበልሽ"ብሎ የወደፊቱን አከለበት።

ሰው ሁሉ እመቤታችን ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ ሲል እንዲህ ያስብ፦
የእመቤታችንንን ንጽሕናዋን
እግዚአብሔር ደስ ብለው ወደ እርሰዋ መጥቶ ደስብሏታልና የእግዚአብሔርን ደስታ
መላእክት አምላካቸውን በድንግል ሥጋ ተገለጦ ያዩት ደስ ብሏቸዋልና የመላእክትን ደስታ
ነቢያት ከድንግል ይጸነሳል ብለው ተስፋ አድርገው ይህ በእመቤታችን ተፈጽሞ ደስ ብሏቸዋልና የነቢያትን ደስታ
አዳምና ልጆቹ የሞትን ሞትን ትሞታላችሁ ተብለው ተከፍተው ሲኖሩ "እግዚአብሔር ምስሌኪ ስትባል አማኑኤልን ወልዳ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሊሆን ነው ብለው ደስ ብሎአቸዋልና ይህን ሁሉ እያሰቡ ሃይመኖት ማለት ይህ ነው።

አበው እንዳስተማሩን አንድ መነኩሴ ቅዱሳን መላእክት የብርሃን ጽጌረዳና የብርሃን መነሳንሥ ይዘው አገኛቸው። የት እየሄዳችሁ ነው ቢላቸው ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተፈሥሒ ፍሥሕት የሚለውን ሲተረጉም ልንሰማ አሉት ብለው አስደምመውናል። ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ ትርጓሜ ተመልከት
ተፈሥሒ ፍሥሕት ሲባል ጌታን መላእክትን ነቢያትን ሐዋርያትን ቅዱሳንን ከአጋንንት በቀር ፍጥረት ሁሉ ደስ ይበላችሁ ማለትነው! እንዲህ ከሆነ ማለዳ ከኪዳን ሒደን ተአምረ ማርያም ሲነበብ እንዳንሰማ የሚያዘገየን ማን ይመስላችኋል? ደግሞ ማን ይሆናል!ቀድሞ እርሱ በሔዋን ጆሮ ያመጣውን ሐዘን በእዝነ ድንግል ቅዱስ ገብርኤል ባመጣው ተሽሮበታልና ለምን ተሻረብኝ የሚለው አርበኛው ዲያብሎስ ነው እንጅ።

አሁንም የተወደዳችሁ ልጆቿ ሁሉ የሐኬታችንን ማቅ አውልቀን እንጣልና መላእክት ወደ ሚገኙበት ጉባኤ እየፈጠን ተፈሥሒ ሲተረጎም እንስማ!
ብዙ ትካዜ በሰማንበት ጀሯችን በእውነተኛይቱ ሙሐዘ ፍስሐ በድንግል ማርያም ደስታን ለመስማት ያብቃን! አሜን!
አሁንም ከቅዱስ ገብርኤል ጋር"ተፈሥሒ ፍሥሒት ፍሥሕት =
ደ ሥ ተ ኛ ይ ቱ ሆ ይ ደ ስ ይ በ ል ሽ!
አባ ገብረ ኪዳን
መጋቢት ፳፱-፯ -፳፻፲፪ ዓም በድጋሜ ያደረሠን አምላክ ይመስገን!
🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
ሰላም ለሁላችን።ወንድሞችና እህቶች ከስልካችሁ 'የቴሌግራም' ተጠቃሚ የሆኑ ጓደኞቻችሁን በሙሉ ወደዚህ ግሩፕ ታስገቧቸው ዘንድ ትጠየቃላችሁ
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
የምንኖርበትን ሕይወት ከወንጌል አንጻር እየመረመሩ ከኑሮ ጋር አዋደውና ገምደው በግሩም ሁኔታ የሚያቀርቡልን አጥንትን የሚያለመልሙ ነፍስን የሚያድሱ ትምህርታቸውን መከታተል ልብን እንዴት ያረካል!
#የመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረኪዳን_ግርማ ሕይወት ቀያሪ ትምህርቶቻቸውን በተለያዩ ዓለማት ለሚገኙ ምዕመናን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ማህበራዊ ደህረ ገጾች ተከፍተዋል።
#ማስፈንጠርያዎችን በመጠቀም ይከታተሉ ።
በተለያዩ ዓለማት ለሚገኙ ምዕመናን ተደራሽ ይሆን ዘንድ ለወንድሞች እና እህቶችም ያጋሩ::
🛑የዩቲዩብ ሊንክ /Youtube link
👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ/Telegrem channel 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ግሩፕ/Whatsapp group 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
🛑የፌስቡክ ፔጅ /Facebook page
👉https://www.facebook.com/114812820265165/posts/266271485119297/?substory_index=0