ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ኮሌጁ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የትብብር ስልጠናና የስራ ትስስር ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ አካሄደ!!
ኮሌጁ ከዚህ ቀደም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የትብብር ስልጠና እና የስራ ትስስር ምን እንደሚመስል ያሳየና በቀጣይም ኢንዱስትሪ መር ስልጠናን ከማጠናከር አንፃር የተቃኘ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች፣ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ አጋር ከሆኑ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ሞደል ከሆኑ ኢንተርፕራይዞች የመጡ እንግዶች ተሳትፈዋል።
የውይይቱ ዓላማም ኢንዱስትሪው ከቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር ያለውን ወሳኝ ግንኙነት ለማጠናከር፣ የትብብር ስልጠናን ውጤታማ ለማድረግ፣ የተመራቂ ሰልጣኞችን የስራ ትስስር አጠናክሮ ለመቀጠል፣ በኢንዱስትሪዎች እና በኮሌጁ ያለውን ሀብት በጋራ ለመጠቀም ያለመ ነው፡፡
በዕለቱ ኮሌጁ በአዲሱ የስልጠና እሳቤ መሰረት ወደ ስራ የገባባቸውና በዕቅድ የያዛቸው ጉዳዮች እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው የስራ ትስስር በገለፃ ቀርቧል፤ በቀጣይ የስራ ግንኙነታችን ምን ይምሰል? በሚለው ዙሪያም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም ለሰልጣኞች በተመቻቹ የትብብር ስልጠና፣ በተፈጠሩ የስራ ትስስር እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በመጡ ለውጦች ዙሪያ ለተሳታፊ ድርጅቶች የምስጋና እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ሐሙስ:- ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የኬንያ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አደረገ!!
ከኬንያ ኪሲሙ ናሽናል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመጣ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አካሄደ፡፡
ልዑካኑ የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር እና ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት /EASTRIP/ ከሚተገበርባቸው 5ቱ የኬንያ ተቋማት መካከል በጋርመንትና ቴክስታይል ዘርፍ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሌጅ ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ስፔሻሊስቶች እንዲሁም የኮሌጁ ዲኖችና የተለያየ ዘርፍ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
ልዑካኑ በቆይታቸው ተቋማዊ የልምድ ልውውጥ ውይይት፣ የወርክሾፖች ጉብኝትና አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ስራ ተከናውኗል፡፡
በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ መሰረት በቀጣይ የሰራተኞች ልምድ ልውውጥ፣ የጋራ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እና የጥናትና ምርምር ስራ ለማከናወን ታቅዷል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ለውጦችና በተፈጠሩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ላይ ወይይት ተካሄደ!!
ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦችና በተከሰቱ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
"ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሰራተኞች ውይይት እንደ ሀገር የመጡ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን እንዲሁም ለሀገራዊ ለውጡ ተግዳሮት የሆኑ ፈታኝ ጉዳዮች ተብራርተዋል፡፡
ከዚህም ባሸገር የውይይት ሰነዱ የሲቪል ሰርቪሱን ሚና በገለፀበት መነሻ ላይ የአመራሩን፣ የሰራተኛውን እና የተገልጋዩን አሁናዊ ሁኔታ በጥንካሬና በድክመት አስቀምጣሉ፡፡
በቀረበው የሰነድ ገለፃ መሰረት ከኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው በኮሌጁ ዲኖች ምላሽና ማብራሪያ ተስጥቷል፡፡
በመጨረሻም ለአንዳንድ ጥያቄዎች ደግሞ ለሚመለከተው አካል ቀርበው ምላሽ እንደሚሰጥባቸው ተገልፆ የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡