General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የትብብር ስልጠናና የስራ ትስስር ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ አካሄደ!!

ኮሌጁ ከዚህ ቀደም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን የትብብር ስልጠና እና የስራ ትስስር ምን እንደሚመስል ያሳየና በቀጣይም ኢንዱስትሪ መር ስልጠናን ከማጠናከር አንፃር የተቃኘ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች፣ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ አጋር ከሆኑ የመንግስት  መስሪያ ቤቶች እና ሞደል ከሆኑ ኢንተርፕራይዞች የመጡ እንግዶች ተሳትፈዋል።

የውይይቱ ዓላማም ኢንዱስትሪው ከቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር ያለውን ወሳኝ ግንኙነት ለማጠናከር፣ የትብብር ስልጠናን ውጤታማ ለማድረግ፣ የተመራቂ ሰልጣኞችን የስራ ትስስር አጠናክሮ ለመቀጠል፣ በኢንዱስትሪዎች እና በኮሌጁ ያለውን ሀብት በጋራ ለመጠቀም ያለመ ነው፡፡

በዕለቱ ኮሌጁ በአዲሱ የስልጠና እሳቤ መሰረት ወደ ስራ የገባባቸውና በዕቅድ የያዛቸው ጉዳዮች እንዲሁም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው የስራ ትስስር በገለፃ ቀርቧል፤ በቀጣይ የስራ ግንኙነታችን ምን ይምሰል? በሚለው ዙሪያም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም ለሰልጣኞች በተመቻቹ የትብብር ስልጠና፣ በተፈጠሩ የስራ ትስስር እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በመጡ ለውጦች ዙሪያ ለተሳታፊ ድርጅቶች የምስጋና እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡   

    "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ለተመራቂ ሰልጣኞች ማስታወቂያ

ለ2017 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ!! እያልን የምረቃ መጽሔትና ባይንደር ህትመትን በተመለከተ የክፍያ መጠንና የአከፋፈል ሂደትን የያዘ መረጃ በሚከተለው መልኩ አያይዘናል።
ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ለስፓርት አፍቃሪያን ቤተሰብ የተላለፈ ማስታወቂያ

እንደ ሀገር ለ4ኛ እንደ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ በነገው ዕለት የኮሌጃችን አሰልጣኞች ከአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አቻቸው ጋር 3:00 ላይ በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስፓርት ሜዳ ግጥሚያ ስለሚያደርጉ በቦታው ተገኝታችሁ ብርታት ሁነን ተብላችኋል።

መረጃውን በሚከተለው መልኩ አያይዘናል።
ሐሙስ:- ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የኬንያ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አደረገ!!

ከኬንያ ኪሲሙ ናሽናል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመጣ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አካሄደ፡፡

ልዑካኑ የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር እና ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት /EASTRIP/ ከሚተገበርባቸው 5ቱ የኬንያ ተቋማት መካከል በጋርመንትና ቴክስታይል ዘርፍ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሌጅ ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ስፔሻሊስቶች እንዲሁም የኮሌጁ ዲኖችና የተለያየ ዘርፍ ባለሙያዎች ናቸው፡፡

ልዑካኑ በቆይታቸው ተቋማዊ የልምድ ልውውጥ ውይይት፣ የወርክሾፖች ጉብኝትና አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ስራ ተከናውኗል፡፡

በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ መሰረት በቀጣይ የሰራተኞች ልምድ ልውውጥ፣ የጋራ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እና የጥናትና ምርምር ስራ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››