በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር በጄነራል ዊንጌት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
ግንቦት 27 ቀን ፤ 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 14ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክንያት በማድረግ ከሚያከናውናቸው ሁነቶች አንዱ የሆነው <<ሙያና ክህሎት ለዘላቂ ልማት>>በሚል መሪ ቃል ሲያካሂድ የቆየው የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ከተማ አቀፍ ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
በማጠቃለያ ውድድሩ በክላስተር ደረጃ በተካሄደው ውድድር የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የተውጣጡ ምሁራን ደግሞ በዳኝነት ተሳትፈ ውበታል።
በዚህ መሰረት #ጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ #ተግባረ-ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ንፋስ ስልክፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል ።
በማጠቃለያ ውድድሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መክብብ ወልደሃና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በስልጠና ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እና በማህበረሰቡ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት እና ችግሮቹ በዘላቂነት እንዲፈቱ ለማድረግ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮች ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
#አቶ መክብብ ወልደሃና አያይዘውም ቢሮው በተግባራዊ ጥናትና ምርምር የተገኙ ግኝቶችን በተግባር ለመለወጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።