ማክሰኞ:- ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ∙ም
ፋዊ ስለስልጠና ድጋፍ ፕሮግራሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ!!
የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም /FAWE/ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር ስለሚያደርገው የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ይዘት ዙሪያ በዛሬ ዕለት ከባለ ድርሻ አካላት በኮሌጁ ውይይት አካሂዷል።
በዕለቱ የፋዊ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅና የድርጅቱ ሰራተኞች፣ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የትምህርት ቢሮ ተሳታፊዎች፣ በአዲስ ከተማና በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ከልዩ ልዩ ድርጅቶች ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
ፋዌ ኢትዮጵያ ቻፕተር እና ፋዌ አፍሪካ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የሃርድ ስኪል ስልጠና ለሚከታተሉ ሰልጣኞች የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲትሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡
እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱ የተተገበርባቸው ጀነራል ዊንጌት እና አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሲሆኑ በሁለቱ ተቋማት እየሰለጠኑ ለሚገኙ ሰልጣኞች የተለያዩ ድጋፎችን እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
የዛሬው መድረክ ዓላማ ባለ ድርሻ አካላቱ ስለቴክኒክና ሙያ ስልጠና በቂ ግንዛቤ ኖሯው ወደ ዘርፉ ለሚቀላቀሉ ሰልጣኞች የማስተዋወቅ ስራ እንዲያካሂዱ ለማድረግ ነው ተብሏል።
ፕሮግራሙ 80 ከመቶ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ5 እስከ 10 ፐርሰንት ለአካል ጉዳተኛ ከ10 እስከ 15 ፐርሰንቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ዕድል መስጠቱ ታውቋል፡፡
የፕሮጀክቱ ትግበራ ሰባት ዓመት ቆይታ ሲኖረው የመጀመሪያው ዓመት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ረቡዕ:- ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ለአሰልጣኞችና ለኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የሶላር ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ!!
ለኮሌጁ ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክ አሰልጣኞችና ከኢንዱስትሪዎች ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ለ7 ቀናት በተግባር ሲሰጥ የነበረው የሶላር ክህሎት ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
ኮሌጁ በኔዘርላንድ ከሚገኘውና የሶላር ክህሎት ስልጠናን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚሰጠው PUM ከሚባለው ድርጅትጋር በመተባበር ለ8 የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ለ11 የተቋሙ አሰልጣኞች በሶላር ኃይል አጠቃቀምና ዝርጋታ ዙሪያ ላይ አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ተግባራዊ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
የፅንሰ ሀሳብ ትምህርቱ በበየነ መረብ እንዲሁም የተግባር ስልጠናው ደግሞ በአካል ሲሰጥ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀትና ከPUM ድርጅት ስልጠናውን ሲሰጡ ለነበሩት ኔዘርላንዳዊ ኤክስፐርት ሚስተር ፒተር አልቤዳ ደግሞ የሀገር ባህል ልብስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ሚስተር ፒተር ስልጠና ከመስጠት ባሻገር ለሶላር ዘርፍ ስልጠና መስጫነት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ለዲፓርትመንቱ በግላቸው አበርክተዋል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

አርብ:- ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ∙ም
የኮሌጁ ዲኖች እና ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ አሰልጣኞች በከተማዋ የተሰሩ ልማቶችን ጎበኙ!!
ወደ 60 የሚሆኑ የኮሌጁ አመራር እና ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ አሰልጣኞች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የከተማይቱ ክፍል በመዘዋወር የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ጉብኝት ካደረጉባቸው መካከል ለመዝናኛው ኢንዱስትሪ ቅንጡ ሆኖ የተሰራው የቦሌ ቡልቡላ ፓርክ፣ ግዙፉና ተጠቃሚው ማኅበረሰብ በቀጥታ ከአምራቹ ሸመታ የሚያደርግበት የለሚ ኩራ ገበያ ማዕከል፣ ዘመናዊው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬክሽን ማዕከል እና በዲጂታላይዜሽን ስርዓት ዘምኖ የተቀላጠፈ አገልግሎት የሚሰጥበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ይገኙበታል።

ሰኞ:- ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ተሞክሮ የማስፋት መድረክ ተካሄደ!!
በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን ቢሮ ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ተሞክሮ የማስፋት መድረክ ተካሄደ፡፡
በቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ በ4ቱ የድጋፍ አግባቦች ተጠቅመው ውጤታማ የሆኑ 2 ኢንተርፕራይዞች ላይ ተሞክሮ በመቀመር ሌሎች አንቀሳቃሾችም ልምዱን ተጋርተው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከበርካታ ኢንተርፕራይዞች ለመጡ አንቀሳቃሾች ተሞክሮውን የማስፋት ስራ ተሰርቷል፡፡
ተሞክሮ የተቀመረባቸው 2ቱ ኢንተርፕራይዞች እስጢፋኖስ፣ ብሩና ጓደኞቹ እጨት ስራ እንዲሁም በጌታ ፍቃድ ልብስ ስፌት የሚባሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ መድረክ ላይ 84 የሚሆኑ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እንዲሁም የክፍለ ከተማና የወረዳዎች ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
በዚህ መድረክ ላይ የተገኙ አንቀሳቃሾችም በቀረበው ሰነድ እጅግ ተደስተው ቀጣይ እንደየ ስራ ዘርፋቸው ባህርይ በማጣጣም ይህንን ልምድ ለኢንተርፕራይዞቻቸው ለውጥ እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል፡፡

ማክሰኞ፦ ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም
"በቀጣይም የጀመርነዉን በማጠናከር አቅም እስካለ፤ ሁኔታዎች እስከፈቀዱ የምናልፋቸዉ ጉዳዮች እና የማንፈታቸዉ ችግሮች የሉም፡፡
አቶ ጃንጥራር አባይ
ከመዲናዋ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ከተዉጣጡ አስተዳደር ሰራተኞች እና አሰልጣኝ መምህራን ጋር በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ ዉይይት ተካሄደ::
"የበቃ አሰልጣኝ፤ክህሎት የጨበጠ ወጣት፤ለሃገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ ከሀገራዊው ለውጥ ማግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሚና ዙሪያ ውይይት ተካሔዷል።
በዉይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ #ጃንጥራር #አባይ ለተሳታፊዎች እንደተናሩት መንግስት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ እንደ ሃገርም ሆነ በከተማ አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊ፤ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ በርካታ አስደማሚ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ሁሉን አካታችና አሳታፊ ስርዓት የማስፈን፤ ዘላቂና ስር-ነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስርዓት የመዘርጋት፤ ሁሉንም ፍትሃዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን የማፅናት እና የሃገርና የዜጎች ክብርና ነፃነት የማስጠበቅ ስራዎች በብዙ ሰዉ ሰራሽ እና ተፈጥራዊ ተግዳሮቶች ታልፈዉ የተመዘገቡ ስለመሆናቸዉ ከተጨባጭ ማሳያዎች ጋር አያይዘዉ አቅርበዋል፡፡
በእነዚህ የብልፅግና ጉዞ የለዉጥ ዓመታት ዉስጥ በሁለተናዊ የልማት ስራዎች ስኬቶቻችን ላይ በሙያዉ ብቁ የሆነ ወርቃማ እጆች ያሉት ትዉልድ በማፍራት እና አሻራቸዉን በማኖር ረገድ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ግንባር ቀደም ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡
በሌላ በኩልም ተሳታፊዎች ላነሷቸው የቤት፤ የጥማጥቅም እና የማትጊያ እንዲሁም ሌሎች የአሰራር እና አደረጃጀት ስራዎች አቶ ጃንጥራር ሲመልሱ ከተማ አስተዳደሩ ለእነዚህ ጥያቄዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ደረጃ በደረጃ በጥናትና በእቅድ እየፈታ መምጣቱን አስታዉሰዉ በቀጣይም ይህን በማጠናከር አቅም እስካለ፤ ሁኔታዎች እስከፈቀዱ የምናልፋቸዉ ጉዳዮች እና የማንፈታቸዉ ችግሮች የሉም ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም አሁንም ከያዝነዉ አዳጊ ፍላጎት አኳያ ጎታች የሆኑትን ጉዳዮች ለማስቀረት ሁሉም ተቋማት በአደረጃጀት በአሰራር በማዘመን እና ራስን በሙያዉ ብቁ በማድረግ በኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታዉ የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት ተቀናጅተዉ በትጋት እንዲወጡ በማለት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸዉ ከተማ አስተዳደሩ ለሙያ ተቋማት በሰጠው ትኩረት አዋጆችን፤ ደንብና መመሪያዎችን እንዲሁም የሪፎርም ስራዎችን ወደ መሬት በማዉረድ በርካታ ትርጉም ያላቸዉ ተጨባጭ ለዉጥ በሃገርና በትዉልድ ላይ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡
በልማት ስራዎች፤ በቴክኖሎጂ ሽግግር፤ ሃብት በመፍጠር እና ምርታማነት በማሳደግ እና ትዉልድን በመቅረፅ ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባና በተቋሙ አካለት የተነሱ ጥያቄዎች በጥናት ተደግፈዉ የወረዱ ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም የተጀመዉ የሪፎርም ስራ በተገቢዉ የሚመልሰዉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ በከተማዋ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በጥራትና በፍትነት መሰራታቸዉንና ሁሉን አካታች መሆናቸዉ እንዲሁም ለቴክኒክና ሙያ ተቋማት መንግስት የሰጠዉ ትኩረት እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዉ ዉይይቱ የበለጠ መግባባት የተፈጠረበትና ችግሮችን በጋራ እየፈቱ ዘላቂ ልማትና እድገትን ለማረጋገጥ ያስቻለ ነዉ ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ